ምጽአተ ዴሞክራሲ፣ ለምጽዐተ ኢኮኖሚ፤ አዙሪተ ምጽአተ ፖለቲካ፣ ለምጽዐተ ኦሮሙማ!!!
ሚሊዮን ዘአማኑኤል (ኢት-ኢኮኖሚ /ET- ECONOMY)
‹‹አብይ ማደሪያ የለው፣ ግንድ ይዞ ይዞራል!!!››
‹‹ምጽአተ ትዮጵያ እንተርፍ ይሆን ባይዋጥልህም እነሆ ፖለቲካ›› በአቶ ልደቱ አያሌው ለቀረበ በጥናት ያልተደገፈ የፖለቲካ ሃተታ የሃገሪቱን ኢኮኖሚ ጠንቅቀው ካለመረዳት የመጣ መሆኑን በመገንዘብ ኢኮኖሚውን ምንያህል ያውቁታል፡፡ ኢኮኖሚውን ሳያውቁ የፖለቲካ ሃተታ መፅፍ ለስህተት ይዳርጋል እንላለን፡፡ ላበረከቱት አወያይ ፁህፍዎ ምስጋና ይገባዎታል፡፡ ለዚህ ጹሁፍ መልስ በቅንነት ቢሰጡበት እንጠይቃለን፡፡
ከምፅዐተ ኢትዮጵያ የ2019ዓ/ም ምርጫ ያድነናል!!! ሠላማዊ የፖለቲካ ትግል ኢትዮጵያን ይታደጋል፣ ኢትዮጵያዊ ህብረ ብሔራዊ ትግል ምፅዐተ-ኢትዮጵያን ይታደጋል!!! የ2016ዓ/ም ታህሣስን፣ ጥርን፣ የካቲትህ ወዘተ በህይወት የመኖር ያለመኖራችንን ዋስትናችን ምንድን ነው? ዛሬን እንኑር አንኑር ሳናውቅ ሳናረጋግጥ የ2019 ዓም ምርጫ እንዴት ይናፍቀን? አቶ ልደቱ አያሌው እውቁ የፖለቲካ ሰው በአሜሪካ ተቀምጠው መሬት ላይ ያለ ሰው ሆኑብን እንደ ፈረስ ጋላቢው፡፡ የአቶ ልደቱ አያሌው መጣጥፍ ‹‹ከሞት በኃላ ህይወት›› አለና ለሰማያዊ ዓለማችሁ አስቡ ምድራዊ ዓለማችሁ አያሳስባችሁ ነው የሚሉን፡፡ ኮነሬል አብይ አህመድ ፋሽስታዊ አገዛዝ እስከ 2019ዓ/ም ምርጫ በሰላማዊ ውድድር እንዲወርድ ማድረግ እንችላለን እስከዚያ ብንታገስ የሚል ጥቅል እንድምታ አለው፡፡
‹‹የአንድ አገር ፖለቲካ የኢኮኖሚው ነጸብራቅ ነው፡፡›› የኦህዴድ ብልጽግና መንግሥት የሃገሪቱን ሃብትና የኃብት ክፍፍልን በተመለከተ የኢኮኖሚ ፍኖተ -ካርታቸው የተነደፈውና የተቃኘው በኬኛ ፖለቲካ ነው፡፡ ፊንፊኔ ኬኛ!፣ አዲሳባ ኬኛ ድሬዳዋ ኬኛ አሰብ ኬኛ፣ ቀይባህር ኬኛ በሚል የተስፋፊነት፣ የያዘውን የጎረሰውን አላምጦ ሳይውጥ ሌላ የሚሮርስ ስግብግብ ሥርዓት ባንኩን፣ ታንኩን፣ መሬቱን፣ ወርቁን፣ ዘርፎ ሲያበቃ የአማራን፣የትግራይን ፣ የአፋርን፣ የደቡብን ህዝብ በማያባራ ጦርነትና በርሃብ አለንጋ በመግረፍ ላይ ይገኛል፡፡ የኦህዴድ ብልጽግና መንግሥት መቶ አመት ለመግዛት ከፈለግህ አማራን፣ ትግሬን ወዘተ ህዝብ አደህይተህ ግዛ መመሪያው ነው፡፡
