ጭራቅ አሕመድ ግርማ የሺጥላን ገድሎታል፤ እንኳን ገደለው !
ጭራቅ አሕመድ ሆይ፣ ጅማሮህ ጡሩ ነውና ቀጥልበት፣ ሳትጨርስ እንዳታቆም፡፡
አማራን ለሚበላው ለጅቡ ለኦነግ ጥላ ከለላ ስለነበር፣ በሂወት ዘመኑ ግርማ የጅብጥላ ይባል የነበረውን ግርማ የሺጥላን የጅቦቹ አለቃ ጭራቅ አሕመድ ገድሎታል፡፡ የገደለበትን ዋና ዋና ምክኒያቶች ደግሞ ግድያውን ከመፈጸሙ በፊት ባዘጋጀው ወይም ደግሞ አማካሪወቹ እነ ዳንኤል ክብረት ባዘጋጁለትና ግድያውን ከፈጸመ በኋላ በብርሃን ፍጥነት ባወጣው መግለጫ በግልጽ ተናግሯል፡፡ እነሱም የሚከተሉት ናቸው፡፡
- አንደኛው ምክኒያት ያማራን ሕዝብ እርስበርሱ ለማጫረስ ነው፡፡ ይህን ዓላማውን የገለጠው ደግሞ “ተወልዶ ባደገበት አካባቢ ከኛ የተለየ ሐሳብ ማሰብ አልነበረበትም ብለው የሚያምኑ ነውጠኛ ጽንፈኞች” በሚለው ሐረግ (phrase) ነው፡፡ ይህን ያለው ደግሞ አማሮች ተወልደው ባደጉባቸው በወለጋና በቤንሻንጉል እንዳይኖሩ ላምስት ዓምታት ያህል ማስጨፍጨፉንና ማፈናቅሉን የረሳንለት መስሎት ነው፡፡ ጭራቅ አሕመድ አማራን በኦነግና በወያኔ ማስጨፍጨፉ ስላላርካው፣ ርስበርሱ ለማጫረስ ማድረግ የሚችለውን ሁሉ አድርጓል፣ እያደረገ ነው፣ ማድረጉንም ይቀጥላል፣ ያማራ ሕዝብ ጭራቅ አሕመድን ባስቸኳይ ጨርቅ አድርጎ እንዳይቀጥል ካላደረገው በስተቀር፡፡
- ሁለተኛው ምክኒያት ያማራን ሕዝብ በጽንፈኝነት ፈርጆ ባማራ ሕዝብ ላይ የከፈተውን የዘር ማጥፋት ዘመቻ ለማጧጧፍ ነው፡፡ ይህን ዓላማውን የገለጠው ደግሞ “ጽንፈኝነትን በጊዜ ታግለን ካላስወገድነው በስተቀር ወደ መጨራረስ እንደሚወስደን ጉልህ ማሳያ ነው” በሚለው ሐረግ (phrase) ነው፡፡ የጭራቅ አሕመድ ሸኔ በመቶ ሺ የሚቆጠሩ አማሮችን አርዶ፣ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩትን ሲያፈናቅል፣ ጭራቅ አሕመድ አንድም ቀን “ጽንፈኝነትን በጊዜ ታግለን ካላስወገድነው” ብሎ መዛት ቀርቶ፣ ያንድ ደቂቃ ሐዘን በፓርላማ እንዳይደረግ ከልከሎ ምንም እንዳልተፈጠረ ድምጹን አጥፈቶ ነበር፡፡ አማራን በጽንፈኝነት ለመክሰስ ሲፈልግ ግን፣ እንደ ጅራፍ እራሱ ገርፎ በዚያኑ ቅጽበት እራሱ ጮኸ፡፡
