>
5:18 pm - Sunday June 15, 5130

የሣጥናኤል ሎሌዎች ኦርቶዶክስንና ሀገርን ለጨለማው መንግሥት እንዴት እንደሸጡ ...! (ይነጋል በላቸው)

የሣጥናኤል ሎሌዎች ኦርቶዶክስንና ሀገርን ለጨለማው መንግሥት እንዴት እንደሸጡ ተመልከቱ!

ይነጋል በላቸው

“መልካም ንባብ” ብዬ እስክሰናበታችሁ ድረስ ያለው ሃሳብ የኔ የይነጋል በላቸው የመግቢያ አንቀጽ ነው፡፡ ሀገራችን አሁን ወዳለችበት አዘቅት እንዴት እንደወረደች መምህር ዘመድኩን በቀለ በግልጽ እንደሚከተለው አስቀምጦታል፡፡ መተፋፈርና ይሉኝታ የለም፡፡ እኔም በበኩሌ ለበርካታ ጊዜያት በተለይ ኦርቶዶክስን ለማጥፋት የሚደረገውን ውስጣዊና ውጫዊ ጥረት ገልጫለሁ – ሙስናውን፣ ድንቁርናውን፣ ሴሰኝነቱንና ሦዶማዊነቱን፣ ዘረኝነቱን፣ ጎሠኝነቱን፣ የቀኖና ጥሰቱን ወዘተ. ብዙዎቻችን ገልጠናል፡፡ ኦርቶዶክስ እየጠፋች ያለችው በውስጧ በተሰገሰጉና አሁን አሁን ደግሞ ለይቶላቸው በቁጥጥራቸው ሥር ባዋሏት የአጋንንት አገልጋዮች መሆኑ ከታወቀ ቆዬ፡፡ ሣጥናኤል ከቫቲካን እስከ አምስት ኪሎ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ተቆጣጥሯል፡፡ የትንቢቱ ፍጻሜም የደረሰ ለመሆኑ ዋቢ መጥቀስ አያሻም፡፡ የተነገረው ሁሉ አንድም ሳይቀር ተፈጽሟል፡፡ ጤናማው የተፈጥሮ ህግ ተሸሮ “ወንድ ለወንድና ሴት ለሴት ቢጋቡ ችግር የለውም፤ የፆታ ምርጫ የግለሰብ ጉዳይ ነው” የሚሉ ሊቃነ ጳጳሣትና የሃይማኖት አባቶች አብያተ ክርስቲያንን በሚመሩባት ምድር ዓለም ልትጠፋ የቀራት የመጨረሻው ፊሽካ ብቻ ነው ቢባል ስህተት የለውም፤የእግዜሩና የሰው የጊዜ አቆጣጠር በመለያየቱ ይመስላል እንዲያውም በጣም ዘገዬ፡፡ ለማንኛውም የሀገራችንን ጉድ ዘመድኩን በቀለ በሚገባ ተንትኖታልና ከዚህ በታች ያስቀመጥኩትን ከቴሌግራም ገጹ የተወሰደ ሰፋ ያለ ማብራሪያ እንድታነቡ እጋብዛለሁ፡፡ መልካም ንባብ፡፡ ⇓

መምህር ዘመድኩን በቀለ

…ሙሉ ለሙሉ እንዳይባል ጥቂቶችን ለዘር አስቀርቶልን አሉልን እንጂ አሁን አሁን በቅድስናው፣ በመንፈሳዊ ሕይወቱ፣ በትምህርቱ፣ በመልካም ሥነ ምግባሩ ተመርጦ፣ ተመዝኖ ጵጵስና መሾም ከቀረ ሰነባበተ። ምንም ብንሸፋፍነው፣ መንፈሳዊ ለማስመሰል፣ አፈቀላጤ አለስልሶ አራጅ በየሚዲያው ልከን መላልሰን ብንወቅጠው ያው እምቦጭ ነው። “ልትጠፋ ግፋ ቢል 50 ዓመት ለቀራት ቤተ ክርስቲያን የምን መጨነቅ ነው” የሚል ደፋር እንጀራዋን እንጂ እሷን የማይፈልግ ጳጳስ የተሾመባት ቤተ ክርስቲያን መከራዋ ባይጸናባት ነው የሚገርመው። 

