>

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ቆሞ ቀር ብለው የሚሳደቡት ኋላ ቀሮቹ ኦነጋውያን ...!(አቻምየለህ ታምሩ)

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ቆሞ ቀር ብለው የሚሳደቡት ኋላ ቀሮቹ ኦነጋውያን …!

አቻምየለህ ታምሩ

የኦሮሙማው ዋና ሥራ አስፈጻሚ በላዔ ሰብዕ ዐቢይ አሕመድ ኦሮምያ በሚባለው በኢትዮጵያ እምብርት ላይ በበቀለው እባጭ በኩል ትናንትና ባወጣው መግለጫ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን “ቆሞ ቀር” ሲል ተሳድቧል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንን ቆሞ ቀር ብለው የሚሳደቡት ኦነጋውያን ገዳ በሚባለው የባንቱ ኋላ ቀር የወረራ፣ የቅሚያና፤ የግድያ ሥርዓት እና የሥርዓቱ ባለቤቶች የሆኑት ባንቱዎች ኋላ ቀር በመሆኑ ከአራት መቶ ዓመት በፊት የተውትን የጭካኔ ሥርዓት እንደ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት የሚቆጥሩ ጉዶች ናቸው።

ዐቢይ አሕመድ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ቆሞ ቀር ብሎ የተሳደበው አማኙን በቋንቋው እንዲማር አታደርግም ብሎ በኦነጋዊ ፈጠራ በመክሰስ ነው። ይህ ኦነጋዊ ፈጠራ የሚመለከተው ብቸኛ ስብስብ ቢኖር ከኦሮሞ ውጭ የሆኑ ዜጎች በቋንቋቸው እንዳይማሩ፣ በተወለዱበት ቀዬ እንዳይሰሩና መንግሥታዊ አገልግሎት በቋንቋቸው እንዳያገኙ በሕግ ያገደው እና ይህንን አፓርታይዳዊ ደንብ ላለፉት ሰላሣ አንድ አመታት ተግባራዊ ያደረገው በኦነጋውያን የደነዘዘ አእምሮ የተፈጠረው ኦሮምያ የሚባለው በኢትዮጵያ እምብርት ላይ የቀለው እባጭ ብቻ ነው። 

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንማ ምዕመኖቿ በቋንቋቸው እንዲማሩ ሕግ አዋዲ ያወጣችና በሕገ ቤተ ክርስቲያኗ የደነገገች ተራማጅ ተቋም ናት። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሃይማኖታዊ፣ መንፍሳዊ አስተዳደርን፣ የሰበካ ጉባኤ አደረጃጀትና ባጠቃላይ ቤተክርስቲያኗ የምትመራበት ዐቢይ መመሪያ ወይም ሕግ አላት። ይህ መመሪያ ቃለ ዓዋዲ ይባላል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቃለ ዓዋዲ የስብከተ ወንጌልን ክፍል ሥራና ኃላፊነት የደነገገበት አንቀጽ 18 ንዑስ አንቀጽ 4 እንዲህ ይላል፤  

 “ምዕመናን በሚረዱት እና በሚያውቁት ቋንቋ ትምህርተ ወንጌል እንዲሰጥ… በማድረግ ሐዋርያዊ ተልዕኮ ይፈጸማል” 

ከዚህ በተጨማሪ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሕገ ቤተክርስቲያን ስለ ቋንቋ በሚደነግግበት አንቀጽ 5 ንጹስ አንቀጽ 3 እንዲህ ይላል፤

“ግዕዝ፣ አማርኛና የየአካባቢው ቋንቋ በጣምራ የቤተክርስቲያኗ የትምሕርትና የአምልኮ ሥርዓት ማከናወኛ ቋንቋ ሆነው ያገለግላሉ።”

