የከሸፈው መንግስት በገዳማት እና በመስጊዶች ላይ የሚያደርሰውን ፈረሳ እና ግድያ በአስቸኳይ እንዲያቆም እንጠይቃለን
ከባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ
መንግስት ለተከታታይ ስድስት ቀናት በደብረ ኤልያስ ገዳም ላይ ከፍተኛ የሆነ የከባድ መሳሪያ ውርጅብኝ በማሳረፉ ምክንያት ገዳሙ በከባድ መሳሪያ እንደተጎዳ እና በርካታ የገዳሙ መነኮሳት ለእልፈተ ህይወት እንደተዳረጉ ለመረዳት ተችሏል፡፡
የደብረ ኤልያስ ገዳም በውስጡ በርካታ አብያተ ክርስቲያናት ያቀፈ ሲሆን ጥቂቶቹ የመድኃኒያለም፣ የዮሐንስ፣ የኪዳነ ምህረት፣ የስላሴ ታቦትት ይገኙበታል፡፡ ላለፉት አምስት እና ስድስት ቀናት የኦህዴድ/ኦነግ ብልፅግናን ጦር ከመቶ ሁለት በላይ ኦራል መኪና አሰልፎ በነዚህ መነኮሳት፣ቀሳውስት እና ፀበልተኞች ላይ የከባድ መሳሪያ ዝናብ ሲያዘንብባቸው ሰንብቷል፡፡ከግንቦት 18/2015 ጅምሮ ደግሞ ከ25 በላይ የኦራል መኪና ተጭኖ እንደገባ የሚደርሱን መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ በዚሁ ገዳም ከ3000 እስከ 3500 ነዋሪዎች የሚገኙ ሲሆን፣የአካባቢው አርሶ አደር ገበሬዎችም የእለት ከእለት እንቅስቃሴያቸውን እንዳያደርጉ እግር ከወረች ታስረዋል፡፡ ገበሬዎች እርሻ እንዳያርሱ መንገድ ተዘግቶባቸዋል፡፡ ገዳሙ በዲሽቃ፣ በሞርታር እንዲሁም በዙ 23 በመደብደቡ ምክንያት በገዳሙ የሚገኙ የጊወርጊስና የመድኃኒያለም ቤተክርስቲያናት ጉልላቶች ተሰበብረው ወድቀዋል፡፡ በተጨማሪም በደብረ ኤሊያስ ወረዳ በገነት ቀበሌ ስር ወደ አባይ በርሃ መውረጃ የሚገኘው ተክለ ሃይማት ገዳም የጥቃቱ ሰለባ ሆኗል፡፡ በተመሳሳይ በገዳሙ የሚገኙ ንፁሃን ፀበልተኞች፣ አባቶች፣ እናቶች፣ መነኮሳት እና ቀሳውስት ባጠቃላይ እነዚህ ሁሉ የዚህ ጥቃት ሰለባ ሁነዋል፡፡ በተጨማሪም በ23/09/2015 ከሁለት መቶ በላይ ሴት መነኮሳትን በማረድ እጅግ ፋሽስታዊ የሆነ ድርጊት ተፈፅሟል፡፡
የኦህዴድ/ኦነግ ብልፅግናን ሠራዊት ይህን ሁሉ ጥቃት የሚፈፅመው በአካባቢው ፋኖ ይሰለጥናል በሚል ምክንያት ሲሆን፣ ዋናው ዓላማ ግን አብያተ ክርስቲያናትንና ገዳማትን እንዲሁም ህዝበ ክርስቲያኑን ለመጨፍጨፍ ታስቦ ነው፡፡ ፋኖ የኦህዴድ/ኦነግ ብልፅግናን በትረ-ስልጣንን ያፀና፤ ሀገርን ከመበታተን የጠበቀ፤ ለሀገሩ ደሙን ያፈሰሰ ኃይል እንጅ የሚሳደድ ኃይል አልነበረም፡፡ የንፁሀንን ደም የሚያፈሱ፣ሀገርን ለማፍረስ ቀን ከሌት የሚባዝኑ ኃይሎችን አቅፎ እና ደግፎ የያዘ መንግሥት፣ለሀገሩ ሲል ደሙን የሚያፈሰውን ፋኖን የሚያሳድድበት ምንም አይነት የህግም ሆነ የሞራል ምክንያት ሊኖረው አይችልም፡፡
የኦህዴድ/ኦነግ ብልፅግና መንግሥት በአማራ ህዝብ ላይ ጦርነት በማወጅ ክልሉን የጦር አውድማ ለማድረግ ያለ የሌለ ኃይሉን እየተጠቀመ ይገኛል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ ላለፉት ሁለት ሳምንታት በአዲስ አበባ እና በአዲስ አበባ ዙሪያ ከሰላሳ ሰባት በላይ መስጊዶች በኦህዴድ/ኦነግ ብልፅግና መራሹ ኃይል ፈርሰዋል፤ እየፈረሱም እንደሚገኙ በመገናኛ ብዙሃን ተገልፆል፡፡ ስርዓቱ ጥንታዊ የሆኑ የእምነት ተቋማትን የሚያፈርስበት