>

መነበብ ያለበት የመምህር ዘመድኩን በቀለ ርዕሰ አንቀጽ!

“ርዕሰ አንቀጽ”

~ ዐማሮች ሆይ አንብቡት…

“…በቀይ ባህር ጉዳይ ከኤርትራ ጋር ጦርነት የሚለው ወሬ የጀመረው መቼ ነው? ከሚለው እንነሣ። ይቆይ ይሆናል እንጂ ከኤርትራ ጋር ጦርነትም አይቀሬ የሚሆንበት ዕድል ዝግ አይደለም። የሥርዓት ለውጥ በኤርትራ ያስፈልጋል የሚሉ ድምጾች ከየቦታው መሰማት ከጀመሩም ሰነባብተዋል። ምዕራቡ ዓለም ኢሳይያስ ከነ ራሺያ ጋር በፈጸመው ወዳጅነት በመብገናቸው ኤርትራን ከኢትዮጵያ ጋር ማዋሃድ ባይፈልጉም የሥርዓት ለውጥ እንዲመጣ ግን ይፈልጋሉ። የጅቡቲ ወደብ ስለራቃቸው የአዲ ዳዕሮን የወርቅ ክምችት እና የወልቃይትን የፖታሽ ክምችት ለማጋዝ ከጅቡቲ ወደብ የቀረበ ወደብ የሚፈልጉ ኃይላትም አሉ። ወያኔም በአቅሟ ወደብ ትፈልጋለች። ኦሮሙማውም በኢትዮጵያ ስም ወደብ ይፈልጋል። ፍላጎቶቹ ብዙ እንደሆኑ እንሰማለን። የሆነው ሆኖ አቢይ አሕመድ በተደጋጋሚ ብዙ ጊዜ የትግሬ ነፃ አውጪዋ ህወሓት በጌምድርን እድትይዝ ወትውቷል። በገደምዳሜም በአፈቀላጤዎቹ በኩል ደጋግሞ አስነግሯል። አልተቻለም እንጂ።
1ኛ፥ ታስታውሱ ከሆነ ከፕሪቶሪያው የኦሮሞና የትግሬዎቹ ስምምነት በኋላ አብይ ጌታቸው ረዳን ወደ ጀዝባዎቹ ብአዴኖች ጋር ባህርዳር ልኮት የሕዝብ ለሕዝብ ዕርቅ ምናምን ብሎ ዐማራን አዘናግቶ በነጋታው ነው በሁለተኛው ቀን መከላከያው ለህወሓቶች በወልቃይት በኩል ስትራቴጂክ የሆነች ቦታ ለቆላቸው ወጣ። ነገር ግን የሁላችንም ጥርጣሬ እና መጯጯህ ተጨምሮበት እንደለመዱት ዥሉ ብአዴንን ቢያታልሉትም እሳት የላሰው አዲሱን የዐማራ ፋኖን ትውልድ ሊያታልሉት አልቻሉም ነበርና አጅሬ ፋኖ ሕወሓቶች ለደቂቃዎች ተቆጣጥረው የነበሩትን የዐማራ መሬት ወዲያኑ በመብረቃዊ ጥቃት ለብልቦ ለብልቦ ቀሚሳቸውን ገልቦ ከግዛቱ አባርሮአቸው መልሶ ተቆጣጠረው። ያኔ ሁለቱም ደነገጡ። አቢይም ወያኔም።
2ኛ፦ ቀጥሎ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን በመማስ ከሲኖዶሱም ጋር ቁርቋሶና ቀውጢ በመፍጠር በጎን በኩል ደግሞ በበጌምድር ሴራ የመጎንጎን ተግባር ሲያከናውኑም ነበር። አሁንም ዐማራው በተለይም የትግሬው ጳጳሳትን ሁከት ኢግኖር ገጭቶ ለምን በአናታችሁ አትተከሉም ብሎ እሱ አይኑን መሬቱ ላይ በመትከሉ ምክንያት ሁለተኛውም ሴራ አፈርደቼ ውኃ በላው።
3ኛ፦ ከዚያ ደግሞ ጎንደሮች ከወገሙ በዚህ በወሎ ገራገሩ በኩል እንሞክረው ብለው መጀመሪያ የዐማራ ልዩ ኃይልን ከራያ አካባቢ አርቀው ለማየት ሞከሩ። ወዲያው ይሆናል ብለው ያልጠበቁት የዐማራ ፋኖ ወጥሮ በቦታው ተተካ። መከላከያም በብዙ ታገለ። ግን አልቻለም። ሌላም ሌላም ብዙ አጀንዳ ፈጥረው ብዙ ሞከሩ ሁሉም ግን አልተሳካም።