- ትግላችን በህይወት የመኖር የህልውና አደጋ ነው ስንል በህይወት የመኖርና ያለመኖር ዋስትና ጥያቄ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ በህይወት ሲኖር አገራችን ኢትዮጵያም ትኖራለች፡፡ ህዝብ ሳይኖር አገር ህልውና አይኖረውም፡፡ የአቶ ልደቱ የህልውና ስጋት የሰው ልጆች ህልውና ሳይሆን የሃገር ህልውና ላይ ያተኩራል፡፡
- ፖለቲካ የኢኮኖሚ ነፀብራቅ ነው!!! የአንድ አገር ፖለቲካ ሲተነተን መጀመሪያ ኢኮኖሚውን አፍታትቶ በመተንተን ካልተጀመረ ፖለቲካውን ለመረዳት ያዳግታል፡፡ የኮነሬል አብይ መንግሥት የኦሮሙማ ሥርዓት አገዛዝ ጅምር ነው ስንል በፖለቲካ መዋቅራዊ አደረጃጀቱ ጠቅላይ ሚንስትሩና የሚኒስትሮች ምክር ቤቱ በአንድ ዘር አደረጃጀት፣ የመከላከያና የፖሊስ ሠራዊቱ በአንድ ዘር አደረጃጀት፣ የአንባሳደሮች ሹመት፣ መንግሥታዊ ተቆማት፣ መንግሥታዊ መስሪያ ቤቶች ሠራተኞች በተለይ ሹሞቹ ከትግራዋይ ብሄር ወደ ኦሮሞ ብሄር ዘረኛና ተረኛነት መሸጋገሩን ማንም ይመሰክራል በዚህም የተነሳ የኦህዴድ ብልጽግና የኦሮሙማ መንግሥት፣ መከላከያ ሠራዊት፣ ብለን የምንጠራው፡፡ የሃገሪቱን ኢኮኖሚ፣ ፖለቲካ ማን እየተቆጣጠረው ነው? ባንኩን፣ ታንኩን፣ ወርቁን፣ መሬቱን ሹመቱን ብለህ በመጠየቅ ሰውዬው ጋ ትደርሳለህ? ጠቅላዩ፣ ኤታማጆር፣ ዓየር ኃይል፣ ፀጥታዉ ወዘተ በመንግሥታዊ መዋቅራዊ የዘር አደረጃጀት ከህወሓት ወደ ኦህዴድ መሸጋገሩን በጥናትህ ካልደረስክበት ዳግም አጥናው፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ህዝብ ንዋሪዎች ህብረ ብሔር ህዝብ በአመዛኙ አማራ፣ ኦሮሞ፣ ትግሬ፣ ጉራጌ ሲሆኑ ሌሎቹ ሱማሌ፣ አፋር፣ ጋምቤላ፣ ሃረሪ፣ ቤኒሻንጉል-ጉሙዝ፣ ደቡብ (ሲዳማ፣ ጉራጌ፣ ወላይታ፣ ሃዲያ ወዘተ) ንዋሪ ህዝብ ሳይመክርበት ከአዲስ አበባ ከተማ መሬት ተቆርሷ፣ የሸገር ከተማ በኦሮሚያ ክልል መንግስት ሽመልስ አብዲሳና በአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ፊርማ የወሰን ክልሉ ፀደቀ፡፡ ጠቅላይ ሚንስትሩ ኮነሬል አብይም አፀደቀው እንዴ እንዴ እያለ የኦሮሙማ የገዳ ሥርዓት በኢትዮጵያ ምድር ወይ ይተከላል ወይ ይነቀላል? በሠላማዊ ትግል ወይስ በትጥቅ ትግል ይነቀል? በምርጫ 2019ዓ/ም ምርጫ ብቻ ችግራችን ይፈታል ወይስ አይፈታም? የዘገነም ያልዘገነም እኩል አዘነ ነው ነገሩ!!!
