>

ደነዝ ምሁር ተብዬዎች፣ አውደልዳይ ፖለቲከኞችና ቦዘኔ ብራሞች አደብ ግዙ! (ሃይሉ አስራት)

ደነዝ ምሁር ተብዬዎች፣ አውደልዳይ ፖለቲከኞችና ቦዘኔ ብራሞች አደብ ግዙ!

ሃይሉ አስራት

 ማሰብ የሚችለው አገሪቱ ያፈራችው ምሁር እንዳይተነፍስ ታፍኖ፣ ያለቀውም አልቆ ሌላውም የሞቀ ኑሮውን ብቻ እያሰበ፣ ቀሪውም እየተንቦቀቦቀ የዘንድሮዋ ኢትዮጵያ ደግሞ እንደነ ዮናስ ብሩ፣ መሳይ ከበደ፣ ብሩክ ሃይሌና አለማየሁ ገ/ማርያም እና የመሳሰሉት የደነዘዙና የነፈዙ ምሁራን የሚወሻክቱባት አገር ሆናለች፡፡ እነዚህ ቀባጣሪዎች በየሜዲያው እየቀረቡ ከማቶስቶስ ውጪ የአንድ ፓርቲ አባል ሆነው ሰምተናቸው ካለማወቃችንም በላይ ውል ያለው ሃሳብም አቋምም የላቸውም፡፡ በተለይም ዮናስ ብሩ የሚባለው ዓለም ባንክ እንኳ አትረባም ብሎ ያባረረው፣ ሲባረርም እንደ አንድ ቆፍጣና (ከየት ያመጣዋል!) ሰው አፍንጫህን ላስ ማለት ያልቻለ በልፍስፍስ አስተሳሰቡ ጥቁር ስለሆንኩ ነው ምናምን እያለ ኢትጵያዊነትን ያዋረደና ደካማ ስብዕናውን በአደባባይ ያሰጣ ግለሰብ ስለእስክንድር ነጋና ሻለቃ ዳዊት ዘባርቋል፡፡ የሚሉሽን ባልሰማሽ ገበያ ባልወጣሽ ነው ነገሩ፡፡ አፉን ባለመሰብሰቡ ሥልጣን ለመረከብ ተፍተፍ ሲል፣ ሲያጎበድድ ሲላላጥና አዲስ ነገር ያመጣ መስሎት አመራር በቴክኖክራቶች መያዝ አለበት እያለ ሲጋጋጥ የነበረ ደዘ ደዝ መሆኑን እንዲህ ባደባባይ እንድንነግረው አስገድዶናል፡፡

 መልከስከሱ እንኳ እንደብጤው ታላቁ ከርሳም ብርሃኑ ነጋ ሳይሳካለት ሲቀር ከየት መጣህ ሳይባል ተቃዋሚ ሆኖ ብቅ አለ፡፡ ከዚያም በምዕራባዊ እሳቤ ሙልጭ ተደርጎ የታጠበውን አስተሳሰቡን ይዘበዝብ ጀመር፡፡ ለዚህም ማስረጃው እግዚአብሔር ይስጠውና ለእርሱም ለሌላው በዘበዝ መሳይ ከበደም ምራቁን በዋጠው ዶክተር ፍቃዱ የተሰጠውን ትችት ማየቱ በቂ ነው፡፡ ለመሆኑ እርሱ ኢትዮጵያ ውስጥ ምን ሰርቷል? ደርሶ እነእስክንድርን ገምጋሚ የሆነው? እርሱ አፉን የከፈተባቸው እስክንድርና ሻለቃ ዳዊት እኮ ላገራቸው ፀሃይ የሞቀው አገልግሎት የሰጡ ብቻ ሳይሆን እጅግ ፈታኝ በሆነው በዚህ ቀውጢ ጊዜ ለአገራቸው ግንባራቸውን የሰጡ የተሟላ ብቃት ያላቸው ሰዎች ናቸው፡፡ ስታርባክስ ተወዝፎ ከመዘባረቅ ይልቅ ስለጦርነትና ጦር ሜዳ ሻለቃ ዳዊትን አሁን ደግሞ እስክንድርን ጠይቅ፡፡  

