>

"…የራያ አሁናዊ መረጃ…!  (መምህር ዘመድኩን በቀለ)

“…የራያ አሁናዊ መረጃ…!

መምህር ዘመድኩን በቀለ


“…ትናንትና ማታ ወደ አላማጣ መስመር ከነተጎታቹ የሄደው የከባድ መኪና ብዛት ከ150 ተሽከርካሪ በላይ  ይሆናል። ዛሬም እንደጉድ እየጎረፈ ነው። ሰሞኑን ኦሮሚኛ ተናጋሪ የመከላከያ ሰራዊት ልብስ የለበሱ ወታደሮች ወደ ትግራይ ክልል በገፍ መግባታቸው ይታወቃል። ነዋሪዎችም የፀጥታ ሠራተኞችም እየሆነ ባለው ከባድ ሴራ የተነሣ በፀጥታ ተውጠዋል።

“…ከመንግሥት አቅጣጫ ተቀምጧል። ራያና ወልቃይት ለትግራይ ይመለሳል። በቁራሽ መሬት ብለን ብልፅግናችን በዶላር እጦት መገታት የለበትም። የዐማራ ኃይላት በፀባይ ከወጡ ወጡ፣ ሞቻለው፣ መሬቴ ነው፣ ቅብጥርሶ የሚሉ ከሆነ ይመታሉ። ዐማራ ቢጮህ እንደትግሬ የሚሰማው ፈረንጅ የለም። እርዳታ የሚጨምርልን እንጂ ዐማራን መታችሁ ብሎ እርዳታ የሚያሳጣን የሚከለክለን የለም። በድሮንም፣ በአየርም፣ በምድርም መደምሰስ ነው ማለታቸው ተነግሯል።

“…በዐማራ ክልልም፣ በፌደራሉ መንግሥት ሚዲያዎች የጥምቀት፣ የልማት፣ እና የህወሓት ትጥቅ የማስረከቧ ዜና ተደጋግሞ እንዲጮህ ይሁን። የዐማራ ኃይሎች እየወጡ ስለመሆናቸውም ይሰበክ። ይለፈፍ። በወልቃይት በሽራሮ በኩል ህወሓትን ማመን ስለማይቻል እንደራያው ሳይሆን የዐማራ ልዩ ኃይል የመውጣቱ ዜና ቢነገርም፣ የፌደራል እና የመከላከያ ልብስ ለብሶ ገሚሱ በዚያው ይቆይ። ትንኮሳ ቢኖር እንኳ የመከላከያ ሠራዊቱ የውጊያ ልምድ ስለሌለው ከበድ ኪሳራ ሊደርስ ስለሚችል በጥንቃቄ ይፈጸም። ይሄን ጉዳይ ተጠሪነቱ በቀጥታ ለጠቅላዩና ፊልድማርሻሉ ሆኖ ጀነራል አበባው  ታደሰ ይምራው፣ ይከታተለው መባሉ ነው የተሰማው።

“…ህወሓት ትጥቅ አስረከበች እያለ መንግሥት ፕሮፖጋንዳ ቢነፋም ህወሓት ግን አብዛኛውን የራያ ገጠራማ ክፍሉን ዳግም በመቆጣጠር ላይ ናት። የታሰበው ከባድ ነው። ልዩ ኃይሉን በግድ ለማስወጣት ሥራ ሠርተው ጨርሰዋል።

አሁን ባለው መረጃ መሠረት፦

• 90% የሚሆነውን የዐማራ ልዩ ኃይል ከራያ አስወጥተውት ከቆቦ በሦስት ኪሜ ርቀት ጮቢ በር ላይ ተከማችቷል። ጮቢ በር ጠጠር መጣያ የእግር መረገጫም የለም። እርኛ እንደሌለው መንጋ ይተራመስ ይዟል። የሞተ ተጎዳ…!

