ይድረስ ለፋኖ አመራር – አስቸኳይ መልእክት!
ዳግማዊ ጉዱ ካሣ
የገጠመን ጠላት በዓለም ታሪክ ማንም ሕዝብ ገጥሞት የማያውቅ በጭካኔው ወደር የማይገኝለት ነው፡፡ የኛ ጠላት የጭካኔው መነሻ እየተጋተ ያደገው የአማራ ጥላቻ ሲሆን ይህ ጥላቻው እያሸተና እየጎመራ እንጂ እየለዘበ ሲሄድ አይታይም፡፡
ሌላው አስገራሚና አሳዛኝ ነገር ደግሞ የኞች የምንላቸው አማራ ነን የሚሉ ዜጎች የጠላቶቻችን አባሪ ተባባሪ ሆነው በባርነት ለኦነግሸኔና ለሕወሓት በማደር የገዛ ሕዝባቸውን የሚያስፈጁ መሆናቸው ነው – ይሄ ደግሞ አስደንጋጭና በየትኛውም የዓለማችን ክፍል በኛ ላይ የተከሰተውን ያህል ያልታዬ ልዩ ተፈጥሮ ነው፡፡ በነዚህና ሌሎች ተያያዥ ምክንያቶች የተነሣ የአማራው የኅልውና ትግል ፈተና የበዛበት ቢመሥልምና ቢሆንም የመጨረሻውን ዋንጫ የሚበላው ግን ከ50 ዓመታት በላይ የተገፋውና በቃላት ሊገለጽ የሚከብድ በደል የደረሰበት አማራ መሆኑ ተብሎ ተብሎ ያለቀ ታሪካዊና ሃይማኖታዊ እውነት ነው፡፡ ለዚህም ነው አማራ ሣይበድላቸው እንደበደላቸው በማስመሠል የአያ ጅቦንና የእመት አህይትን የውኃውን አታደፍርሽብኝ ተረት በሚዘክር መልኩ አማራን ካለሥራው ስሙን እያጠለሹ በጋራ ሊያጠፉት እየዶለቱ የሚገኙት፡፡ ለትግሬ ከአማራ ይልቅ ኦሮሞ የሚቀርብ መሆኑን መቀሌ ላይ አባገዳዎች ሊያውም ያላንዳች ሀፍረት በአማርኝ ቋንቋ ሲናገሩ መስማታችን እነዚህ ወገኖቻችን ምን ያህል ጭንቀት ውስጥ እንደገቡ ይጠቁማል፡፡ ሰው ግራ ሲጋባ ከማንኛውም ዓይነት አመክንዮና ሎጂክ ያፈነግጣል፡፡ እንጂ ሌላው ሁሉ ቀርቶ ዋቄፈና ኦሮሞና ኦርቶዶክስ ትግሬ፣ አባገዳ ኦሮሞና አሸንድዬ ትግሬ ምንና ምን እንደሆኑ እንኳንስ አማራው ጠምባሮውና ደራሳው ያውቀዋልና በነዚህ ጅላንፎዎች የ”አንድ ሕዝብነት” ‹አዲስ ግኝት› የማይስቅ የለም፡፡ በዚያም ላይ “አትግደሉኝ፤ ያወጃችሁብኝን የዘር ፍጂት አንሱልኝ፤ ሹመት ሥልጣኑ ቀርቶብኝ በሀገሬ ሠርቼ ልኑር” በማለቱ ብቻ “አንድ ቋንቋ፣ አንድ ብሔር፣ አንድ ሃይማኖት ልጫንባችሁ ብሎ የተነሣብን ጽንፈኛ ኃይል አለና አብረን እናጥፋው” ብለው መቀሌ ላይ ሲዋዋሉ መስማት ከማስደንገጡም በላይ ሰዎቹ ሀፍረትንና ይሉኝታን ሸጠው ስለመብላታቸው ተጨማሪ ማስረጃ ሳያስፈልግ መገንዘብ ይቻላል፡፡ ድንቁርናቸው ገደብ አጣ፡፡