ከጽሁፎቹና ከንግግሩ እንደምንረዳው  ከምሁርነቱም ጎራ ቢሆን የለበትም፡፡ ወርልድ ባንክ ከክለርክ በማይሻል ስር መጣድ ምሁር አያስብልም፡፡ ዓለም ባንክም አብዛኞቹ ለሚከፈለቻው ከፍተኛ ደመወዝ ብለው ትዕዛዝ ፈጻሚና ወሽካቶች ቢሆኑም እየተቃወሙትም የነጠሩ ባለሙያዎችን የያዘ ድርጅት እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ለመሆኑ በየሜዲያው ከመለፍለፍ እንደ አለም ባንክ ባለሙያዎች ለምን አንድ መጽሐፍ አልጻፍክም? መቼም ጽፈህ ቢሆን ሌት ተቀን ስለሱ እየለፈለፍክ ታሰለቸን ነበር፡፡ ግን ደግሞ  የረባ ነገር እንደማትጽፍ ከአጫጭር ጽሁፎችህ መረዳት ይቻላል፡፡ ብትጽፍም ከለገሃር ክምርነት አያልፍም፡፡ ስለዚህ ዮናስ ብሩ አደብ ግዛ፡፡

ሌላው ጉምቱ ዶክተር መሳይ ከበደም በሚገርም ሁኔታ ተሸውጃለሁ ይላል፡፡ መሸወዱን ማመኑና ይቅርታ መጠየቁ ጨውነቱንና ትልቅነቱን ቢያሳይም የርሱ መሸወድ የሌጣ ትምህርትን፣ ዱክትርናም ሆነ ፕሮፌሰርነት ፋይዳ ቢስነት ያመለክታልና ሳንጠቅሰው ማለፍ የለብንም፡፡ ከህብረተሰብ የራቁ፣ በራሳቸው፣ በቤተሰባቸውና በስራቸው ዙሪያ ብቻ የሚሽከረከሩ ሌጣ ዶክተሮችና ፕሮፌሰሮች ሌሎችም ባለሙያዎች የበዙባት አገር ውሰጥ  ስለምንኖርና አብዛኞቹም ባደባባይ ራሳቸውን ባይገልጹም ከመሸወድም በባሰ አገሪቷ ይሄ ሁሉ መዓት ሲወርድባት አልሰማሁም አላየሁም ባዮች መሆናቸውን መናገሪያው ጊዜ አሁን በመሆኑ ነው ዶክተር መሳይ ከበደ የተጠቀሰው፡፡

 ብሩክ ሃይሌ የሚባለው ደግሞ ምን ያህል ዶላር ቢከፈለው ነው በአድርባይነት በወሽካቶቹ ኢሳት፣ኢኤምኤስ ወዘተ እየቀረበ የሚያቶሰትሰው? ሰው የለም ብሎ ነው? ቶስቷሳ! አርፈህ ተቀመጥ፡፡ አልማርያም እንኳ የተረበሸ ሰብዕና ተጠቂ ሳይሆን አይቀርም ከዚያ ውጪ ስንት ዓመት ያለማቋረጥ በጽናት ወያኔ ላይ ሲጽፍ የነበረ ሰው እንዲህ አውሬ ስር ይደፋል ብሎ ማሰብ ይከብዳል፡፡ ነገረ ጸጉሩም ሁኔታውም የተረበሸ ነው፡፡እዚያው ረብሻህን ይዘህ ብትቀመጥ ይሻልሃል፡፡ 

ከምሁራኑ ተራ ወደ አውደልዳዮቹ ፖለቲከኞችና አክቲቪስት ተብዬዎች ስንመለስ በመጀመሪያ ረድፍ የሚገኘው ልደቱ የሚባል የህወሐት ካድሬ ነው፡፡ የኢሕአዴግን ጡጦ እየጠባ ያደገ ሰው ዕውቀቱም ዕይታውም ከወረዳ ካድሬነት አያልፍም፡፡ ይሄም ልደቱ የሚባል ለፍላፊ ካድሬና ኤርሚያስ ለገሰም ጭምር ትልቁ ብቃታቸውም ድክመታቸውም ሁሉንም ነገር በወያኔ ሕገመንግሥት፣ ሰነዶችና ትርኪምርኪዎች ዙሪያ ብቻ እየመተሩ የሚቀባጥሩ ካድሬዎች መሆናቸው ነው፡፡ ከኢህአዴግ ጋር የተሻሸና የነበረ ሰው በግምገማ የላሸቀ አስተሳሰብ ስለሚይዝ ሀፍረት የሚባል ነገር አያቅም፡፡ የግምገማ ትልቁ ግቡ ሀፍረትን ማጥፋት ስለሆነ በቀላሉ ወደ ተፋው ሲመለስ ቅር አይለውም፡፡ ልደቱ ስንቴ የተፋውን ላሰ? ኤርሚያስም በሚያሳዝን ሁኔታ ባለቀ ሰዓት ወደቀደመ ትፋቱ ተመልሷል፡፡

