>
5:31 pm - Saturday November 12, 2411

ኢትዮጵያን ለማዳን የአማራውን ትግል መቀላቀል  ግድ ይላል (በዲቻ ጫሞ)

ኢትዮጵያን ለማዳን የአማራውን ትግል መቀላቀል ግድ ይላል

በ ዲቻ ጫሞ

ህብር ኢትዮጵያን የመሠረተው አማራው ነው። ነገር ግን አማራው ህብር  ኢትዮጵያን ሲመሠርታት ኢትዮጵያ የሱና ለሱ ብቻ እንድትሆን አድርጎ አይደለም።   አማራው ለኢትዮጵያ አስተሳሰብና ማንነት ለሺ ዓመታት ሲተዳደርበት፣ የኖረውን የዳበረውን የአስተዳደር ፣ የታሪክ ፣ የባህል ፣  የቴክኖሎጂ፣ የፍልስፍና፣ የሥነ-ጽሁፍ፣ የሥነ-ጥበብ፣ የሙዚቃ፣  የትምህርት፣ የሃይማኖት፣  የመንፈሳዊነት ፣ የአርበኝነት መገለጫዎቹንና ከሁሉም በላይ አማራዊ ስነልቦናውን  ለኢትዮጵያዊነት መሠረት እንዲሆን በማበርከት በር።

አማራው ለመላው የኢትዮጵያ ህዝቦች  ሥልጣኔውንና ታሪኩን ብቻ ሳይሆን ሥልጣኑንም እያጋራ  ለኢትዮጵያዊነት አስተሳሰብ እድገትና ብልጽግና መላው ኢትዮጵያውያን የበኩላቸውን አስተዋጽዎ እንዲያበረክቱ ሁኔታዎችን አመቻችቷል። ይህን በማድረጉም ሁሉም ኢትዮጵያዊ የነገድ አባላት እንደየ ችሎታቸው እንደየ ባህላቸውና እንደደረሡበት ሥልጣኔ  ደረጃ ኢትዮጵያን ለመገንባት የበኩላቸውን አስተዋጽዎ የማድረግ እድል አግኝተዋል።

ለምሳሌ ያህል፣ የሸዋ ኦሮሞዎች ሀገርን በማስተዳደር ከአማራው ጋር በመዋሀድ በብዛት ተሳትፈዋል።   በቅርብ ጊዜ የኢትዮጵያ የአርበኝነትና የውትድርና ታሪክ ሀገርን ከጠላት በመከላከልና በመጠበቅ  ብዙ የአርበኝነት አኩሪ ታሪክ የፈፀሙ እንደ ሥመጥር አርበኛ ጀነራል ጃካማ ኬሎ  ያሉ የሀገር ባለውለታ ጀግኖችን ማፍራት ተችሏል። ጉራጌዎች በንግዱ ዘርፍ በመላው ኢትዮጵያ ተሠማርተው ኢትዮጵያን በንግድና በባህል በማስተሳሰርና በማገናኘት ሥራ የበኩላቸውን ከፍተኛ አስተዋጽዎ አበርክተዋል።  ይህ አይነቱ  ህብረት የተገኘው አማራው ባደላደለው ሁሉም ነገዶች በወደዱትና በተቀበሉት በተጋሩት ጥልቅ ኢትዮጵያዊነት ስሜት ነው። ለስኬቱም የአማራ ነገሥታት ብልህና ጊዜውን የዋጀ ፍትህሃዊ አስተዳደር ያበረከተው አስተዋጽዎ ከፍተኛ ነው። አማርኛ ቋንቋ  በመላው የኢትዮጵያ ግዛት  መነገር መቻሉ   የጋራ ኢትዮጵያዊ አስተሳሰብና ማንነትን ለመገንባት አስችሏል። አማርኛ ቋንቋ የኢትዮጵያን ጎሳዎች ሁሉ ያስተሳሰረና አንድ ያደረገ ለሁሉም ኢትዮጵያዊ ጎሳ   ከአካባቢው ወጥቶ በመላው ኢትዮጵያ ተንቀሳቅሶ በነፃነት ለመማር ለመሥራት ለመኖር  እንዲችል እድል የሰጠ ነው። የትግራይና የወላይታ ልጆች አዲስ አበባ እንደ ልብ  መጥተው ለመሥራትና ኑሯቸውን ለመመሥረት የቻሉት አማርኛ ቋንቋን በመናገራቸው ነው።   ለትግሬው ኢትዮጵያዊና ለኦሮሞው ኢትዮጵያዊ  ግንኙነት ድልድይ የኾነው የአማርኛ ቋንቋ ነው።  ትግሬው በኦሮሞ ምድር በነፃነት እንዲሠራ እንዲንቀሳቀስ ያደረገው አማራው የመሠረተው በነገድ ሳይሆን በችሎታ ብቻ ወደ ላይ ከፍ የሚባልበትን የሀገር አስተዳደርና ግንባታ ሥርዓት በማነፁ ነው። ለዚህ ነው፤  አማርኛ ቋንቋን ሳንጠቀም ስለኢትዮጵያ ልናወራ የማንችለው።

ኢትዮጵያዊ አስተሳሰብ አይዲዮሎጂ ለመሆን የበቃ  በመላው አፍሪካና በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ጥቁር ህዝቦች ከኮሎኒያሊዝምና ከባርነት ለመላቀቅ ደረጉት ትግል ዋና የማታገያ ሃሳብ ሆኖ ያገለገለ የነጻነት ሥነ-ልቦና፣ የፖለቲካ፣የኢኮኖሚ፣የማንነት ፣ የባህል፣የእምነት፣ የታሪክ ቅርሶችንና  እሴቶችን በውስጡ አጭቆ የያዘ ነው።  ብዙ ነገዶች ከሚገኙበት ከደቡብ የኢትዮጵያ ክፍል   የተወለዱት ታዋቂው ኢትዮጵያዊ የታሪክ ተመራማሪ ፕ/ር ኃይሌ ላሬቦ   ኢትዮጵያኒዝም ባጭሩ ሲገልጹት  ‘’ኢትዮጵያኒዝም ረቂቅ ሃሳብ’’  ነው ነበር ያሉት።

