>

"…ነገሩ የሆነው እንዲህ ነው…!(ዘመድኩን በቀለ)

“…ነገሩ የሆነው እንዲህ ነው…! 

 ቀሽም ድራማ …. የከሸፈ ድራማ…!

ዘመድኩን በቀለ

*…. ችግሩን እነ አቢይ ፈጠሩ። የፈጠሩትን ችግር ግን በሚፈልጉት መጠን መቆጣጠር ከበዳቸው፣ አቃታቸውም። ስለዚህ ጉዳዩን በእርቅ ሰበብ በተሎ ለማዳፈን ፈለጉ። ሁለተኛው በጂኦፖለቲክሱ ጉዳይ ጥቅሟ አደጋ ላይ ሊወድቅ እንደሆነ ከተረዳችው ከሩሲያው ፕሬዘዳንት ለአብይ አህመድ የተላከው የፑቲን ቀጭን ትእዛዝ ነው እሱ ወድያው ተፈጽሟል። ይሄ መግቢያው ነው። ዋነኛው ግን። 

“…ድንገት እነ ሳዊሮስ ተከራይተው ያረፉበት የጅማዋ የአቢይ ደጋፊ ወ/ሮ አይንሸት አፓርታማ ፔኒሲዮን በሪፐብሊካን ጋርድ ይከበባል። የኦሮሚያ ልዩ ኃይል የመደባቸው ፖሊሶችና ደኅንነቶችም ይደነግጣሉ። ገለልም ይደረጋሉ። ከብዙ ዘመናዊ መኪኖች ከአንደኛው መኪና ውስጥ የበሻሻው አራዳ ፈገግ እያለ ይወርድና ወደ ህንፃው ይገባል። የጨረቃ ጳጳሳቱን ሁሉንም ሰላም ካለ በኋላ እናንተ ሦስታችሁ ግን ተከተሉኝ። ሰሞኑን ብዙ ስለደከማችሁ ትንሽ ሻይ ቡና እንበል ብሎ ሳዊሮስ፣ ኤውስጣቴዎስንና ዜናማርቆስን ለይቶ ነጥሎ ይዞ ይወጣል። 

“…የቀሩት ጨሬቅሶች ደነገጡ። በአቢይ ተጠልፈው የሄዱትን ጓዶቻቸውን ያዩት አባ ሳዊሮስ በቤተ መንግሥት ደብዳቤ ሲያነብ፣ ፓትርያርኩም ጋር ገብተው 3ቱም የቅዱስነታቸውን ጉልበት ሲስሙ ነው። በቃ ያ ዜና ሲሠራ ነው ያዩት። የደነገጡትም። ኃይለሚካኤልማ በፍርድቤት የደም ስሩ እስኪገታተር ድረስ ይሟገት፣ ይከራከር ነበር። የኦሮሞ ቤርቤረሰብ ሲኖዶስ ካረፈበት ከፔኒሲዮኑ ሲደርስ እነ ሳዊሮስ የሉም። አሁን አቢይ እና ይሁዳው ዳንኤል ድራማውን ከሠሩ በኋላ እነ ሳዊሮስም ተመልሰው ወደ ቦሌ ወደ ጎሬያቸው ወደ ፔኒሲዮናቸው ተመለስዋል። ይሄ ቀሽም ድራማ ነው። ድራማውም ይከሽፋል። 

“…እኔ በህይወቴ ተስፋ አልቆርጥም። ይሄንንም ሴራ አሳምረን እናከሽፈዋለን። እነ ብፁዕ አብርሃም ከተረጋጉ፣ እነ አቡነ ጴጥሮስ ከተረጋጉ ማሸነፍ ቀላል ነው። እነሱ ባይረጋጉም እኛ ማሸነፍ እንችላለን። እነ አቢይ አንድ ቀን የሚያሳድራቸውን እቅድ ብቻ ነድፈው ስከሚንቀሳቀሱ እኛ ከእነሱ ልቀን ካሰብን እናሸንፋቸዋለን። እነ አቡነ አብርሃም ለሰከን እንዲዋሹን አልፈቅድላቸውም። ብዙ ጥያቄዎች አሉኝ። እርሱን ቀስ እያልኩ በጨዋ ደንብ መጠየቁን እገፋበተለሁ። 

