>

ጭራቅ አሕመድ ሲንድሮም እና የዳንኤል ክብረት እየሱስ  (መስፍን አረጋ)

ጭራቅ አሕመድ ሲንድሮም እና የዳንኤል ክብረት እየሱስ

መስፍን አረጋ

ሲንድሮም (syndrome) ማለት በተለያዩ ተዛማጅ ምልክቶች (symptoms) የሚንፀባረቅ፣ የተለያዩ ተዛማጅ በሽታወች (በተለይም ደግሞ ያይምሮ በሽታወች) ጥምር በሽታ ማለት ነው።  ስለዚህም ለሲንድሮም ያማረኛ አቻ ይሆን ዘንድ ፅምር እና ተውሳክ ከሚሉት ቃሎች ፅምርሳክ (syndrome) የሚለውን ቃል መፍጠር እንችላለን።  የፅምርሳክ ተጠቂ ወይም ሰለባ የሆነ ግለሰብ ደግሞ ፅምርሳካም ወይም ፅምርሳከኛ ሊባል ይቻላል። 

ለምሳሌ ያህል ስቶኮልድ ፅምርሳክ (stockholm syndrome) ማለት ዘወትር የሚያጎሳቁልን፣ የሚያሰቃይን ወይም የሚያዋርድን ባጠቃላይ አነጋገር ደግሞ በአካል (physical) ወይም/እና በስሜት (mental) የሚነውርን (ነውር የሚፈፅምን፣ abuse) ሰው ወይም ቡድን መውደድ ማለት ነው።  ፅምርሳከኛው ነውር የሚፈፅምበትን ሰው ወይም ቡድን የሚወደው በሚፈፀምበት ነውር (abuse) ሳቢያ የሚሰማውን የቁጭት ስሜት ለማለዘብ ሲል (coping mechanism) ሊሆን ይችላል።  አለበለዚያ ደግሞ በዚያ ደረጃ ሲነወር (ነውር ሲፈፀምበት) ምንም ማድረግ ባለመቻሉ ምክኒያት በርግጥም ራሱን በመናቅ ጠልቶ /ነዋሪው/ (ነውር ፈጻሜው) በዚያ ደረጃ ሊነውረው በመቻሉ ደግሞ እጅጉን አድነቆት በእውነትም ስለወደደው ይሆናል።

ወደ ጭራቅ አሕመድ ስንመለስ ደግሞ ግለሰቡ ያይምሮ በሽተኛ ነው ማለት ያዋጁን በጆሮ ነው።  በሽታው ደግሞ የተለያዩ ምልከቶች (በተለይም ደግሞ አለቅጥ የመለማመጥና የመሽቆጥቆጥ፣ ሲበዛ የመዋሸትና ሽምጥጥ አድርጎ የመካድ፣  የከረረ ማጭበርበርና የመረረ ጭካኔ) ተጣምረው የሚታዩበት ጥምር በሽታ መሆኑ አገር ያወቀው ፀሐይ የሞቀው ነው።  በኔ በመስፍን አረጋ እይታ ደግሞ እነዚህ የጭራቅ አሕመድ ያይምሮ በሽቶች የተነጣጠሉ ሳይሆኑ፣ ርስበርስ የሚተጋገዙ ተዛማጅ በሽታወች ናቸው።  ስለዚህም በሙያየ ልቦናሲነኛ (psychologyist) ባልሆንም፣ ስለ ልቦናሲን (psychology) ያለኝን መጠነኛ እውቀት መሠረት በማድረግ የጭራቅ አሕመድን በሽታ ጭራቅ አሕመድ ፅምርሳክ (Abiy Ahmed Syndrome) የሚል ስያሜ ሰጥቸዋለሁ፣ ላጉል ድፍረቴ ልቦናሲነኛወችን ይቅርታ እየጠየኩ። 

ጭራቅ አሕመድ ፅምርሳክ ማለት ዘርጥጦ ለመጣል እግርን መሳም ተብሎ ባጭሩ ሊበየን (defined) ማለትም ብያኔ (definition) ወይም ትርጓሜ ሊሰጠው ይችላል።  ስለዚህም ጭራቅ አሕመድ ፅምርሳክ ይሁዳ ክርስቶስን አጋልጦ ከሰጠበት የይሁዳ መሳም (Juda’s kiss) ከሚባለው ክስተት ጋር በተወሰነ ደረጃ ይመሳሰላል።  የጭራቅ አሕመድ ፅምርሳክን ምንነት በሚከተለው ምሳሌ መረዳት ይቻላል።  

