ሦዶማዊ አገዛዝን ማስወገድ የሁሉም ድርሻ ነው!
ይነጋል በላቸው
ወቅቱ የትግል ነው፡፡ ከብዙ ወሬ ብዙ ተግባርን ይጠይቃል፡፡ ቢሆንም መረጃን መለዋወጥ ደግሞ ተገቢ ነው፡፡ እናም በስሱም ቢሆን በተወሰኑ ጠቃሚና አንገብጋቢ ነጥቦች ዙሪያ ሃሳብ እንለዋወጥ፡፡ ታላላቆች በተለይ ስሙኝና ወጣቶቻችንን እንምከር፡፡
አጣዳፊውን ላስቀድም፡፡ የወያኔና የኦነግ-ሸኔ አቢይ ወሽመልስ መንግሥት ሦዶማዊ መሆኑን መናገር የዐዋጁን በጆሮ እንዲሉ ነውና ጠያፍ አይደለም፡፡ እነዚህ መንግሥታት ለጥልቁ የጨለማው መንግሥት የፈረሙ ስለመሆናቸው ዕኩይ ድርጊቶቻቸው በገሃድ ይመሰክራሉ፡፡ አሁን ሰሞኑን እንኳን አራት የአማራ ልጆችን በዚያው በአማራ ክልል በቡድን አስገድደው መድፈራቸውንና ህክምናም እንዳያገኙ ማድረጋቸውን እየሰማን ነው፡፡ አራቱ ታውቀው ወሬው በይፋ ተገለጠ እንጂ የሚዲያ ሽፋን ሳያገኙ በየቦታው በኦነግ ሸኔ የመከላከያ ተብዬ ሠራዊት እየተደፈሩ በስቃይ ላይ የሚገኙ ወገኖቻችን ቁጥር እጅግ ብዙ ሊሆን እንደሚችል መገመቱ አይከብድም፡፡ ከአራቱ ተደፋሪ ወንዶች መካከል አንዱ ራሱን ማጥፋቱንም ለማወቅ ተችሏል፡፡ የሴቶቹንማ ቤቱ ይቁጠረው፡፡ ጅምላ ርሽናውንም እንዲሁ፡፡ ፋኖ ፍጠን ታዲያ!!
“ኦነግ-ሸኔና ኦህዲድ ብል*ግና ባልጠፋ ሴት ለምን ወንዶችን ይደፍራሉ?” ብሎ መጠየቅ ተገቢ ነው፡፡ ብዙ ሰው አያውቅምና፡፡
መለስ ዜናዊ ሦዶማዊ ስለመሆኑ አላውቅም፤ ለመጠራጠር የሚያበቁኝ ነገሮችን ማድረጉንም አላስታውስም፡፡ ስለሆነም ምንም እንኳን በርካታ ተግባራቱ ከክፋትና ከተንኮል ጋር የተያያዙ መሆናቸው የማይካድ ቢሆንም መለስን በሦዶማዊነት ማማት ለኔ ብዙም ስሜት አይሰጠኝም፡፡ እርሱን የተካው አቢይ ግን ከተግባሩም ሆነ ከሰውነት እንቅስቃሴው እንዲሁም ከሚያደርጋቸው አጠቃላይ የዲፕሎማሲን ሥርዓት ያልጠበቁ ግንኙነቶች ተነስቼ ስገምት ይህ ቀበጥና ኩንስንስ ጎልማሣ ዓለምን የሚገዛው ዲያቢሎስ ተከታይ ስለመሆኑና የዲያቢሎስንም ህግጋት አንድም ሳይሸራርፍ እንደሚያከብር ማመን አይከብደኝም፡፡ በታላቅ ብሔራዊም ሆነ ዓለም አቀፋዊ ስብስባ ላይ ያልተዛነፉ ሸሚዞችንና ክራቫቶችን በርሱ የፍጹምነት ሚዛን ለማስተካከል በሚመስል ሰበብ ወደታዋቂ መሪዎች ጉያ ያለፈቃዳቸው እየተወተፈ የሚተሻሽና ጤፍ የሚቆላ ከእርሱ በስተቀር ሌላ መሪ አላውቅም፡፡ በመሆኑም እርሱም ሆነ እርሱን መሰሎቹ የሚያሰማሯቸው የጦር አባላት ከሰይጣናዊ ትዕዛዛት ያፈነግጣሉ ብሎ መገመት ሞኝነት ነው፡፡ አባባሉም “የማን ነሽና ትባረኪያለሽ” ነው፡፡ በወለጋና በመላው ኦሮሚያ የተሰገሰገው ኦነግሸኔ ሁሉ ልክ እንደአለቃው ፍናፍንት መሆኑ በሚለቃቸው የወንድና የወንድ ፍቅረኛ ፎቶዎች መገንዘብ አይከብድም፡፡ እነሱ አያፍሩበትም፤ እንዲያውም ይኮሩበታል፡፡ ምክንያቱም አባታቸው ዲያቢሎስ ይበልጥ ይሾማቸዋል፤ ሰማይ ጥግ ድረስም ያወጣቸዋል፤ ሲጠግባቸውና ነፍሳቸውን መረከቡን ሲያረጋግጥ አውርዶ እስኪፈጠፍጣቸው ነው ይህም የሚሆነው፡፡ የነሱ ቤት ምድር ናትና፡፡
የሣጥናኤል ቃል ኪዳን ደግሞ ተፈጥሮንና ሕገ እግዚአብሔርን መሻርና ማሻር ነው፡፡ ከዚህ አኳያ ሴትን ከሴት፣ ወንድንም ከወንድ በወሲብ ማገናኘት የሰይጣንን አዳራሽ ለመቀላቀል የመጀመሪያው የማይታለፍ ግዴታ ነው – ሕወሓትና ልጁ ኦነግ/ኦህዲድ-ሸኔም በዚህ በስፋት ይታወቃሉ፡፡ አንድ ሰው ወደኦነግ-ሸኔ ማኅበር ሲገባ ይህን የሦዶማዊያን ትዕዛዝ ማክበር ካልቻለ ወደቡድኑ አይገባም፡፡ ገንዘብ፣ ሀብትና ሥልጣንም አያገኝም፡፡ ስለሆነም ወያኔና ኦህዲድ-ሸኔ በየገቡበት ሁሉ ይህን ዕኩይ ሰይጣናዊ ድርጊት በንጹሓን ላይ መፈጸም ዋናው ሰውን ማርከሻ መንገዳቸው ነውና ይህን ሥርዓት በአፋጣኝ ኦሮሞ ትግሬ፣ አማራ ጉራጌ ሳይባል ሁሉም ተረባርቦ ማስወገድ አለበት፡፡ ሌላ ጠብና ግጭት ካለ ቢያንስ ይህን የአጋንንት መንግሥት ካስወገዱ በኋላ በድርድርም ሆነ በሌላ ወቅቱ በሚፈቅደው መንገድ መፍታት ይቻላል፡፡ አሁን ግን የመጣብን ጠላት በሰውነታችን ነው፤ በተፈጥሮ ነው፤ በሃይማኖታችንም ነው፡፡ በዘር ልክፍት ተጠምደህ ዛሬ ኦሮሞ ኦሮሞ እያልክ ኦነግሸኔን ብትደግፍ አንተንም ቤተሰብህንም ነገ ጧት ሦዶማዊ ያደርግህና ከዘላለማዊ ሕይወት ይነጥልሃል፡፡ ከስልሳና ሰማንያ ለማይበልጥ ምድራዊ ዕድሜ ብለህ በዘረኝነት የበሸቀጠ ቁልፍ ራስህን ብትቆልፍ የመርገምቱ በረከት ባንተና በልጆችህ ላይ ይወርዳል፡፡ እያስፈራራሁህ አይደለም፡፡ ተባብረህ ይህን የተረገመ የ666 ስብስብ ከላይህ ላይ አውርደህ ካልጣልክ ከጎንህ ታገኘዋለህ፡፡ ተናግሬያለሁ!!