“…የተወሰኑ የዐማራ ልዩ ኃይል ብርጌዶች አሁንም ሞተን ካልሆነ በስተቀር የስንት ጀግና ወንድም እህቶቻችንን ደም ከገበርንበት ከዚህ ቦታ ንቅንቅ አንልም ብለው በዚያው መሆናቸው ተመልክቷል። እንዲያውም መሆኒ ላይ ከመከላከያ ሠራዊቱ ጋር መዋጋት ጀምረው መከላከያው መሸሽ ከጀመረ በኋላ የጥንቱን ባንዲራ በማውለብለብ ይቅርታ በመጠየቅ ነው ግጭቱ የቆመው ተብሏል። ምስኪን ዐማራ።

“…ዛሬ በአላማጣና በዋጃ መካከል አየር ማረፊያ አካባቢ የሚኖር ሕብረተሰብ ወደ ትግራይ ክልል የሚገባን አንድ ቢራ የጫነ ተሳቢ መኪና አስቁመው ወደ ትግራይ ክልል አይገባም በማለት ሙሉ በሙሉ አቃጥለውታል። ይሄ ነገር በሁሉም የዐማራ ክልል አካባቢዎች ይስፋፋል ተብሎም ይጠበቃል። እርቁ መንግሥት ከመንግሥት ስለሆነ ያኮረፈውና ኖረም ሞተም ምንም የማይቀርበት ሕዝብ ወደ እርምጃ ይገባል። ይሄንን ነው መፍራት።

“…TDF የሚባለው የሕውሓት ጦር ከኩኩፍቱ ጀምሮ በዚያ አካባቢ ባሉ ገጠራማው ክፍል ላይ ከነ ሙሉ ትጥቁ ተቀምጦ ኧሮጌ ትጥቅ እያሳየ ትጥቅ እያስፈታሁ ነው የሚለው የፌዴራል መንግሥቱ ፕሮፖጋንዳ በሕዝቡ ዘንድ መሳቂያ መሳለቂያ ሆኗል። ይሄ ሴራ የገባቸው የዐማራ ልዩ ኃይሎችም ተፋጠው ተቀምጠዋል። በራያ ነገሩ ከብዷል። የሚበላኝ አሞራ ሲዞረኝ ነው የማውቀው የሚለው የሀገሬው አባባል በስፋት እየተነገረ ነው።

“…በወልቃይት አካባቢ እንዲሰፍር የተላከው ወታደር በአብዛኛው በአማራ አክቲቪስቶች ውትወታ በቅርቡ መከላከያውን የተቀላቀለ እንደሆነ ነው የተመለከተው። በወልቃይት መንግሥትና ዐማራ መጋጨት ቢጀምሩ ተጎጂው አዲስ ሰልጣኙ የዐማራ ወታደር ነው የሚሆነው ተብሏል። ይሄም ለኦሮሙማው መንግሥት በወለጋ እየወሰደ ከሚያሳርደው የዐማራ ወታደር በተጨማሪ በገዛ ወገኑ ራያና ወልቃይት ላይ እንዲያልቅ ፈርደውበታል ነው የሚሉት የመከላከያ ምንጮቹ።

“…የመሃል ሃገር ሰው ትኩረቱን ወደ ሰሜን አቅጣጫ እንዳያዞር የኦሮሞው መንግሥት ሕዝቡ በቤት ፈረሳ፣ በኦሮምኛ ቋንቋና በኦሮሞ ባንዲራ ማውለብለብ፣ በመብራት፣ እና ውኃ፣ በፀጥታ ጉዳይ እንዲወጠር ይደረግ፣ መጪውንም የጥምቀት በዓል በስጋት እንዲያሳልፍ ይዋከብ መባሉን ነው ወፌ የምትነግረኝ። ከበዓለ ጥምቀቱ በፊት ወጣቶችን በገፍ በማሰር ሕዝቡ ትኩረቱን ወደ ራሱ እንዲያዞር እንዲረግም አቅጣጫ መቀመጡን ነው ርግቤ የምታወራው።

• ሻሎም…!  ሰላም…!

Filed in: Amharic