ማናቸውንም አጋጣሚ ካገኘ ሊገድልህ ቁርጥ ውሳኔ የወሰነ፣ ካልገደልከው የሚገድልህ የመረረ ጠላት አለህ እንበል።  ይህ ጠላትህ ደግሞ ባንድ ወቅት እጅህ ላይ ወደቀና ልትገድለው ተነሳህ እንበል።  ልትገድለው ስትነሳ ግን እግርህ ሥር ወድቆ እግርህን በምላሱ እየላሰ፣ በእንባው እያራሰ ራሱን አለቅጥ በማዋረድ እንዳትገድለው ይለማመጥህ ጀመር እንበል።  ይህ ጠላትህ በዚህ ደረጃ ራሱን በራሱ ሲያዋረድ ስታይ አለቅጥ ትፀየፈውና ፊትህን ስታዞር እንደሚገድልህ በርግጠኝነት እያውክ ፊትህን ታዞራለህ።  እሱም ፊትህ ስታዞርለት ማጅራትህን ብሎ ይገድልሃል።  ጭራቅ አሕመድ አያሌ ጉምቱወችን የገደለውና ያመከነው በዚህ መንገድ ነው።  ባጭሩ ለመናገር ጭራቅ አሕመድ ማለት ስታፈጥበት የሚጥመለመል ስትዞርለት የሚናደፍ ዐሲል ዕባብ ማለት ነው።  

ለመሳሌ ያህል ጭራቅ አሕምድ የተዋሕዶን ዐብዮት አክሽፎ ተዋሕዶን ከሞት አፋፍ እንድትደርስ ያበቃት በዚሁ የመለማመጥና የመናደፍ ዘዴው ነው።  ተዋሕዶ ሐይማኖት በሕልውናዋ ላይ የመጣባትን ጭራቅ አሕመድን ለመቆራርጥ ሰይፏን ካፎቱ አውጥታ በጭራቁ ላይ አቃጣችበት፡፡  ጭራቁም በተዋሕዶ ሰይፍ ሊቆራርጥ መሆኑን አውቆ፣ በፍርሃት እየራደ ተዋሕዶ አባቶች እግር ሥር ወድቆ ጫማቸውን በምላሱ እየላስ በእንባው ያርስ ጀመር።  የተዋሕዶ አባቶች ደግሞ ያገር መሪ ቀርቶ ተራ ግለሰብ ያደረገዋል ተብሎ በማይታሰበው በጭራቁ ያልተለመደ ድርጊት ከመገረም አልፈው በመደመም ከወደቀበት ሊያነሱት ጎንበስ ብለው እጃቸውን ሰጡት።  ጭራቁ ግን የተወሕዶ አባቶች የሰጡትን እጅ ስቦ መሬት ላይ በግንባራቸው ፈጠፈጣቸው።  እነሱ ከግራቸው ሊያነሱት ሲሞከሩ እሱ እግሩ ሥር ጣላቸው።  እግሩ ሥር ከጣላቸው በኋላ ደግሞ እግራቸው ሥር እንዲወድቅ በማድረጋቸው የያዘባቸውን ቂም በደንብ ተወጣባቸው። 

የዳንኤል ክብረት እየሱስ

ዳቆን ዳንኤል ክብረት እየሱስን ባይኔ በብረቱ አየሁት ያለው፣ ጭራቅ አሕምድ የተዋሕዶ አባቶችን እግር በምላሱ እየላስ በእንባው ሲያብስ አይቶ ነው።  ዳቆን ዳንኤል ያላወቀው ይልቁንም ደግሞ አውቆ እንዳላወቀ የሆነው ግን የጭራቅ አሕመድ ዓላማና የእየሱስ ዓላማ ዱባና ቅል እየቅል ብቻ ሳይሆኑ፣ ሐራምባና ቆቦ (ፍፁም ተቃራኒ፣ እንጦጦና የረር) መሆናቸውን ነው።  እየሱስ የሐዋርያወቹ እግር ያጠበው ትሕትናን ሊያስተምራቸው ነበር።  ጭራቅ አሕመድ ተዋሕዶ አባቶች እግር ሥር የወደቀው ግን፣ ሊያነሱት እጃቸውን ሲሰጡት ስቦ ለመፈጥፈጥ ነው።  ስለዚህም ጭራቅ አሕመድ እየሱስ ሳይሆን የእየሱስ ፈፁም ተቃራኒ ዳቢሎስ ነው።  ዳቆን ዳንኤል ክብረት ባይኑ በብረቱ ያየው እየሱስን ሳይሆን ዳቢሎስን ነው።  የሚያገለግለውም እየሱስን ሳይሆን ዳቢሎስን ነው።

