>

̈́''ዐማራ በራሱ ስንቅ በጠላቱ ትጥቅ ነፃነቱን ያረጋግጣል…!''

መነበብ ያለበት የመምህር ዘመድኩን በቀለ  “ርዕሰ አንቀጽ”

“…ዛሬም የዐማራውን ፋኖ እንመክራለን። ምክሩንም ያለ ክፍያ በነፃ እንለግሳለን። ሰሞኑን በአንድ ተወዳጅ ሚዲያ ላይ ሁለት ጋዜጠኛ ወዳጆቼ በውይይታቸው “የዐማራ ትግልም ሆነ የዐማራ ታጋዮች መተቸት የለባቸውም። ትግሬና ኦሮሞ ልዩነት ቢኖራቸው እንኳ ልዩነታቸውን አቻችለው በውስጥ ይፈቱታል እንጂ አደባባይ አያወጡትም። ስለዚህ በዳያስጶራ የሚገኙ የዐማራ ማኅበራትም፣ ግለሰቦችም፣ በሃገር ቤት ያሉም የፋኖ አባላት፣ መሪዎች፣ አስተባባሪዎች ችግር ቢኖርባቸው እንኳ አደባባይ አውጥቶ መተቸት አስፈላጊ አይደለም። ነውርም ነው። ኃጢአትም ነው። በደልም ነው። ወንጀልም ነው” ሲሉ ሰማኋቸው። አባባሉን በቅንነት ለሚሰማው ሰው ምስኪን ቅዱስ ሃሳብ ይመስላል። ነገር ግን ይሄ አስተያየት ለዐማራ ትግል አይጠቅመውም።
“…ዛሬም እንደ ሁልጊዜው እደግመዋለሁ። የዐማራ ትግል ቅዱስ ነው። የዐማራ ትግል ንጹሕ ነው። የዐማራ ትግል ነጭ ጸአዳ ወረቀት ነው። ከሩቅም ከቅርብም ለሚያየው ጽድት ብሎ የሚታይ ነው። ምንም ዓይነት ቆሻሻ ቢያርፍበት የዐማራ ትግል ያስጠላል። የዐማራን ትግል ሁሉም የወደደው፣ ሁሉ ያፈቀረው፣ ሁሉም ተስፋ ያደረገበት የዐማራ ትግል ግልፅ እና ንፁሕ ነጭ ወረቀት ስለሆነ ነው። ሃጫ በረዶ ነው የዐማራ ትግል። ጠብታ ጥቁር ነጥብ ቢያርፍበት ዓይን የሚኮሰኩስ ነው የዐማራ ትግል። ስለዚህ የዐማራን ትግል የሚደግፉ ሁሉ ልክ እንደ ዐማራ ትግል ንፁሕ፣ ቅዱስ፣ ነጭ ወረቀት፣ ኮተት፣ ገተት፣ አተት የሌለባቸው፣ አሸንክታብ የማይደራርቡ፣ ሁሉም ሰው ሊያነባቸው፣ ሊያያቸው፣ ሊመለከታቸው የሚችል መሆን አለባቸው። ከኋላም፣ ከፊትም፣ ከቀኝ ከግራ ቢያገላብጧቸው እንከን የሌላቸው ንፁሕ የዐማራ ታጋይ መሆን አለባቸው ባይ ነኝ።
“…የዐማራ ትግል በሃቅ ላይ የተመሠረተ ነው። የዐማራ ትግል ሃቅ አለው። ጠግቦ፣ ተብቶ፣ ጥጋብ ወጥሮት፣ ትዕቢት ነፍቶት፣ ቀብጦ እስቲ ልታገል፣ ሥልጣን አማረኝ፣ እንደ ትግሬ ነፃ አውጪና እንደ ኦሮሞ ነፃ አውጪ ልዝረፍ፣ ልግደል፣ ላፈናቅል፣ ሕዝብን ከሕዝብ ላናክስ፣ መስጊድ ላፍርስ፣ ቤተ ክርስቲያን ላንድድ፣ ካህን፣ ሼክ ልረድ ብሎ የተነሣ አይደለም። በምድሪቱ ላይ በህይወት እንዳይኖር ሞት ስለታወጀበት፣ በጅምላ ስለተጨፈጨፈ፣ ሀብት አፍርቶ፣ ትዳር መስርቶ፣ ጎጆ ቀልሶ፣ አርሶና ነግዶ፣ ተምሮም መኖር እንዳይችል ባልተጻፈ ዐዋጅ የዘር ማጥፋት ስለታወጀበት ነው መታገል የጀመረው። እንደ ትግሬ ነፃ አውጪ ጠግቦ፣ እንደ ኦሮሞ ነፃ አውጪ ተብቶ አይደለም