>

የተጣሉ አባቶች አልነበሩም!

የተጣሉ አባቶች አልነበሩም!

መጀመሪያ በአባቶች መካከል ችግር አልተፈጠረም። የተወሰኑ አባቶችን አብይ አደራጃቸው። ነገር ግን የተደራጁት አባቶች ወንጌሉን የሚያውቁ ናቸውና  ቢበሉ አልጠጋቸው፤ ቢተኙ እንቅልፍ ነሳቸው። ”ሁላችንም ሄደን ይቅርታ ልንጠይቅ ነው አሉ።”

አብይ ”እኔን ጨረቃ ላይ ጥላችሁ አለ።እኔ ማደራጀቴን ለማንም እንዳታወሩ፤ ነገር ግን ያጣላኋች ሁ፣ያፋጀ ሁዋችሁ እኔ ብሆንም  እናንተ ተጸጽታችሁ ገቡ የሚባለው ይበልጥ ያሳምመኛልና የምወስዳችሁ እኔ ነኝ ” በማለት  አብይ ያደራጃቸውን ሶስቱን ጳጳሳቶች ይዟቸው ወደ ተቀደሰው ቤተ-ክህነት አስረክቧቸዋል።

ወንጌሉን የሚያውቅ ማንኛውም ካህንም ይሁን ጳጳስ፤ ዲያቆንም ይሁን ምዕመናን ለአፍታም የማይጠራጠርበትና  ሊመክርበት የማይችልበት ነገር አለ። ይሄውም ውጊያው ከሰዎች ጋር  ሳይሆን ከጌታችን መድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጋር መሆኑን  ነው። ለዚህም ነው ቃሉንና ወንጌሉን የሚረዱ ሰዎች የፈለገው ዓይነት  ንዋይ ስልጣን ቢያንገበግባቸው በተጓዳኝ የእግዚአብሔር ቃል እንቅልፍ ይነሳቸዋል። ያሳምማቸዋል። ይረብሻቸዋል። ወዘተ። ስለዚህም ዛሬ ሶስት ከቤተ ክህነት ወጥተው የተመለሱት የአዋቂ አጥፊዎች  ቅዱስ ሲኖዶሱ ምህረት አድርጎላቸው እራሳቸውም ተጸጽተው ይቅርታ ብለውና ነገር ግን ብቻቸውን አንድ ቀን እንደሚሄዱ የተረዳው አብይ ጎትቶ ወደ ቤተ ክህነት ወሰዳቸው በሚለው ይስተካከል።

ምክን ያቱም ቀደም ሲልም የተጣሉ አባቶች አልነበሩምና!

Filed in: Amharic