የተዋሕዶ አባቶች ደግሞ ዳቢሎሱ ጭራቅ አሕመድ በተዋሕዶ ላይ ሲመጣ ሲመለከቱ፣ ለመዕምናቸው ዘወትር የሚሰብኩትን የሰይፈኛውን የቅዱስ ሚካኤልን ወይም ደግሞ የፈረሰኛውን የቅዱስ ጎርጊስን ገድል መርሳት አልነበረባቸውም።  እነዚህ የተዋሕዶ አባቶች ተዋሕዶን ከኦነጋዊው ዳቢሎስ በቀላሉ ማዳን ይችሉ የነበሩት፣ መዕምናዊ ኃይላቸውን ፈርቶ በመንቀጥቀጥ እግራቸው ሥር ሲወድቅ፣ በተዋሕዶ አባትነታቸው በታጠቁት የሥላሴ ሠይፍ አንገቱን ቀንጥሰው በመጣል በወደቀበት ማስቀረት ነበር።  እነሱ ግን አጉል ይቅርባይ በመሆን ዳቢሎሱን ከግራቸው ሥር ሊያነሱት ሲሞከሩ ዳቢሎሱ እግሩ ሥር ጥሏቸው፣ እነሱ ወድቀው ተዋሕዶን ይዘው ወደቁ።     

የጭራቅ አሕመድ ድርድር፣ አዘናግቶ ለመቅበር

ጭራቅ አሕመድ ፅምርሳከኛ (የፅምርሳክ በሽተኛ) ስለሆነ፣ ለድርድር የሚነሳው ሊሸነፍ መሆኑን ሲረዳ ብቻ ነው።  የሚደራደረው ደግሞ ሰጥቶ በመቀበል ለመስማማት ብሎ ሳይሆን፣ ሊያሽንፈው የተቃረበውን ኃይል በድርድር ሰበብ እየተለማመጠ ካዘናጋ በኋላ ድባቅ ለመምታት ሲል ብቻ ነው። ስለዚህም ማናቸውም ግለሰብም ሆነ ቡድን ከጭራቅ አሕመድ ጋር እደረደራለሁ ብሎ የተነሳ ቀን፣ ቀብሩን መማስ መጀመሩን ሊያውቅ ይገባል። 

በተለይም ደግሞ ፋኖ ሆይ ከጭራቅ አሕመድ ጋር እደራደራለሁ ብልህ የተነሳህ ቀን፣ ቀብርህን መማስ መጀመርህን እወቀው።  ያማራ ሕልውና ትግል አመራሮች እውነትም የሚታገሉት ላማራ ሕልውና ከሆነ፣ የሚከተሉትን ሁለት ቅድመሁኔታወች (preconditions) ባላስቀመጠ በማናቸውም ድርድር ውስጥ አንገታቸው ቢቆረጥ መሳተፍ የለባቸውም።  የመጀመርያው የድርድር ቅድመሁኔታ የጭራቅ አሕመድ በላዔ አማራ ኦነጋዊ መንግሥት ሙሉ በሙሉ መገርሰስና ሙሉ በሙሉ መፈራረስ ሲሆን፣ ሁለተኛው የድርድር ቅድመሁኔታ ደግሞ ጭራቅ አሕመድና ግብራበሮቹ (በተለይም ደግሞ ደመቀ መኮንንተመስግን ጡሩነህስማ ጡሩነህአበባው ታደሰይልቃል ከፋለ እና የመሳሰሉት ብአዴናዊ ግብራበሮቹ) ባማራ ሕዝብ ላይ ለፈፀሙት ወንጀል አይቀጡ ቅጣት ተቀጥተው ዘላለማዊ መቀጣጫ መሆን ነው።

   መስፍን አረጋ

mesfin.arega@gmail.com

Filed in: Amharic