>

ፀረ-ባንዳ/ከሀዲ ልዩ ግዳጅ (ኦፐሬሽን) ባስቸኳይ!!! 

ፀረ-ባንዳ/ከሀዲ ልዩ ግዳጅ (ኦፐሬሽን) ባስቸኳይ!!! 

ከይኄይስ እውነቱ

በዐዲስ ድምፅ ሚዲያ ሐሙስ ታኅሣሥ 18 ቀን 2016 ዓ.ም. በተላለፈው መደበኛ መርሐ ግብር ላይ የዐምሐራ ሕዝብ ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያ ሕዝብ ባጠቃላይ የጠላት ጠላት የሆነው ብአዴን ላይ የህልውናው ትግል ልዩ ትኩረትና ቅድሚያ ሰጥቶ፣ በዐምሐራ ፋኖና በሕዝቡም በኩል ቅድሚያ ተሰጥቶት በልዩ ኦፐሬሽን ዘመቻ ሊካሔድበት እንደሚገባና ሌሎችም ለተመሳሳይ ዓላማ የቆሙ ሚዲያዎች ቅድሚያ ትኩረት ሰጥተውት እንዲሠሩበት ወንድማችን አበበ በለው ያደረገው ጥሪ እንኳን የህልውና ፍልሚያ እያደረገ ላለው ዐምሐራ፣ ከፋሺስታዊው ሥርዓት ተገላግሎ ለሁላችን የሚበጅ የእኩልነት ሥርዓት የሚናፍቅ ኢትዮጵያዊ ሁሉ በሙሉ ልቡ ሊደግፈው የሚገባ አስቸኳይ ጥሪ ነው፡፡ ይህ ጥሪ ዘግይቷል ከሚባል በቀር በእጅጉ አስፈላጊ ነው፡፡ በመሆኑም የትግል ሚዲያዎች በሙሉ ትኩረታቸውን ከዚህ አንፃር መቃኘት ይኖርባቸዋል፡፡ ‹ትንተናው› ለጊዜው ይቆየንና ዋና ሽፋናችን ቀዳሚ ጠላታችን ብአዴን ለህልውና ትግላችን በጭራሽ ሥጋት የማይሆንበት ደረጃ እስከሚደርስ ምድር ላይ ለሚካሔደው ትግል አስተማማኝ ድጋፍ መሆን ይኖርበታል፡፡