“…በነገራችን ላይ የአብይን ካምፕ እንደዚህ የረበሸው ነገርየውን ፈጥሮ ሳይቋጨው ቸኩሎ ወደ እርቅ የፈጣጠነበትስ ምክንያት ምንድነው? ያልን እንደሆነ ሁለት ለእውነት የቀረቡ መላምቶችን እናገኛለን። አንደኛው ችግሩን እነ አቢይ ፈጠሩ። የፈጠሩትን ችግር ግን በሚፈልጉት መጠን መቆጣጠር ከበዳቸው፣ አቃታቸውም። ስለዚህ ጉዳዩን በእርቅ ሰበብ በተሎ ለማዳፈን ፈለጉ። ሁለተኛው በጂኦፖለቲክሱ ጉዳይ ጥቅሟ አደጋ ላይ ሊወድቅ እንደሆነ ከተረዳችው ከሩሲያው ፕሬዘዳንት ለአብይ አህመድ የተላከው የፑቲን ቀጭን ትእዛዝ ነው እሱ ወድያው ተፈጽሟል። ይሄ መግቢያው ነው። ዋነኛው ግን። 

፩ኛ፦ ይሄ ነገር ከተፈጠረ በኋላ የጦር መኮንኖች የሃይማኖትና የኦሮሞ የበላይነት ሰለሰፈነ የራሳቸውን እርምጃ ሊወስዱ መዘጋጀታቸው፣ ብአዴን በተለይ ሄጵ ማለቱ። 

፪ኛ፦ ወያኔ አዲስ ሥልጠና በረኻ ላይ መጀመሯ እና ወደ ራያ አካባቢ አዳዲስ ቦታዎችን መያዝ በወልቃይትም ሙከራ መድረግ መጀመሯ። 

፫ኛ፦ 20,000 የኦሮሞ ወታደር ባህርዳር አካባቢ መስፈሩ። 

፬ኛ፦ ከኬንያ በሞያሌ በኩል ጦር ማስጠጋታቸው። 

፭ኛ፦ ወታደሩ ብዙም ትዕዛዝ እንደማይቀበል በድፍረት መግለፅ መጀመሩ። በተለይ ወለጋ ላይ። 

፮ኛ፦ እነ ግንቦት 7 ን የመሳሰሉ ጎምቱ ደጋፊዎቹ፣ ከነ ሚዲያዎቻቸው በድንገት ሄጵ ስላሉ። 

፰፦ በውጭ ያለው ዳያስፖራ በድጋሚ ሰልፍ መውጣት በመጀመሩ። 

፯ኛ፦ ደቡብ ኢትዮጵያ ሸኔ አለ ተብሎ ወታደር እንዲገባ መደረጉ በደቡብ የፈጠረው ጉርምርምታ እና ድርጊቱን ይደግፉ ከጀርባ ይዘውሩ የነበሩ ባለሃብቶች እና የገንዘብ ተቋማት በተለይ በዘመድኩን በኩል መጋለጥ መጀመራቸውና ወደ ኪሣራ ለማምራት ቀይ መብራት እንደበራባቸው ሲያውቁ በአንዴ ብዙ ጣጣ ስላመጣበት ነገርየውን ለሌላ ጊዜ እንዲተላለፍ አድርጓል። እንጂ አልቆመም። አይቆምም። አልቀረምም። 

“…ቀጥሎ የሚፈጠረው ቢሆን እንደሚከተለው ነው። እነ አቢይ ሽመልስ አሁን በዚህ ሰበብ የኦርቶዶክሱን ሙቀት በደንብ ለክተውበታል። ደካማውንና ጠንካራ ጎኑንም ዓይተውበታል። በደንብም ይገመግሙታል። ማን መገደል፣ ማን መታሰር፣ ማን ከሥራው ገበታው መፈናቀል እንዳለበትም ለቅመው ወስነዋል። ለምሳሌ አዋሽ ባንክ ኦርቶዶክሳውያንን በዲሲፒሊን ወዘተ ለማባረር ከጫፍ ደርሶ ነበር እኔን ጣለበትና አሁን ብናደርገው የበለጠ እንከስራለን ብለው ያዝ አደረጉት እንጂ አልተዉትም። በነገራችን ላይ ከአዋሽ ባንክ የሚባረር አንድ ባለማዕተብ ካለ ይንገረኝ። አሳያቸዋለሁ። ሰዎቹ ቂመኞች ስለሆኑ ባለማዕተቡን አርቲስት በለው፣ ጋዜጠኛ፣ ባለሃብት፣ ቄስ መነኩሴ ጳጳስ ሳይቀር ይበቀሉታል። ቱ…! ምንአለ በሉኝ። እሱን ደግሞ ጠብቁ። 