“…ይሄ ሁሉ ሲሆን ህወሓት ግን ምንድነው ስትል ነበር የምትሰማው? መጀመሪያ አካባቢ ጌታቸው ረዳ መቀሌ ሮጵላን ጣቢያ ሆኖ እነ ዳግማዊት ሞገስን በተቀበለ ጊዜ “ፌደራል መንግሥቱና እኛ ከተስማማን ሌላው ተራ ነገር ነው፣ ቀላል ነው” ነበር ሲል የነበረው። ቆይቶ ግን ዐማራ ወግሞ፣ አጀንዳም አንጃ ግራንጃም አልቀበል ብሎ ካልኩሌተሩም ካልኩሌሽኑም አልሠራ ሲል አጅሬ ህወሓት ራሷን ከጨዋታው ያገለለች መስላ “እኛ ከዐማራ ጋር መዋጋት አንፈልግም። በስምምነታችን መሰረት ፌደራል መንግሥቱ ዐማራን ከመሬታችን ላይ አስወጥቶ ያስረክበን” በማለት ጣድቅ ጣድቅ መጫወት ጀመረች።
“…አጅሬ አቢይ ግን ግግም ብሎ ዐማራ ከእኔ ጋር ሆኖ እንደወጋችሁ እናንተም ከእኔጋር ተባብራችሁ ዐማራን ወግተን እናስወጣውና ከዚያ የተወሰደባችሁን መሬት በጋራ እናስመልስ ነበር የሚላቸው። በሱዳን በኩል ሞክሮ ሱዳንን የዐማራ አምላክ ቀሰፈበት። ኤርትራንም ዐማራን እንደ ትግሬ እንዲወጋለት ጠይቆ እንደነበርም ሻአቢያዎቹ አሁን እያወሩ ነው። እኛ እምቢ አልነው ነው እንጂ አቢይማ ዐማራን በመውጋቱ በኩል አገዙኝ ብሎን ነበር ነው እያሉ ያሉት። ህወሓት ከኦሮሞው ይልቅ የጎረቤቷን የዐማራ ፈኖን አቋም ስለምታውቅ ስላስፈራቸውም እንዲያውም “እኛ ዐማራ እንዲህ ዓይነት ጦርነት ውስጥ ሆኖ በጦርነት መሬታችንን ማስመለስ አንፈልግም። በሰላም ነው መሬታችንን የምናስመልሰው በማለት ከላይ እንደገለጽኩላችሁ ጻድቅ ጻድቅ መጨዋት እንደ ጨዋ ጎረቤትም መታየት፣ በዐማራው ልብም ውስጥ መጎዝጎዝም ፈለጋ ነበር። ዐማራ ግን እዚያው በጠበልሽ ብሎ ውግሞ ግግም አለ። ወይ ፍንክች።
“…ህወሓቶቹ ሳያስቡት አቅማቸውም ቅስማቸው እንኩትኩቱ ስለወጣ የትኛውም መንገድ ዝግ ነው የሆነባቸው። ሽመልስ አብዲሳ እንዳለው ለኦሮሞ ከመታዘዝ ውጪ አማራጭም ምርጫም የላቸውም። እነሱ የሚያስቡት ምን አልባት አቢይ አህመድ እነሱን ዱቄት እንዳደረገው ጎረቤት ዐማራንም ለብልቦ ዱቄት አድርጎ ካሸንፈ እኛ ኃይላችንን ቆጥበን የተዳከመውን ዐማራ አፈር ከደቼ አብልተን፣ በጌምድርንም ሆነ የወሎን መሬት እንቀበልና ከዚያ ኦሮሞ ሞኝ ነው ገረድ ያደረግነውን ደመቀ መኮንን የመሰለ ባርያ ዐማራ ይዘን ተመልሰን መንበረ ሥልጣኑን እንይዘዋለን ብለው እንዳሰቡም በእኔ በኩል እጠረጥራለሁ። ጻድቃንም ሆነ ጌታቸው ረዳ፣ ደብረ ጽዮንም በተለያዩ ጊዜያት ከዳያስጶራው ለተነሣባቸው “የታል የፕሪቶሪያው ስምምነት ውጤት? ተፈናቃዮች የታል የተመለሱት? በወር በሁለት ወር ያላችሁት እኮ ዓመት ሞላው። ሌላው ትጥቅ ሳይፈታ ተጋሩ ትጥቅ የምንፈታው ለምንድነው? ዋስትናችንስ ምንድነው? ለሚለው