>
5:18 pm - Thursday June 15, 1076

መነበብ ያለበት! ''የዐማራ ትግል የወንበዴ መደበቂያ ዋሻ አይደለም!!'' (መምህር ዘመድኩን በቀለ)

“ርዕሰ አንቀጽ”

 “…ወለበል አልኩህ እኔ ዘመዴ መስማትም፣ ማየትም የምፈልገው ስለ አሮጌ ብአዴኖቹ ስለ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው እና ስለ አቶ ዮሐንስ ቧያለው አይደለም። እኔ መስማት፣ ማየት የምፈልገው ስለ አዲሶቹ ፋኖዎች ለዐማራ ነጻነት ሲሉ በረሃ ለወረዱት ስለ እነ እስክንድር ነጋ እና ስለ እነ ኮሎኔል ፈንታሁን ሙሃባው፣ ስለ እነ ፋኖ ደረጄ፣ ስለ እነ ምሬ ወዳጆ፣ ስለ እነ አቶ አሰግድ፣ ስለ እነ ዘመነ ካሤ ነው። እኔ መጻፍ፣ መዘገብ የምፈልገውም ስለ አሮጌ ብአዴኖቹ አይደለም። እኔ እንቅልፌን አጥቼ ስቸከችክ የምውለው፣ የማድረው አቅም ሥልጣን በነበራቸው ጊዜ የዐማራን ትግል አሽቀንጥረው ጥለው ገፍተው ገደል ከከተቱ በኋላ የሕዝባቸውን ዋይታ ላለመስማት ጆሮአቸውን በጥጥ ደፍነው የራሳቸውን ጥቅም ሲያሳድዱ፣ ከርሳቸውን ሲሞሉ ከአራጁ ጋር አንሶላ ሲጋፈፉና በሸነና ሲሉ ከርመው፣ በአራጁ ከሃዲ እንደ ሸንኮራ ተመጠው፣ እንደኮንደም ስለተጣሉት ፀረ ዐማራ ነፍሰ በላ አሮጌ ጅቦቹ ብአዴኖች አይደለም። በፍጹም ስለ እነሱ የምጽፈው፣ በማንም ይሁን በማን ከተቻለ ለፍርድ እንዲቀርቡ፣ ካልተቻለ ደግሞ እንዲደመሰሱ ብቻ ነው። ምንአገባኝ። ለእነሱ ብአዴኖች ይጨነቁ እንጂ አንተ ፀረ ብአዴን ትግል ለጀመርከው ሶዬ ምን አገባህ? ይመለከትሃል? ”

…የጠለምትን መሬት ቆርሶ በእጁ ፈርሞ ለትግሬዋ ህወሓት ለሰጠው ለከሃዲው ገዱ አንዳርጋቸው ምን ብዬ እንድጽፍ ነው የምትፈልገው? ለውጡ ነው ነውጡ ከመጣ ጊዜ ጀምሮ ኧረ ተዉ ይሄ ለውጥ ዐማራን ያገለለ ነው። ከሥልጣንም ያራቀ ነው ሲባል በግልፅ “እኛ ኢትዮጵያን ብለን ነው የተነሣነው፣ ለሥልጣን ብለንም አልታገልንም ለምን ኦሮሞ ሥልጣኑን ሁሉ ተቆጣጠረ ማለት ፀረ ዲሞክራሲ፣ ፀረ ብልፅግና ነው ብሎ በአደባባይ ዐማራን ከሥልጣን አርቆ ለኦነግ ግርድና ለገባ ሰው ነው እንድጽፍ የሚፈለገው? አበደን አላደርገውም።