…አንድ ዲያቆን በአንድ ደብር ለመቀጠር ከሊቀ ጳጳሱ ጀምሮ በተዋረድ በተሰለፉ ደላሎች አማካኝነት የተመደበበትን ጉቦ ከፍተኛ ገንዘብ መክፈል ዶግማ ከሆነ ቆየ። ካህንም እንደዚያው። የደብር አለቆች ክፍያም ከፍ ያለ ነው። ጳጳስ ለመሆን ደግሞ አሁን እንደምትሰሙት ዋጋው 3 ሚልዮን ብር ደርሷል። 3 ሚልዮን ብር ከፍሎ የጰጰሰ ሰው ምን ሊፈጥር እንደሚችል ብቻ መገመት ነው። በአሁኑ ሹመት 3 ሚልዮን የከፈሉቱ ወላዶች በደስታ የራት ግብዣ ሲደረግላቸውም ተመልከተናል። በትምህርታቸው፣ በሥነ ምግባራቸው የተመረጡ የሉም ማለት ግን አይደለም። አሉ። 

…ተሿሚዎቹ አራጣ ተበድረው፣ የባንክ ዕዳ ገብተው፣ ገሚሶቹ ሃብት ንብረታቸውን ሽጠው፣ ከምዕመናንና ከካህናት መዋጮ ተደርጎላቸው፣ የተጠየቀውን ጉቦ ከፍለው እስከመሾም የደረሱ አሉ። የፖለቲካ ድርጅቶች፣ ለጥቅማቸው ሲሉ ያሾሟቸው፣ በማኅበራት ፍላጎት ለጥቅማቸው ሲሉ ከፍለው ያሾሟቸው፣ አንዳንድ ግለሰቦችም ጭምር ስለ ብዙ ምክንያት ከፍለው ጭምር ያሾሟቸው አሉ። በዘር፣ በጎሳ፣ በዝምድና፣ በጎጥ፣ በጓደኝነትም የሚመረጡም አሉ። ቀድመህ አንተ ግባ ከዚያ እኔ እከተላለሁ የሚለውም ብዙ ነው። 

…የ3 ልጆች አባት ሆኖ ጳጳስ መሆን ነውር ነው። ዕቁባት አስቀምጦ መሾምም ነውርም፣ በደልም፣ ወንጀልም ነው። የተቀረጸ የፎን ሴክስ ያለው ሰው፣ ሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎች የሚንቁት ሰው አባት ነኝ ብሎ ሲባርከኝ እግዚአብሔር ያሳያችሁ። ፈረንጅ ሴት ያውም አሜሪካዊት በመንበረ ጵጵስናው አምጥቶ የሚተኛ፣ ከዚያም አልፎ በቴክስት ፍቅር የሚሠራ ቅሌታም ከእኔ የባሰ ወራዳ ተግባር ላይ ያለ ሰው እንዴት አባቴ ነው እለዋለሁ። በዝሙት ቅሌት ምክንያት የተባረረን ሰው መስቀል አስይዞ በሹመቱ ማስቀጠል በራሱ የጥፋቱ ተባባሪ መሆን ነው። 

…ቤቱ ልትጠይቀው የሄደችን መነኩሴ አስገድዶ የሚደፍር፣ ከደፈረም በኋላ የሚያስወልድ ጰጳስ እንዴት ነው አባቴ ብዬ የምከተለው። ” ዘመዴ ሁሉም ልጅ አለው ለምን እኔን ብቻ በአግቦ፣ በሽሙጥ ትሰድበኛለህ” ብሎ ሽምግልና የሚመጣብኝን ቅሌታም እንዴት ጳጳስ ብዬ ከእጁ ቡራኬ እቀበላለሁ? አራት ኪሎ የቤተ ክርስቲያኒቱ ቤቶች ላይ ከገዳም አስኮብልለው አምጥተው ያስቀመጧቸው ሴት መነኮሳት ለላንቲካ ነው እንዴ? ከሴት በዘለለ ነውር ውስጥ የተዘፈቁም እንዳሉ እኮ ግልፅ የሆነ ነገር ነው ያለው። ሴት መነኮሳትን ለማነውር፣ ከክብር ለማሳነስ የሚታትሩ የተቀረጸ ዶክመንት ያለባቸው የትየለሌ ናቸው። ብንሸፍነው መከራው ነው የተረፈን። 

…የሆነ ሰይጣናዊ ግሩፕ ሰተት ብሎ ገብቶ መንበሩን እየተቆጣጠረው እንዳለም ይሰማኛል። ሴቶቹ ተደፈርን ብለው አልታመን ሲሉ ሲደፈሩ የሚያሳይ ቪድዮ ቀርጸው ወስደው ለሊቀ ጳጳሱ አሳይተውም “ተዉ ተዉ ሰው ቢሰማ ሃይማኖታችን ነው የሚዋረደው፣ ሰይጣን አሳስቶት ነው፣ ተዉ ተዉ እምቢ ብላችሁ ወደ ሕዝብ ከወሰዳችሁ፣ ራሴው ሂዳችሁ ጠይቁ እና የሚሏችሁን ንገሩኝ ብዬ የላኳቸውን ተጎጂ ሴቶች “ዘመድኩን እጅ ይሄ መረጃ ከገባ በይፋ ነው የማወግዛችሁ፣ ለሕይወታችሁም ያሰጋችኋል” ተብለው ከከባድ ማስጠንቀቂያ ጋር ተሸማቀው የተመለሱ እህቶች አሉ። መነኩሴ ለመነኩሴ ተደራጅቶ እየዘረፈ፣ እየዘሞተ በሃይማኖት አባትነት ስም እስከመቼ ነው ወንጀል የሚሠራው። አንድ ሰባኪ፣ አንድ መነኩሴ ከአንድ ዓለማዊ የበለጠ ነውሩን እንደ ጀግና በአደባባይ ሲያዝረከርክ አሳፋሪ ነው። ይዘገንናል። 