ይህ የቤተ ክርስቲያን ሕገ መንግሥት ነው። ተራማጇ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሕገ መንግሥቷ የየአካባቢው ቋንቋ የትምህርትና የስርዓተ አምልኮ ማከናወኛ ቋንቋዎች እንዲሆኑ በሕገ ቤተክርስቲያንና በቃለ ዓዋዲዋ ደንግጋለች። ኋላ ቀሩ በኦነጋዊ የደነዘዘ አእምሮ የሚዘወረውና ጨካኝ አረመኔዎች በንጹሐን ላይ የጭካኔ ጥማቸውን የሚወጡበት የግፉአን መታረጃ ቄራ የሆነው ኦሮምያ የሚባለው ክልል ግን እንኳን ዜጎች በቋንቋቸው እንዲማሩ፣ እንዲሰሩና መንግሥታዊ አገልግሎት እንዲያገኙ ሊያደርግ ቀርቶ ከኦሮምኛ ቋንቋ ውጭ ሲናገር የተገኘ ኢትዮጵያዊ ከክልል ተብዮው እንዲጸዳ ያወጀ የሲኦል ምድር ነው።         

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቆሞ ቀር ብሎ የሰደበው ይህ የዐቢይ አሕመድ ክልል የሚመራበት ሕገ መንግሥት አንቀጽ 5 ደግሞ ስለ ቋንቋ ፖሊሲው እንዲህ ይላል፤ 

“ኦሮምኛ የክልሉ መንግሥት የሥራና የትምህርት ቋንቋ ይሆናል፤ የሚጻፈውም በላቲን ፊደል ነው፤” 

የዚህ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 8 ደግሞ እንዲህ ይላል፤

“የኦሮሞ ሕዝብ የክልሉ ባለቤትና የበላይ ባለሥልጣን ነው”

ልብ በሉ ከኦሮምኛ ውጭ እንዳይሰራበት እና ከኦሮሞ ሕዝብ ውጭ ሌላውን አናውቅም የሚለው የነ ዐቢይ አሕመድ ኦሮምያ ክልል ሕገ መንግሥት በአስር ሚሊዮኖች የሚቆጠር የአማራ፣ የጉራጌ፣ የትግሬ፣ የሐድያ፣ የዎላይታ፣ የጋሞ፣ ወዘተ ተወላጆች በሰባተኛ ዜግነት ከሁሉም መንግሥታዊ አገልግሎት ተገልለው የሚኖሩበት አፓርታይዳዊ ክልል ነው።  

ከኦሮሞ ሕዝብና ከኦሮምኛ ቋንቋ በስተቀር ቀሪው የኢትዮጵያ ሕዝብ በክልል ተብዮው ኅልውና እንዳይኖረው በሕግ የደነገገው የእነ ዐቢይ  አሕመድ አፓርታይዳዊ ክልል ነው እንግዲህ የየአካባቢውን ቋንቋ የትምህርትና የአምልኮ ቋንቋዎች አድርጋ በሕገ መንግሥቷ ያወጀችውና በስራ ላይ ያዋለችውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በቆሞ ቀርነት የሚከሰው።  

ከኦሮሞ ቋንቋ ውጭ እንዳይሰራበት በሕግ ያገደው የነ ዐቢይ አሕመድ  ኦሮምያ ሕገ መንግሥት የቋንቋና የሥራ ፖሊሲ የተቀዳው ገዳ ከሚባለው የባንቱ ሥርዓት የቋንቋ ፖሊሲ ነው። የኦሮሞ አባ ገዳዎች በገዳ ወታደራዊ ሥርዓት እየተመሩ ከኢትዮጵያ ውጭ መጥተው  ለምለሙን የኢትዮጵያ ክፍል ሲወሩ የሚወሩትን ነባር ሕዝብ እንዴት መያዝ እንዳለባቸው የሚከተሉት የቋንቋ ፖሊሲ ነበራቸው። ይህ የቋንቋ ፖሊሲያቸው «ኦሮምኛ የሚናገር “ቢርመዱዳ እንጡቂና” ኦሮምኛ የማይናገር “ዲና በሌሣ”» የሚል ነበር። 