“…ሁለቱም ፀረ ዐማራዎች ናቸው። አቢይም ወያኔም አስብተው አርደው እንደሚበሏቸው የታወቀ ነው። ከሕዝብ ጋር ሁኑ ሲባሉ ገሸሽ ያሉ ብአዴኖች በሙሉ ተራ በተራ አብይ ይበላቸዋል። አገኘሁ ተሻገር ከሃዲ ባንዳውን ይበላዋል። አገው ሸንጎዎቹን የአውቶቡስ ጫኝና አውራጅ የነበረውን እነ ሰማ ጥሩነህን እስኪበላቸው ወደፊት ያመጣቸውና ተጥቅሞባቸው ይበላቸዋል። እና ለእነዚህ የህዳር አህዮች፣ አገልግሎት የጨረሱና ለጅብ የተሰጡ አጋሰሶችን ምን ብዬ ነው አጀንዳ የማደርገው። ወዳጄ የጊዜ ጉዳይ እንጂ በምድር በሰው እጅ፣ በሰማይ በእግዚአብሔር ዘንድ ቅጣታቸውን የሚቀበሉ አረመኔዎችን አጀንዳ የማደርግበት ምክንያት የለም። አቶ ዮሐንስ ቧያለው ጄነራል አሳምነው ጽጌ ላይ በቴሌቭዥን ቀርቦ ሲያላግጥ፣ ሲላላጥ፣ ሲያሾፍ የነበረ፣ ዐማራ ሲታረድ፣ ሲፈናቀል ለተቃውሞ የወጡትን ዐማሮች ሲያሾፍባቸው ሲያላግጥባቸው የነበረ። ከብልጥግና በላይ ብልጥግና ሆኖ ሲኮፈስ የኖረ፣ አሁን አረመኔው አቢይ አሕመድ የአገልግሎት ዘመኑን ሲጨርስ ዓይቶ እንደ ኮንዶም ተጠቅሞ ወደ ጋርቤጅ የወረወራቸው፣ እንደ አክታ የተፋቸውን ራስ ወዳድ፣ ፀረ ዐማራ ግለሰቦች ምን ብዬ ነው አጀንዳዬ አድርጌ ስለእነሱ እንድጽፍ የምትፈልገው?

“…ሥልጣን፣ የመወሰን አቅም፣ ጉልበት በነበረው ጊዜ ያልሰማህን፣ ያልረዳህ ፀረ ዐማራ ግብስብስ ሆዱ የጣለውን ሁላ አሁን በከዘራ እየሄደ፣ ብቻውን ቀርቶ፣ የመወሰን ሥልጣኑም ተገፎ፣ ጠባቂ ጋርዶቹ ተባረው፣ እሱ ራሱ ሕዝብ ከሆነ በኋላ፣ እንኳን ሕዝብን ራሱን ማዳን አቅቶት ከመኖሪያ ቤቱ በካልቾ ተብሎ እንደ ሌሎቹ ንፁሐን ዐማሮች ተባርሮ፣ መጠጊያም አጥቶ፣ በጓደኞቹ ድጋፍ እየተመጸወተ ለሚኖር የዐማራ ግፍ በምድር የቀጣውን ሰውዬ ምን ብዬ እንድጽፍለት ነው የምትፈልገው? እኔ የምጽፈው ስለ ዐማራ ፋኖ ነው። የሕዝቡን ነፃነት ለማብሠር ስለሚደክመው፣ ደሙን ስለሚያፈሰው ስለ ዐማራ ፋኖ ነው። ቢመጣም፣ ቢቀርም ምንም ለማይረባ ስለ አሮጌ የብአዴን ጅብ አያገባኝም። ለምን ሰቅሎ አይበላውም።

“…ብአዴን ሆነው የመሳሪያ ግምጃ ቤት ሰብረው፣ ለፋኖ ያስታጠቁ፣ እነርሱም ከፋኖ ጋር በረሃ የገቡ አርበኞች አሉ። እነርሱ ቢጻፍላቸው፣ ቢወደሱ፣ ቢሞገሱ የአባት ነው። ብአዴን ሆነው በተዘዋዋሪ መንገድ ለፋኖ ለሕዝባዊ ሠራዊቱና ግንባሩ ድጋፋቸውን የሚሰጡ ብአዴኖች አሉ። ስለ እነርሱ ቢወራ፣ ቢጻፍ ነውር የለውም። ነገር ግን ከዓመት በፊት ፋኖን በመድረክ ሲሰድብ፣ ሲያዋርድ፣ ሲያንቋሽሽ የነበረን የጠንቋይ ስብስብ ዛሬ ሁላችን ስንጮህለት የከረምነውን ነገር በተጠና መልኩ እንዲናገር ተደርጎ፣ ያም ደግሞ ከምክርቤቱ ዕውቅና ውጪ በድብቅ በሚል ማፏገሪያ ቃል ታጅቦ፣ የህወሓት መሥራቹ በአቶ አማረ አረጋዊ ሪፖርተር ጋዜጣ የዩቲዩብ ቻናል እንዲለቀቅ ተደርጎ፣ ከዚያ የትግሬና የኦሮሞ ነፃ አውጪ የማኅበራዊ ሚድያ ሠራዊቶች እንዲንጫጩበት ተደርጎ፣ ወዳጆቼ ኢትዮ 360 ዎችም ልክ ተአምር እንደተፈጠረ አድርገው ሲያጨበጨቡ ላመሹበት የፉገራ ሴራ አልዘግብም። አላወራምም።

