>
5:14 pm - Sunday April 30, 9420

ዶ/ር ሄኔሪ ኪሲንጀርም ሞተ...

ዶ/ር ሄኔሪ ኪሲንጀርም ሞተ

“…የኢትዮጵያን ክብር የዘውድ ሥርዓትን የደመሰሰ፣ የገነደሰው፣ ኢትዮጵያ በሶማሌ እንድትወረር ዐውቃ ገንዘብ ከፍላ የሸመተችውን የጦር መሳሪያ ያስከለከለ፣ በግድ ገፍቷትትም ወደ ሶሻሊስቱ ካምፕ ከቷት እንድትማቅቅ ያደረገ፣ ኤርትራን አስገንጥሎ ኢትዮጵያን ከባህር በር ያራቀ። እነ ሻአቢያን፣ ኦነግና ህወሓትን የመሰሉ የዘር ነቀርሳዎች በኢትዮጵያ ላይ እንዲፋፉም ያደረገ።

ኢትዮጵያዊ ማንነት፣ ከነ ሰንደቅ ዓላማዋ ርካሽ እንዲሆን ያደረገ፣ ሰላም ካገኘች ባለ አዕምሮ ሕዝብ ስላላት ለቁጥጥር አትመችም። ስለዚህ እንደተበጠበጠች ትኑር ብሎ አሜሪካን በኢትዮጵያ ላይ እንድትከተለው ቋሚ የማይቀየር ዐምድ አድርጎ እንደ ዶግማ የማይለወጥ ሕግ አድርጎ የሠራብን፣ በዘር እየተባላን፣ እየተራረድን፣ እየተገዳደልን እንድንኖር ያደረገን።

ወያኔን በማቅረብ፣ ኦነግን በማቅረብ፣ ዐማራን የጋራ ጠላት አድርገው ሁሉም እንዲያዩት፣ ሞቱ፣ ስደቱ እንዳይዘገብ፣ በመንግሥታቱ ድርጅት ውስጥ ድምጹ እንዳይሰማ፣ እንደ ዓለሙ ሁሉ ሕዝብ ጠላት ተደርጎም እንዲታይ፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አሁን የገጠማት ሁሉ እንዲገጥማት፣ ከተቻለ ከምድረ ገጽ እንድትጠፋ የሚደረገው ሴራ ሁሉ እንዲተገበርብን ያደረገው ዶር ሄኔሪ ኪሲንጀር በ100 ዓመቱ የአሜሪካን ጥቅሟን አስከብሮ፣ ኢትዮጵያን ፍደዋን ያየች እንዳትድን እንዳትሞት ሆና እያቃሰተች እንድትኖርም ሥርዓት ሠርቶ አፈር ከደቼም አብልቶን ሞተ። ኢትዮጵያ ግን እንዳለች አለች።

ይሄንንም የፈተና ዘመን በጽንዓት ትሻገረዋለች።

• ማርያምን ኢትዮጵያማ ትነሣለች…!

በመምህር ዘመድኩን በቀለ

 

Filed in: Amharic