ብረት ያነሣው ዐማራ። ቤቱ ፈርሶበት፣ ሕጋዊ ደሀ አደረግኩህ ተብሎ በቴሌቭዥን ጭምር ኦሮሞዎቹ ስላወጁበት፣ ቅስሙን ሰብረነዋል፣ ጅስሙን መጠነዋል ተብሎ ስለተነገረበት ነው የተነሣው ዐማራ። ቤት መከራየት አትችልም። ለዐማራ በኦሮሚያ ምድር በሸገር ሲቲ ከተማ ያከራየ ሰው እንኳ ቢኖር፣ ኦሮሞም ቢሆን 50ሺ በገንዘብ ይቀጣል፣ ቤቱ ይፈርሳል፣ መሬቱ ይወሰዳል ሲባል ነው ዐማራ እንግዲያውስ ምንቀረኝ ብሎ ብረት ያነሳው። እናም የዐማራ ትግል ንፁሕ ነው። የሚፈልገውም ንጹሕ ደጋፊ፣ መከሪ፣ ረጂ ቆሻሻ፣ ጥንባታም ኮተታም የድል አጥቢያ አርበኛ አይደለም።
“…የዐማራን ትግል የትግሬ ነፃ አውጪ አይደግፈውም። የትግሬ ሕዝብ ግን የሚነቅፍበት አንዳች ምክንያት የለውም። የኦሮሞ ቦለጢቀኞች ለሥልጣናቸው ሲሉ ይታገሉታል፣ ይነቅፉታል፣ የኦሮሞ ሕዝብ ግን እውነቱን ስለሚያውቀው የሚነቅፍበት ምክንያት የለውም። ከገዢው ካድሬዎች በቀር ቤርቤረሰቦች የዐማራ ትግል ቅዱስ እንደሆነ አሳምረው ያውቃሉ። ለዚህ ቅዱስ፣ ግልጽ፣ ምስጢራዊ ላልሆነ፣ ሰምና ወርቅ ለሌለው ለዐማራ ትግል በአፋ ለመናገር ቢያፍር፣ ቢፈራ በልቡ የሚጸልይ፣ የሚደግፈው ሚልዮን ሕዝብ ነው። ሱማሌ በለው፣ አፋር በለው፣ ደቡብ በለው፣ ለዐማራ ትግል ድጋፍ ሰጪ ሕዝብ ነው። ምክንያቱም የዐማራ ትግል የተቀባባ አሳሳች ምክንያት ስለሌለው ነው።
“…ታዲያ የዐማራ ትግል ቅዱስ ከሆነ በዳያስጶራ ያለው ዶላር ብቻ በእጁ የሚገኘው ግሳንግስ አርፍዶ መጪ የበግ ለምድ የለበሰ ተኩላ ሁሉ የዐማራን ትግል ለምን ለማቆሸሽ ይጣደፋል? የዐማራ ትግል የሚተቸው፣ የሚወቀሰውም፣ የሚሰደበውም እኮ በእነዚህ ዋይፋይ እንደልቡ በሆኑ፣ በሰከሩና በጦዙ ቁጥር፣ ሜካፕ ተለቅልቀው በቲክቶክ፣ በዩቲዩብ፣ በፌስቡክ ወጥተው በሚበጠረቁ ተራ ግለሰቦች ነው። በሀገር ቤት ያለው፣ ብረት አንሥቶ የሚታገለው የዐማራ ታጋይ ቅዱስ ከሆነ በውጭ ሃገር ያለው ዶላር አንሥቶ ሊታገል የተነሣው ለምን ትግሉን ያረክሰዋል? ለምን ትግሉን ለማቆሸሽ ይራወጣል? ቆሻሻ ሁላ። ጢሮይቱ ሁንዳ። የዐማራን ትግል በሃሳብ፣ በዕውቀት፣ በሙያ፣ በጸሎትም ቢሆን ለማገዝ ከፈለክ መጀመሪያ ታጠብ። መጀመሪያ እንደ ዐማራ ትግል ንጹሕ ሁን። ከነግማትህ፣ ከነክርፋትህ፣ ከነነውርህ፣ ከነኮተተህ የዐማራን ትግል ለመቀላቀል አትራወጥ። የኢሰፓነትህን ኮት፣ የኢህአዲግነትህን ጃኬት፣ የብልፅግና ፓንት አጥልቀህ እየሸተትክ ለምን ትንጋፈፋለህ? የብአዴን ጫማ በኦነግ ካልሲ አድርገህ ለምን የዐማራን ትግል ለማግማማት ትራወጣለህ? ራስህን ቻል። የዐማራ ትግል ሱሪ በቀበቶ የታጠቀ ንፁሕ የጀግኖች ትግል ነው።