“…ኢትዮ 360 እነ ሃብታሙ አያሌው የገዱን የመጨረሻውን ቃል ሳይሰሙ ሲያጨበጭቡ አያቸው ነበር። ገዱ አንዳርጋቸው “የዐማራ ክልል ፈርሶ አዲስ ሁሉን አካታች መንግሥት ይመስረት” እያለ እነ ሃብትሽ አልሰሙትም። ጭብጨባ ላይ ነበሩ። የምንአባቱ የሽግግር መንግሥት ነው። በዐማራ ክልል የብአዴን መንግሥት ፈርሷል። ብልጽግና ከከክልሉ ተወግዷል። በሕዝቡ ዘንድ ቅቡል ፓርቲ አይደለም። ሰሞኑን ስናወራበት የከረምነውን ከብአዴን የእንግዴ ልጅ ከአብን፣ ወያኔ ካቋቋመችው ከአገው ሸንጎና፣ ከቅማንት ሃይማኖት የተዘጋጁትን የዐማራን አንድነት ሽጠው የበሉ ሆድ አደሮችን ማለት ነው አይደል “ሁሉን አጀኘካታች የሽግግር መንግሥት የሚለው? ሃኣ…? እግርህን ብላ። ሲያምርህ ይቅር።

“…የጊዜ ጉዳይ ነው አንጂ ዐማራን ክልል የሚመራው ለዐማራ ነፃነት በረሃ በወረደው የዐማራ ፋኖ እንጂ በእነዚህ በስደተኛ የብአዴንና አብኖች መንጋ ግሪሳዎች አይደለም። የዐማራ ክልል ሥልጣን በዐማራ እጅ ነው የሚገባው እንጂ ለባንዳ ተላልፎ አይሰጥም። ማንኛውም አገዛዙን የሚቃወም ሰው አገዛዙን የመቃወም መብት አለው። ነገር ግን በዐማራ ጉዳይ የዐማራን ትግል ከፊት ሆኖ መምራት አይችልም። አይፈቀደለትም። የዐማራ ትግል በተጀመረበት መንገድ እየወደቀ እየተነሣ፣ ስህተቱን እያረመ ወደፊት ይቀጥላል። ለጊዜው ይደፈርሳል ከዚያ ይጠራል። ድል ከዐማራ ልጆች ጋር ነው። በአንድ ሳምንት ብአዴንን ውልቅልቁን ያወጣ የዐማራ ትግል በጥቂት ጊዜ መላ ኢትዮጵያ ላይ የተዘፈዘፈውን አውሬ አንገቱ ላይ ቆሞ እንደሚገላግለን ተስፋዬ ከፍ ያለ ነው። እምነቴም ሙሉ ነው።