ጥያቄ መልስ ሲሰጡ “እባካችሁ አትጨቅጭቁን፣ አታስጨንቁንም። ሁሉንም ነገር በአደባባይ እንድንነግራችሁም አትጠብቁ። የሚፈርስ ጦር፣ የሚበተንም ሠራዊት የለንም። በሚዲያ ላይ የሚወራውን አይታችሁ አትደንግጡ። ትግራይ ዘመናዊ መሣሪያ የታጠቀ ከሩብ ሚልዮን በላይ ሠራዊትም አላት” እያሉ ሲናገሩም ሰምተናል። ይሄ ማለት ህወሓት ያለችው አድፍጣ የተዳከመች መስላ ቀን እየጠበቀች ነው ማለት ነው። ይሄን ደግሞ አሁን ብአዴን ስለሌለ ዐማራ አሳምሮ ያውቃል።
“…አቢይ ደጋግሞ በጋራ ዐማራን እንውጋ ቢልም ህወሓቶች ገግመው አንዋጋም አሉት። አቢይም እናንተ እምቢ ብትሉም እኔ ዐማራን ሱሪ አስፈትቼው አሳያችኋለሁ በማለት ዐማራን በጦርነት የሚያሸንፍ መስሎት ሰተት ብሎ ዘሎ ወደ ዐማራ ሜዳ ገባ። አቢይ የሰው ልክ አለማወቁ እና የ4 ተኛ ክፍል አውርቶ አደር የበሻሻ አራዳ መሆኑ አዋረደው። ዐማራን እንኳን ወግቶ ሊያሸንፍ፣ መሬት ሊቀበላቸውም ይቅርና ጭራሽ ዐማራ የገዛ ወንበሩን ሊቀማው ከጫፍ መድረሱ ቁርጥ ሆነበት። ይኸነዜ ህውሓት ሆዬ ደነገጠች። አቢይም ዐማራን እንደማያሸንፍም ዐወቀች። ወዲያውኑ ግን የበግ ለምዷን አውልቃ የአቢይን ጥሪም ተቀብላ ዐማራን ለመውጋት ከነ ጀነራሎቿ ከች አለች። የኤርትራ፣ የቀይ ባህር፣ የአሰብ ወሬ ከዚህ ግዜ ጀምሮ ነው ከጓዳ ወደ አደባባይ መውጣትና መወራትም የጀመረው።
• መጀመሪያ አቢይ አሰብን ለማስመለስ ኤርትራን እወጋለሁ የሚለው ወሬ በወያኔ ልሣኑ በኢትዮ ፎረም በኩል በጓሮ ነው ሲወራ የከረመው። ይህችም ሴራ ነችና እኛም ወንድ ከሆነ በአደባባይ ወጥቶ በኢቲቪም ቢሆን ይንገረን አልን። • ቀጠለ እና ኤርትራ የትግራይን መሬት ድጋሚ ወርራ ያዘች ተባለ። ተወራም። እኛም ድሮስ ማን አስወጣት? ማንስ ተቃወማት? ማንስ ውጪ ብሎ ጠየቃት? አቢይም፣ ብልፅግናም እኮ ኤርትራን ከያዝሽው የትግራይ ግዛቶች ውጪ ብለው አልጠየቁ። የምን ተወረርኩ ብሎ መንበጫበጭ ነው ብለን አፍ አፋቸውን አልናቸው። …
 • ቆየት አለና አቢይ አሕመድ በጓሮ በጓዳ በኢትዮ ፎረሞች በኩል እና በጎጃሜው ጌትነት አልማው በኩል በስሱ ሲበጠርቅበት የነበረውን አሰብ፣ ቀይባህር የሚለውን ወሬ በስንት መከራ ፊት ለፊት አመቻችቶ አመጣው። ነገሩ አሁንም ግልጽ አይደለም ግርማዊ ቀዳማዊ አፄ ኃይለ ሥላሴ ስለዓባይ ግድብ እንደተናገሩት እሱም “እኔ አቅም የለኝም ልጆቻችን ግን ያስመልሱታል፣ ወይ ደግሞ ከህዳሴው ግድብ፣ ወይ ከአየር መንገዱ፣ ወይ ከቴሌ ሼር ይውሰዱ የሚል የጦርነት ሳይሆን የጠረጴዛ ዙሪያ ውይይት የሚመስል ሰበካ እና ቱሪናፋውን ነው የነፋብን። ግሪሳውም ነገሩ ሳይገባው ግርር ብሎ “ገላነ ዲማ፣ አሰብ ቀይባህሪ” እያለ ሲያላዝን