…ጳጳስ በሞተ ቁጥር የቤተ ክርስቲያን ንብረት ከመውረስ ልጅ ነኝ ብለው የሚመጡትን ቤት ይቁጠራቸው። የጳጳስ አስከሬን አፅሙ ወጥቶ በዲኤንኤ ልጅነቴ ይረጋገጥልኝ ብለው በፍርድ ቤት ያስወሰኑ የጳጳሳት ልጆችን የሰማነው በዘመናችን ነው። አሁን ለጳጳሳት ሹመት ዋነኛ ገንዘብ አቀባባይ ደላላ የሆነው ዳዊት የማንን ሴት ልጅ እንዳገባ ብትሰሙ ትደመማላችሁ። በሕዝብ የሙዳየ ምጽዋት የስለት ገንዘብ በአዲስ አበባና በክልል ከተሞች ምን የመሰለ ቪላ የገነቡ ጳጳሳትን ማየት ይዘገንናል። መነኮሰ ሞተ ድሮ ቀርቷል። አሁን ጵጵስና ማለት ለብዙዎች የሳዑዲ አረቢያ አዲስ የነዳጅ ጉድጓድ ቆፍሮ በባለቤትነት እንደማግኘት ማለት ነው። 

…አሁን አንድ መነኮስ የሚጋደለው እንደምንም ብሎ ጳጳስ ለመሆን ነው። ገንዘብ ካለው መልካም ከሌለው ያው እንዳዘነ እንደተመኘ ይቀራታል። ጳጳስ ሲኮን ጥቅሙ ብዙ ነው። ነፃ የዲፕሎማቲክ ፓስፖርት ይኖረዋል። ከዚያ የናፈቃት አሜሪካ በነፃነት ይበራል። አንድ ታቦት 4ሺ 5ሺ ዶላር ይሸጣል። ከምእመናን ለገዳሜ፣ ለአዲስ ቤተ ክርስቲያን እያለ በቤተ ክርስቲያን ስም እንደጉድ ይሄን ዶላር ይሰበስባል። ታምሜያለሁ ብሎ በነፃነት የፈለገበት ሆስፒታል በነፃ በምእመናን ወጪ ይታከማል። ከዚያ የዘለለ ቅሌት ውስጥ ገብተው ሁለተኛ ወደ አሜሪካም ወደ እንግሊዝም እንዳይገቡ የተደረጉም አሉ። በድፍረት በዚህ ጉዳይ ልንነጋገር ይገባል። በድፍረት። 

…በየማሳጅ ቤቱ ያለው ጉድ እንዴት ያስጠላል መሰላችሁ። አንድ መነኩሴ ቤት የሚበላው የፍየል ቁርጥ፣ ከዚያም የዘለለ ነገር ያስጠላል። አንድ ሊቀጳጳስ ስክር ብሎ ሲምበዛበዝ የሚያሳይ ቪድዮውን እንደማየት የሚቀፍስ ምን ነገር አለ? ዲያቆናት ካህናቱ ሲያሾፉበት፣ ሲያላግጡበት እንደማየት የሚያሳፍር ምን አለ? እኔ ሁላቸውንም መረጃዎች ያቀበሉኝን ሰዎች ተማጽኜም፣ ለምኜም ግድየለም እግዚአብሔር የሚቀጣውን ይቀጣል። ተዉት፣ ያዙት፣ ብዬ የያዝኩት የትየለሌ ነው። የሚገርመው ነገር እግዚአብሔር ያበርታኝ እንጂ “ለአባቶች ያለኝ ክብር በሚገርም ሁኔታ እያሽቆለቆለ መጥቷል። በጣም እየወረድኩ ነው። ከባድ ጸሎት ነው የሚያስፈልገኝ። መናፍቃን እኔን ለማብሸቅ ብለው የሚልኩልኝ ፀያፍ ነገር ያሳብዳል። አሜሪካን አውሮጳ ሄዶ ለሴቶች ቀሚስ፣ ታይት፣ ለህፃናት ጥብቆ ለመግዛት ሲሰለፍ፣ ቆንጆ ውድ የሴት ሽቶ ገዝታችሁ አምጡልኝ የሚል ጳጳስ ለምእመናኑ አዕምሮ እንኳ ለምን እንደማይጠነቀቅ አይገባኝም። 

