ያለን ጊዜ በጣም አጭር ነው!
ዳግማዊ ጉዱ ከሣ
ሰሚ ጠፋ እንጂ ብዙ ጊዜ ተናገርን፤ ለፈለፍን፡፡ የአማራና የኦሮሙማ ነገር በፍጹም በአጭበርባሪ የሽምግልና hidte አይፈታም፡፡ ዳግማዊ ወያኔ ኦነግ/ኦህዲድ አየር ባጠረው ቁጥር አማራን በቄስና በቃልቻ የሚያጃጅለው ነገር መቆም አለበት፡፡ የሚያቆመው ደግሞ አማራ እንጂ ብአዴን ወይም ጌታው ኦነግ/ኦህዲድ አይደለም፡፡ በአጭር ቃል ኦሮሙማና አማራ ዕረፍት የሚያገኙት ከሚከተሉት በአንደኛው ብቻ ነው፡፡ ከዚያ ውጪ መፍትሔ ብሎ ነገር የለም፡፡
- በኦሮሙማ ሤራና በባንዳው ብአዴን ሆዳም ተላላኪነት አማራ ከምድረ ገጽ ሲጠፋ ወይም በሞጋሣ ሥርዓት የገዳ ሥርዓትን ተቀብሎ ኦሮሞ ሲሆን – እሱም ከሆነ ነው – ካዘኑለት፡፡ ጥላቻቸው ገደብ ስላጣ ይህ የሚሣካ አይመስለኝም፡፡
- አማራው በጀመረው የኅልውና ትግል ገፍቶ ራሱንና ቀሪ ወገኖቹን ከተደገሰላቸው ዕልቂት ነፃ ሲያወጣና አዲሲቷ የጋራ ኢትዮጵያ ስትወለድ፡፡ ይህ እውነት የማይቀር ቢሆንም አማራ ለራሱ ካላወቀና ባንዳውን ብአዴንን ሳይውል ሳያድር ካላስወገደ የትንሣኤ ዘመን እየናፈቀን ብዙ ልንቆይ እንችላለን፡፡ እኛው ለኛው ካላወቅን ሁሉንም ነገር ለፈጣሪ መስጠት ከንቱነትና ስንፍናም ነው፡፡ በምድር ላይ ስንኖር ለመሞትም ላለመሞትም የራሳችን ሚናና አስተዋፅዖ አለው፡፡ ደምና ዕንባ ወደሰማይ አርገው የፈጣሪን በቀል በበዳዮች ላይ ቢያወርዱም ከእኛም አንዳች እንቅስቃሴ ከሌለ ፍርድ ሊዘገይ እንደሚችል መረዳት ተገቢ ነው፡፡ ስለሆነም አማራውና መሰል የኦሮሙማ የጥፋት ዐዋጅ የታወጀባቸው ወገኖች ሁሉ ተባብረው ይህን የአጋንንት መንጋ ኦሮሙማ ወደመጣበት የሲዖል በረት መመልስ አለባቸው፡፡ ጊዜ የለንም፡፡ ቶሎ በሉ፡፡ እነሱ ዓላማቸውን ሊያሳኩ ጫፍ ደርሰዋል፡፡
ከዚህ ውጪ በሽምግልና መፍትሔ አገኛለሁ ብሎ መጃጃል የአማራን IQ (የአእምሮ ጤንነት) ለትዝብት መዳረግና የለዬለት ቂልነት ነው፡፡ ሰው አሁን በ11ኛው ሰዓት እንኳን እንዴት አይባንንም? ጅብና አህያ፥ ነብርና ሚዳቋ፥ አንበሣና ድኩላ ከመቼ ጀምሮ ነው ተፈጥሯዊ የአጥፊና ጠፊ ግንኙነታቸው በዕርቅ ተደምድሞ በመካከላቸው ያለመደራረስ ውል ተፈርሞ የሚያውቀው?