“…የትግሬና የኦሮሞ ነፃ አውጪዎች ችግራቸውን፣ ስህተታቸውን በውስጥ ደብቀው፣ በአደባባይ ፍቅር መስለው የሚታዩት እኮ ትግላቸው ሃቅ ስለሌለው ነው። ውሸታሞች ስለሆኑ ነው። ገበናቸውን በምላስ፣ በውሸት ድሪቶ ስለሚሸፍኑት ነው። የዐማራ ትግል ግን እንደዚያ አይደለም። የዐማራ ትግል ሃላል ነው። የዐማራ ትግል መቅደሱ ክፍት ነው። መንበሩን እያየህ በክብር፣ በፍርሃት የምትመለከተው ነው። ከነጫማህ ሰገራ ረግጠህ የምትቀላቀልበት አይደለም የዐማራ ትግል። ነጭ ሽንኩርት በልተህ ሳትታጠብ ከነ ክርፋታም፣ ግማታም፣ ጥንባታም አፍህ ዘው ብለህ ገብተህ የምታግማማው አይደለም የዐማራ ትግል። ታጠብ አልኩህ።
“…የትግሬና የኦሮሞ ነፃ አውጪዎች ትግል ጨለማ ነው። ጥቁር ነው። ጨለማና ጥቁር ደግሞ ነገሮችን ይሰውራል፣ ይሸሽጋል፣ ይደብቃል። ለዚህ ነው የትግሬ ነጻ አውጪዎች ሚልዮን ትግሬ አስፈጅተው ምንም እንዳልተነካባቸው አሁንም እየሳቁ የሚሽለጠለጡት። የኦሮሞም እንደዛው። የዐማራ ትግል ግን ነጭ ወረቀት ነው። ፀአዳ ፏ ያለ ሃጫ በረዶ። መንገደኛ ሁሉ ሲያየው ፐ ብሎ የሚያደንቀው። በዚህ ነጭ ፀአዳ ሃጫ በረዶ በመሰለ ትግል ላይ የፈለገ ዶክተር፣ ፕሮፌሰር፣ ኢንጂነር፣ ቄስም ሆነ ሼክ፣ ጋዜጠኛም ሆነ ኢንቬስተር፣ ወላ ያፈለገው ይሁን ትግሉን ቢቀላቀል መደበቅ አይችልም። መሸሸግ አይችልም። እንደ ትግሬና ኦሮሞ በሃሰት ትርክት፣ በቀይ እና በጥቁር ከለር ውስጥ ለመደበቅ አይመችም። ነጭ ወረቀት ነው የዐማራ ትግል። ጥቁር ነጥብ ይዘህ ብትመጣበት ጎልጉሎ ያወጣሃል። ስህተትህ ነጥብ ቢያክልም አገልቶ ያወጣሃል። የዐማራ ትግል ቆሻሾችን አይደብቅም።
“…ለዚህ ነው ብዙዎች ወደ ዐማራ ትግል ሲመጡ የሚመረመሩት። የሚተቹት፣ የሚወቀሱት። ነጭ ወረቀት ላይ ለማረፍ ከመጣህ ነጭ ወረቀት፣ ነጭ ለብሰህ ነው መምጣት ያለብህ። ኮተትህን፣ መርዝህን በጉያህ ይዘህ ብትመጣ ወዲያው ነው የምትጋለጠው። ወዲያው ነው የምትሰጣው። እስክንድር ነጋ፣ ዘመነ ካሴ፣ አቶ አሰግድ፣ ፋኖ ደረጀ፣ መከታው፣ አቶ መሳፍንት፣ እነ ኮነሬል፣ ምሬ ወዳጆ ይመረመሯታል። ይተቻሉ። አፈር ከሆኑ ደቅቀው ይቀራሉ። ወርቅ ከሆኑ አምሮባቸው፣ አጊጠው ይወጣሉ። አፈር እሳት የሚፈራው አፈር ከሆነ ብቻ ነው። አፈር እሳት የማይፈራው ወርቅ ከሆነ ብቻ ነው። የዐማራ ትግልም እንደዚያ ነው። መጀመሪያ ታጠብ፣ ተመርመር፣ ከዚያ የዐማራን ትግል ተቀላቀል። እሱ ነው የሚያዋጣው እንጂ ዝም ብሎ እንደ ትግሬና እንደ ኦሮሞ ቦለጢቀኞች ገመና እንሸፍን ብሎ በደፈናው መናገር ከሌቦቹ፣ ከቆሻሾቹ፣ ከሴረኞቹ ጎራ እንደመሰለፍ ነው የምቆጥረው። ይህቺ ጠጋ ጠጋ ዕቃ ለማንሳት ነው ይል ነበር አጎቴ ሌኒን።