…ብዙዎች መናፍቅ፣ ከሃዲ የሚሆኑት ወደው እንዳልሆነ እያየሁ ነው። እየገባኝም ነው። እሰይ ባሌ ጳጳስ ሆነልኝ፣ የልጆቼ አባት ጰጰሰልኝ ብላ ለወዳጆቿ የምሥራች የምትነግር ሴት ካየሁ በኋላ ሁሉን ባልጠራጠርስ እንዴት ይፈረድብኛል ወይ? የካህን እህት ያገባ ሰው ካህኑ የእህቱ ባል ጳጳስ ሲሆን እያየ ይደሰታል ወይስ ምንድነው የሚሆነው? ከሁለት ሴት የወለደ ሁሉ መቅደስ ገብቶ እያገለገለ መስዋዕቱስ እንዴት ይሰምራል? ጸሎት ምስጋናውስ እንዴት ያርጋል? የቤተ ክርስቲያንም የኢትዮጵያም ፈተናዋ እንዴት ይቆማል? ግብፆች “ከኢትዮጵያ ሰዎች ለራሳቸው ጳጳሳትን አይምረጡ፣ አይሹሙ” ብለው በፍትሃ ነገሥቱ ላይ የጻፉት እውነታቸውን ይሆን ብዬ ወደማመን መጥቻለሁ። የእነ አባ ሩፋኤል መቀለጃ የሆነ ጵጵስና ክብሩን ጥሎ እንደማየት የሚያሳዝን፣ የሚያስለቅስ ጉዳይ ከወዴት ይመጣል።… 

…በኑሮ የጎሰቆሉ ደሀ ሴቶች፣ ኑሮ የከበደባቸውን ምስኪን ሴቶችን፣ ተስፋ የቆረጡ ምስኪኖቹን፣ ቢናገሩ፣ ቢጮሁ ሰሚ የሌላቸውን፣ በክስ ወንበር ቢቀመጡ ፍርድ የሚጠምባቸውን ምስኪን ሴቶች እያነወሩ የሚኖሩት እስከመቼ ነው። ሱሉልታ ፖሊስ ጣቢያ በሒሳብ አልከፈለኝም የሴተኛ አዳሪ ጠብ ገዳማውያንን ለውርደት የዳረጉ አሁንም ከፍ ባለው የክቡር ዙፋን ላይ የሚቀመጡት፣ ሃብታም ኢንቨስተር የማይችለውን ከአሜሪካ በወር በወር እየተመላለሱ ናዝሬት አዳማ በሸነና የሚሉ፣ ታክስ፣ ግብር፣ ቀረጥ የማያውቀው ገንዘብ እንደ ጉድ የሚፈሰው ከዚያ ሥፍራ ነው በማለት የመነኩሴ ገርል ፍሬንድ ለመሆን ሽሚያ ውስጥ የሚገቡ ሴቶች የተፈጠሩት እኮ ዘንድሮ ነው። ካህናት አመድ ነፍቶባቸው አንዳንድ ጩሉሌ ማፍያ መነኮሳት ገድለውም ዘርፈውም ተንቀባረው ያለ ጉድለት የሚኖሩት በእኛው ዘመን ነው። ታዲያ ይሄን ነውር አሁኑኑ ሳይቃጠል በቅጠል በስንት ጩኸት ካላስቆመነው ነገ ከዚህ የሚከፋ ነገር ነው የሚጠብቀን። 

…ተጯጩኸን በጊዜ አስቆምነው እንጂ ከፒያሳ ኢንተር ኮንትኔንታል የታወቀች ሴተኛ አዳሪ አምጥተው ሃገረ ስብከት የቀጠሩ ማፈሪያዎች የገጠሙን በዚህ በእኛ ዘመን እኮ ነው። የአክስት ልጅ፣ የአጎት እየተባለ በየመነኮሱ ቤት የሚያድሩ ሴቶችን ማየት እየተለመደ መጥቷል። እነዚያ የአክስትና የአጎት ልጆች የተባሉቱ ከማን እንደሆነ ሳይታወቅ እዚያው ቤት አርግዘው ወልደው ጉድ ያስባሉን ጉደኞችን ያየነውም በእኛ ዘመን ነው። በየ መጠት ቤቱ ከፒያሳ ቦዘኔ በላይ ነውረኛ ቃል የሚጠቀሙ፣ በቲክቶክና ፌስቡክ ሲጀናጀኑ የሚውሉ መነኩሴ ቅብ መነኮሳት ያየነውም በእኛው ዘመን ነው። ጨካኞች፣ አንዳች ርህራሄ የሌላቸው ነውረኞችን እያዩ መስመር የሳቱ ዲያቆናት እና ካህናት ክህነት ለምኔ ብለው ሴት አሳዳጅ ጨፍጫፊ ሆነው ያየነው በእኛው ዘመን ነው። 