ኮነሬል አብይ አህመድ ቀሪውን የአዲስ አበባ ከተማ ኢንቨስተሮች ምንም እንደይሰሩ በማድረግ የተለያዩ የከተማ ቦታዎችን ያለ አንዳች የማስተር ፕላን ጥናት ለፓርኮች፣ ለቤተመንግሥት፣ ኢሬቻ ወዘተ በመሸንሸን በኦሮሙማ የእጅ አዙር አገዛዝ በአዲስ አበባ ሠፍኖል፤-
(1) የጫካ ፕሮጀክት ቤተ-መንግሥት በ503 (አምስት መቶ ሦስት) ሄክታር መሬት ወይም 5030000 (አምስት ሚሊዮን ሠላሳ ሽህ ) ካሬ ሜትር መሬት የያዘ ቦታ ነው፡፡ ኮነሬል አብይ አህመድ ቤተ-መንግስታቸውን በ503 ሄክታር መሬት ላይ በማነጽ ላይ ይገኛሉ፡፡ የአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣን የ29 ኪሎሜትር የውስጥ ለውስጥ መንገድ ሠርቶል፡፡ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች የቤተመንግሥቱን ግንባታ እንዲያከናውን ውል ተሰጥቶታል፡፡ የቻይናው መንግሥታዊ የኮንስትራክሽን ኩባንያ ሲሲሲሲ ደግሞ ቅንጡ የሆቴል ግንባታዎች ‹ስካይ ቪው› ግንባታ ያከናውናል፡፡ የቻይና መንግሥትን ሃገሪቱን በዕዳ ነክሮ እያለ፣ ሰው ሰው ያልሸተተ ግንባታ የጫካው ፕሮጀክት እንዲያቆም ኢንባሲዎቹ በሚገኙበት ቦታ ሁሉ ማጋለጥ ያስፈልጋል፡፡ የጫካው ፕሮጀክት ሦስት ሰው ሰራሽ ሃይቆች በ ኢ ቶሎ ተቆራጭ በመገንባት ላይ ይገኛል፡፡ የጫካው ፕሮጀክት በምዕራቡ ዓለም የዲፕሎማቲክ ምንጮች 850 ቢሊዮን ብር የሚያወጣ ፕሮጀክት መሆኑን ሲገምቱ የውጪ ምንዛሪ የሚጠይቁ ከፍተኛ ወጪዎች እንዳሉበት ሙያተኞች ገልጸዋል፡፡ የኢትዮጵያ የገንዘብ ሚኒስቴር አህመድ ሸዴ፣ የኢትዮጵያ የገንዘብ ሚንስትር እዮብ ተካልኝ ቶሊና፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዢ ማሞ ምህረቱ አድርባይ ምሁራን በጦርነቱ የተጎዱ መሠረተ-ልማታቸው የወደሙ የትግራይ ፣አማራና አፋር ህዝብ ችግሮችን መቅረፍ በተገባቸው ነበር እንላለን፡፡ ምንጭ ጠቅላይ ሚንስትሩ የቤተመንግስት ፕሮጀክት ለሶስት ተቋራጮች ተሰጠ (ዋዜማ)/May 11, 2023
(2) ኢሬቻ ፕሮጀክት ሆራ ፊንፊኔ አዲስ ካርታ በአዲስ አበባ ማዘጋጃ ሲሰጠው፣ የመስቀል አደባባይ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ንብረት የነበረ ነባር ካርታ መክኖል