“…አንዳርጋቸው ጽጌን እንደማላምነው ሁሉ፣ ነአምን ዘለቀ፣ አበበ ገላው፣ መሳይ መኮንን፣ እነ ፋሲል የእኔ ዓለም በዚህ ሳምንት ከአቢይ አሕመድ ጋር ስለተጣሉ የዐማራን ትግል ልምራ ቢሉ ባለቤት ስላለው አርፈህ ተቀመጥ ነው የምለው። የዐማራ ትግል ባለቤት አለው። ማንኛውም የአቢይ ገረድ የነበረ ሁሉ የዐማራን ትግል በሙያ ማገዝ ይችላል። ሲመጡም እንኳን ደኅና መጣችሁ ማለት ወግ ነው። ደንብም ነው። በተሸናፊ ላይ፣ በምርኮኛ ላይ፣ አግኝቶ ባጣ ሰው ላይ መጨከን እንዳይገባም ዐውቃለሁ። ትግሉን ልምራው ቢል ግን ካካ ነው፣ እፉ ነው ሊባል ይገባል። እነርሱ ሼም የላቸውም እና እኛ ሼም ላይኖረን አይገባም እንዴ? የመንቀሳቀሻ ስፔሳቸውን ሰጥተን በፈቀድንላቸው የመጫወቻ ሜዳ ላይ እንዲያግዙ ማድረግ እንጂ የዐማራን ትግል እንዲጠልፉ፣ ከፊት ሆነው እንዲመሩ፣ በስሙም ጎፈንድሚ  ከፍተው እንዲሸቅሉ ለእነዚህ አሮጌ ጅቦች ሊፈቀድ አይገባም።

“…አቶነአንዳርጋቸው ገና ትናንት ከመምጣቱ በሚዲያ ሰዎቻቸው በኩል እንዴት እንደተቆለጳጰሱ አይታችኋል። አንዳርጋቸው በአውሮጵላን ወጥቶ ተሰደድኩ ይላል። በኤርትራ በረሃ የኤርትራውያንን ፍየል ጠባቂ ጥቂት የግንቦት ሰባትን ሚሊሻዎች ልክ እንደ ግዙፍ ጦር እያጋነነ፣ በአርማጨሆ፣ በታች ጋይንት የወያኔን ጦር ደመሰሰ እያለ ጥይት ተኩሰው የማያውቁ የምናብ አርበኞች በኢሳት እያስተዋወቀ፣ በፕሮፓጋንዳ የኢትዮጵያን ሕዝብ ሆድ በተስፋ ሞልቶ፣ በቁንጣን ቀፍድዶ ሲያወራጭ የነበረው ጋዜጠኛ መሳይ መኮንን ወዲያው ነው የተቀበለው። አጮኸለት፣ አደበላለቀለት። ከዚያ ሌላኛው የኢሳት አሜባ የሆነው EMSም ተቀበለው፣ አጀገኑት። ወናፍ ሁላ። የእኔ ጀግናዬ በእነዚህ ከንቱዎች የተካደው እስኬ ብረቱ ነው። እስክንድር ነጋ። ቢቀብሩት አልቀበር ያለ ፍም እሳት።

“…አምስት ዓመት ሙሉ ዐማራ የሚባል የለም እያለ የእንግሊዝ ድማሚት በዐማራ ማንነት ላይ ሲቀብር የከረመ አካይስት፣ ካታሊስት፣ በዓድዋ ጦርነት እስላሞቹን ዘማቾች ሲሞቱ ኦርቶዶክሳውያኑ አልቀበሯቸውም እያለ ለወሃቢይ እስላም የዐማራ የማረጃ ካራ ሲያቀብል የነበረ፣ በየመድረኩ ኦሮሞ ነኝ በማለት የዐማራን ግፍና መከራ ትንፍሽ ሳይል የከረመ፣ የለውጡን ሮድማፕ ያዘጋጀገኘነው እኛ ነን በማለት በሮድማፑ አማካኝነት ጓደኛውን ብርሃኑ ነጋን የትምህርት ሚንስትር ያስደረገን ሰው፤ ዐማራ የለም የሚለውን እምነቱን የት አስቀምጦ ነው አሁን የዐማራን ትግል የሚመራው? ማናቸውም ከህወሓት፣ ከኢህአዴግ፣ ከግንቦት ሰባት፣ ከብልጽግናና ከበድኑ ብአዴን ጋር የተነካኩ፣ ቫይረሱ ያለባቸው ሰዎች የዐማራን ትግል ከሩቅ እንዲደግፉ እንጂ ቀርበው እንዲያቦኩ አለመፍቀድ ይገባል። ጨካኝ መሆን ነው ለዐማራ የሚያዋጣው።  አለቀ።