“…እስከዛሬ የዐማራው ትግል የማንም መንገደኛ የሚነዳው ነበር። በኢትዮጵያኒስት ካባ የተጠቀለሉ አዝጎችም መጫወቻቸው፣ የጥገት ላማቸው፣ የገንዘብ ምንጫቸው ነበር የዐማራው ትግል። ኢትዮጵያኒስቶቹ ዐማራን ይጠቀሙበት የነበረው እንደ ነዳጅ ጉድጓድ ነበር። አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ሰንደቅ ዓላማ እንደ አሞሌ ጨው እያሳዩ፣ ገንዘቡን አልበው፣ አልበው፣ ግጠውት በአጥንቱ ነበር የሚያስቀሩት። ዐማራውን ዐማራ ነኝ እንዳይል አፉን ለጉመውት እንደ ኮንደም እየተጠቀሙ፣ እንደ ሸንኮራ እየመጠጡ ነበር የሚጫወቱበት። ሃገር ተደፈረ ብለው ገንዘብ፣ ጎርፍ ጎረፈ ብለው ገንዘብ፣ ፓርቲ ልናቋቁም ነው። ኤርትራ በረሃ ልንገባ ነው። መፈንቅለ መንግሥት ልናካሂድ ነው ገንዘብ፣ ገንዘብ ገንዘብ ግጠውት እነሱ ሰቡ፣ ረቡ፣ ወፈሩ፣ ዐማራው ግን ከሳ፣ ጫጨ፣ መነመነ፣ ደቀቀ፣ ቀጨጨ፣ ብን ብሎ በአፅሙ ቀረላቸው።
“…አሁን ግን ዘመን ተለውጧል። ዘመን ተቀይሯል። በቅዱሱ የዐማራ ትግል ላይ ርኩሳኑ እነ አንዳርጋቸው ጽጌ ዐማራም፣ ኦሮሞም ሆነው መተወን አይችሉም። እነ ታማኝ በየነ ጎፈንድሚ እየቀፈሉ ሊበሉት፣ ሊግጡት አይችሉም። እነ አበበ ገላው የጠሉትን ዐማራ ዛሬ ቀን ሲጨልምባቸው ሊመሩት አይችልም። ጽንፈኛ ነው ሲሉት የከረሙትን ዐማራ ዛሬ እነ ነአምን ዘለቀ፣ እነ ዶክተር ዮናስ ብሩ አለንለት፣ የዐማራ ትግል እንዲህና እንዲያ መሆን አለበት ሊሉት አይገባም። የዐማራ ትግል የወዳጄን የአቶ ልደቱን ምክር የሚሰማበት ጆሮ የለውም። ዐማራ እንደ ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት የሚመሰክርለት ሰው ብቻ ነው የሚፈልገው። ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት በኢትዮጵያኒስት ጎራ ያሉ ሰው ናቸው። ነገር ግን በዲሲ የፋኖ ምሽት ላይ ምን አሉ?
“…በዳያስፖራ ሆናችሁ ፋኖ የፖለቲካ መሪ የለውም፣ መሪ ስለሚያስፈልግ የፖለቲካ መሪ እንሁነው የምትሉ ሰዎች አርፋችሁ ተቀመጡ። ቁርጣችሁንም ዕውቁ። ፋኖ በመላው ዐማራ በአንድ ቀን ከ40 በላይ ወረዳዎችን የያዘው ያለ መሪ ነው? መልሱልኝ? ፋኖ ብሬንና ስናይፐር ስለተሸከመ ፖለቲካ የማያውቅ ከመሰላችሁ ፋኖ ውስጥ ኢንጅነሮች አሉ። ሕግ ዐዋቂዎች አሉ። ዶክተሮች አሉ። ፋኖ የዐማራ መገፋት ያንገበገበው የሰፊው የዐማራ ሕዝብ ሰብስብ ነው። ስለዚህ መሪ እንድትሆኑት አይፈልግም። ይልቁንስ አትከፋፍሉት። ከቻላችሁ በገንዘብና በዲፕሎማሲ አግዙ። ከዚያ ውጭ ግን መሪ እንሁንህ የምትሉትን ነገር ተስፋ ቁረጡ። ፋኖ የፖለቲካ መሪ አለው። ፔሬድ…!