ዐማራው ግን የሱዳኑ አዚም ለቅቆታልና “ኬሬዳሽ እንኳን ደሜን ጠብታ ውኃ አላፈስም፣ እንዲያውም ሥራ ላይ ነኝ” ብሎ ወገመ። የሚያስቀው የኦነግና የትግሬ አክቲቪስቶች ዐማራን በኢትዮጵያ ጉዳይ ባንዳነት ከሰው እንደለመዱት ይሰድቡት አፋቸውንም ሲከፍቱበት መታየታቸው ነው። ኦሮሞ ነፃ አውጪና የትግሬ ነፃ አውጪዎች ዐማራን በኢትዮጵያዊነት ሲከሱት ይታያችሁ። ሼምለሶች… ጀመር። ሃሃሃ
“…እዚህ ጋር ካስታወስን በአሁኑ ትግራይ ጦርነት ግዜ ጁንታዋ ዐማራን የወረረችው ከተሞችንም የተቆጣጠረችው መጀመሪያ ከኤርትራ ጋር ጦርነት ልገጥም ነው በሚል አስወርታ ያንን ዘዴ ተጠቅማ ነበር። ከዚያ ዐማራው ሲዘናጋ ከኤርትራ ጋር ነው የምትዋጋው ብሎም ራሱን ጥሎ ዘጭ ብሎ ሲተኛ ሰርጎ ገብ አስገብታ፣ እንደከፍት እየነዳች ከከተሞቹ አስወጣችው። በዚያን ጊዜ ደግሞ ይነስም ይብዛም ዐማራ እንደ አሁኑ ራሱን በራሱ ማስተዳደር አልጀመረም ነበር። መከላከያውንም እንደ አጋር ነበር የሚያየው። መከላከያው ሲፈረጥጥ ዐማራም መኬን ተከትሎ ከመፈርጠጥ ውጪ ሌላ አማራጭም አልነበረውም። አሁን ግን ብአዴን የለም። የዐማራ ልዩ ኃይል፣ ፋኖ እና ሚሊሻው ነው በክልሉ አዛዡ። መከላከያም በዐማራ በጠላትነት ተፈርጆ እየተለጠለጠ ነው። ለውጥማ አለ። አሁን ብአዴን የለም። አዛዡ ራሱ ዐማራው ነው።
“…ስለዚህ ይሄ አሰብ የሚለው ገተት ዲስኩር የህውሓትም ሴራ ነው ማለት እንችላለን። ኢሳይያስም ከአቢይም ከወያኔም ተመካክረው የጋራ ጠላት ለመምታት፣ የውስጥ ችግራቸውን ለማስተንፈስም ነው ማለት እንችላለን። ብርጌን ነሀመዱ ቀላል ኢሱን ረብሾታል መሰላችሁ? በተለይ ጻድቃን ገብረ ተንሳይ እንዲህ ብሎ ነበር ወዘተ እየተባለ ከበሮ ሲደለቅ እንዴት ህውሓት በኤርትራ የተያዘባት በመሬቱ ካለ በጉዳዩ ላይ ዋይ ዋይ አላለችም? መሬቷን ከሻአቢያ እጅ ከማስለቀቅ ይልቅ እንዴት የአቢይን የቀይ ባሕር ዲስኩር ተቀብላ አሰብ አሰብ ብላ ለመጮህ  በረታች? ስለ በጌምድር እና ወሎ መሬቶች እንዲህ ከሆነች? ገና ለገና አሰብ ተመልሶ፣ ከዚያም በጌምድርን አገኛለሁ የሚል ትእግስትስ ከየት አመጣች? አቢይ ኤርትራን አይወጋም እንጂ ቢወጋም ለምዕራባውያን ቤዝ፣ ምድሪቱን በእምነት እስላምና ጴንጤ በማድረግ የኤርትራ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንን ሊያጠፋና ሊያወድም፣ በኦሮሚያ፣ በደቡብ፣ በሶማሊያ፣ በቤኒሻንጉል፣ በዐማራና በትግራይ እንዳደረገው እንደ ልማዱ የኤርትራን ትግሬዎች ሊያርድ ካለሆነ በቀር ሌላ ምን የሚያደርግ አይመስለኝም።