ምክንያት የብልፅግና ወንጌልን በኢትዮጵያ ዋንኛ እምነት አድርጎ ለመትከል በጀመረው ጉዞ ዋንኛ እንቅፋቶች ሆነውብኛል ብሎ ስለሚያምን ነው፡፡እነዚህ ሁሉ የኦሮሙማ አገዛዝ ድርጊቶች የስርዓተ መንስግቱ እብሪት መገለጫዎች ብቻ ሳይሆኑ፣ እንደውም የድርጊቱ ዋንኛ ተልእኮ በኢትዮጵያ ጥንታዊ፣ ሃገራዊ እና ህዝባዊ የሆኑ የኦርቶዶክስ ክርስትናና የእስልምና እምነቶችን አጥፍቶ በምትካቸው ከፈረንጅ ገንዘብ የሚያገኝበትን የብልፅግና ወንጌል “እምነት” ለማስፋፋት አመች ሁኔታ እንዲፈጠርለት ለማድረግ ነው፡፡
ከላይ በተጠቀሱ እሳቤዎች ላይ በመንተራስ ባልደራስ ለሚከተሉት ጉዳዬች ትኩረት እንዲሰጣቸው ጥሪውን ለሰፊው ህዝብ ያቀርባል።
- የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ድምፅዋን በማሰማት እና ምዕመኑን በማስተባበር በመንግስት ላይ ተፅዕኖዋን እንድትፈጥር ጥሪያችንን እናቀርባለን፤
- የኢትዮጵያ የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት (መጅሊስ) መስሊሙን ማህበረሰብ በማስተባበር በመንግስት ላይ ተፅዕኖውን እንዲፈጥር ጥሪያችንን እናቀርባለን፤
- የኦህዴድ/ኦነግብልፅግና መንግስት የአማራን ህዝብ ለመጨፍጨፍ እና ክልሉን የጦር አውድማ ለማድረግ አቅዶ እየተንቀሳቀሰ ስለሆነ፣የአማራ ህዝብ ትግሉን ህዝባዊ በማድረግ የተቃጣበትን ወረራ ለመመከት በሰላማዊ መንገድ ትግሉን እንዲያቀጣጥል ጥሪያችንን እናቀርባለን፣
- የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን፣ የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ጉባኤ፣ የሰብዓዊ መብት ተቋማት፣ የምርምር ተቋማት፣ ምሁራን፣ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ወዘተ በሙሉ ድምፃችሁን ከፍ አድርጋችሁ ይህን በአማራ ህዝብ ላይ የተቃጣ፣ የኦሮምያና የትግራይ ሪፖብሊኮችን ለመመስረት አልሞ የተነሳ ፀረ- ኢትዮጵያ የሆነን ህገ ወጥ ዘመቻ እንድታወግዙ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡
ይህን በፅንፈኛ ብሔርተኝነት የሚመራ ስርዓት በፅናት እስካልታገልነው ድረስ ሀገርን ለመበታተን ከመቸውም ጊዜ በላይ እየተንቀሳቀሰ ስለሆነ፣ የክልል መንግስታት፣ አመራሮች፣ የስርዓቱ ሹመኞች ከወደፊት ሃገራዊ ተጠያቂነት ለማምለጥ ካሰባችሁ የተቃውሞ ድምፃችሁን በማሰማት እና አቋማችሁን ግልፅ አድርጋችሁ እንድትቃወሙ እናሳስባለን!
የዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ጥንታዊ በሆኑ የኢትዮጵያ ቤተ-እምነቶች ላይ የኦሮሙማው መንግስት እያደረገው ያለውን ኢሰብዓዊ ድርጊት ማውገዝ ብቻ ሳይሆን፣ ጉዳዮን በሄግ የሚገኘው የዓለም አቀፍ የወንጀል ዳኝነት ሰጭ ፍርድ ቤት እንዲያየው እንዲደረግ ግፊት እንዲያደርግ እንጠይቃለን፡፡
ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ
የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ
ግንቦት 24/2015
አዲስአበባ
Tel. 251-1- 26 86 77 / 09 83 01 77 69