“…እንዲህ ዓይነት መካሪ ነው ለዐማራ ትግል የሚያስፈልገው። ደርግን ስታገለግል፣ መሬት ላራሹ፣ ትርፍ የከተማ ቦታና ቤቶች ብለህ ዐማራውን በአቢዮት ስም ዘርፈህ፣ እርቃኑን አውጥተህ፣ ሙልጩን አስቀርተህ፣ ለማኝና ደሀ ስታደርገው ከርመህ ዛሬ ለዐማራው ልታገል ነው ስትል አለማፈርህ። ኢሀአፓ፣ ኢዲዩ፣ ህወሓት ኦነግ፣ ኢህአዴግ መኤሶን፣ ብአዴን፣ ኢህድን፣ አዴፓ፣ ግንቦት ሰባት፣ ኢዜማ፣ ቁዘማ ነኝ ስትል ከርመህ፣ ከብልጽግና ጋር ባልተቀደሰ ጋብቻ ተጣምረህ፣ ስትሸረሙጥ፣ ይቅርታ ስታመነዝር ከርመህ፣ ንስሀ ሳትገባ፣ ይቅርታ ሳትጠይቅ፣ ሂስ ግለሂስ ሳታወርድ፣ ሳትናዘዝ እንዲሁ ከነጥንባትህ ዘው ስትል አለማፈርህ። ግሞ መጀመሪያ ታጠብ።
“…ለዚህ ነው የዐማራ ትግል በብላሽ አርፍበታለሁ የሚለውን ኮተታም ዝንብ ሁሉ ገና ብቅ ሲል አፍጥጦ የሚያሳየው። የዐማራ ትግል ቆሻሻ ቻይ ጥቁር ጨርቅ አይደለም። የዐማራ ትግል ነጭ ወረቀት ነው። ፕሮፌሰር፣ ዶክተር፣ ኢንጂነር፣ ኢንኩዩቤተር፣ ትራክተር፣ ባራክተር፣ ደባትር ሆነህ ብትመጣም ገና ብቅ ስትል ነጭ ወረቀት የመሰለ የዐማራ ትግልና ታጋይ ነው የሚጠብቅህ። በዐማራ ስም እስከዛሬ የቀፈላችሁት ይበቃችኋል። የዘረፋችሁት ይበቃችኋል። የሸቀላችሁት ይበቃችኋል። አሁን ግን የዐማራ ትግል ወንድኛ አዳሪ የፖለቲካ ሸርሙጦችን አያስተናግድም። ስለዚህ የዐማራ ትግል ችግር ካለም እንደትግሬና እንደኦሮሞ በውስጥ ይፈታ ብሎ ነገር አይሠራም። የዐማራ ታጋይ ነኝ ብሎ የመጣ ነጭ ወረቀት ላይ ማረፉን ዐውቆ ይምጣ። ሌባ ሁላ።
“…ፋኖ ውስጥም ድረስ ሄዶ የገባም ተኩላ ካለ ይጋለጣል። በወለጋ የፈሰሰው የዐማራ ደም ባንዳ ያጋልጣል። የዐማራ ፋኖ ትግል እንደ ጠበል ያለ ነው። ስትገባበት ዝም ብሎ ያይህና ሳትቆይ ያስለፈልፍህሃል። ያስጓራሃል። ዐማራ በቃኝ ብሏል። ዐማራ ልበ ብርሃን ሕዝብ ነው። በተደጋጋሚ ሰልፍ ወጥቶ ሰሚ ቢያጣ ነው ሰይፍ ማንሳት የጀመረው። ዐማራ በሽማግሌዎቹ ሲቀለድባቸው ስለከረመ ነው አሁን ጉዳዩ በሽምግልና የሚፈታ አይደለም ብሎ የተነሣው። ዐማራን እንደፋራ የሚቆጥረው የበሻሻና የዓደዋ ሰገጤ ስለበዛ ነው አራዳማ ማን እንደሆነ ላሳይህ ብሎ የተነሣው። ዐማራ በመሠረታት ሃገር ዓባይን አትሻገርም፣ ሸኖን አታልፍም ሲባል ጊዜ ነው አሳይሃለሁ ብሎ ነፍጥ ይዞ ሊያናፍጠው የተነሣው። ዐማራ ትግሉ ቅዱስ ነው የምልህ ለዚህ ነው።