“…ስናጠቃልለው አሁን ዐማራ በጀመረው መንገድ በነፃ መሬቶቹ ላይ ተመጣጣኝ ኃይል ማዘጋጀቱን መቀጠል አለበት። ወታደራዊ ሥልጠናም በዐማራ ልክ እንደ እስራኤል ግዴታ መሆን አለበት። ሰውን ማንቃትም እንዲሁ ግዴታ መሆን አለበት። በየግዜው ስለ አሰብም ሆነ ቀይ ባሕር ከአቢይ ጋር እንካሰለንቲያ መልስ መሰጣጠቱን ትቶ የራሱን ሥራ ወጥሮ መሥራትም አለበት። እንበልና በዚህ በአሰብ ጉዳይ እነ አቢይ አሕመድ እየገፉበት ከሄዱ እንኳ በሻአቢያ ቢሸነፉም ባይሸነፉም የዐማራ ፋኖ በየሚዲያው መከላከያውን እየማረከ ማሳየቱን በመጥቀስ ፋኖ ባንዳ ነው። ኢትዮጵያ ለወደብ ስትዋጋ እሱ ከኋላ እየወጋን ነው በማለት ከፍተኛ የድሮን እና የአየር ድብደባም በማራ ክልል ውስጥ ማድረጋቸው ስለማይቀር ሁኔታውን አይቶና ተመካክሮ ፋኖ አሁንም የመማረኩን እና የመደምሰሱን ጀብዱ፣ ትጥቅና ተተኳሽም ወደ ክልሉ ከሚገባው የጁላ ሠራዊት መረከቡን አጠናክሮ መቀጠል አለበት።
“…ዐማራ ኢሳያስንም ቢሆን አጋሬ ነው ብሎ በሙሉ ልቡ ማመን የለበትም። ሻአቢያን በአንድ አይኑ እየጠበቀ፣ ወያኔና እና ኦሮሙማውንም እየመከተ የራሱን ፖለቲካ ነው መሥራት ያለበት። ግንቦት ሰባት ለትግል ነው የገባው ብለው ኤርትራ የሄዱ የግንቦት ሰባት የዐማራ ልጆች ጦርነት በሌለበት በሻአቢያ እስኳዶች እየተደፉ መሳይ መኮንን የአዞ እንባ እያነባላቸው ደመከልብ ሆነው እንደቀሩ ማስታወስ አስፈላጊ ነው። ሻአቢያ ኦነግን ከነመሳሪያው ወለጋ ወስዶ እንዳሰፈረውም ማስታወስ አስፈላጊ ነው። ከዚያ ከብልፅግና ወያኔ ጓዳ እንደ ጉድ የሚጎርፈውን የወያኔና የኦሮሙማውን አጀንዳ ኢግኖር መግጨትም ያስፈልጋል። እነሱ ስለ አሰብ ሲያወሩ እናንተ ስለ ወለጋና ሸዋ ማውራት፣ ሲሳይ አጌና ተሸለመ ሲሏችሁ እናንተ ስለ ጋሽ አሰግድ፣ ስለ እነ ጋሽ መሳፍንት ማውራት መተረክ። ከወደ ብልጽግና የሚመጣ አጀንዳን ከምር አለመቁጠር። ዮኒ ማኛን ሰምታችሁ አለማበድ፣ ሞጣ ቀራኒዮ ቤት ገብታችሁ አለመሸርሞጥ፣ በኢቢኤስ፣ ኢቢሲና ፋና ድራማዎች፣ የሙዚቃና የአዝማሪ ውድድር አለመዛግ። በየመንግሥት ፔጆች ሁሉ ገብታችሁ በቀን አንዴ ፋኖ ያሸንፋል። ድል ለዐማራ ፋኖ ብላችሁ ጽፋችሁ መውጣት። እንዲህ በማድረግ ብልጽግና የተባሉቱን በሙሉ የኮመንት መስጫ በራቸውን እንደ ዳንኤል ክብረት እና መሳይ መኮንን ከርችመው ብቻቸውን አሞሌ ጨው፣ ጃርት፣ አማሌሌሌ እያሉ እንዲዘፍኑ ማደርግ። ሃላስ… እኔ ዘመዴ ደግሞ አንድ ጊዜ አሸበርቲ ተብዬ የለ ሳልታክት ቀኝ ትከሻዬን የሸከከኝን በሙሉ እብድ እብድ በመጫወት እና በትምሮ ኔፓ ሙድ መሰገጥ። አከተመ። ወጥር ዐማራ…!
 • ድል ለዐማራው ፋኖ…!
• ድል ለተገፋው ለዐማራ ሕዝብ…!
• ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ አሸበርቲው…!
Filed in: Amharic