>

እንደ ቱትሲ የኾነው የአማራ ሕዝብ ያለው ብቸኛ አማራጭ እንደ ፖል ካጋሜ መሆን ነው! (አቻምየለህ ታምሩ)

እንደ ቱትሲ የኾነው የአማራ ሕዝብ ያለው ብቸኛ አማራጭ እንደ ፖል ካጋሜ መሆን ነው!     

አቻምየለህ ታምሩ

ከታች በስተ ግራ በኩል የሚታየው ፎቶ በሩዋንዳ በመንግሥትነት ተሰይሞ የነበረው የሁቱ እንተርሀሞዮች አገዛዝ በቱትሲዎች ላይ ያካሂድ የነበረውን የዘር ማጥፋት ጦርነት በመሸሽ ከዋና ከተማቸው ከኪጋሊ የሚሸሹ ሩዋንዳውያንን የሚያሳይ ፎቶ ነው። 

በቀኝ በኩል የሚታየው ፎቶ ደግሞ በዐቢይ አሕመድ የሚመራው የኦሮሙማ አረመኔያዊ  አገዛዝ በአማራ ሕዝብ ላይ የሚያካሂደውን የዘር ማጥፋት በመሸሽ ከዋና ከተማቸው ከአዲስ አበባ  ነፍሳቸውን ለማትረፍ የሚሸሹ የአማራ ተወላጆችን የሚያሳይ ፎቶ ነው።    

የተቀረው አለም ጆሮ ዳባ ልበስ ብሎ በየዕለቱ እስከ አስር ሺሕ የሚደርሱ ቱትሲዎችና ለዘብተኛ ሁቱዎች ለሶስት ወራት የተጨፈጨፉበት የሁቱ አገዛዝ የዘር ማጥፋት መቋጫ ያገኘው በወቅቱ የ36 አመት ጎልማሳ በነበሩት ስደተኛ ፖል ካጋሜ የሚመራው የርዋንዳ አርበኞች ግንባር ሥልጣን ላይ ያለውን መንግሥት አሸንፎ አገሪቱን በቁጥጥር ሥር ሲያውል ነበር።

በአገራችንም በዐቢይ አሕመድ የሚመራው የኦሮሙማ አረመኔያዊ አገዛዝ በአማራ ሕዝብና ኦሮሞ አይደላችኹም ወይም ኦሮሞ አትመስሉም በተባሉ ኢትዮጵያውያን ላይ እየተካሄደ ያለው የቱትሲ ቅጂ  የዘር ማጥፋትና የጅምላ ፍጅት እንዲቆም ማድረግ የሚቻለው ግፉአን የዐቢይ አሕመድን የኦሮሙማ አፓርታይዳዊ አገዛዝ አሰወግደው  አገራቸውን ቁጥጥር ስር ሲያውሉ ብቻ ነው።

ባጭሩ እንደ ቱትሲ የኾነው የአማራ ሕዝብ ያለው እንደ ሁቱዎቹ ኢንተርሃሞዮች ከኾነበት የኦሮሙማው አረመኔ የዘር ማጥፋት ለመትረፍ ያለው ብቸኛ አማራጭ እንደ ፖል ካጋሜ መሆን ብቻ ነው!

Filed in: Amharic