>

አባታችን አቡን ማትያስና የጭራቅ አሕመድ ሲሳይ አጌና ዘዴ (መስፍን አረጋ)

አባታችን አቡን ማትያስና የጭራቅ አሕመድ ሲሳይ አጌና ዘዴ 

ጭራቅ አሕመድ ኢሳትን ለመበታተን ሲነሳ፣ በኢሳት ውስጥ በቀላሉ ሊደለል የሚችል ቁልፍ ሰው ነው ብሎ ያሰበውን ሲሳይ አጌናን በስም ጠርቶ አመሰገነው፡፡  ሲሳይ አጌናም ልክ ጭራቅ አሕመድ እንዳሰበው ሆነና፣ ከሁሉም ባልደረቦቸ እኔ ብቻ ተለይቸ፣ በስም ተጠርቸ በጠቅላይ ሚኒስትር ተሞገስኩ ብሎ በትዕቢት ተወጣጥሮ ዝሆን አከለ፡፡  ጭራቅ አሕመድም ተወጣጥሮ በተነፋው በሲሳይ አጌና ሆድ ውስጥ ገብቶ ሲሳይን በማፈንዳት ኢሳትን በታተነው፡፡ 

አባታችን አቡነ ማትያስ ሆይ፣ ትናንት በነ ዳንኤል ክብረት አማካኝነት ከፍ ዝቅ እያደረገ ሲሰድብወና ሲያሰድብወ የነበረው ባለጌው ጭራቅ አሕመድ፣ ዛሬ እርስወን ለይቶ ያመሰገነወ፣ በርስወ ውስጥ ገብቶ ተዋሕዶን ለመበታትን ሲል ብቻ መሆኑን ይጠፋወታል ብየ ስለማላስብና፣ እንደ ሲሳይ አጌና በቀላሉ ተደላይ ነወት ብየ ስለማልገምት፣ እኛም አውቀናል ጉድጓድ ምሰናል ይበሉትና ቁርጡን ያሳውቁት፡፡  የጭራቅ አሕመድ መውደቂያው ስለቀረበ የሚያልፍ ዝናብ አይምታወ፡፡   

ጭራቅ አሕመድ ዐሊ የኦነጉ ኦቦ

አፉና ምግባሩ ሐራምባና ቆቦ፡፡

ባንደበቱ መስሎ የኢትዮጵያ ሙሴ

በምግባሩ ሆነ የኦነግ ራምሴ፡፡

በመውረስ ያገኘው ከወያኔ አባቱ

መዋሸት ማጭበርበር ነውና ፍጥረቱ፣

አንዴ ቢያታልለን የሱ ነው ኀፍረቱ

ሁለቴ ቢደግም የኛ ነው ጥፋቱ፡፡

መስፍን አረጋ     

mesfin.arega@gmail.com

Filed in: Amharic