ለማንኛውም ይህን መሠሉ ተደጋጋሚ ስህተታቸው በተለይም አማራው ላይ ያወጁት የዘር ማጥፋት ዐዋጅ እንወክለዋለን በሚሉት ማኅበረሰብ ቀጣይ ትውልድ ላይ የሚያሣርፈውን የታሪክ ጠባሳ ተገንዝበው ከተጨማሪ ጥፋት ቢታቀቡ ጥሩ ነበር፡፡ ግና ምን ዋጋ አለው – አንዴውኑ በጥላቻና ጥላቻውን በወለደው የሀብትና የሥልጣን ጥቅም ታውረዋልና አሁን ማንንም አይሰሙም፡፡ ይሁንና ሞትንም ሆነ ምድራዊ ሥቃይን የባሕርይ ገንዘቡ ያህል አድርጎ የተለማመደው አማራው ከምን ጊዜውም በበለጠ አሁን ክፉኛ አምርሯል፡፡ የቅጣት ብትሩን አይችሉትም፡፡ እናም እነዚህን ገልቱዎች በመለሳዊ አነጋገር “መንገዱን ጨርቅ ያድርግላቸው” ብሎ በመመረቅ ወደሚጠብቃቸው እንጦርጦስ ከመሸኘት ባለፈ የተሻለ አማራጭ አናገኝላቸውም፡፡ ያም ቀን ቀርቧል፡፡ መስዋዕትነቱ ብዙ ነው፤ ድሉ ግን የአማራውና የኢትዮጵያ ነው፡፡ ጠብቅ፤ ጠብቂ፤ እንጠብቅ፡፡ ወደ ብርሃናማው የዋሻው ጫፍ እየደረስን ነው፡፡
የአማራ ፋኖ በኦሮሙማ ሠራዊት ላይ ከሚያሣየው ቆራጥ እርምጃ ላቅ የሚል የማያዳግም እርምጃ በአማራ ባንዳዎች ላይ ካላሣዬ ትግሉ ታጥቦ ጭቃ ነው፡፡ “የዳኛ ልል ያማታል፤ ‘የወንድ’ ልል ያፋታል” እንደሚባለው እንዳይሆን ፋኖዎች እባካችሁን ለሆዳም ባንዳና ይሁዲዎች የሚራራ ልብ አይኑራችሁ፡፡ ይህ ዓይነቱ የተለሳለሰ አካሄድ ብዙ ዋጋ እያስከፈለን ነውና በቅጡ ይታሰብበት፡፡ 120 ሚሊዮን ሕዝብ የትም ታይቶ በማይታወቅ ከፍተኛ ጉጉት እየጠበቃችሁ ሣለ እፍኝ በማይሞሉ የአማራና የብአዴን ከርሣሞች ምክንያት የሚሊዮኖች ተስፋ እንዲጨልም በር አትክፈቱ፡፡ በዚያ ላይ በነዚሁ መርዘኞች ጥቆማና እገዛ ብዙ አማራ በቀየውም ከቀየው ውጪም እንደሣር እየታጨደና በየማጎሪያው ማዕከላት እንደነዶ እየታሠረ በርሀብና በጊንጣዊ ግርፋት ፍዳውን እያዬ ነው፡፡ ይህ አካሄድ በፍጥነት መስመር ይዞ ዕልባት ካልተበጀለት ከወረቱ ስንቁ እንዳይሆን ያሰጋል፡፡ የምትችሉ ሁሉ ይህን መልእክቴን ለበላይ የፋኖ አመራር በአስቸኳይ እንዲደርስ አድርጉ፡፡ ቀን ቀንን በወለደ ቁጥር አሁን መናገር የማልፈልጋቸው ችግሮች ይገነግኑና ለጠላቶች ማንሠራራት ምቹ ሁኔታ ይፈጠራል – “ቀድሞ ነበር እንጂ መጥኖ መደቆስ፤ አሁን ምን ያደርጋል ወጪት ጥዶ ማልቀስ …” እያለ የነገሮችን አካሄድና ተጠባቂ ውጤት በተረት ሣይቀር በሚተነብይ ማኅበረሰብ ውስጥ የጊዜን፣ የሁኔታንና የቦታን ተገጣጥሞሽ በማጤን ለፀፀትና ለቁጭት የማይዳርግ ወቅታዊ እርምጃ መውሰድ ከፋኖ አመራር ይጠበቃል፡፡ በአሁናችን ላይ አንዲት ደቂቃ ወሳኝ ናት፡፡ ፈረንጆችም ይላሉ – “Hit the iron when it is hot!.”