“…እና ወዳጄ እኔ አሁን ስለ ፍኖተሰላም ጭፍጨፋ፣ ስለቡሬ ጄኖሳይድ እንጂ መጻፍ ያለብኝ አሮጌ ጅብ የብአዴን ከንቱ ወንጀለኛ የዘር አጥፊ ተባባሪ ሆኖ የከረመው ዮሐንስ ቧያለው ታሰረ፣ በወሳኝ ሰዓት ጀርባውን ሰጥቶት በሽምግልናው ወራት ከዘራ ይዞ፣ እሱ ራሱ ረዳት ደጋፊ በሚፈልግበት ሰዓት፣ በድዱ እየበላ፣ ዳይፐር የሚፈጅ አሮጌ አራጅ አሳራጅ የነበረ ገዱ አንዳርጋቸው ተከበበ፣ ታሰረ ብዬ፣ ፍሪ ቧያለው፣ ፍሪ ገዱ ብዬ እንድጮህ ነው የምትፈልገው? በባህርዳር ስለተረሸኑት ንጹሐን፣ በጎንደር በጅምላ ስለተገኘው መቃብር ነው መጮህ ማጋለጥ ያለብኝ ወይስ የዐማራ ደም በእጁ ስላለውና ብልፅግናን ከስሶ ብልፅግናን ለማዳን ስለሚንተፋተፈው ሰው? ሃኣ…? በየከተማው በገፍ እንደከብት ስለሚታሰረው ዐማራ መጮሁ ነው የሚያዋጣው ወይስ ለአሮጌ ገዳይ ለብአዴን? ወዳጄ ህወሓት አሁን ወደ ፌደራሉ አገዛዝ ሰተት ብላ መጥታለች። ድራማ የሚሠራውን ታሠራዋለች፣ የምትበቀለውን ደግሞ ትበቀለዋለች። አንተ ከድራማው ላይ ዓይንህን ነቅለህ ንሥሮችህ ላይ አተኩር።

“…እስኬው እንዴት ዋለ? ዘመነ ካሴስ፣ አቶ አሰግድስ፣ እነ ፋኖ ደረጀ? እነ የዋርካው ምሬ ወዳጆ፣ እነ ኪሎኔል ፋንታሁን ሙሀባው እና የአባይ ሸለቆ ብርጌድ፣ የዐማራ ሕዝባዊ ግንባር፣ የዐማራ ሕዝባዊ ኃይል እንዴት ዋሉ? እንዴትስ አደሩ? ምንስ ጎደላቸው? ምንስ እናግዛቸው በማለት ስለ ነፃ አውጪዎችህ አስብ አንጂ ስለአሮጌ ጅቦቹ ፀረ ዐማራ ስብስቦች፣ ስለ እስስቶቹ ተለዋውጦ አዳሪ ሼምለስ አክሮባቲስቶቹ፣ በ180 ፍጥነት ፍሬቻ ሳያሳዩ መጠምዘዝ ስለለመዱ የፖለቲካ ሸርሙጦች ማሰብ፣ መጻፍ፣ ማውራት የለብህም። ኢግኖር መግጨት ነው ወዳጄ። ሲመጡ እንኳን ደኅና መጣችሁ ብለህ ትቀበልና በዐማራ ስም ግን የትኛውም አደረጃጀት ውስጥ እንዳይገቡ እንደ መርዝ ብልቃጥ አርቀህ ተሳቀምጣቸዋለህ። በተለይ የ60 ዎቹን ኮቪድ 60 በሙሉ ከዐማራ ፖለቲካም ከኢትዮጵያም ጭምር ማራቅ ነው። አከተመ።