…በድንግልና ያለ አንድ መሪጌታ እባክህ ናና በሃገረ ስብከቴ ክብረ በዓል አገልግለን እንምጣ ይሉታል። እሺ ብሎ ታዞ በማግስቱ ሲሄድ አንዲት ፀዳ ያለች ደንደሳም ሴትም አብራ ለመሄድ ከመኪናው ውስጥ ተቀምጣለች። መሪጌታው ለወዲያው ምንም አልመሰለው። ጭንቅ ውስጥ የገባው መሽቶ ወደ መኝታ በሄዱ ጊዜ ባየው ነገር ነበር። ገጠር የኖረ፣ እንዲህ ዓይነት ቀፋፊ ጉድ የማያውቅ፣ በዚህ ሁኔታ ውስጥ ከድምጽም ከምንም መሸሽ በማይችልበት ሁኔታ የሚሆነውን ሲያይ ሲሰማ ምን እንደሚከሰት አስባችሁታል…? ይሄን ሰው ለማጽናናትም፣ ለመምከርም የበቃ ጻድቅ መሆንን ይጠይቃል። 

…በብድር ገንዘብ 3 ሚልዮን ብር ከፍሎ የተሾመ ሰው እስቲ ቀጥሎ ምን ዓይነት አገልግሎት ነው ለቤተ ክርስቲያንም፣ ለምእመናንም የሚሰጠው? እንዲያውም በዚህ መንገድ የተሾመ ሰው የሌለ በቀለኛ ነው የሚሆነው። ሰካራም በክሬን ተጎትቶ የሚነሳ የጋን ልጅ ጳጳስ ተደርጎ መሾም ለቤተ ክርስቲያን ምንድነው የሚጠቅማት። በነውሩ ምክንያት፣ በሌብነቱ ከቤተ ክርስቲያን የተባረረን ሰው መልሶ አምጥቶ ጳጳስ አድርጎ መሾም ምንያህል ቤተ ክርስቲያኗን ቢጠሏትና አሳልፈው ቢሸጧት ነው? አሁን የእነ አጥማቂ ግርማ ወዳጆችም በግልፅ ወደ ጵጵስናው መጥተዋል። ሻሸመኔ እግዚአብሔር ይሁንሽ። 

…ደግሞ አንዳንድ ለፍዳዶች አሉ የአባቶችን ገመና አደባባይ ባናወጣ የሚሉ። የብልት ማቆሚያ አጋዥ መድሃኅኒት ተጠይቆ ደንግጦ ለማበድ ጥቂት ስለቀረው ዶክተር የማይጨነቁ፣ ቤተ ክርስቲያን ቅፅር ውስጥ ከያዟት የፈረንጅ ውሽማ ጋር በግልጽ በመረጃ ከሚማግጡ ጳጳስ ጋር ስለምን ክብር ነው የምናወራው? የቤተ ክርስቲያን ክብር ሲጎድፍ ለማይሰማቸው ቅሌታሞች የምን ክብር ነው ለግለሰብ የምሰጠው? ሲሰክሩ፣ ሲቀነዝርባቸው ስልክ ቃለ ምልልስ እንኳ እቀረጻለሁ ብለው ለማይጠነቀቁ፣ እጋለጣለሁ ብለው የማይሰጉ፣ ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን ክብር ሳይሆን ለራሳቸውም ስም እንኳ የማይጠነቀቁ ነውረኞች የምን ክብር ነው። እኔ እንደውም ብዙዉን ጊዜ የሚወስድብኝ በጳጳስና በመነኩሴ፣ በቄስና በዲያቆን፣ በሰባኪና በዘማሪ የተደፈሩ ሰዎችን ስለማመጥ፣ ስማጸን መዋል ማደሩ ነው። ይቀፋል። 

