>

ሚዲያን በማዘጋት የሚቆም ትግል የለም! (ራስ ሚዲያ)

ሚዲያን በማዘጋት የሚቆም ትግል የለም

ራስ ሚዲያ

በእምየ ምኒልክ ዓርማ እና “ራስ ሚዲያ”(RasMedia) በተሰኝ መጠሪያ ለድምፅ አልባው ሁሉ ድምፅ በመሆን ላለፉት ሁለት ዓመት ተኩል ስንሰራበት የነበረውን ሚዲያ ኦህዴድ/ኦነግ ከፍተኛ ገንዘብ በመክፈል በትናንተናው ዕለት አዘግቶብናል።

በዚህ ሚዲያ ውስጥ አንጋፋው የታሪክ ሙሁር እና ጋዜጠኛ ታዲዎስ ታንቱ(በዕስር ላይ የሚገኙ)፣ጋዜጠኛ ጌጥዬ ያለው(ከመኖሪያው የተፈናቀለ)፣ጋዜጠኛ ወግደረስ ጤናው(ከመኖሪያው የተፈናቀለ)፣ጋዜጠኛ ሙልዬ ንጋት(የመዝናኛ ፕሮግራም አዘጋጅ)፣ፕሮፌሰር ሰለሞን ጉግሳ(በአሜሪካን አገር የሚኖር) እና እያሱ ኤፍሬየም(በለንደን የሚኖር) የመሳሰሉ ጠንካራ፣ታማኝ እና ፅኑ ባልደረቦች ይዞ ይገኛል።ከሁለት ዓመት ተኩል በላይ በፅናት ተጉዟል።ለድምፅ አልባዎቹ ያለአንዳች ጥቅማጥቅምም ሆነ ክፍያ በነፃ ሲያገለግሉ ቆይተዋል።

ይሁን እንጅ የኦህዴድ/ኦነግ ስርዓት ለተለያዮ አካላት ዳጎስ ያለ ገንዘብ በመክፈል ከ60ሺህ በላይ ሰብስክራይበር የነበረውን #RasMedia  ከሶስት ጊዜ በላይ ለአጭር እና ለረጅም ጊዜ ሲያሳግደው ከቆየ በኋላ በትናንትናው ዕለት ከነጭራሹ አዘግቶታል።ምንም አይነት ክፍያ እንዳይሰጥም ሆኖ ቆይቷል።

በሚዲያችን እና በጋዜጠኞቻችን በኦህዴድ/ኦነግ ስርዓት በተደጋጋሚ የሚደርሰውን አፈና ተቋቁመን፣ሌላ #RASMEDIA INTERNATIONAL” የተሰኘ ሚዲያ ከፍተን የነበረ ቢሆንም ሰርዓቱ በትናንትናው ዕለት አዲሱን ሚዲያ ጭምር አዘግቶብናል።

በመሆኑም ዛሬም ለህዝባችን ድምፅ ለመሆን ስንል ለሶስተኛ ጊዜ አዲስ “Ras Media Network (ራስ ሚዲያ መረብ) የተሰኘ ከፍተናል።

በመሆኑም ወቅታዊ፣ፈጣን እና ሃቀኛ መረጃ ከምንጩ ማግኘት የምትፈልጉ በውጭና በሃገር ውስጥ ያላችሁ እና  የትግሉ አንድ አካል የሆናችሁ በሙሉ ከታች የተያያዘውን ምንም አይነት ክፍያ የማያጠይቀውን አዲሱን ሚዲያ ሰብስክራይብ፣ላይክ እና ሼር በማድረግ እንድትቀላቀሉ በታላቅ አክብሮት አንጠይቃለን።

Filed in: Amharic