ይህ የኦሮሞ አባገዳዎች የቋንቋ ፖሊሲ ወደ አማርኛ ሲተረጎም «ኦሮምኛ የሚናገር ወገናችን ነው ይገብር፤ ኦሮምኛ የማይናገር ጠላታችን ነው ይጥፋ”» እንደ ማለት ነው። የነ ዐቢይ አሕመድ ኦሮምያ ክልል ከኦሮምኛ ቋንቋ ውጭ ባለው የየአካባቢው ቋንቋ  እንዳይሰራበት በሕግ ደንግገው የባንቱስታን ሥርዓት የፈጠሩት ይህን የጥንቶቹን አባ ገዳዎች የቋንቋ ፖሊሲ ቃል በቃል በመቅዳት ነው። የዚህ አፓርታይዳዊ የቋንቋ ፖሊሲ ባለቤቶች ተፈጥሮ ለሰው ልጆች ሁሉ የለገሰችው ማፈር የሚባለው ስሜት ስለሌላቸው ምዕመኑን በቋንቋው ለመድረስ በሕገ መንግሥቷ የደነገገችውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በቆሞ ቀርነትና በነገዶች ቋንቋዎች መንፈሳዊ አገልግሎት ባለመስጠት ይከሷታል።  

ከላይ ከቀረበው የኦነጋውያኑ አፓርታይዳዊ የቋንቋ ፖሊሲ በተጨማሪ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ አስተዳደርን እነ ዐቢይ አሕመድ ከሚምሉበት ከገዳው የአባ ሙዳ ወይም መራሔ ዋቃ ሥርዓት ጋር በማነጻጸር ቆሞ ቀር ማን እንደኾነ በተጨማሪ ማሳየት ይቻላል።  

ንጽጽሩን ፈር ለማስያዝ  በቅድሚያ ከዋና መዲናችን ከጥንታዊቷ በራራ ከአሁኑ አዲስ አበባ ብዙ ሳንርቅ ጥንታዊው የደብረ ሊባኖስ ገዳም መንፈሳዊ አስተዳደር ምን እንደሚመስል እንመልከት።

 የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ደብረ ሊባኖስ ገዳም አስተዳዳሩ በጥንታዊ ስሙ እጬጌ ይባላል። የአስተዳዳሪው የአኹን ስም ፀባቴ ይባላል። ፀባቴው ገዳሙን ብቻውን የማስተዳደርና በገዳሙ ላይ እንዳሻም የማዘዝ መብት የለውም። ገዳሙ የሚተዳደረው ምርፋቅ በሚል ስም በሚጠራ 12 ተመራጭ መነኮሳት በሚሰየሙበት የመማክርት ጉባኤ ነው፡፡ ምሩፋቁ የሚመራጠው በገዳሙ መላ አባላት ነው። 12ቱ ተመራጮቹ አጠቃላዩን የገዳሙን አስተዳደር ከፀባቴ ጋር በመሆን ይመራሉ፤ ሕግ ይደነግጋሉ፣ ያጠፋውን ቀኖና ይሰጣሉ፤ የአባላትን ቅሬታ በመመርመር ይፈታሉ፤ ፀባቴውንንም ይቆጣጠራሉ።

በገዳሙ ውስጥ ወጣ ያለ ባሕርይ የሚያሳይ መነኩሴ ካለ ጾምና ስግደት በመበየን በገዳሙ የንስሐ ማዕከል እስከመላክ የሚያደርስ የውስጥ ሕግ ያወጣሉ፤ ያስፈጽማሉ። የገዳሙ አባል መነኮሳት በምርፋቅ አባላት ላይ ቅሬታ ካላቸው እንዲሁ ቅሬታቸውን በማቅረብ ምርፋቁን አውርደው በሌላ ምርፋቅ ይተኩታል፡፡ይህ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስልጡን ሥርዓት ትናንት ነበረ፤ ዛሬም አለ፤ ወደፊትም ይኖራል። የተቀሩት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ገዳማትም ከላይ የቀረበው የደብረ ሊባኖስ ገዳም  አይነት ተመሳሳይ ዘመናዊ የአስተዳደር ሥርዓት አላቸው።  