“…ከታሰሩት ውስጥ አብዛኞቹ ወደ አዋሽ አርባ ነው የተጋዙት። ይሄ በእነ ምህረተአብ፣ በእነ ልጅ ቢኒ፣ በእነፌቨን ላይ አልፈጸምም። እሱ ሌላ ጨዋታ አለው። አሁን ስለሚፈቱ ጊዜው ሲደርስ በድፍረት እናወጋለን። ለአሁኑ ከእነ ምህረተአብ ውጪ በግፍ ስለታሰሩ ምስኪኖችን ነው የማወራው። አዋሽ ዐርባ ስተወሰዱ፣ ወደ ሸዋሮቢት ስለተጋዙ ምስኪን ባለማዕተቦች፣ ስለሞቱ፣ ስለቆሰሉቱ ሁሉ ስለ እነሱ ነው የማዝነው። እነዚህ ሁሉ በአባቶች እንዳይካዱ ፍርሃት አለኝ። የብፁዕ አቡነ አብርሃም ለዘንዶው አቢይ የበዛ ምስጋና ማዥጎድጎድም ብዙም አላማረኝም። ሸክኮኛል።

“…የሆነው ሆኖ እነ አቡነ ሳዊሮስ ልክ እንደ እነ አባ ፀጋዘአብ ሲኖዶሱን ይቅርታ የጠየቁበትን ደብደባቤ ወይም ንግግር ሰእስከአሁን አላየሁም። ዐቢይ አሕመድ አርቅቆ በግድ አንብቡ ካላቸው ደብዳቤ በቀር ያየሁት ነገርም የለም። የደረሳችሁ ካላችሁ አጋሩኝ። በዚህ ሁኔታ ቅዱስ ሲኖዶሱም ያወገዘውን ውግዘት ሲያነሣ አላየሁም። ደግሞስ ለዚህ ሁሉ ኦርቶዶክሳዊ ደም መፍሰስ ምክንያት የሆኑ ነፍሰ ገዳዮች እንዴት እና በምን አግባብ ነው በዚህ ፍጥነት ወደ ክህነት አገልግሎታቸው የሚመለሱት? አይደለም እነሱ ልክ እንደ አቡነ እስጢፋኖስ እና እንደ አቡነ ሕዝቅኤል ተገደው ሳይሆን በራሳቸው ፈርተው የሸሹ እንደነ አቡነ ሩፋኤል ዓይነቱን ስለ ኤጴስ ቆጶሳት በተጻፍ ድንጋጌ መሠረት በሰባተኛ ጾክ 17 ላይ ባለው ሕግ ተቀጪ ናቸው። አይደለም ነፍሰ ገዳይ ጳጳስ ከሃገረ ስብከቱ የሸሸ ጳጳስ ከሹመቱ ይሻር ነው የሚለው የሥርዓት መጽሐፉ። 

“…መፍትሔው አሁንም ከእግዚአብሔር ጋር እኛው እጅ ላይ ነው ያለው። አቢይን ባለማመን፣ አባቶቻችንን ግን በማመን በትግላችን መቀጠል ነው። አቢይና ፓርቲው ወይ በባዮሎጂ፣ ወይ በራሱ ጉዳይ ይወገዳሉ። እሱ አያሳስበኝም። ከመወገዱ በፊት ግን ይተኛልናል ወይ ነው ጥያቄዬ። ለምሳሌ ትናንት ጎንደር ላይ የበረከት ስምኦንን ኔትወርክ ፈትቶ በመልቀቅ በብልፅግና ካድሬ ስም በጎንደር እስላሞቹን ሰብስበው ፈንጂ ለመቅበር ሲጥሩ ነበር የዋሉት። የጎንደር እስላሞችን ሰብስበው “በብጥብጡ ወቅት ማነው ያጠቃችሁ? ማነው የገደላችሁ? ማነው የሰደባችሁ? ብለው ነበር የብልፄ ካድሬዎች ሲወተውቷቸው የዋሉት።

“…ብልሆቹ የጎንደር ሙስሊሞች ግን “የተረሳ ነገር፣ ታርቀን ተስማምተን የቋጨነውን ለምንድነው እንደ አዲስ ማንሣት የፈለጋችሁት? ምን አስባችሁ ነው? በማለት ለጊዜውም ቢሆን የካድሬውን ሴራ ቢያከሽፉም ለዐማራ የታሰበ አደገኛ ነገር መኖሩን ግን ኢዩ ጩፋን መሆን አይጠበቅብኝም። የኦሮሚያ ብቻዋን መበጥበጥ እነ አቢይን እንቅልፍ ነሥቷቸዋል። ብአዴንም ቢሆን “አቢይ አህመድ በረከትን በዚህ ሰዓት የፈታው ለምን እነደሆነ ስለሚያውቁ አይተኙለትም። ብአዴኖች የማይተኙት ለዐማራ አዝነው ሳይሆን በበረከት ኔትወርክ ላለመበላት ሲሉም ጭምር ነው የማይተኙት።  

Filed in: Amharic