- ሶስተኛው ምክኒያት ደግሞ ባማራ ሕዝብ ላይ ለከፈተው መጠነ ሰፊ የዘር ማጥፋት ዘመቻ በተዛዋሪ መንገድ ገንዘባዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ዲፐሎማሲያዊና ፕሮፓጋንዳዊ ደጋፍ የሚያደርጉለት ምዕራባውያን መንግስታትና ሚዲያወች፣ ያማራን ሕዝብ ባሸባሪነት ፈርጀው የጭራቅ አሕመድን የዘር ማጥፋት ዘመቻ በግልጽ እንዲደግፉ ምክኒያት (pretex) ለመፍጠር ነው፡፡ ይህን ዓላማውን የገለጠው ደግሞ “ሐሳብን በሐሳብ ማሸነፍ ያቃታቸው” በሚለው ሐረግ (phrase) ነው፡፡ ይህን ያለው ደግሞ እስክንድር ነጋ ሐሳብ በማቅረቡ ብቻ “ጦርነት እንገባለን” ማለቱን የጦቢያ ሕዝብ የሚረሳለት መስሎት ነው፡፡ እሱ ራሱ ዛሬ የተናገረውን ነገ የማይደግም የሾርት ሜመሪ ሰለባ በመሆኑ፣ ሁሉንም ኢትዮጵያዊ እንደሱ ሾርት ሜሞሪያም አድርጎ በመቁጠሩ ነው፡፡
ጭራቅ አሕምድ ግርማ የሽጥላን የገደለው፣ ባማራ ሕዝብ ላይ የሚያካሂደውን ጭፍጨፋ አጥናክሮ ለመቀጠል ምክኒያት ለመፍጥር ቢሆንም፣ በሌላ በኩል ግን ያማራን ሕዝብ ከውስጥ ሁኖ ይቦረቡር የነበረውን ነቀርሳ ነቅሎ በመጣሉ ላማራ ሕዝብ ከፍተኛ ውለታ ውሎለታል፡፡ ጭራቅ አሕመድ አማራን ቆረጣጥሞ የሚበላ ኦነጋዊ አውሬ ቢሆንም፣ ጥርሶቹ ግን ሙሉ በሙሉ ብአዴኖች ናቸው፡፡ ብአዴኖች በድን ከሆኑ ደግሞ፣ ጭራቅ አሕመድ ጥርስ የሌለው ጭራቅ ስለሚሆን፣ ያማራ ሕዝብ ጭራቅ አሕመድን ባጭር ጊዜ ውስጥ ጨርቅ ይደርገዋል፡፡ ያማራ ሕዝብ ጭራቅ አሕመድን ጨርቅ ካደረገ ደግሞ ወያኔና ኦነግ እዳቸው ገብስ (ቀላል) ነው፡፡
ስለዚህም፣ ጭራቅ አሕመድ ግርማ የሺጥላን በመግደሉ ያወለቀው አማራን የሚቆረጣጥምበትን የገዛ ራሱን ጥርስ ነውና፣ ያማራ ሕዝብ እንኳን ገደልከው ሊለው ይገባል፡፡ በተጨማሪ ደግሞ የቀሩትን ብአዴናዊ ጥርሶቹን (ይልቃል ከፋለ፣ አገኘሁ ተሻገር፣ ሰማ ጡሩንህ፣ አበባው ታደስ ….) ባስቸኳይ እንዲነቅላቸው ያማራ ሕዝብ ጭራቅ አሕመድን ሊያበረታታው ይገባል፡፡ በተለይም ደግሞ ጭራቅ አሕመድ ያማራን ሕዝብ የሚዘነጣጥልባቸውን ሁለቱን ክራንቻ ጥርሶቹን (canine teeth) ማለትም ደመቀ መኮንንን እና ተመስገን ጡሩነህን ቢመነግላቸው፣ ያማራ ሕዝብ ለኢትዮጵያ አምላክ ትልቅ ምስጋና ማቅረብ አለበት፡፡ ጭራቅ አሕመድ ሆይ፣ ጅማሮህ ጡሩ ነውና ቀጥልበት፣ ሳትጨርስ እንዳታቆም፡፡
መስፍን አረጋ
mesfin.arega@gmail.com