>

የተዋሕዶ አብዮት መቀልበስ፤ ሐይማኖትና መንግስት ወይስ ሐይማኖትና ፖለቲካ? (መስፍን አረጋ)

የተዋሕዶ አብዮት መቀልበስ፤ ሐይማኖትና መንግስት ወይስ ሐይማኖትና ፖለቲካ?  

ካንድ አገር መንግስት የሚጠበቀው በሐይማኖት ጉዳይ እጁን አስገብቶ የማይፈተፍት፣ የሚደግፈውም ሆነ የሚቃወመው ሐይማኖት የሌለ ገለልተኛ መንግስት እንዲሆን ነው፡፡  መንግስት በሐይማኖት ጉዳይ እጁን አያስገባ ማለት ግን ሐይማኖት በመንግስት ጉዳይ አይግባ ማለት አይደለም፡፡  

መንግስት ስልጣን ከያዘ በኋላ የደጋፊወቹ ብቻ ሳይሆን ያገር መንግስት ስለሆነ፣ ሁሉንም ያገሪቱን ዜጎች (የመረጡትንና ያልመረጡትን) በእኩል ዓይን ማየትና ማስተናገድ ግዴታው ነው፡፡  ዜጎቹ ግን ያገሪቱን ሕግ ማክበር እንጅ መንግስቱን መውደድ አይጠበቅባቸውም፣ የማይውዱት ከሆነ ደግሞ መንግስቱን ለማውረድ ሕጋዊ መንገዶችን መጠቅም ሙሉ መብታቸው ነው፡፡  

በተመሳሳይ መንገድ መንግስት ሁሉንም ሐይማኖቶች በእኩል ዓይን ማየት ግዴታው ቢሆንም፣ ሐይማኖቶች ግን ሐይማኖታቸውን እንደ ፖለቲካ ኃይል በመጠቀም በምግባሩ የማይወዱትን መንግስት አለመደገፍና በሕጋዊ መንገድ ለማውረድ መእምኖቻቸውን ማነሳሳት ሙሉ መብታቸው ነው፡፡  የተዋሕዶ ብፁዓን አባቶች በተለይም ደግሞ አቡነ አብርሃም እና አቡነ ጴጥሮስ ያላወቁት ወይም ደግሞ ቢያውቁትም ለመተግበር የማይፈልጉት ይህን መብታቸውን ነው፡፡  ይህን መብታቸውን ባለመተግበር ደግሞ፣ ተዋሕዶን ለማጥፋት ቆርጦ የተነሳውን የጭራቅ አሕመድን ኦነጋዊ መንግስት ለማውረድ የተቀሰቀሰውን የተዋሐዶን አብዮት በማስቀልበስ ራሳችውን፣ ተዋሕዶንና ጦቢያን በጭራቅ አሕመድ ቁርጥምጥም አድርገው ለማስበላት አፋፍ ላይ ደርሰዋል፡፡ 

ሐይማኖት ፖለቲካ ነው፣ ቅልጥ ያለ ፖለቲካ፡፡  የክርስትና ሐይማኖት አባት ራሱ እየሱስ ክርስቶስ በሐብት ክፍፍል የሚያምን (ሁለት ካለህ አንዱን ስጥ የሚል)፣ ስግብግባዊ ብልጽግናን በጽኑ የሚኮንን (ሐብታም ከሚጸድቅ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ቢያልፍ ይቀላል የሚል)፣ 12ቱን ሐዋርያወቹን ከሐብታሞች ወይም ከምሁሮች ሳይሆን ከሠርቷደሮች (ዓሣ አጥማጆች) የመረጠ፣ ከማርክስ (Marx) የሚቀድም ከቡድሃ (Buddha) የሚከተል ሁለተኛው ያለማችን ኮሚኒስት (communist) ነው፡፡  የኩባው መሪ ፊደል ካስትሮ (Fidel Castro) በትክክል እንዳስቀመጡት “አዲስ ኪዳን በትክክል ቢተገበር ኖሮ ኮሚኒዝም ባላስፈለገ ነበር”።  የማርክስ ኮሚኒዝም ስብከት ከእየሱስ የትራራው ስብከት እምብዛም አይለይም፡፡ 