“…ዐማራው አሁን የውስጥ ጽዳት በሚገባ አከናውኗል። አሁን አሜሪካ ልዑካኗን መቀሌ ድረስ ልካ ከህወሓት ተወያይታለች። አቢይ አሕመድን አግልላም ከብርሃኑ ጁላ ጋር ዘግታ ተወያይታለች። ህወሓትም ከፕሪቶሪያው ስምምነት ወዲህ እንኳ ወልቃይትንና ራያን ሳንረከብ ይኸው ዓመት ሞላን። ሕዝቡም ተስፋ እየቆረጠብን ነው። የሆነ ነገር ፍጠሩና መሬቶቹን አስረክቡን ብለው በመቀሌ አሜሪካኖቹ ላይ አልቅሰዋል። አሜሪካኖቹም የወያኔ ምርኮኛው ፀረ ዐማራው ብራኑ ጁላን አግኝተው መክረዋል። እናም ከልቅሶውና ከምክክሩ በኋላ በዛሬው ዕለት የፌደራል ከፍተኛ የጦር መኮንኖች እና የህወሓት ከፍተኛ የጦር መኮንኖች በተገኙበት በ ዐማራዎቹ መሬት በወልቃይትና በራያ ጉዳይ፣ በኤርትራም በተያዙ በተባሉ የትግራይ መሬቶች ላይ ሰፈሮ ስለሚገኝ ባሉት ኃይል ላይ ርምጃ ተወስዶ በአስቸኳይ የሚወጣበት እና የትግሬ ተፈናቃዮች ወደ ወልቃይትና ራያ ተመልሰው በሚሰፍሩበት ጉዳይ ላይ ከውሳኔ ለመድረስ ስብሰባ ተቀምጠዋል ተብሏል።
ተመልከት ዐማራ ንፁሕ ትግል፣ ቅዱስ ትግል ጀምሮ ፈጣሪ ባይረዳው ኖሮ ይሄን ጊዜ የትግሬ ነፃ አውጪዋም ሆነች የኦሮሞ ነፃ አውጪው አይደለም ድሮን ሽመል ይዞ ነበር ዐማራን እንደ በግ እየነዳ የሚያስወጣው። አሁን ግን እንዲያ ማድረግ አይቻልም። ዐማራ ተራራ ሆኗል። የማትወጣው፣ የማታፈርሰው ተራራ። ያውም ቅዱስ ተራራ። ርኩሳን፣ ቆሻሻ ሃሳብ ተሸክመው ሊያቆሽሹት የሚቀርቡትን እየፈጠፈጠ የሚያርቅ ተራራ፣ ንፁሐንን፣ ቅዱስ ሃሳብ ይዘው የሚመጡትን የሚያማልል፣ የሚማርክ፣ በዚያው የሚያስቀር ቅዱስ ተራራ ነው የሆነው።
…ይሄን የምለው እኔ ነኝ። እኔ አንድ ለእናቱ ሺ ለጠላቱ የምሥራቁ ሰው የሐረርጌው ቆቱ መራታው ዘመዴ ባለማዕተቡ የተዋሕዶ ልጅ የሥላሴ ባርያ የድንግል አሽከር በስመ ጥምቀቴ አክሊለ ገብርኤል ነኝ። ትግል እውነት ይፈልጋል። ሃቅ ይፈልጋል። ሃቅን የያዘ ያሸንፋል። ይሄን በማለቴ ቅር የሚላችሁ ካላችሁ ራሴን ዝቅ አድርጌ በትህትና እማጸናችኋለሁ፣ በአናትህ ተተከል። ዱቄታም። ደግሞ ሰደብከን በል አለሁ። ወሬያም ሃዸ ኦዱ ወዪ…

• ዐማራ በራሱ ስንቅ በጠላቱ ትጥቅ ነፃነቱን ያረጋግጣል…!

 • ድል ለዐማራ ፋኖ…! 
• ድል ለተገፋው ለዐማራ ሕዝብ…!
 • ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ አሸበርቲው…!
Filed in: Amharic