>

በሕይወቴ ጥቁር ጠባሳ የጣለብኝ እስር !! (ናትናኤል ያለምዘውድ)

በሕይወቴ ጥቁር ጠባሳ የጣለብኝ እስር !!

ናትናኤል ያለምዘውድ

ከታሰርኩባቸው እስሮች ትንሹ የሚባለው ይሄኛው እስር ቢሆንም ከፍተኛ ግፍና ማስጠንቀቂያ ያዘለ እስር ነው ፤  ዝርዝሩን በሰፊው እመለስበታለሁ ። ከመጀመሪያ ጀምሮ ማህተቤን እንድበጥስ ግፊት ቢደረግብኝም  ያንን ማደረግ እንደማልችል እና ለእኔ ሞት እንደሆነ ነግሬ አልበጥስም አልኩ !!  ከአንድ ቀን ጭቅጭቅ በኋላ  አራት ፖሊሶች ብቻዬን በማስጠራት ሳላስበው እጆቼን ከያዙ በኋላ

 በምላጭ ያንገቴን ማህተብ በጠሱት እቅም የማጣት ስሜት ተሰማኝ ፤ እንዲደበድብኝ ተሳደብኩ እነሱ ከድላ በላይ የሆነ ነገር እንዳደረሱብኝ ስለገባቸው ዝም አሉኝ ። መብላት መጠጣት አቃተኝ በአይኤስ አይኤስ በሰው ሀገር ማህተባችንን አልበጥስም ብለው የተሰው ወንድሞቼ  አይነት አቅም እንደሌለኝ ሲሰማኝ ልቤ ክፉኛ ተሰበረ ፤ኡፍፍ  ይህ ክፉ ቀን መቼም አረሳወም !!

ይህ እንዲህ እንዳለ ፤ሁሌም ከግፉዓን ጎን የሚቆመው ወንድማችን ጠበቃ ቤተማርያም አለማየሁ በዚህ ፈተና ወቅት ሙያዊ ግዴታው እንዳለ ሆኖ! እንደወትሮ አሁንም ፤ስለ ፍትህ ፤ስለ እውነት በማለት ከእኔ በደለኛ ጎን በመቆም ወንድሜ ቤተ እግዚአብሔር እድሜና ጤና ይስጥህ ፤ አመሰግናለሁ ።

ሁሌም ቢሆን የግፉአን ዓይንና ጆሮ በመሆን የበደለኞችን ድምጽ የምታሰሙ ፤ጋዜጠኞች ፤አክቲቪስቶች ክብር ለእናንተ ይሁን !!

ብቻ ፈተውኛል ለሁላቹም እግዚአብሔር ይስጥልኝ !!

Filed in: Amharic