በዚህ አጋጣሚ ለወጣቶች መልእክት አለኝ፡፡
እባካችሁ ለገንዘብ ብላችሁ መቀመጫችሁን አታስደፍሩ፡፡ ለመቀመጫችሁ ጤንነትም እዘኑ፤ አስቡለትም፡፡ የገቡበት ሰዎች እንደሚናገሩት ከሆነ እጅግ ክፉ የኅሊና ቁስልና የአካል ደዌ የሚያስከትል ታላቅ ሰይጣናዊ መርገምት ነው – “ውኃ ሲወስድ እያሳሳቀ ነው” እንዲሉ ሆኖ ሲጀምር ገንዘቡ የሚጥም መስሎ ቢታይም እየቆዬ የሚያመጣው ዳፋ ግን ራስን እስከማጥፋት ያደርሳልና በዚህ ቀለበት ዙሪያ የተኮለኮላችሁ ወገኖቼ እባካችሁን በቶሎ ንስሃ ገብታችሁ ወደጤናማው ሕይወት ተመለሱ፡፡ ሲጀመር ድህነት በሽታ አይደለም፡፡ አስቡና አቅዱና ትምህርትም ሆነ ሙያ ቅሰሙና ገንዘብ ልታገኙ የምትችሉበትን ብልሃት ፍጠሩ እንጂ በአቋራጭ ለመክበርና የተንደላቀቀ ኑሮ ለመኖር ብላችሁ ይህን 666 የሚባል የነአቢይና ሽመልስ ጎራ አትቀላቀሉ፡፡ ብዙ ሰው እየተጎዳብን ነው፤ ሀገርም ሰው አልባ ልትሆን ነው፡፡ ከዕውቀት ማነስ እንደዚሁም ከገንዘብ ማፍቀርና መውደድ የተነሣ እጅግ ብዙ ሰው በዚህ ሰፊ መንገድ እየነጎደ ጠባቡ የጽድቅ መንገድ ተጓዥ እያጣ መሆኑ በግልጽ ይታያል፡፡ በጣም አስቸጋሪ ዘመን ሆኗል፡፡ በዚያ ላይ የሰውን ስሜት የሚለውጡ ልዩ ልዩ ኬሚካሎች ወይም ንጥረ ነገሮችና መጠጦች፣ ሀሽሽና ጫት ወዘተ. ትውልዱን ግዴለሽና የለዬለት እንስሳ እያደረጉት ነው፡፡ ቀድሞ የተነገረ ቢሆንም ዘመኑ እጅግ አሳሳቢ ነው በውነት፡፡ አዲስ አበባ ላይ ከሚርመሰመሰው ዘመናዊ አውቶሞቢልና ከተገተረው ሕይወት-አልባ ሕንጻ መካከል ምን ያህሉ በላብ የተገዛ እንደሆነ ሳስበው ይጨንቀኛል፡፡ በዚህ የዐውሬ መንግሥት መደለያ እየተሸወደ ከመንገድ የሚወጣው የሕዝብ ቁጥር የትዬለሌ ነው፡፡ ይህ ሂደት ደግሞ የሃይማኖት መሪዎችንም ከራስጌ እስከግርጌ ያካትታል፡፡ ለዚህ ነው አንድ እንኳን ጴጥሮስ አጥተን በጎች መሀል ሜዳ ላይ የተበተንነውና የመጣ የሄደ ቀበሮና ተኩላ ሁሉ እንዳሻው እየቦጫጨቀን የሚገኘው፡፡ በእውነቱ የኅሊና በራችንን ገርበብ አድርገን በአርምሞ ስናሰላስለው ብዙ አስጨናቂ ነገር እናያለን፡፡ ሀገርን ማን ሊረከባት እንደሚችል ማሰቡ ራሱ ራስ ምታት ነው፡፡ ጸሎታችንም ከጣርያና ከኮርኒስ ዘልቆ የወጣ አይመስልም፡፡ ልብን ማንጻት እንጂ ልብስን ማንጻት ፈጣሪን አይማርክምና ወደእምነት ቤቶች ስንሄድ ክልባችን ይሁን፡፡ ሰው መሳይ በሸንጎ በዛና ሀገራችን መቀመቅ ልትወርድ ተገደደች፡፡ ማጭበርበርና ሙስና ደግሞ በህግ የተፈቀደ ያህል ነው፡፡
