>

የዩቲዩብ አፈና፤ ያማራ ሕዝብ አሸናፊነት ብሥራት

የዩቲዩብ አፈና፤ ያማራ ሕዝብ አሸናፊነት ብሥራት

መስፍን አረጋ 

“በመጀመርያ ይንቁሃል፣ ቀጥለው ይዘልፉሃል፣ ከዚያም ይፋለሙሃል፣ በመጨረሻም ትረታቸዋለህ::” 

“First they ignore you, then they ridicule you, then  they fight you, then you win”

 ማህተማ ጋንዲ (Mahatma Gandhi) 

ወያኔና ኦነግ አማራን አከርካሪውን ሰብረነዋል እያሉ ይታበዩ ስለነበረ ሽንታም ምናምን እያሉ ይንቁት ነበር።  የናቁት አማራ ማንገራገር ሲጀምር ደግሞ ነፍጠኛ ምናምን እያሉ ያሸማቅቁት ጀመር።  ከማንገራገር ወደ መወራወር ሲሻገር ደግሞ ድምጹን ሲሰሙት ብቻ መርበድበድ ጀመሩና ለማፈን ይሯሯጡ ጀመር።  ከዚህ በኋላ የሚቀራቸው ደግሞ ኮለኔል ፈንታሁን ሙሐባ እንዳለው በፋኖ እምሽክ እየተደረጉ የሽንፈት ጽዋቸውን መጎንጨት ብቻ ነው፣ ምንም እንኳን ጨርሰው እስኪመሽኩ ድረስ ከፍተኛ መስዋእትነት ቢያስከፍሉም።

የጠላትህን ድምጽ በመፍራት ያፈንክ ወይም ለማፈን የሞከርክ ቀን፣ በጠላትህ የመሸነፍህን አይቀሬነት ለጠላትህ ታብሥራለህ፣ ለወዳጆችህ ደግሞ ታረዳለህ።  ወያኔና ኦነግ እያደረጉ ያሉትም ይሄንኑ ነው።  

ወያኔና ኦነግ ያማራን ድምጽ ለማፈን የሚሞከሩት አማራዊ ዩቲዩቦችን (YouTube) በመዝጋት መሆኑ ደግሞ የዩቲዩብን ምንነት ባጠቃላይ ደግሞ ያሜሪቃን መንግሥት ምንነት ላማራ ሕዝብ ቁልጭ አድርጎ በማሳየት ላማራ ሕዝብ ትልቅ ትምሕርት አስተምሮታል።  ካሁን በኋላ ያሜሪቃ መንግሥት ባጠቃላይ ደግሞ ምዕራባውያን ስለ አንደበት ነጻነት (free speech)፣ ዲሞክራሲ (democracy) እና ሰብዓዊ መብት (Human right) የሚያወሩትን ተረት ተረት እውነት ብሎ የሚቀበል አማራ ካለ፣ እሱ አላዋቂ ሳይሆን ጥሬ መሐይም ነው።  

ያሜሪቃ መንግሥት ስለ ዲሞክራሲና ሰብዓዊ መብት ቀን ከሌት የሚያላዝነው፣ የዲሞክራሲና የሰብዓዊ መብት አፍቃሪ ሁኖ ሳይሆን፣ ብሔራዊ ጥቅሙን ለማስጠበቅ ፍቱን መሣርያወች ሁነው ስላገኛቸው ብቻ ነው።  ፍቱን መሣርያወች የሆኑለት ደግሞ በግዙፍ ሚዲያወቹ (CNN, BBC ወዘተ.) እና በሆሊወድ (Hollywood) አማካኝነት የፕሮፓጋንዳ የበላይነትን ስለጨበጠ፣ ትርክቶችን (narration) ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ በመቆጣጠር የማይፈልገውን ሰይጣን አስብሎ የሚፈልገውን መልዓክ በማስባል በመደዴው ሕዝብ እንዲመረጥ የማድረግ አቅሙ ከፍተኛ ስለሆነ ነው።  

ያሜሪቃ ዲሞክራሲ በዘረኝነት (racism)፣ በጀሪማንደሪንግ (gerrymandering) እና በመሳሰሉት የተጨመላለቀ፣ ውስጡ ለቄስ የሆነ ዲሞክራሲ ነው።  የዲሞክራሲው አብዛኛው ክፍል ደግሞ እጅግም ረብ የሌለው፣ በእንቶ ፈንቶወች ላይ የሚያተኩር ቢከፍቱት ተልባ የሆነ የይስሙላ ዲሞክራሲ ነው። ስለዚህም፣ ያሜሪቃ መንግሥት ዲሞክራቲክ ነው ቢባል፣ ዲሞክራቲክነቱ ላሜሪቃ ሕዝብ ብቻ ነው፣ ለዚያውም ደግሞ እንደሚጋነነው ሳይሆን በተወሰነ ደረጃ ብቻ።  

ካሜሪካ ውጭ ግን ካሜሪቃ መንግሥት የበለጠ የዲሞክራሲና የሰብዓዊ መብት ጠላት ባለማችን ላይ አይገኝም።  ለምሳሌ ያህል ዲሞክራሲና ሰብዓዊ መብት አፍሪቃ ውስጥ ሥር ሊሰዱ ያልቻሉበት ዋናው ምክኒያት፣ ሥር ከሰደዱ አፍሪቃ ላፍሪቃውያን (African for Africans) ሁና ያሜሪቃ ጥቅም ስለሚቀርና፣ ይህ እንዳይሆን ደግሞ ያሜሪቃ መንግሥት የሱ ቡችሎች የሆኑ አምባገነኖችን ባፍሪቃውያን ላይ በቀጥታና በተዛዋሪ ስለሚጭን ነው። 

በወያኔ ዘመን መለስ ዜናዊ ያሜሪቃ ቡችላ እንደነበረ ሁሉ፣ በኦነግ ዘመን ደግሞ ጭራቅ አሕመድ ያሜሪቃ ቡችላ ነው።  ስለዚህም፣ አሜሪቃ የቡችላዋን የጭራቅ አሕመድን እድሜ በተቻላት መጠን ለማስረዘም የምትችለውን ያህል ትጣጣራለች።  የዩቲዩቡ አፈናም የዚሁ ጥረት አካል ነው። 

ሳሞዛ ውሻ ቢሆንም፣ የኛ ውሻ ነው፡፡”

“Somoza may be a son of a bitch, but he’s our son of a bitch”

President F. D. Roosevelt (about the brutal dictator of Nicaragua)

መስፍን አረጋ     

mesfin.arega@gmail.com

Filed in: Amharic