>

መንግስት ለቀጣይ ፕሮጀክቱ ጵጵስናን የማራከስና የማቃለል ስራ በሰፊው እየሰራ ነው ...!

መንግስት ለቀጣይ ፕሮጀክቱ  ጵጵስናን የማራከስና የማቃለል ስራ በሰፊው እየሰራ ነው …!

ዘ የኔታ

1 ጳጳሳት ልክ እንዳንተ ውሸታምና ቀጣፊ እንደሆኑ አድርገህ እንድታስብ ትላንት ተስማምተው ዛሬ ይሽራሉ እንድትል ነው ለምን እንደዛ እንድታስብ ተፈለገ???

መንፈስ ቅዱስ የሚመራውን የአባቶችህን ጉባኤና ትዕዛዝ ሰምተህ አንገትህን ለሰይፍ ግንባርህንም ለጥይት ሰጥተሀል።  ነገ ላይ  ቤተክርስቲያን እና አባቶች ድረስልን ሲሉህ ደሞ ነገ ዞረው ለሚስማሙት ለምን ብዬ ከፊት ልሰለፍ እንድትል ይህ ሴራ እየተጎነጎነ ነው::

2 ጡረታ ልውጣ ያሉትም አባት ያውቁታል ስርዓቱን መኖራቸው ለስጋቸው  እንዳልሆነ ታዲያ ለምን አሉ አትልም?

ሲነዶስን እንደ መስሪያ ቤት አባቶችን  እንደ ሰራተኛ አድርገህ እንድታስብ እና መንፈስ ቅዱስ የሚመራውን ቅዱስ ሲኖዶስ ከልብህ ላይ አስክዶ እንደመዘጋጃ አንድ ተቋም መሆኑን እንድታስብ ይህ ሴራ በእቅድ እየተሰራ ነው። 

የመጨረሻው ይሄን ሁሉ ለምን አትልም?

የበቀደመ ሴራ ለምን ከሸፈ? ሕዝቡ ቅዱስ ሲኖዶስ ሚለውን ብቻ ስለሰማ እና የአባቶችን ቃል እንደ እግዚአብሔር  ቃል ቆጥሮ ከፊት ስለቆመ ሊሰሩት ያሰቡት ሁሉ ከሽፏል። 

ስለዚህ የመንጋውን መሪ ክብርና መደመጥ  የቅዱስ ሲኖዶስንም ክብር ከልብህ ካወጣ በቀላሉ መንጋው ተበተነ ማለት አይደል?

ይሄ ደግሞ ቤተክርስቲያኗን ለማፍረስ ከግማሽ በላይ መንገድ ያስጉዛቸዋል።  

 ወንድሜ እየሆነ ያለው ይኸው ነው ታዱያ መፍትሔው ምንድነው አትልም?

ዛሬም ከትናንቱ በላይ  ዐይንህን ከቤተክርስቲያን  ጆሮህንም  ከቅዱስ ሲኖዶስ  ትዕዛዝ ላይ አታንሳ!!

Filed in: Amharic