ወያኔ በጋተው የአማራ ጥላቻ የሰከረው ሌላው ለፍላፊ ቴድሮስ የሚባል የወያኔ ጡሩንባ ጋር በሌሎችም ሜዲያዎች ለሃጩን የሚያዝረበርበው ልደቱ ከመዐሕድና ፕሮፌሰር አስራት እስከ ቅንጅት/መኢአድና ሃይሉ ሻውል ድረስ የሰራውንና ትናንት ወያኔ ፓርላማ ገብቶ ሲፈተፍት እንደነበረ የረሳነው መስሎት አሁንም ወያኔያዊ ክፍት አፉን ይከፍታል፡፡ ልደቱ ቢያጥቡት የማይጠራ ከዚያም በላይ ካላቅሙ በመንጠራራት በተፈጠረበት ዝቅተኝነት በሽታ የሚሰቃይ ደካማ ግለሰብ ነው፡፡ ስለዚህም የልደቱ ልፍለፋ የሚስማማው ለርሱ ብጤ ለኢህአዴግ ካድሬዎችና ለወረዳ አመራሮች ነው፡፡ በኢትዮጵያ ደረጃ ማሰብ የሚያስችል ሰፋ ያለ አመለካከትና አቅም ማለትም በቂ የታሪክ ዕውቀትም ሆነ የአስተዳደግ ዝግጅት የሌለው ሰው ነው፡፡ ከሁሉም በላይ ደግሞ ራሱ በፈጠረው የዝቅተኝነት ስሜት በሽታ የተጠቃ በመሆኑ ሻል ሻል ያሉ ሰዎች ላይ ሲያደባ መኖሩ የሚቀጥል ይሆናል፡፡ አብዛኞቹ ደዘደዝ ምሁራንና አውደልዳይ ፖለቲከኞች የሚጋሩት የጋራ ባህሪያቸው ይህቺ የዝቅተኝነት ኮምፕሌክስ ወይም የስሪት ችግር ናት፡፡   

አስክንድር ላይ የሚረባረቡትም ለሌላ ሳይሆን እነርሱ እዚያና እዚህ እየረገጡ ሲዘላብዱ፣ሲቀላውጡና ሲልከሰከሱ እርሱ ግን እስከመጨረሻው በዓላማ የጸና በመሆኑ ከእርሱ እኩል መሰለፍ ባለመቻላቸውና ከእርሱ አንጻር ሲታዩ ኮስማና ባህሪያቸው ስለሚገለጥባቸው ነው፡፡ ሺህ ጊዜ ምድረ ኮምፕሌክሳም ቢለፈልፍ አዲሱ ትውልድ አንዴ ፖለቲካ በቃኝ ከዚያ ደግሞ ወያኔ ቀና ያለች መስሎት አገሬ ገብቼ እታሰራለሁ  ብሎ ሲዘባርቅ እንደነበረው እንደ ልደቱ ዓይነት ሰገጤ አያታልለውም፡፡ አፉን ቢዘጋ ይሻለዋል፡፡