…በቅርቡ አሜሪካ የገባ አንድ ወጣት ልጅ የሆነ ታሪክ ደውሎ ይነግረኛል። ልጁ ዝማሬ ይሞክራል። ታዋቂ አይደለም። አንድ የአደባባይ ላይ ታዋቂ መነኩሴ ፀያፍ እንደሚያወራው ነው የሚያጫውተኝ። ስለመነኩሴው አንድ ኤርትራዊም ከጀርመን ተመሳሳይ ነገር ነግሮኝ ስለነበር ተደገመብኝ። ሆኖም ግን ውሸት ብዬ ሞገትኩት። ቀጥሎም እስቲ ቀርጸህ ላክልኝ አልኩት። ቀርጾ ላከልኝ። ያኛው መነኩሴ ብልቱን አውጥቶ እየተንጀላጀለ መጀመሪያ እኔ ነኝ የምቀምስህ እያለው ነው በቫይበር ቀርጾት የላከልኝ። እኔ ልጁን ያልኩት ምንድነው? በቃ ሁለተኛ አታግኘው። እኔ መነኩሴውን አናግረዋለሁ አሉኩት። መነኩሴውን ምንድነው ነውር የምትሠራው ስለው “አንተ ከሳሽ፣ ደግሞ ወደ እኔ መጣህ፣ ስንትና ስንት አባቶችን አዋረድክ፣ አሸማቀቅክ፣ እኔን እንኳን አትሞክር፣ ምንም አታገኝብኝም ብሎም የጎፈረ ፂሙን እያሻሸ ደነፋብኝ። እኔም ብዙ ሳላወራ የነውር ቪድዮውን ለሰውየው ላኩለት። “ከዚያ የሆነውን ዝርዝር አላወራም። አንዲት ቃል ብቻ ተናገርኩት። ከቻልክ ንስሐ ግባ፣ በሕይወት እስካለሁ ድረስ ግን ሚድያ ላይ እንዳላይህ አልኩት። ይኸው እስከዛሬ አይቼው አላውቅም። 

…ሌላም አለ። አንዱ ሳይማር ሃገር ምድሩን በድፍረት የተቆጣጠረ ሰው ወደ አውሮጳ ሊጋብዙት መሆኑን ጋባዦቹ ስለሰውየው ምክር እንድለግሳቸው ይጠይቁኛል። እኔም እሱ ባለበት ነው ወይስ ለብቻችሁ አልኳቸው። ኧረ እኔና ሚስቴ ነን ዘመዴ ያለነው እባክህ ንገረን ይለኛል። እሱ ባለበት ቢሆን መልካም ነበር እሺ አልኩና ነገርኳቸው። “እናስመጣዋለን የምትሉት ሰው ከእኔ የባሰ ጋለሞታ ነው። አንደኛ የትም አልተማረም። እንዳትዋረዱ አልኳቸው። ባልየው ቅር እያለው መጣ። ቀጠልኩኝ። ሚስትየውን ሰውየውን ካመጡት አንቺን ብቻሽን እንዳያገኝሽ፣ አንድ አራት ሙታንቲ ግልገል ሱሪና ድርብርብ ሱሪም ልበሺ ባላት አልኳት። አለቀ። ባልየው ” ደደብ ነህ፣ እንዴት የምታውቀውን ሰው እንደዚህ ትላለህ? ምቀኛ ማፈሪያ ነህ ብሎኝ ስልክ ዘግተን ተለያየን። እኔ የኅሊና ዕረፍት አግኝቻለሁ። ሌላው ለደንታው ነው። 

…ቆይቶ የተባለው ሰው አውሮጳ አስመጡት። ብዙም አልቆየ አንዲት አሮጊት ቤት አድሮ እንዲሁ ሲያስቸግራቸው አመሸ አሉኝ። አምጪዎቹ ሰምተው ደነገጡ። ቆየና ደግሞ መስከረም ላይ አዲስ አበባ የምታገባ ዕጩ ድንግል ሙሽራ የሆነች ሴት ቤት ካላደርኩ አለ። እዚያም ኢትዮጵያ ደሀ ሴቶችን ሲጫወትባቸው እንደሚያድረው መስሎት ገተት ውስጥ ገባ። ልጅቷም የዋዛ አልነበረችምና የሴት ጓደኛዋን ጠራች፣ ፖሊስም ጋር ሊደወል ሆነ። አምጪዎቹ ሰሙ፣ ዘሪሁን ሙላትም እንደ ድንገት በዚያው በአውሮጳ ነበርና ሽምግልና ተገባ። ውርደቱ ለቤተ ክርስቲያን ነው ተብሎ በስንት ደጅ ጥናት ከእስር ተርፎ፣ በድንጋጤ ደም እየተፋ ወደ ሸገር ተመለሰ። ወዲያው አምጪው ደወለልኝ። ዘመዴ ይቅር በለኝ አለ። ፈጣሪ ይቅር ይበለን ብዬው በወዳጅነታችን ቀጠልን።… 👇 ከታች የቀጠለ…