(3) የአዲስ አበባ የወንዝ ዳር ፕሮጀክት ከእንጦጦ ተራራ አካሎ አቃቂ ድረስ ሸፍኖ 56 ሳምሳ ስድስት ኪሎ ሜትር የክረምት ወንዞቹን ተከትሎ የሚፈሱ ሲሆን በበጋ ወራቶች ወኃው ይቀንሳል ብሎም ይደርቃሉ፣ በወንዞቹ ዳርቻ ያሉ አረንጎዴ ዕፅዋቶችን የሸፈነ ፕሮጀክት ባሻወልዴ ችሎት ከፓርላማ ፊት ለፊት አራት ኪሎ፣ ፒያሳ ያካትታል፡፡ የፕሮጀክቱ የመጀመሪያው ምዕራፍ ከእንጦጦ ተራራ በኩል ባንፒስ ድልድይ ያለው በቻይና መንግስት ሲሲሲሲ ኮንስትራክሽን ካንፓኒ እየተሠራ ያለ ሲሆን እስከ 2020እኤአ ያልቃል ተብሎ ነበር ሆኖም (55)በመቶ የደረሰ ነበር፡፡ በታላቁ የዳግማዊ ሚኒሊክ ቤተ-መንግሥት በአስናቀች መንደር ቦታው ብቻ እንጂ የድሮ ንዋሪዎች የሉም፣ ዘለቄታዊ ልማት ለማስቀጠል ተፈናቃይ ዜጎችን ህይወት የመኖሪያ ቤቶች መስራት የመሳሰሉትን ያላካተተ ሰው ሰው ያልሸተተ ልማት አሰኝቶታል፡፡
(4) የኮነሬል አብይ ኦህዴድ ብልጽግና መንግሥት የፓርኮች ግንባታ ጊዜውን ያላገናዘበ፣ ጥቂት የሥራ ዕድል የሚፈጥር፣ ጥቂት የገቢ ምንጭ ብቻ የሚያስገኙ ፣ በውጭ ምንዛሪ ያራቆቹ ፎፎቴዎች፣ ብልጭልች መብራቶች ኢኮኖሚውን አራቁቶት፣ የውጪ ብድር ከነወለድ መክፈል አቅቶቸው አገሪቱ ዋና ኃብት ተሸጦ የምንከፍልበት ጊዜ ላይ ደርሰናል፡፡ አቶ ልደቱ አያሌው ለኮነሬል አብይ መንግሥት እስከ 2019 ዓ/ም ምርጫ በሠላማዊ መንገድ እናውርደው ማለት ኮማ ውስጥ ያለን የሚሞት መንግሥትን መደገፍ ነው ፡፡ ኢኮኖሚውን ያላወቁ ፖለቲካውንም አያውቁ የሚባለው ለዚህ ነው፡፡ (ሀ) ለአንድነት ፓርክ አምስት ቢሊየን ብር ወጪ፣ (ለ) እንጦጦ ፓርክሁለት ነጥብ አምስት ቢሊየን ብር ወጪ፣ (ሐ) አድዋ ዜሮ ኪሎሜትር አራት ነጥብ ስድስት ቢሊየን ብር ወጪ፣ (መ) መስቀል አደባባይ ሁለት ነጥብ ስድስት ቢሊየን ብር ወጪ፣ (ሠ) ወዳጅነት ፓርክ ሁለት ነጥብ አምስት ቢሊየን ብር ወጪ፣ (ረ) ቢተወድድ ጎሹ ወ/ፃዲቅፓርክ መቶ አንድ ሚሊዮን ብር ወጪ፣ (ሰ) አንባሳደር ፓርክ አርባ ዘጠኝ ቢሊየን ብር ወጪ፣ እንዲሁም (ሸ) የአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት እድሳት ሁለት ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ብር ወጪ በጀት ተይዞላቸው የተገነቡ አይደሉም፡፡
(5) ኦሮሚያ ሚድያ ኔት ወርክ በ45000 (አርባ አምስት ሽህ) ካሬ ሜትር ቦታ ቦሌ እንብርት ደንበል ጀርባ ቦታ ተሠጥቶት ህንጻውን ገንብቶል፡፡
(6) አንድነት የመኪና ማቆሚያ ፕሮጀክት ዘጠን ሽህ ሜትር ካሬ ቦታ ላይ የተሠራ በ1.7 (አንድ ነጥብ ሰባት) ሚሊዮን ብር ወጪ
(7) ሃላላ ኬላ ደቡብ ክልል ዳውሮ ዞን በሦስት ቢሊዮን ብር ወጪ የተገነባ መዝናኛ ሎጂ ለትንግርት ነው፡፡ በሰቃ ሃይቅ፣ ጎርጎራ፣ኮይሻ ፓርክና ሎጂ ለቱሪስት መስብና ለውጪ ምንዛሪ ማግኛ ቢታሰብም በሃገሪቱ ውስጥ ሰላም አለመኖር አሳሳቢ ደረጃ ደርሶል፡፡ ኮነሬል አብይ እንደ ቱሪዝም ሚኒስቴር የሚተውነውና በየመዝናኛ ሎጂ የሚያድረው አዲስ አበባ ከተማ መፈንቅለ መንግሥት ፍራቻ ነው ይባላል፣‹አብይ ማደሪያ የለው› አዲስ አበቤ ሰዉ