ሌሎቹም የርሱ ብጤ ቴክኖሎጂው ተመቸኝ ብላችሁ በዩቲዩቡ የምትዘባርቁ ከመቧደን ይልቅ መጀመሪያ የኢትጵያን ታሪክ በሚገባ ተረዱ፣ ካለፉት ፖለቲካዊ ስህተቶች ያልተዛባ አመለካከት ቅረጹ፡፡ ፍራንክ ለወረወረላችሁ ሁሉ ማሰራጫ አትሁኑ፡፡ በዚህ አጋጣሚ ታዲያ በዚህ ቀውጢ ወቅት ጥርት ያለ የአማራ/ኢትዮጵያዊ አቋም ይዘው ይሄን አረመኔ ሥርዓት ከፋኖ ጎን ሆነው በዩቲዩቡ እየተገተጉት ያሉት ጀግኖች የዩቲዩቡ አርበኞችን ማመስገን ብቻ አይደለም ማድነቅ ይገባል፡፡ ያለንበት ዘመን የወሬም ጦርነት ዘመን ነውና ጠላቶቻችን በዚህ ሲዘጉባቸው በዚያ እየተሯሯጡ ለህዝብ መረጃ በማድረሳቸው ድጋሚ ሊደነቁ ይገባል፡፡ 

ሰሞኑን ደግሞ ከአውደልዳዮቹ መሀከል አንዱ መሳይ የሚባል ጋዜጠኛ በግልጽ እንደ ለመደው ጸረ አማራ/ኢትዮጵያ አቋሙን አሳውቋል፡፡ ኤርትራ ሄዶ ግንቦት ሰባት ምናምን እያለ ሲወሻክት የነበረውን ታሪኩን የረሳንለት መስሎት እንደገና ደግሞ በዚህ ቀውጢ ወቅት ከከሸፈው ቡድኑ ጋር አንከር ብሎ ብቅ ብሏል፡፡ አንድ  አብዩ የሚባል ቀደም ሲል ወልቃይት ጠገዴ ምናምን ነኝ ይል የነበረ ቀባጣሪ አቅርቦ መዘባረቅ ጀምረዋል፡፡ የት የነበረ ገገማ ነው ደግሞ አብዩ የሚባለው? ሰውየው እንኳ እዚህ ግባ የሚባል ባይሆንም ከጀርባ ያው የተለመደ የወሽካቶችና የጅቦች ስብስበ እንዳለ መገመት ይቻላል፡፡ መሳይና ግብረ አበሮቹ በግልጽ እስክንድር ላይ ዘመቻ በመጀመር ፋኖን ለመከፋፈልና ትግሉ ላይ ውሃ ሊቸልሱበት እየተንደረደሩ ነው፡፡ ልደቱ፣ ብርሃኑ ነጋ፣ መሳይ፣ ነዓምን፣ አበበ ገላው፣ ታማኝ ወዘተ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ያለአቅማቸው ገብተው የጎበጡ የውሸት፣ የክህደትና ማጭበርበር ሥራ ውስጥ የተዘፈቁና የተዳደፉ ስለሆነ እንደ እስክንድር አይነቱን ኢንተግሪቲ ያለው ሰው በፖለቲካው መድረክ ማየት አይፈልጉም፡፡ ከዚያ ይልቅ አገሪቷ አራት እግሯን ብትበላ ይመርጣሉ፡፡

ሌባ ሁላ! የሚሰረቅ ስላጡ፣  በውጪ ያለው አማራ ሲተፋቸውና በመላው ዓለም ያለ አማራ ተረባርቦ ሚሊዮን ዶላር በመሰብሰቡ ዐይናቸው ደም ለብሷል፡፡ ምናለ ከታሪክ ብትማሩ? ባትስማሙ እንኳ ቢያንስ ከሚመጥን ተቃዋሚ ጋር እየተሻሹ ለመኖር ሞክሩ፡፡ የኢትዮጵያ የቅርብ ጊዜ ፖለቲካ ታሪክ ዋናው በሽታ ይህ ነው፡፡ የሚመጥንህን ግን የሚቃወምህን አጥፍተህ በኋላ ካንተ ዝቅ ባለ ወራዳ ትዋረዳለህ፡፡

