>
5:14 pm - Monday April 30, 5979

የኢትዮጵያ ዘውድ ምክርቤት ፕሬዘዳንት ያልጠበቁትን የ ለንደን ከተማ ነጻነት ን የክብር ሽልማት ተቀበሉ

የድል በዓል በማክበር ላይ የነበሩት የኢትዮጵያ ዘውድ ምክርቤት ፕሬዘዳንት ያልጠበቁትን የ ለንደን ከተማ ነጻነት ን የክብር ሽልማት ተቀበሉ

ልዑልነታቸው ልዑል ኤርሚያስ ሳህለሥላሴ ኃይለሥላሴ የኢትዮጵያ ዘውድ ምክርቤት ፕሬዘዳንት፤ ትልቅ ክብር ያለውን ለንደን ከተማ ነጻነት ሽልማት ህዳር 7 ቀን 2016 . ተቀበሉ፡፡ ይህም የክብር ሽልማት፤ አያታቸው ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ታላቋ ብሪታኒያን 1947 . በጎበኙ ግዜ የተቀበሉት አይነት ነው፡፡

ልዑልነታቸው የክብር ሽልማቱን ለንደን ውስጥ በጊልድሆል የተቀበሉት፤ ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ በግዞት ላይ በነበሩ ግዜ ይኖሩበት የነበረውን በባዝስ ከተማ የሚገኘውን የፌየርፊልድ ሀውስ ለመጎብኘት በሄዱበት ሳመንት ውስጥ ነው፡፡ በዚያን ግዜ፤ ማለትም ህዳር 4 ቀን፤ የባዝስ ከተማ ከንቲባ ለልዑልነታቸውና ለባለቤታቸው ልዕልት ሳባ ከበደ የክብር አቀባበል በማድረግ ከተማውን አስጎብኝተዋቸዋል፡፡ በተጨማሪም 2 አመት በላይ እድሜ ያላቸውን የሮማን የገላ መታጠቢያ ቤቶች ጎብኝተዋል፡፡  ጃንሆይ በግዞት ላይ በነበሩበት ግዜ የተነሱትም ፎቶግራፍ በግርግዳ ላይ የተሰቀለበትን የመታጠቢያ ቤት ጎብኝተዋል፡፡ 

ጃንሆይ ስለ ኢትዮጵያ ጉዳይ ሲከራከሩና ሲታገሉ የነበሩት፤ እንደዚሁም የታላቋ ብሪታኒያን እርዳታም ለማግኝት የቻሉት በባዝስ ከተማ ውስጥ በፌየርፊልድ ሀውስ እዬኖሩ ነበር፡፡

በሚቀጥለው ቀን (ህዳር 5) ልዑልነታቸው ለንደን አጠገብ በሚገኘው በዊንድሶር ቤተመንግስት በቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተመቅደስ ውስጥ፤ ጃንሆይና የኢትዮጵያ አርበኞች ከታላቋ ብሪታኒያና የቅርብ አጋሮቿ ጋር በመሆን 1934 . ተዋግተው የተቀዳጁትን ድል የሚያበስርና የሚያስታውስ፤ በብረት ላይ የተቀረጸ የጎንደር ድል የጽሁፍ ቅርስ ለከተማው በማበርከት አስመርቀዋል፡፡   

ልዑልነታቸውና ልዕልት ሳባ ዊንድሶር ቤተመንግስት በነበሩበት ግዜ፤ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተመቅደስ ውጭ የሚገኘውን የአጼ ቴዎድሮስን ልጅ፤ የልጅ አለማየሁን መቃብር ጎብኝተዋል፡፡ ልጅ አለማየሁ በንግሥት ቪክቶሪያ እንክብካቤ ያደገና ተወዳጅ የነበረ መስፍን ነበር፡፡ ለዚህም ነው ንግሥት ቪክቶሪያ ለብዙ ሰው የማይደረገውን፤ 40 በላይ የሚሆኑ የእንግሊዝ የዘውድ ቤተሰብ አባላት በተቀበሩበት ቤተመንግስት ግቢ ውስጥ፤ ልጅ አለማየሁ እንዲቀበር ያደረጉት፡፡  

ልዑል ኤርሚያስ የጎንደርን ድል የመታሰቢያ ቅርስ በመጀመሪያ ግዜ ከሽፋኑ የገለጡት፤ በልጅ አለማየሁ መቃብር ፊት ለፊት ነበር፡፡ በዚህም ግዜ፤ የቤተመቅደሱ ካህን ጆናታን ኩር በእንግሊዝኛና በግዕዝ ቋንቋዎች ከመጽሀፈ ሄኖክ በመጥቀስ ጸሎት አድርጓል፡፡ ልዑል ኤርሚያስም ለጆናታን ኩር የኢትዮጵያንና የታላቋ ብሪታኒያን የጦር አጋርነት የሚያበስረውን የታላቁን የጎንደር ድል መዳሊያ ሸልመዋቸዋል፡፡

 

ልዑልነታቸው ልዑል ኤርሚያስ ሳህለሥላሴ ኃይለሥላሴ የኢትዮጵያ ዘውድ ምክርቤት ፕሬዘዳንት
በጎንደር ድል እራት ላይ ህዳር 7 ቀን 2016 ዓ.ም በለንደን ከተማ ያደረጉት ንግግር

Leul Ermias Remarks-Gondar-Nof 17 2023 

Filed in: Amharic