“…ትናንት ገዱንም ጆኒንም፣ አንዳርጋቸውንም ተቃውሜ ስጽፍ የስድብ ናዳ ሊያወርዱብኝ አፋቸውን አሹለው ሙጢ ከንፈራቸውን አሞጥመጠው በሚገረም ሁኔታ ግርር ብለው እንደ ግሪሳ ፔጄ ላይ ሰፍረው የነበሩት የብአዴን አባላት ናቸው። ሃሃሃሃ ሌባ ሁላ። ሳጸዳቸው ነው ነው ያመሸሁት። እኔስ መች አጣኋችሁ እና የምዋጋው እናንተን አይደል እንዴ? የኢዜማ እና የግንቦት 7 ካዳሚዎች ደግሞ ለአንዳርጋቸው ጽጌ ዋይ ዋይ ሊሉ አሰፍስፈው መጡ። ጥፋ ከዚህ ምድረ ኮተት ብዬ ሳጸዳቸው ነው ያመሸሁት። እኔ ዘመዴ ሾርት ሚሞሪያም አይደለሁም። እኔ የቀረበልኝን ሁሉ አግበስብሼ የምበላ ሆዳም አይደለሁም። እኔ ዘመዴ በቃላት ጨዋታ፣ በወሬ ቀደዳ የምትሸውደኝ አይደለሁም። እኔ ዘመዴ ሴራ አፍራሽ ነኝ። እግዚአብሔር የሴረኞችን ሴራ አከሽፍ ዘንድ፣ ክንብንባቸውንም የበግ ለምዳቸውንም ገልጬ ተኩላቸውን እገልጥ ዘንድ የተላኩ የፀረ ኢትዮጵያ ሃሳውያንን ራስ ራሳቸውን እቀጠቅጥ ዘንድ የተቀባሁ የሥላሴ ባርያ የድንግል አሽከር፣ የምሥራቁ ሰው የሐረርጌው ቆቱ መራታው ባለማዕተቡ ዘመዴ ነኝ። ትሰማኛለህ እንጂ አልሰማህም። ትከተለኛለህ እንጂ አልከተልህም። ፍረጃ፣ ስድብ ከመጤፍም አልቆጥር፣ አሸማቅቃለሁ እንጂ አልሸማቀቅም። ሰምተሃል።

“…አዎ እኔ ዘመዴ ነፃ ያወጣኛል ብዬ ቅንጣት ለማልጠራጠረው ለዐማራ ትግል ደሜን እሰጣለሁ። እሰደብለታለሁ፣ አሸባሪ ተብዬም እከሰስለታለሁ። በዚህ የነጻነቴ ጮራ፣ በነፃነቴ ቀንዲል ፊት የሚቆም ማንኛውንም ደንቃራ ሁላ አይደለም ሌላ ሰው ራሴ ዘመዴንም ብሆን እንኳ አልምረውም፣ አልፋታውምም። ከራስ በላይ የሚራራለት ከሌለ ደግሞ ሌላው ተራ ኢምንት ነገር ነው ማለት ነው። “ወያኔ ነፍሰ ገዳይ አረመኔዎቿን ደብቃለች። ኦህዴድም እንደዚያው፣ ዐማሮችም ሲመጡ ባናሸማቅቃቸው” የሚሉም አሉ። የዐማራ ትግል የአራጅ፣ የሌባ፣ የአረመኔ መደበቂያ አይደለም። የዐማራ ትግል ሌባ ዘመነ ካሴን፣ ሌባ እስክንድር ነጋን፣ ሌባ ምሬወዳጆን አይፈልግም። የዐማራ ትግል ቅዱስ ትግል ነው። የዐማራ ትግል የወንበዴ መደበቂያ ዋሻ አይደለም። የዐማራ ትግል መንፈሳዊ ነው። ጿሚ ሰጋጅ የዐማራ እስላሞች እና ዳዊት ደጋሚ፣ ጸሎተኛ ጿሚ አስቀዳሽ የዐማራ ኦርቶዶክሶች፣ ፕሮቴስታንቶች ሆነው ከምዕራቡ ሸቀጥ ራሳቸውን ያራቁ ዐማሮች፣ መነሻቸውን ዐማራ፣ መዳረሻቸውን ኢትዮጵያ ያደረጉ ንፁሓን የሚሳተፉበት ቅዱስ ትግል ነው። እንጂ የኮተታሞች የብልፅግናና ወያኔ ኦነግ ዓይነት የጨለማው ዓለም ተላላኪዎች ምሽግ አይደለም። ዐማሮቹ ይሄን የጨለማ አውሬ የንጹሐን ደም ግብሩ የሆነ አገዛዝ ለመግረሰስ የእግዚአብሔር ጣት ሆነው የተላኩ፣ የተነሡ ነፃ አውጪዎች ናቸው እንጂ እንደ ወያኔና ኦነግ የአረመኔ መደበቂያ ምሳሌ ሊሆኑ አይገባም። ተግባባን። ኢንደዣ ኖ…!

• ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ አሸበርቲው… !

Filed in: Amharic