 የነመሳይ፣ አንዳርጋቸው፣ ነዓምን፣ አበበ ገላው ታማኝ ወዘተ ስብስብ የፈረንጆቹ ድጋፍም ያለው ይመስላል ኢትዮጵያ መሬት ላይ መና ነው እንጂ፡፡ ለዚህም ነው የመሳይ ዩቲዩብ ምንም ሳይሆን ሶስት ስልሳና አበበ በለው መከራቸውን የሚያዩት፡፡ አንዳርጋቸው ደግሞ ያንን የታሪክ ቅሌታም መጽሐፉን አሳትሞ ለሥርዓቱ እጅ መንሻ ከሰጠ በኋላ ዛሬ ሹመት ተሰጥቶኝ ነበር አልፈልግም ብዬ ነው ምናምን ይላል፡፡ ሲጀመር አንዳርጋቸው የመጨረሻ መጽሐፉን በገዛ እጁ የመቀበሪያ ሳጥኑ አድርጎታል፡፡ በርግጥ ሌላ የተሻለ የሬሳ ሳጥን ውስጥ የመቀበር ጠባብ ዕድል ያለው ከመሆኑም በላይ ከደዘደዝ ምሁር ተብዬዎችና አውደልዳይ ፖለቲከኞች ተርታ ውጪ ነው፡፡ የአቅም አጠቃቀሙ ነው እንጂ በምሁርነቱም በፖለቲከኛነቱም በቂ አቅም  ያለው ሰው ነው ችግሩ ከደዘ ደዞችና አውደለወዳዮች ጋር እየዋለ እንትን ተምሮ ይመጣል፡፡ ለዚህም አንዱ ምሳሌ የለውጡን አካሄድ ያልተቀበሉትን እንደ ዕብድ ቆጥሮ ጤነኛ ሰው በለውጡ መጀመሪያ መሸወዱ ትክክል ነበር ይለናል፡፡ ለነገሩ ሽፋን ሲፈልግና እርሱ የፈለገውን ስላላገኘ እንጂ አለመሸወድ አይደለም ገና በጠዋቱ የሚሆነውን የተነበዩ ነበሩ፡፡ ሰሚ አጡ እንጂ ጥርሳቸውን በኢትዮጵያ ፖለቲካ ከነቀሉት መሀል ገና በግርግሩ ወቅት ሁሉም ደጋፊ ሆኖ ሲያራግብ ስለኮለኔሉ ቅልብጭ አድርገው ነግረውን ነበር፡፡ ዞር ብሎ ስለኮረኔሉ የተጻፈውን ዓይነት ጽሑፍ ላስታወሰ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ማሰብ ከሚችሉት ፖለቲከኞች እጅግ እየራቀ የማንም ድንባዣም ደዘደዝ ምሁር ተብዬና አውደልዳይ ፖለቲከኛ እጅ መውደቁን ያረጋግጣል፡፡

ደሞ አንድ ዘጥ ዘጥ የሚል ወርቁ የሚባል ከብአዴን ጋር ሲሞዳሞድ የነበረ ብራም ያዙኝ ልቀቁኝ እያለ ነው፡፡ እውነት አማራን/ፋኖን እደግፋለሁ ካልክ እሰየው ነው በተረፈ የምን መቀባጠር ነው? ሲጀመር ባለሃብት – ጥሮ ግሮ ለፍቶ ሀብት የሚያፈራ –  በንጉሱ ዘመን ቀርቷል፡፡ በደርግ የድህንት እኩልነት እንጂ ሃብት ማፍራት አልነበረም፡፡ ደርጎች እራሳቸውም በድህነት ማቀው ህዝቡንም በደህነት አማቀውና አቅመ ቢስ ካደረጉ በኋላ ኢትዮጵያን የምታህል ሀብታም አገር በወርቅ ሳህን በልቶ ለማይጠረቃ የባሰ ድሃ ወያኔ አስረከቡ፡፡ በድንቁርና ላይ የባሰ ድህነት ያጥለቀለቀው ዘረኛ የወያኔ ስብስብ ደግሞ ከአቅሙ በላይ አገሪቱን ግጦ ግጦ የበላውን መትፋት አይደለም ትግሬ የሚባልን ዘር ቅስሙን ሰባብሮ ከንቱና ከርታታ አደረገው፡፡ የዛሬዎቹ የወያኔ ፍልፍሎች ተረኞች ደግሞ የቦዘኔ ስብስባቸውን አጠናክረው የበሉትን ሳይውጡ በራቸው እየተንኳኳ እንኳ መላ መፈለግ አቅቷቸው በመዓት ላይ መዓት እየጨመሩብን አገራችንን ከአገር ተራ እያወጧት ነው፡፡

