የኢ/ኦ/ተ/ ቤተክርስቲያን በመንግስት የተለያዩ ተቋማት፤ በተወገዙት የቀድሞ ሶስት ጳጳሳትና የተሾሙ 25 ጳጳሳት ላይ ክስ መሰረተች …!
የትነበርክ ታደለ
ክሱ ዝርዝሩ ብዙ ነው። ዋና ዋናዎቹ የሚከተሉት ናቸው
√ የቤትክርስቲያንን ክብርና ስም በመንካት
√ በህይወት የመኖር፣ የመዘዋወር እና የማምለክ መብትን በመንካት
√ መንግስት ሁሉን ሰው በእኩል ህጋዊ ጥበቃ እና በእኩልነት የማየት ህገመንግስታዊ ሀላፊነትን ባለመወጣት
√ የቤተክህነት ንብረት ሲዘረፍ እርምጃ ባለመውሰድ
√ ጳጳሳትን እና የቤተክህነት ህጋዊ መዋቅር ውስጥ ያሉትን በማፈን፣ በማሰርና በማስፈራራት
√ የመንግስት ሚዲያ በህዝብ ሀብት እየተዳደረ የቤተክርስቲያኗን መግለጫ እና የደረሰባትን የህግ ጥሰት ባለመዘገብ ህገመንግስታዊ ሀላፊነትን ባለመወጣት
√ አቶ ሀይለሚካኤል ታደሰ የተባሉ የህገወጦቹ ቃላቀባይ ህዝብን ከህዝብ የሚያጋጭ ፀብ አጫሪ ቅስቀሳ በማድረጋቸው
ተከሰዋል።
ክሱ ሰኞ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድቤት በስምንት ሰዓት ይሰማል።
በተጨማሪም
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ማንም የካቤኔ አባል በዚህ ጉዳይ እንዳይገባ በማለታቸው በህግ ሰውነት የታወቀች ቤተክርስቲያን የህግ ከለላ እንዳታገኝ የፀጥታ አካላት አቤቱታዋን እና በደሏን ስታሰማ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጣልቃ እንዳይገቡ በማዘዛቸው ለህግጦች ተላልፋ ተሰጥታ አድሎ ተፈፅሞባታል። ስለዚህም መንግስት በህገመንግስቱ የተጣለበትን ሀላፊነት እንዲወጣ ፍርድቤት ትዕዛዝ እንዲሰጥ
መንግስት የሀገር ቅርፅ የያዘች ቤተክርስቲያን ስትዘረፍ ሀላፊነቱን ባለመወጣቱ እንዲጠየቅ (በተለይ የኦሮሚያ መንግስት ፖሊስ ኮሚሽን እና የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን
የቤተክርስቲያን አባቶች የመዘዋወር መብት በመንግስት ታግደዋል። ጥበቃቸው ተነስቶ፣ የህገወጡ ቡድን ግን በመንግስት ጥበቃ እየታጀበ ነው።
ይህም የእኩልነት አንቀፅ የሆነው አንቀፅ 25 ተጥሶ መንግስት አድሎ ፈፅሟል
የአለለማቀፍ የሰብአዊ መብቶች፣ የማምለክና የመዘዋወር መብቶች ተጥሰው አገልጋዮች በእስርና በአፈና ተቸግረዋል
በመሆኑ ከፍተኛ ፍርድቤት
የእግድ ትዕዛዝ እንዲሰጥ
እግዱም
ህገወጡ ቡድን ወደ ቤተክርስቲያን ቅጥር እንዳይደርስ
ንብረት እንዳያንቀሳቅስ
የቤተክርስቲያኗ ጥቅምና መብት እንዲከበር ይህ ክስ በዝርዝር እስኪታይ እግድ ትዕዛዝ እንዲተላለፍ
ቤተክርስቶያኗን የወከሉት ጠበቆች ፍርድቤትን ጠይቀዋል