እንዳለመታደል ሆኖ በአሁኑ ወቅት፣ በሥልጣን ላይ ያሉት የኦሮሞ ገዢዎች  ከአባቶቻቸው የተላለፈላቸውን  የኢትዮያዊ የጀግንነት የጋራ ታሪክና የኢትዮያዊነት  አስተሳብና ማንነት በመካድ፤   ልክ እንደ ፖለቲካ ደቀመዝሙራቸው የፈረንጅ ተላላኪው ሕ.ወ.ሓ.ት በፈረንጆች አይዞህ ባይነትና እርዳታ ሥልጣን ከተቆናጠጡ በዃላ ኢትዮጵያዊነትን በመሠረተው በአማራው ማህበረሰብና በኦርቶዶክስ እምነት ላይ ግልፅ ጦርነት ከፍተውበታል። እነዚህ ኦነጋውያን  የፈረንጅ ተላላኪ ባንዳዎች  ባለፉት አምስት ዓመታት ለመናገር የሚሰቀጥጥ የዘር ማጥፋት ፍጅት  ፈጽመውበታል። በወለጋ ምድር በግፍ  የፈሰሰው  የንፁሃን የአማራ ገበሬዎችን ደም ምስክር ነው።   በወለጋ በሸኔ አመሃኝተው የጨረሱትና ያስጨረሱት የንፁሃን አማራ ደም አልበቃ ብሏቸው፤ አሁን ደሞ በመከላከያ ሥም ያደራጁትን ግዙፍ ኦነጋዊ ጦር የአማራውን ህልውና ለማጥፋት ወደ ሸዋ፣ ወሎ፣ ጎጃምና ጎንደር አዝምተዋል።

የአማራው የሞራል ልእልና  ከፍተኛ በመሆኑ  ምንም እንኳን በገንጣይና በጎሰኛ ፖለቲከኞች ለዘመናት ቢበደልም ለኢትዮጵያ አንድነትና ክብር ሲል  ሁሉንም እስካሁን ሲታገስ ቆይቷል።

አሁን ግን  አማራው ትእግስቱ ተሟጦ አልቋል!!!። በአሁኑ ወቅት እነዚህን ፀረ-አማራና ፀረ- ኢትዮጵያ ጡት ነካሽ የትግሬና የኦሮሞ  ባንዳ የፈረንጅ ተላላኪ የኦነግና የሕወሓት  ኃይሎች ለመፋለም ነፍጡን ወልውሎ ተነስቷል።  አማራው እራሱን ከጥፋት የማዳንና ኢትዮጵያን ወደቀደመ ክብሯ የመመለስ ታሪካዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት እስካሁን ዋነኛ እንቅፋት ሆነው በውስጡ ተሰግስገው  ለሠላሳ ሦስት ዓመታት ሲያስደሙትና ሲያስበድሉት የኖሩትን የባንዳ  ተላላኪ፤ የውስጥ ሆዳም ብአዴን ኃይሎች ላይ  እርምጃ መውሰድ በመጀመር በሸዋ ፣ በወሎ፣በጎጃም በጎንደር ያለ ፋኖ ላይመለስ አንድ ሆኖ ተነስቷል።  አማራው ከእንግዲህ  የአማራነቱን ክብር ወደቀድሞው ቦታ የመመለስ ታሪካዊ ግዴታውን ሊወጣ ተማምሏል።  አማራው መነሻውን አማራ መዳረሻውን ኢትዮጵያ ያደረገውን ትግል አቀጣጥሏል።  ከእንግዲህ  ከአማራው ፊት የሚቆም ባንዳ እጣፈንታው የውሻ ሞት መሞት ብቻ ይሆናል።  አማራው፤ አማራዊ ነፃነቱን ካገኘ ጀግኖች አባቶቹ የመሠረቷትን ኢትዮጵያ መልሶ ወደነበረችበት ክብሯ ይመልሳታል።  ከፀረ-አማራና ፀረ-ኢትዮጵያ መሪ ከሆነው አራት ኪሎ ምኒሊክ ቤተመንግሥት  የተተከለውን  አውሬና ጀሌዎቹን ለመጥረግ በሚደረገው ትግል መላው የኢትዮጵያ ነገዶች ህብረት የሚያስፈልግበት ሰዓት ነው። የአዲስ አበባም ህዝብ ከተኛበት እንቅልፉ ነቅቶ ኢትዮጵያዊነቱንና የሚወደውን አረንጓዴ፣ቢጫ ፣ቀይ ሰንደቅዓላማውን፣ ኑሮውን  ሊነጥቁት የተነሱትን ጎሰኛና ስግብግብ ባንዳ የኦሮሙማ ፕሮጀክት ፋራ ቁማርተኞች በቃ ብሎ፣  በውድ ልጁ በጀግናው እስክንድር ነጋ መሪነት የተጀመረውንና የሚመራውን  “መነሻው አማራ መዳረሻው ውዲቷ ኢትዮጵያ” የኾነውን ትግል በቁርጠኝነት የመቀላቀያው ሰዓት አሁን ነው።

ክብርና ድል  ባንዶችን እየተፋለሙ ላሉት ፋኖዎቹ ለእነ እስክንድር ነጋ ይሁን!

ድል ለውዲቷ ኢትዮጵያ!!

Filed in: Amharic