…በስንተኛው ዓመት ይሄው ሰው ከአሜሪካ ግብዣ መጣለት። ጋባዦች እንደአጋጣሚ ደወሉልኝ። ደዋይዋ የማላወቃቸው ትልቅ ሴት ናቸው። ስለሰውየው ጠየቁኝ በአውሮጳ የገጠመውን ነገርኳቸው። ከዚያ ቀጥሎ የሰማሁት የቀፋል። ግን ጀግና አሮጊት ነበሩና ቅሌት አከናንበው አሳፍረው ከቤታቸው አባረሩት። ሴቱም፣ ምእመኑም ሲነገረው አይሰማም። ደፈር ብለህ የምታውቀውን ስትነግረው እንደ ምቀኛ፣ እንደስም አጥፊ ነው የሚያይህ። ኃጢአት መሥራት ሁላችንም እንሠራለን፣ በተለይ እኔ የዓለም ቁጥር አንድ አንደኛ ኃጢአተኛም ነኝ። ነገር ግን ኃጢአቴ የተከደነ፣ እግዚአብሔርና የንስሐ አባቴ ብቻ የሚሸከሙት፣ ለማንም መሰናክል የማልሆን ኃጢአተኛ ነኝ። 

…አሁን ደፍረን መነጋገር አለብን። ሁላችንም ነውረኛ መሆን የለብንም። ዘልዛላ ሰባኪ ለምንአባቱ ነው ዐውደ ምሕረት ላይ የሚወጣው? ሰካራም የደንበጃን ታናሽ ወንድም ስካር ለእሱ ተፈቅዶ ምእመኑኑ የሚከለከልበት ሞራል ከየት አምጥቶ እንዲያስተምረን ነው የምንጠብቀው። በግል የቀረቡትን እና ሊተኟት የፈለጉትን ሁሉ ዝሙትን እንደጽድቅ ቀለል አድርገው የሚሰብኩ ሰዎችን እስከመቼ ነው የምንታገሰው? ስንትና ስንት ሴቶች እየተደፈሩ ነው። ወንዶች ጭምር እየተደፈሩ ነው። ከወንዶችም ህጻን ወንዶች እየተደፈሩ ነው። ከሚስቱ የተፋታ፣ ሌላ ሴት ያገባ፣ ክህነቱን ያፈረሰ ሁላ በምን አግባብ ነው እንደ ከበረ ካህን የሚንበጫበጨው? ጠንቋይ፣ መተተኛ፣ ጋኔን ሳቢ በመቅደሱ ውስጥ ክብር አግኝቶ የሚወደሰው እሰከመቼ ነው? “…እንግዲህ በነቢዩ በዳንኤል የተባለውን የጥፋትን ርኩሰት በተቀደሰችው ስፍራ ቆሞ ስታዩ፥ አንባቢው ያስተውል፥” ማቴ 24፥15። ይሄ ሁሉ ምልክት የጌታ መምጫ ሰዓት መድረሱን የሚያረጋግልን ነው። 

…በመጨረሻም በበምህር በትረ ማርያም አባ አጋግዮስ ታሪክ ርዕሰ አንቀጼን እቋጫለሁ። በዲዮቅልጢያኖስ ዘመን ክርስቲያኖች በየቦታው ታርደዋል። አብያተ ክርስቲያናት በየቦታው ተቃጥለዋል። የዚህ ሁሉ መነሻ ምክንያት ግን አባ-አጋግዮስ የተባለ ሆዳም መነኩሴ ነው። ነገሩ እንዲህ ነው። ሮም ከሌላ ሀገር ጋር ጦርነት ውስጥ ትገባለች። የሮም ወታደሮችም በተለይ ታላቁ ቅዱስ ሰማዕት ቴዎድሮስ መሪ ሆኖ ያችን ሀገር አሸንፈው የዚያችን ሀገር ንጉሥ ልጅ ማርከው ሮም ይመለሳሉ። ዲዮቅጢያኖስም ተማራኪውን ልጅ ለአባ አጋግዮስ አደራ ይሰጣል። አባ አጋግዮስ ግን ጉቦ ወርቅ ተቀብለው በምስጢር የተማረከውን ልጅ ወደ ሀገሩ ይልኩታል። ዛሬም ጦርነቱ እንዳይበርድ የሚያደርጉ አባቶች እንዳሉን ማለት ነው። 

