እንከባበራ…!
ዘመድኩን በቀለ
“…በአባቶች መካከል የተፈጠረ አለመግባባት ብሎ ዜና የለም። ይሄ ዜና አይሆንም። በግል የተጣላ እኮ የለም። በጥቂት የኦሮሞ ወሃቢይ እስላሞችና በኦሮሞና በደቡብ የጴንጤ ባለሃብቶች የገንዘብ ድጋፍ በኦነግና በኦሮሞ ብልፅግና ፅንፈኞች ተታለው አፈንግጠው በወጡ አፈንጋጮች ላይ ተወስዶ በነበረው እርምጃ፣ ተወጋዦቹ ማሩን፣ ይቀርም በሉን ብለው ደብዳቤ ጽፈው እግር ላይ ወድቀው ነው ተመለሱ መባል ያለበት። ወዴት ወዴት ነው ነገሩ?
“…ይሄ እኮ የባልና ሚስት ጸብ፣ ይሄ እኮ ተራ ቀላል ነገርም አይደለም። የማንም ሸርሙ* ከድር የተባለ እስላም ለጅማ ጳጳስ አድርገናል ብለው ሾመው፣ ብፁአን ሊቃነ ጳጳሳትን አዋርደው ከኦሮሚያ የመለሱብን ዋጋ የተከፈለበት የቀኖና ጥሰት ጉዳይ እኮ ነው።
“…በሻሸመኔ ለ52 ሰዎች መጨፍጨፍ ምክንያት የሆኑ ነፍሰ ገዳዮች፣ ከዚህ በኋላ መቀደስ፣ መባረክ ሁላ የማይገባቸው ደም አፍሳሾች፣ ጨካኝ አረመኔዎች እኮ ናቸው። በኦሮሞ ፖሊስና በአረመኔው ቄሮ በዱላ፣ በጩቤ፣ በገጀራ የተጨፈጨፉትን ልንረሳ ትፈልጋላችሁ እንዴ? በወለቴ በአለም ገና ላይቭ እያየነው የረሸናችሁትንስ መች ረሳነው? እናም ኢቲቪ ዛሬ መጥቶ ፖለቲካ ሲሠራ ዝም ብለን አናየውም።
“…አባቶቼም ዝም ብለው የሚያዩት አይመስለኝም። ዝም ካሉ ግን እኔ ዘመዴ በግልጽ አውግዙኝ ብዬ ከእነርሱም ጋር የለየለት ጦርነት ውስጥ እገባለሁ። የታሰሩት ሳይፈቱ፣ የተጨፈጨፉት በይፋ ሃገር አቀፍ ፍታት ሳይደረግላቸው፣ ሳይካሱ በለሆሳስ እናልፈዋለን ቢሉ መስሚያዬ ጥጥ ነው።
“…እንዲያ ከሆነ እስከዛሬ ያ ሁሉ ሰው ሲገደል፣ አብያተ ክርስቲያናት ሲቃጠሉ፣ ገዳማት ሲደፈሩ ዝም ጭጭ ያሉት ከትእግስ አይደለም እንድል እገደዳለሁ። ዛሬ እንዲህ የተንቀሳቀሱት በሥልጣናቸው ስለመጡባቸው ነው ብዬ ለማመን እገደዳለሁ።
“…ኳስ በመሬት…!