ሐይማኖት ፖለቲካ መሆኑን በትክክል ለመረዳት የዶናልደ ትራምፕን (Donald Trump) ክስተት ማጤን ብቻ ይበቃል፡፡  የዶናልድ ትራምፕ ጽንፈኛ ደጋፊወች ቁርዓን አቃጥሉ፣ ስደተኞች አትቀበሉ የሚሉ፣ አሜሪቃን በባርነትና በጅምላ ጭፍጨፋ ወደ ጨቀየው ወደ “ቀድሞ ታላቅነቷ” ለመመለስ (make America great AGAIN) ቆርጠው የተነሱ ጽንፈኛ ነጭ ብሔርተኞች (white nationalists) ናቸው፡፡  ሁሉም ተግባራቸውና ንግግራቸው ከክርስትና አስትምህሮ ጋር ፍጹም የሚቃረን፣ ባሁኗ አሜሪቃ ላይ ልክ እንደ ቀድሞዋ አሜሪቃ ነጮች አዛዥና ናዛዥ እንዲሆኑና የጌታሎሌ ግንኙነት ዳግም እንዲመሠረት የሚተጉ ነጭ ላዕልተኞች (white supremacists) ናቸው፡፡  እነዚህ ያሜሪቃ ነጭ ላዕልተኞች ራሳቸውን ወንጌላዊ ብለው የሚጠሩት፣ በክርስቶስ ወንጌል ስለሚያምኑ ሳይሆን፣ የነጭ ላዕልተኛ አጀንዳቸውን ለማራመድ የወንጌላዊነት ለምድ መልበስ ፍቱን ሆኖ ስላገኙት ብቻ ነው፡፡ 

  ፊታችንን ወዳገራችን ወደ ጦቢያ ስንመልስ ደግሞ በኦነጋዊው በጭራቅ አሕመድ የሚመሩት ኦነጋዊ አቶ ጳጳሶች ማለትም አቶ ሳዊሮስና ጓደኞቹ ሐይማኖት ፓለቲካ መሆኑን በግልጽ የተረዱ፣ ያማራ ጥላቻቸው ከፊታቸው ላይ በግልጽ የሚነበብ፣ አዲሳባ የኦሮሞ ናት ሲሉ ዓይናቸውን የማያሹ፣ ወንጌላቸው አዲስ ኪዳን ሳይሆን ኦሮሙማ የሆነ፣ ኦሮሚያና ብሔር ብሔረሰቦች እያሉ ስለ ኦሮሞ የበላይነት በግልጽ የሚናገሩ ኦነጋዊ ፖለቲከኞች ናቸው፡፡  እነዚህ ኦነጋዊ አቶ ጳጳሶች ተዋሕዶ ነን የሚሉት በተዋሕዶ አስትምህሮት ስለሚያምኑ ሳይሆን፣ የተዋሕዶን ለምድ መልበስ ኦነጋዊ አጀንዳቸውን ለማራመድ ፍቱን ሆኖ ስላግኙት ብቻ ነው፡፡ 

በፖለቲካዊ ብልጦቹ በነ አቶ ሳዊሮስ አንጻር የቆሙት አቡነ አብርሃምና አቡነ ጴጥሮስ ደግሞ ኦነጋዊው ጭራቅ አሕመድ በይሁዳው በዳንኤል ክብረት አማካኝነት እነሱንና ተዋሕዶን በልቶ ጦቢያን እንዳይበላ የሚታገሉትን አገር ወዳዶች ሁሉ ፓለቲካችሁን ከሐይማኖታችን ጋር አትቀላቅሉብን እያሉ የሚግስጹ፣ የሐይማኖትን ፓለቲካዊነት ያልተረዱ ፖለቲካዊ የዋሆች ናቸው፡፡  በዚሁ ፖለቲካዊ የዋህነታቸው ከቀጠሉበትና መጫወት የሚገባቸውን ፖለቲካዊ ጨዋታ ካልተጫወቱ ደግሞ፣ ጭራቅ አሕመድ በማስታረቅ ሰበብ በመኻላቸው ያስገባቸው ፖለቲከኞቹ እነ አቶ ሳዊሮስ በሚጫወቱት ፖለቲካዊ ጨዋታ በዝረራ ተሸንፈው፣ እንደ አሮጌ ቁና ተወርውረው የሚጣሉበት ጊዜ ሩቅ እንደማይሆን ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡

በታሪክ አጋጣሚ ምክኒያት የቅድስት አገራችን የጦቢያ ሞት ሽረት ያለው፣ ጦቢያን ለመግደል ቆርጦ በተነሳው በጭራቅ አሕመድ እጅ ሳይሆን፣ በብፁዓን የተዋሕዶ አባቶች እጅ ላይ ነው፡፡  እነዚህ ብፁዓን አባቶች ደግሞ ጦቢያን በነጭ ጅቦች ከመበላት ለማዳን አድዋ እንደ ዘመቱት እንድ ቀድሞ አባቶቻቸው ሐይማኖት ፖለቲካ መሆኑን ተርደተው፣ መጫወት የሚገባቸውን ፖለቲካዊ ጨዋታ ባግባቡ ከተጫወቱ፣ የጭራቅ አሕመድን ኦነጋዊ መንግስት ባጭር ጊዜ ውስጥ በማስወገድ፣ ራሳቸውንም፣ ተዋሕዶንም፣ ጦቢያንም በኦነጋዊ ጅቦች ከመበላት ማዳን ይችላሉ፡፡  አልመሸም፡፡   

በመጨረሻም ተዋሕዶን ለማጥፋት ቆርጦ የተነሳውን የጭራቅ አሕመድን ኦነጋዊ መንግስት ለማስወገድ የተቀሰቀሰው የተዋሕዶ አብዮት ባለቤት መላው የተዋሕዶ መዕምናን እንጅ ጥቂት ብፁዓን አባቶች ብቻ አይደሉም፡፡  ባለመሆናቸውም አውቀውም ሆነ ባለማወቅ፣ ባንድም በሌላም መንገድ ለዚህ አብዮት እንቅፋት በመሆን የተዋሕዶንና የልጆቿን ሞት እያፋጠኑ ያሉ የተዋሕዶ አባቶችን፣ የተዋሕዶ መዕምኖች አለመስማት ብቻ ሳይሆን ገለል ማድረግ ግዴታቸው ነው፣ ጉዳዩ የሞት ሽረት ጉዳይ ነውና፡፡  

ድኀረ ኪታብ (postscript)  

ኦነጋዊው ጭራቅ አሕመድ አባቶችን ማስታረቅ በሚል ሰበብ በተውነው ተውኔት ላይ በግራኝ አሕመድ ዘመን የተፈጸመውን የዝዋይን ታሪክ ያነሳው በዚያ ዘመን ኦሮሞ የሚባል ብሔር ቀርቶ ብሐረሰብ በጦቢያ ውስጥ እንዳልነበር ጠፍቶት ሳይሆን፣ አዲሳባን ኬኛ ብሎ ለመሰልቅጥ እንዳሰበው፣ ተዋሕዶንም ኬኛ ብሎ ለመሰልቀጥ በነደፈው (ይልቁንም ደግሞ እነ ሌንጮ ለታ በነደፉለት) ፖለቲካዊ ጨዋታ መሠረት ብቻ ነው፡፡  ኦሮሞ ጦቢያ የገባው ግራኝ በቀደደለት በር ነበር፣ ኦሮሙማ ጦቢያ የገባው ወያኔ በቀደደለት በር እንደሆነ ሁሉ፡፡  ኦነግ ደግሞ ጨለማን ተገን አድርጎ ተክላካይአልባ (defenceless) ደካሞችን ከማረድና ከማወራርድ በስተቀር፣ በታሪኩ አንድም ቀን ከታጠቀ ባላጋራ ጋር ተዋግቶም ሆነ አሸንፎ የማያቅ፣ ያልተዋጋውን ተዋጋሁ፣ ያልሰበረውን ሰበርኩ የሚል፣ የሌሎችን ትግል የራሱ አስመስሎ በባዶ ጉራ የሚንጫጫ፣ ባንድ ሙቀጫ የሚወቅጥ ተልባ ነው፡፡    

መስፍን አረጋ 

mesfin.arega@gmail.com

Filed in: Amharic