(8) ጨበራ ጩርጩራ ብሄራዊ ፓርክ የዝሆን ዳና ሎጂ ደቡብ ክልል ዳውሮ ዞን ተሠርቶ ተመርቆል፡፡
(9) የሸገር ከተማ ፕሮጀክት፡- የኮነሬል አብይ የኦሮሙማ የእጅ አዙር አገዛዝ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ላይ ተቆርሷ የተሠጠ የሸገር ከተማ 1600 (አንድ ሽህ ስድስት መቶ) ስኩየር ኪሎሜትር ወይም 1600 000 000 (አንድ ቢሊዮን ስድስት መቶ ሚሊዮን) ካሬ ሜትር ቦታ ህገ-መንግሥቱን በጣሰ መንገድ ተዘርፎል፣ ህዝብ ያላማከረና 600000 (ስድስት መቶ ሽህ) ሰዎችን በግፍ ያፈናቀለ የኦሮሙማ አገዛዝ ያለአንዳች ማስተር ፕላን ጥናት በኦህዴድ ብልጽግና ዘረኛና ተረኛ የኦሮሙማ ሥርዓት የከተማ ህዝብ ንቅለ ተከላ የተከናወነበት ዘመን ነው፡፡ ማንነት ተኮር በአማራነታቸው ምክንያት የተፈላቀሉ ነበሩ፣ ከኦሮሞ ገበሬዎች በማፈናቀሉ የተነሳ ኮነሬል አብይና ሽመልስ አብዲሳና አዳነች አቤቤ ተቃውሞ ገጥሞቸው ነበር፡፡ ኦሮሞ ያልሆኑ ንዋሪዎችም በተለይ አማራዎች የኦሮሞ አስተዳደር ድብቅ አጀንዳ የአዲስ አበባን ከተማ ወደ ኦሮሚያ ለማካተትና ለመሰልቀጥ የተወጠነ መሆኑን በሸገር ከተማ ምስረታ ማግስት ህገወጥ ተብለው የፈረሱት የአማራ ቤቶች በመሆናቸው ተቃውሟቸውን አሰምተው ነበር፡፡
የሸገር ከተማ ኩታ ገጠም የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ህዝብን ሳያማክር በኦክቶበር 2022 እኤአ የሸገር ከተማ መሠረተ አዲስ የከተማ ማዕከል ስትሆን የአዲስ አበባን ዙሪያ ገባ ተከትላ የተዋቀረች ከተማ ናት፡፡ የሸገር ከተማ ኩታ ገጠም መሬት 1600 (አንድ ሽህ ስድስት መቶ) ስኩየር ኪሎሜትር ስፍት አላት፡፡ Covering an area of over 1,600 square kilometers, Sheger City encompasses six Oromia towns.የሸገር ከተማ በስድስት ክፍለ ከተሞች የተመሠረተች ስትሆን እነሱም ሰበታ፣ ቡራዩ፣ ለገጣፎ፣ለገዳዲ፣ ሱሉልታ፣ ገላን፣ እና መናገሻ ያካትታሉ፡፡ የሸገር ከተማ አዲስ አበባን ዙሪያዎን ከበዋታል፡፡