ባጭሩ የኢሕአዴግ/ ብልጽግና ዘመን ብዙ ቦዘኔዎችን ሀብታም ያደረገ፣ ለሥልጣን ያበቃ የበሰበሰ ሥርዓት እንደ መሆኑ ብር በብር የሆኑ ቦዘኔዎች ባለሃብት እየተባሉ ተጠሩ፡፡ ሌባ ሁላ! ሀብት ተሰርቶ የሚፈራ ነው እንጂ ከኢሕአዴግ/ብልጽግና ጋር ተሞዳምደህ ያመጣኸው ብር እንጂ ሃብት አይባልም፡፡ የአማራውን ትግል እስከአሁን ሰቅዘው በተጠበቀው ፍጥነት እንዳይጓዝ ያደረጉት አደገኝ የቤት ውስጥ ጠላቶች እንደነዚህ ያሉ ቦዘኔ የአማራ ብራሞች ናቸው፡፡  ለማንኝኛውም አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ በተለይ የአማራ ብራሞች በመጀመሪያ ከብልጽግና ጋር መሞዳሞድ ማቆም፣ ከደፈራችሁ እውነተኛውን የፋኖ ተጋድሎ ደግፋችሁ መቆም አለበለዚያ ደግሞ አፋችሁን መዝጋት ብራችሁንም በግልጽም ሆነ በድብቅ ለአማራ ትግል ማዳከሚያ ከማዋል መቆጠብ አለባችሁ፡፡

ወርቁም አሁንም በብርህ ፋኖን በማገዝ ያለፈውን ለታሪክ ትቶ ለወደፊቷ ብሩህ ኢትዮጵያ ለማሰብ  ጊዜው አልረፈደም፣ እንደውም ትክክለኛው ሰዓት ነውና እግዚአብሔር ቀናው መንገድ ይምራህ፡፡ በተረፈ ለዩቲዩበር ፍራንክ እየወረወሩ እንደሚያቅራሩት ብአዴን/ብልጽግናዎች ፍራንክ በመወርወርና በዩቲዩብ ወሬ ራስን ማታለል የትም አያደርስምና ወደ ቀልብ መመለስ ይሻላል፡፡ ካገር መውጣትህ ጥሩ ነው – ፋኖን ካገዝክበት – ግን ደግሞ የወጣኸው ተቃዋሚ መስለህ የአማራ ነጻነት ላይ ከብአዴን/ብልጽግናዎች ጋር ለመሸረብ ከሆነ  አትድከም አይሳካም፡፡ ለሽረባ የተዘጋጀህ ለመሆኑ ድግሞ አንዱ ጠቋሚ ገና ከመውጣትህ ስለብር ማውራትህ (እሱን እንኳ የብር ሰው ነህ ብለን እንለፈውና)፣  ይቺ መረጃ አለኝ  ምናምን የምትላት ግን አወጣጥህ የጤና አለመሆኑን ያሳብቅብሃልና አርፈህ ተቀመጥ፡፡ እውነተኛ መረጃ ከሆነ እኮ ሁሉም ይጠቀምበታል ምን ችግር አለው? ግን አጀንዳው የሽረባ ከሆነ፣ ለመከፋፈል ከሆነ ብትጠነቀቅ ይሻልሃል፡፡

ባጠቃላይ ኢትዮጵያ ውስጥ ለውጥ ሊመጣ ነው ብላችሁ የተንሰፈሰፋችሁ በተለይ ልማደኛ አውደልዳይ ፖለቲከኞችና አክቲቪስት ነን የምትሉ በአስተሳሰብም በገንዘብም  የአማራን ሕዝባዊ ትግል ያልደገፋችሁ እንዲያውም ፋኖን እንመራለን፣ እንወክላለን የምትሉ ቀልማዶች እስኪ መቀላመዳችሁን ተወት አድርጉትና መጀመሪያ ህዝቡ ከዚህ ዲያብሎሳዊ አገዛዝ ይላቀቅ፡፡ አይ ካላችሁም የሳይበሩ ፋኖ እያንዳንድህን በሥም እየጠራ በየማህበራዊ ሜዲያው እያራወጠ ይጠዘጥዝሃል፡፡ ደሞ ለወሬ! ፋኖ በየተራራውና በረሃው ደሙን እያፈሰሰ አይደለም እንዴ?

Filed in: Amharic