ውጊያ የሰለቸው አማራ ፋኖ ካለ ሰበብ ሳያበዛ ሕዝቡን ይቀላቀልና እንደነፍሰ ጡር ልክ እንደኛው አዲስ አበባ ውስጥ እንዳለነው ምሥኪን አማሮች የመታረጃ ቀኑን ይጠብቅ፡፡ ይሄም አንድ አማራጭ ነው፡፡ በተረፈ ጀምረሃል፥ አትዝረጥረጥ፡፡ ገጥመህ መስሎኝ፡፡ ይህን የምለው ሰሞኑን ኦሮሙማ በታማኝ ሎሌው በብአዴን አማካይነት ላሊበላ አካባቢ የተወሰኑ ፋኖዎችን በሽምግልና አሳብቦ በመክበብ ሊፈጃቸው ሲል አስቀድሞ በደረሳቸው ጥቆማ ለጥቂት መትረፋቸውን በመስማቴ ነው፡፡ ለሆዳቸው ያደሩ ቄሶችና የሌሎች ሃይማኖቶች አባቶች በገንዘብ ተታለውም ይሁን በዓላማ ተፋትለው ሲመጡባችሁ ቀንዳቸውን ብሎ መመለስ ወይንም ሌላ አስፈላጊ ሆኖ የተገኘውን እርምጃ ሁሉ መውሰድ ለነገ አይባልም፡፡ ነገሩ የኅልውና ጉዳይ ነውና መዘናጋት ለጠቅላላ ዕልቂት ይዳርጋል፡፡
መናገር ቀላል መሆኑን አጥቼው አይደለም፡፡ የተደቀነው አደጋ ግን ከዚህም በላይ ያናግራል፤ ያሣብዳልም፤ እንቅልፍ አሳጥቶ ያስጮሃል፡፡ ከዚህ ፍጂት ለመትረፍ ሁሉም እንደዬአቅምና ችሎታው ካልተደጋገፈ ደግሞ በ”ከመረቁ አውጡልኝ ከሥጋው ጦመኛ ነኝ” የብልጦች አካሄድ አመርቂ ውጤት አይገኝም፡፡ “እባብ ለባብ ይተያያል ካብ ለካብ” የሚለው ብሂል በቃ’ቃ ጨዋታ እንጂ በዚህ የሞት የሽረት ጉዳይ እንደማይሠራ ተልእኳቸውን በጨረሱ ማግሥት ልክ እንደኛው ባልተወለደ አንጀት የሚታረዱት እነአገኘሁ ተሻገርና ብናልፍ አንዷለምም ከአሁኑ ሊረዱት ይገባል፡፡ ብዙው አማራ እየሆነ ያለው ነገር የገባው አይመስልም፤ እንደቀልድ የወሰደውም አይጠፋም፡፡ ገና አልተነካማ! በአማራነቱ ነገ ጧት አንገቱ ሲቆረጥ ብሩን ኦሮሞ የሚጫወትበት ሀብታም አማራ ዛሬ ሰስቶ ፋኖን (ትግሉን) ባይረዳ ከናካቴው ባይፈጠር የሚሻለው ገልቱ ነው፤ የዚህ ዓይነት አማሮች ብዙ ናቸው – የማይሞቃቸው የማይበርዳቸው፡፡ ሀብት አላፊ ጠፊ ነው፡፡ ሁሉም ነገር ለሚያልፈው፣ ዛሬ የኛን ሸክም የተሸከሙትንና የኛን ሞት የሚሞቱትን፣ የኛን ጭንቅ የሚጨነቁትንና የኛን ርሀብ የሚራቡትን በረሃ የወረዱ ጀግኖች ለመደገፍ ፈቃደኛ አለመሆን የነገን ተስፋ እንደማጨለም ይቆጠራልና በተለይ ትግሉን የማገዝ ሁለንተናዊ አቅምና ችሎታ ያላችሁ ወገኖች ኢትዮጵያንና አማራን የማዳኑን ኃላፊነት ፋኖ ላይ ብቻ ጥላችሁ በአሼሼ ገዳሜ ዓለም አትዋጡ፡፡ ማለፉ የማይቀረው ይህ ቀን ሲያልፍ እንተዛዘባለን፡፡ ያኔ በባዶ ሜዳ “እንዲህ አድርጌ ነበር እኮ፤ በእገሌ በኩል እኮ ….” ብትሉ ሀሰት መሆኑ ይረጋገጥና ልክ እንደሃሳዊ ክርስቶሳውያን በመጨረሻው ቀን ትዋረዳላችሁ፡፡ ከአንዲት ሴት ጋር አድሮ የሚገዛላት አንዲት ቪትዝ፣ አንድ ምሽት ተዝናንቶ በቸበር ቻቻ የሚያወድመው 50 እና 100 ሽህ ብር ብዙ ፋዎችን ለብዙ ቀናት ኮቸሮ ያቃምሳል፡፡ በአንድ ዐውድ ውስጥ በተለያዩ የማይግባቡ ዓለማት ውስጥ መኖር አለመታደል ነው፡፡ በስንቱ እንደምንቃጠል መረዳት ከባድ እንዳልሆነ አንባቢ ይገምተዋል፡፡፡
ወጣቱም በጫትና በመጠጥ በሀሽሽና በወሲብ ደንዝዞ ባልሰማ ባላዬ ከትግሉ ገሸሽ ቢል ተጎጂው ራሱ ነው፡፡ ይህን መልእክት አዳርሱልኝ፡፡ ያለን ጊዜ አጭር ነው፡፡ እጅግ በጣም አጭር፡፡