>

"ዛሬ በትግራይ ክልል የማይለቀስበት ቤት የለም።ይህ እንዳይመጣ ብዙ ተማጽኖ ስናቀርብ ነበረ'' (ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ)

ለቅዱስ ሲኖዶሱ አባላት በሙሉ

“ዛሬ በትግራይ ክልል የማይለቀስበት ቤት የለም ። ይህ እንዳይመጣ ብዙ ተማጽኖ ስናቀርብ የነበረ ቢሆንም ሽበት እና ክህነት የማይከበርበት ዘመን ላይ ደርሰን ለዚህ ኅዘን በቅተናል

 

” ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ዛሬ ከተናገሩት መልእክት የተወሰደ ፦

ለቅዱስ ሲኖዶሱ አባላት ነገም በአማራ ክልል የተደገሰው ይኽው ነው ።

ኢትዮ ቤተሰብ ሚዲያ

• ገዳዩ መግደሉን ካላቆመ በዘር ፓለቲካ የሰከረው መንግሥት ፣ እናንተንም ቀኖናን በመጣስ ጵጵስናን በዘር ለመሾም አበቅችሁ፣ ክብራችሁ በራሳችሁ መንገድ አረከሳችሁ ፣

•  የጵጵስናው ማዕረግ ረከሰ ፣ ውግዘታችሁም በከንቱ መወጋገዝ ሆነ ፣ አብዛኞቻችሁ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ለክብራችሁ እና ለገንዘብ ስትሉ በገዳዩ መንግሥት መዳፍ ስር ወደቃችሁ ፣

• ከሚጠፋው እና ከሚያልቀው ሕዝብ ጋር መከራን ከመቀበል ይልቅ በግልም በግሩፕም እየተጠራችሁ ከገዳዩ መንግሥት የሚተላለፍላችሁን መልእክት በሕዝቡ ላይ ቀንበር ለመጫን መረጣችሁ

• ከሚሞተው ሕዝብ በላይ የሚያሳስባችሁ የእናንተ የወር ደመዝ ጭማሪ ፣ የምትነዱት ዘመናዊ መኪና መለዋወጥ ሆነ ፣ በእውቀትም ሆነ በመንፈሳዊ ሕይወት እንድትጠብቁት የተሾማችሁለት ሕዝብ እንደ መስዋዕት በግ ሲታረድ እናንተ ዛሬ አጀንዳችሁ የግል ጥቅም ላይ ያተኮረ ሀሳብ ሆነ፣

• ለይምሰል ስለ “ሀገር ሰላም” የሚል የፈረደበት አጀንዳ በየጊዜው ይነሳል ማጠቃለያው ፣ ኮሚቴ ይሰየማይ ፣ ይጠና ይባላል በዚህ እሾክ ውስጥ እንደ ተዘራ ዘር በገዳዩ መንግሥት ካድሬ ተቀብሮ ይቀራል ፣ እንዴት ሆነ ብሎ የሚጠይቅም እንዳይኖር ከነስም አጠራሩ ይደለዛል ፣

• እንዴት ግን መሽቶ ይነጋላችኃል ፣ ለነገሩ የኑሮ ውድነት አይነካችሁ ፣ ደሞዝ አይቆረጥባችሁ ፣ የፈለጋችሁት አይቀርባችሁ ፣ በፈለጋችሁት ወቅት እና ጊዜ እንደ ላም የሚታለበውን ዳያስፖራ ለመጋጥ ቪዛ አትከለከሉ ፣ ትኬት ማን ይቆርጥልኛል ብላችሁ አትጨነቁ ብቻ ስንቱ ይነገር ፣ ሀገር ቤት ግርግር ሲባዛ ጉዞ ወደ አሜሪካ ፣ ወደ አውሮፓ የፈረደበት ምክንያት ለሕክምና ፣ ለዋሐሪያ ጉዞ ይባላል

• ግን ይህም ቢሆን ዛሬም አልረፈደም እንደ አንደ አንድ ቃል እና እንደ አንፍ ልብ መስካሪ በራችሁን ዘግታችሁ የጣሳችሁትን ቀኖና አስተካክላችሁ መንግሥት እያደረገ ያለው እኩይ ተግባር በአደባባይ በማውገዝ ፣ ከዘር ቋት ወጥታችሁ የጠራችሁ እግዚአብሔር ለማገልገል እና ቤተክርስቲያን በአንድ መንፈስ ለማገልገል ፣ብሎም መመሪያ ለመስጠት ቃል ግቡ ፣

• በእናንተ ምክንያት የከበረ ነፍሳቸውን ለተሰዉ ብርቅዬ የተዋሕዶ ልጆች እና ሀብት ንብረታቸውን ላጡ ፣ ለተጎሳቆሉ ፣ለተጎዱ ይቅርታ ጠይቃችሁ ፣ የሾማችሁን እግዚአብሔር ፈርታችሁ የቀደመ ክብራችሁን ለመመለስ መንፈሳዊ ተጋድሎ ብታደርጉ በማለት በተማጽኖ እንጠይቃለን ።

 

Filed in: Amharic