ይህን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ አስተዳደር ሥርዓት እነ ዐቢይ አሕመድ ከሚምሉበት ከገዳው አባ ሙዳ ወይም መራሔ ዋቄ ፈታ ሥርዓት ጋር እናነጻጸረው።

የኦነግ የፕሮፓጋንዳ ጸሐፊው መኩሪያ ሙልቻ Being and Becoming Oromo በሚል በታተመው መጽሐፍ ገጽ ገጽ 53 ላይ ስለ አባ ሙዳ እንዲህ ይላል፤ 

“The Office of Aba Muuda  was open to the Oromo people and was visited by delegates from every gosa and from different parts of Oromoland, but non-Oromos were not allowed to participate in rituals”

ከዚህ የመኩሪያ ቡልቻ ጽሑፍ መራሔ ዋቄ ፈታ ከኦሮሞ ውጭ መሆን አይቻለውም፤ ሥርዓቱ በሚፈተትበት ቦታም ከኦሮሞ ውጭ ማንም ድርሽ ማለት አይችልም። አባ ሙዳው  ወይም መራሔ ዋቄ ፈታው ከኦሮሞ ውጭ መሆን አለመቻሉ ብቻ ሳይሆን ከኦሮሞም ውስጥም መንበሩ በዘር ከአባት ወደ ልጅ የሚተላለፍ ነው። 

የገዳው አባ ሙዳ ከአባት ወደ ልጅ በሚተላለፍ የተወላጅነት ሰንሰለት ብቻ እና ሲመቱም እስከ እድሜ ልክ እንደሆነ ታቦር ዋሚ የሚባለው ሌላው የኦነግ ፕሮፓጋንዳ ፀሐፊ “የውገና ድርሰቶችና የታሪክ እውነቶች” በሚል በደረተው ድሪቶ ገጽ 221 ላይ ነግሮናል። 

እንግዲህ! ላመነ፣ ለተጠመቀና መንፈሳዊውን እውቀት ለጨበጠ ሁሉ እንኳንስ ነገድ ዜግነት ሳትመርጥ ለሰብዓዊ ፍጡር ሁሉ ክፍት ሆኖ የኖረ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ያቆመችውን፤ ሁሉም እንዳቅሙ እንዲወዳደር እድል የፈጠረ የአስተዳደር መዋቅር የዘረጋችውን፤ ምዕመናን በቋንቋቸው ሥርዓተ አምልኮ እንዲፈጽሙና ሃይማኖታዊ ትምሕርት እንዲማሩ በሕግ የደነገገችውና በስራ ላይ ያዋለችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቆሞ ቀር እያሉ የሚሳደቡት ኦነጋውያን ከላይ በዚህ ጽሑፍ እንደቀረበው ክልላችን በሚሉት ከኦሮምኛ ነን በስተቀር እንዳይዘራበት በሕግ የደነገጉ፣ ኦሮምያቸውን ለኦሮሞ ብቻ ብለው በሕገ መንግሥታቸው ያወጁና ከኦሮሞ ውጭ ያለውን ኢትዮጵያዊ ሲፈጁ የሚውሉ እንዲሁም እንደ ኦሪት ሌዋውያን እጅግ ኋላ ቀር የሆነን ዘርና ቋንቋን የሥርዓቱ መሰረት አድርጎ የተዘረጋውንና ኦሮሞን ብቻ የሃይማኖት መሪነትን የሚያወራርሰውን ዋቄ ፈታን ሥርዓትና እሱን የወለደውን ገዳ የሚባለውን ኋላ ቀር የባንቱ ሥርዓት ሲያወድሱ የሚውሉ ጉዶች ናቸው።

Filed in: Amharic