የሸገር ከተማ ምሥረታ የተረጋገጠው ከኦግስት 2022 አኤአ በኃላ የአዲስ አበባ ከተማና በፍንፍኔ አካባቢ ያሉ የኦሮሚያ ልዩ ዞን ወሰን በተካለለ ጊዜ ነበር፡፡ ወሰኑ ግልጽ ባለመሆኑ ምክንያት ግጭትና አለመረጋጋት አስከትሎ ነበር፡፡ ኮነሬል አብይ አህመድ ቤተ-መንግስት አንድ ትሪሊየን ብር የግንባታ ወጪና በአዲስ አበባ ዙሪያ አዲስ የሸገር ከተማ ለመመሥረት የሚወጣ ሌላ ትሪሊዮን ብር በአስቸኳይ እንዲቆም በማስደረግ ለሚሊዮን ተፈናቃዬች ህይወትን መታደግ፣ በትግራይ በአማራና አፋር ክልሎች የወደሙ መሠረተ-ልማቶች በተለይ የጤና፣ የትምህርት፣ የመብራት፣ የውኃ፣ የስልክ አገልግሎቶች ቅድሚያ እንዲሠጣቸው ማድረግና በህዝቡ ላይ የደረሰውን የኑሮ ውድነት ለመቅረፍ መንግሥታዊ ድጎማዎች ማድረግ፣ ግብርና ታክስ መቀነስ፣ በአዲስ አበባ ከተማ የቤቶች ማፍረስ ማስቆም አንገብጋቢ የህዝብ ጥያቄዎች እሰከ 2019 ዓ/ም ምርጫ ድረስ በሠላማዊ መንገድ ታገሉ እንደማለት ነው፡፡
የኦህዴድ ብልጽግና የኦሮሙማ መስፋፋት በሁሉም ክልሎች ድንበር በኩል የድንበር ግጪት ከሱማሌ፣ አማራ፣ ሲዳማ፣ ደቡብ ህዝቦች፣ ጋምቤላ፣ ቤኒሻንጉል፣ አዲስ አበባ፣ ድሬዳዎ ወዘተ ህዝብ ጋር ጦርነት በመጫር ላይ ይገኛል፡፡ የኦሮሞ ምሁራን ይሄንን የግዛት የመስፋፋት ጥያቄ የአስራስድስተኛውና የአስራሰበተኛው ዘመን ጥያቄ መሆኑን በማጤን ለኦሮሞ ህዝብ ጠላት አታብዙበት እንላለን፡፡ የኦሮሞ ህዝብ ከሌሎች ኢትዮጵያዊያን ወገኖቹ ጋር በሠላምና በህብረት እንዲኖር ማድረግ የስልጣኔ መንገድ በመሆኑ መምከር ይጠበቅባችሆል፡፡
መደምደሚያ
ከኮነሬል አብይ የኦህዴድ ብልፅግና መንግሥት ከሥልጣን ከተወገደ በኃላ ኢትዮጵያ ትኖር ይሆን ወይ? የሚለው የኢትዮጵያ ህልውና መንግሥት የለሽነትና ወደ ሦስትና አራት መንግስትነት መከፋፈል ይከተላል? የሚል ድምዳሜ አስቀምጠዋል፡፡ አቶ ልደቱ አያሌው አሁን ያለው የኮነሬል አብይ መንግስት ሰባ በመቶ የሚሆነውን የኢትዮጵን ግዛት እንደማይቆጣጠር አልተገነዘቡም፡፡ ኮነሬል አብይ ፋሽታዊ አገዛዝ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ወጣቶች ህይወት መጥፋት ተጠያቂ ሲሆን ለሃያ ስምንት ቢሊዮን ዶላር መሠረተ-ልማቶች ውድመት ተጠያቂ መንግሥትን ኮነሬል አብይ አህመድ፣ አዳነች አቤቤና ሽመልስ አብዲሳ ሰው ሰው ያልሸተተ ልማት ለመዐት ብለን ለማስቆም መታገል ግድ ይለናል እንላለን፡፡ በኮነሬል አብይ አገዛዝ የጦርነት ኢኮኖሚው የማክሮና የማይክሮ ፖሊሲ ውድቀት ለስድስት አመታት ቀጥሎል ዛሬ ሃገሪቶ ብድርና ወለድ መክፈል ከማይችሉ ተርታ መመደቦ ይታወቃል፡፡ የውጭ ምንዛሪ እጦት፣ የውጭ ንግድና የገቢ ንግድ ሚዛን መዛባት፣ የመሳሰሉትን አንኮር የኢኮኖሚ ትንተናዎትን መደምደሚያ አድርገውታል፡፡ አቶ ልደቱ አያሌው ኮነሬል አብይ አህመድን የኢትዮጵ ህዝብ ‹‹አባይ ማደሪያ የለው፣ ግንድ ይዞ ይዞራል!!!›› የሚለውን ‹‹አብይ ማደሪያ የለው፣ ግንድ ይዞ ይዞራል!!!›› ለ2019 ዓ/ም ምርጫ በሠላማዊ መንገድ እንታገለው ማለት ግን የትኛው ምርጫ የትኛው ዴሞክራሲ እንደማረከህ ማሰብ ምጽአተ ህልውና ይሆንብሃል፡፡