ላጠቃልል፡፡ በቅርቡ የተጀመረው የአማራ ትግል አሸናፊ መሆኑን ማንም እንዳይጠራጠር፡፡ በዚህ ትግል ለመሳተፍ ታዲያ ተፈጥሮንና ፈጣሪን ማወቅ ህግጋታቸውንም ማክበር የግድ ይላል፡፡ እግዚአብሔርን ማታለል አይቻልም፡፡ “ሲሞቅ በማንኪያ ሲቀዘቅዝ በእጅ”ም አይሠራም፡፡ “ቢያዩኝ እስቅ ባያዩኝ እሰርቅ”ም እንዲሁ፡፡ አንዱን መምረጥ ነው፡፡ በንጹሕ ልቦናና በቅንነት ክፋትን በመሸሽ ከፋኖ ጋር መቀላቀልና ለማይቀረው ሀገራዊ ትንሣኤ መታገል ወይንም በተቃራኒው ከነአቢይ የ666 ጎራ ጋር ወግኖ የሚደርስበትን መለኮታዊ መቅሰፍት ለማስተናገድ መዘጋጀት፡፡ አቢያዊ ስብዕናን ይዞ ፋኖ እሆናለሁ ማለት አሮጌውን ወይን በአዲስ አቅማዳ እንደመጨመር ነውና ጥንቃቄ ይደረግ፤ ፋኖም ወተቱን የሚያጠቁሩ ዝምቦችንና ጉንዳኖችን እዬለዬ ያስወግድ፡፡ በሞቀበት ዘፋኞችን ያርቅ፡፡ አዳዲስና ያልተበረዙ ያልተከለሱ በተሞክሮም የበለፀጉ በሀብትም ሆነ በሥልጣን ተፈትነው ያለፉ ሰዎችን በአመራር ቦታ ያስቀምጥ፡፡ የአፍ ምላጮችን እንደነ ልደቱ አያሌውና ታማኝ በየነን የመሳሰሉ ተንከረባባቾችን ይጠንቀቅ፡፡ (በምለው እንደማዝን ይታወቅልኝ፤ ግን ትግል ነውና ምንም ማድረግ አልችልም፤ ትግል ደግሞ በይሉኝታ ገመድ አይታሰርም፤ ዕድሜ ለዕድሜየ ስለነዚህና ሌሎች አጭቤዎች ብዙ መናገር እችላለሁ)፡፡
ከፍ ሲል ወደጀመርኩት ልግባ፡፡ እርግጥ ነው ሁሉም ሰው መቼም ጻዲቅና ንጹሕ ነው አይባልም፡፡ ግና የምንሳሳተውን እንወቅ፡፡ ኃጢኣት ዓይነቱ ብዙ መሆኑ ግልጽ ነው – ይቅርታ የሚያሰጥ አለ፤ የማያሰጥም አለ፡፡ ኃጢኣት በንስሃ ተሰረዘም አልተሰረዘም በዋናነት ግን ከታላላቅ ኃጢኣቶች መራቅ ለድል ያበቃልና እርምጃችንን በዚህ አቅጣጫ እንቃኝ፡፡ ከዚህ አኳያ በተለይ ወጣቱ የሰውነት ክፍተቶችን (ቀዳዳዎችን ላለማለት መጠንቀቄ ነው!) አገልግሎትና ጠቀሜታ ጠንቅቆ ማወቅ አለበት፡፡ ምሣሌ ቢያስፈልግ ጆሮ መስሚያ ነው፤ ዐይን መመልከቻ ነው፤ አፍንጫ ማሽተቻና መናፈጫ ነው፤ አፍ መመገቢያና መልካም ነገርን መናገሪያ፣ በጨዋነትም መከራከሪያ ነው …. ፡፡ እንዲህ እያሉ ከደረት ወደላይ መውጣትም ወደታች መውረድም ይቻላልና አንድን አባለ-ሰውነት ከተፈጥሯዊ አገልግሎቱ ውጪ መጠቀም ከራስ ኅሊና ጀምሮ በተፈጥሮና በፈጣሪ ዘንድ ለከፍተኛ ወቀሣና የወዲያኛው ዓለም ቅጣት ይዳርጋልና እንጠንቀቅ፡፡ “ምክር የድሃ ነበርሽ፣ ማን ቢሰማሽ”፡፡ ከከፍተኛ ይቅርታ ጋር እዚህ ላይ መልእክቴን ጨረስኩ፡፡