…እንደገና ጦርነት ይጀመራል። ይህን ጊዜ እነ ቅዱስ ቴዎድሮስ ያን አስቀድመው ማርከው የነበሩትን ሰው ይመለከቱታል። ይህን ሲያይ ቴዎድሮስ መጥቶ አባታችን አባ አጋግዮስ ሆይ ያ ልጅ አምልጦዎት ሄዶ ነወይ? ከጦር ሜዳ አገኘነው አሏቸው። አባ አጋግዮስ ግን ያ ልጅ እሥራት ጸንቶበት ስለነበር ወዲያው ሞቶ እኔ ራሴ ነኝ የቀበርኩት ብለው ዋሹ። እንደገና ያ ልጅ በጦርነቱ ዳግም ተማርኮ ከዲዮቅልጢያኖስ ያቀርቡታል። ዲዮቅልጢያኖስም ልጁን ከቤቱ ደብቆ ሄዶ አባ አጋግዮስን ያን ልጅ ስጠኝ አለው። አባ አጋግዮስም ሞቶ ቀበርኩት ብሎ ዋሸ። ዲዮቅልጢያኖስም በዚህ ትምላለህ ወይ አለው። አዎ እምላለሁ ብሎ ቅዳሴ ቁርባን ሊያቆርብ ገብቶ በቁርባኑ ማለ። ይህን ጊዜ ዲዮቅልጢያኖስ በአባ አጋግዮስ ላይ ከሰማይ እሳት ወርዶ ያቃጥለዋል ብሎ ቢጠብቅ ቢጠብቅ ቀረ። ይህን ጊዜ ነው እንግዳህ ዲዮቅልጢያኖስ መነኩሴው የተቀበለውን ወርቅ (ጉቦ) በእሳት አቅልጦ አባ አጋግዮስን ያጠጣው። አባም የፈላ ወርቅ በጠጣ ጊዜ ተንተክትኮ ሞተ ይላል። 

…አስተውሉ ዲዮቅልጢያኖስ አስቀድሞ ክርስቲያን ነበር። ያ አባ አጋግዮስ በሸወደው ጊዜ እና እግዚአብሔር መቅሰፍት ያመጣበታል እያለ ሲጠብቅ መቅሰፍት ባለመውረዱ ክርስቶስን ካደና አምላክ ማለት አጋግዮስን የገደለ ወርቅ ነው ብሎ ለወርቅ ምስል መስገድ የጀመረ ለዚያ ነው። (ዲዮቅልጢያኖስ የእግዚአብሔርን መሓሪነት ባለመረዳት ነው የካደው። ዛሬም እንደ ዲዮቅልጢያኖስ ቤተክርስቲያን ስትቃጠል እግዚአብሔር መቅሰፍት ካላወረደ ትክክለኛ አይደለም የሚሉ የዋሀን ምሕረቱን የማያውቁ ዲዮቅልጥያኖሳውያን ናቸው)።  

…በቤተክርስቲያን ላይ መከራ የሚያደርሱ ሰዎች ምንም ያህል የቆየን ቢመስላቸውም በመጨረሻ ፍርድ እንደሚፈረድባቸው ልንረዳ ይገባል። ዛሬም የክርስቶስ ሙሽራ የተባለችውን ቤተክርስቲያን ለማዋረድ ሌት ከቀን የሚሰሩ ብዙ አባ አጋግዮሶች አሉ።  እነ አባ አጋግዮስ ከክርስቶስ ይልቅ ሆዳቸው ይበልጥባቸዋል። ገንዘብ ወዳድ ናቸው። ስለዚህ ጌታ ሆይ እነ አባ አጋግዮስን   ከቤተክርስቲያን መዋቅር ልታስወግዳቸው ይገባል። ሲኖዶስ ተቀባይነት የሚኖረው የክርስቶስን አስተምህሮና ሕገ ቤተ ክርስቲያንን ሲያስጠብቅና ሕገ ወጦችን ሲቃወም ነው። 

…እኔም እቀጥላለሁ…! ነገር ግን በእናታችሁ በማየው በምሰማው በሚደርሰኝ መረጃ እንዳላብድ ጸልዩልኝ። እስከአሁን በግፍ የሚታረዱ ሰዎችን ንጹሓን አስከሬን እያየሁ ከማበድ፣ ከመቀወስ የጠበቀኝ አምላክ በእነዚህ ነውረኛ አሳፋሪ ቅሌታም አፈ ቅቤ፣ ሆደ ጩቤ የቆብ ውስጥ ወንበዴዎች ፀያፍ ተግባር ምክንያት በማይ በምሰማው እንዳልበጭጭ ጸልዩልኝ። በቅሌታም ነውረኞች የተነሣ በሃይማኖቴ እንኳን ጥርጥር አይገባኝም። ፀሐይ ቆሻሻ ላይ ስላረፈች አትቆሽሽም።  ማርያምን እውነቴ ነው። መምህር ቀሲስ ንዋይ ካሣሁን ግን ፅናቱን ይስጥህ። 

ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ አሸበርቲው…! [7/7/2023 7:22 PM]

https://t.me/ZemedkunBekeleZ/20874?single

 

Filed in: Amharic