(1) የትግራይ መንግሥት ቲዲኤፍ የትግራይ መከላከያ ኃይል በመቶ ሽህ የሚቆጠር የትግራይ ሠራዊት ይዞ ክልሉን በመምራት ላይ ይገኛል
(2) የአማራ መንግሥት ፋኖ ብአዴን/ኢህዴን ባንዳ ካድሬዎች አስወግዶ ህዝባዊ ኃይል እራሱን እያስተዳደረ፣ ሁለት መቶ ሴቶችን የደፈረ መከላከያ ሠራዊት ዳግም ወንጀል እንዳይሠራ ብረት በማንሳት በሚሊዮን የሚቆጠር ህዝባዊ ኃይል ገንብቶል፡፡ የፋኖ አመራሮች በዩኒቨርሲቲ አስተማሪዎች ፕሮፌሰሮች፣ ዶክተሮች፣ ኢንጅነሮች፣ ወዘተ ያሉበት ስብስብ ሲሆኑ የሃገሪቱን የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ፣ የማህበራዊ ጉዳዩችን በተመለከተ ፍኖተ ካርታ አዘጋጅተው ለህዝብ የሚያሰራጩበት ቀን ይጠበቃል በፋኖ ውስጥ የተለያዩ ብሔር ብሔረሰቦች ጋር አብረው ለመሥራት የሚደረገው ውሥት ሚስጢራዊ ግንኙነት ይፋ የሚሆንበት ቀን ይጠበቃል፡፡ የፋኖ ድርጅት ለዘመናዊ ዴሞክራሲዊ አስተሳሰብ ለሲስና ግለሂስ፣ ለውስጣዊ ዴሞክራሲ ማበብ ጠንክረው መስራት ከህወሓትና ኦህዴድ መንግሥት አሠራር የተሸለ እንደሚሆን ከህዝባዊ ስብሰባዎች መረዳት ይቻላል፡፡ ፋኖ ህብረ- ብሄር ዜጎች በሃገሪቱ ጉዳይ ጥናታዊ ፁሁፍ እንዲያወጡ ማበረታታት ይጠበቅበታል፡፡
(3) የኦሮሚያ መንግሥት የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት የኦህዴድ ባንዳ ካድሬዎችን አስወግዶ ከመከላከያ ሠራዊት ጋር በመፋለም ላይ ይገኛል፡፡
(4) ልዩ ኃይል የፖሊስ ሠራዊት ያላቸው የሱማሌ፣ አፋር፣ ሐረሪ፣ ቤኒሻንጉል፣ ጋምቤላ፣ ሲዳማ፣ ደቡብ ህዝብ፣ መንግሥቶች ከትግራይ፣ አማራ፣ ኦሮሚያ ጋር በማበር ህብረ-ብሔር የሽግግር መንግሥት አይመሰርቱም ብሎ አለማመንና 2016ዓ/ም ወደ 2019ዓ/ም ለማሸጋገር መሞከር ‹‹የደንቆሮ ለቅሶ መልሶ መላልሶ ›› እያለ ኢትዮጵያ ህዝብ ትግል የማይዋጥ የማይተፋ የጉሮሮ ላይ አጥንት ናት እንላለን፡፡ በ2016 ዓ/ም ኮነሬል አብይ አህመድ መንግሥት ይወገዳል፡፡ ለአንተም ባይዋጥልህም እነሆ ኢኮኖሚ እንልኃለን፡፡ የኦሮሙማን ፍኖተ ካርታ በኢንዱስትሪ ፣ግብርና አገልግሎት ዘርፍ፣ (በባንኪንግና ፋይናንስ ዘርፍ) ዘ-ሐበሻ ድረገፅ ኢኮኖሚ አምድ ውስጥ ገብተህ አንብብ!!!
የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ!!!