የዚህ አስተያየት አድራሽ ወንድማችሁ አሁን በይፋ ጦርነት ሳይታወጅብን ከወያኔ ዘመን ጀምሮ፣ ከዚያም በርጉም ዐቢይ ፋሺስታዊ አገዛዝ በገፍና በግፍ ኦሮሚያ በተባለው የዐምሐራ ቄራ ስንታረድ ስለዚህ ጥላ ቢስ ጠላት የተሰማኝን ማሳሰቢያና ማስጠንቀቂያ ያለመታክት አድርሻለሁ፡፡ እነዚህ የአእምሮ ድኩማኖች ‹ሰው› ለመሆን ባይታደሉም በቅጥረኝነት ለሚፈጽሙት ክፋት ግን ሌት ተቀን  እንደሚሠሩ ምስክሩ ርጉም ዐቢይ በሁሉም ግምባር ያጣውን ጦርነትና አንድ ሐሙስ የቀረውን አገዛዝ እስትንፋስ ለመስጠት የሚያደርጉት መሯሯጥ በቃላት ለመግለጽ የሚያስቸግርና ንዴትን ሁሉ የሚያስጨርስ ነው፡፡ ርጉም ዐቢይ በዐምሐራ ግዛቶች ብቻ ሳይሆን አራት ኪሎም ቢሆን አለሁ የሚለው በነዚህ በጣት በሚቆጠሩ ምናምንቴዎች ሲሆን፣ ‹ከየቆሻሻ መጣያው› ተለቃቅመው የተሰባሰቡ፣ በእኛ ዝምታ ዕለት ከዕለት እየተንሠራፉ ከራሳችን ሕዝብ ሠራዊት መልምለውና አሠልጥነው ሲወጉን፣ የኦነግን ጦር በምሪት አምጥተው ንጹሐንን በከባድ መሣሪያ ሲያስፈጁ፣ እናቶቻችንን እና እኅቶቻችንን ሲያስደፍሩ፣ በንጹሐን ወገኖቻችንን በሰው አልባ አውሮፕላን (ድሮን) የዘር ፍጅት ሲያስፈጽሙ፣ የገበሬዎቻችንን የእህል ክምር በማሳ ላይ ያለውን ጭምር እንዲቃጠል ሲያደርጉ÷ ንብረት አስወድመውና አስዘርፈው ሲፈነጩ፣ የገዛ ሕዝባችን አካል የሆኑትን የአገውና ቅማንት ወገኖቻችን መካከል ጥቂቱን በገንዘብና በጥቅማ ጥቅም እያማለሉ ክፍፍልና ልዩነት ለመፍጠር ሲያሴሩ፣ ከዛም አልፈው ተርፈው በየአዳራሹ ሔደንላቸው እየሰበሰቡን በከፍተኛ ንቀት የጦርነቱን ምድር ሰላም ነው፣ በየዩኒቨርስቲው ባሰቀመጧቸው ባንዳዎች አማካይነት ለተማሪ ጥሪ በማድረግ አፍነው ለመውሰድና ሕዝባቸውን መልሰው እንዲወጉ ለማድረግ ሲዘጋጁ፣ አልፈው ተርፈው የዐዲስ አበባው ሳያንስ ዐምሐራው ባሕር ዳር ከተማ እንዳይገባ ሲከለክሉ፣ ለልማት እየሠራን ነው እያሉ ሲያላግጡብን የነሱ የባርነት መንፈስ ተጋባብን ወይ የሚያስብል ነው፡፡ ምን ነካን ጎበዝ!? ጀግኖቻችን ሕይወታቸውን ያለ ስስት እየገበሩ? በተሰማሩበት ዐውደ ወጊያ ሁሉ አምላክ ድል እያጎናጸፋቸው የግፉ ምንጭ የሆነውን ብአዴን ጨርሶ ማድረቅ እየተቻለ ለምን ቀዳሚ የትኩረት አቅጣጫችን ሳይሆን ቀረ? የርጉም ዐቢይ ፈሪና ዓላማ የለሽ ጦር እኮ ያለ ‹አሽከሮቹ› የትኛውንም ግዳጅ መፈጸም አይችልም፡፡  ታዲያ እንዴት የነዚህ ምውታን ስብስብ መጫወቻ እንሆናለን? የኦነግና የወያኔ ንቀት ሳያንስ እንዴት ለኹለቱ ያደሩ ባሮች መቀለጃ እንሆናለን? በእጅጉ ያማል ያሳፍራልም፡፡ እነዚህ ደናቊርት የሚማሩ ባለመሆናቸው÷ አእምሮ ኖሮአቸውም ስለማያውቅ የሚያስተምር ርምጃ ሳይሆን የማያዳግም ርምጃ ወስዶ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ማስወገድ ያስፈልጋል፡፡

ብአዴን ስለሚባሉ የምድር ጉዶች ስናስብ በተረጋጋ አእምሮ መናገርም ሆነ መጻፍ ይከብዳል፡፡ አገር ምን ዓይነት ደዌ ነው የተጣባት? ብአዴንን ለመሆን ከሰው ተፈጥሮ መውጣትን ይጠይቃል፡፡ አንዳንዴ ስሕተት ጉድለት ከሌለበት ፍጹም ከሆነው÷ ሥራው ጥበቡ ከሕሊና በላይ ከሆነው ፈጣሪ ጋር ውስጤ ይሟገታል፡፡ እንዴት አድርገን  ብንበድለው ይሆን እነዚህን ሥጋ የለበሱ አጋንንት ያውም በተበደለው፣ በተገፋው፣ አማኝ በሆነው፣ ሳይተርፈው ‹ትዳሩን› እንኳን ከሚሰጠው፣ አገሩን ከሕይወቱ ለሚያሰቀድመው፣ ጨውነት÷ እውነት÷ ፍትሕና ሥርዓት ገንዘቡ ከሆነው፣ ጦሙን እያደረና ባዶ እግሩን እየሔደ አገርን÷ ታሪክን÷ ዕሤትን÷ ቅርስና ባህልን ካቆየው የዐምሐራ ሕዝብ መካከል ሆነው ቁም ስቅሉን እንዲያሳዩት ዕዳ ፍዳውን እንዲያፀኑበት የፈቀደው እላለሁ፡፡ ቤተ ክህነቱም ቤተ መስጂዱም ለፋሺስታውያን አገዛዞች በማደራቸው ይሆን? እምነታችን የማስመሰል ሆኖ ሁላችን ተካክለን ስለበደልን ይሆን? ብዙ የሚጠበቅበት ፊደል ቈጠርሁ፣ ተማርሁ፣ ሀብት ንብረት አለኝ የሚለው እንደማያገባው ጥጉን ይዞ የደሀ ልጅ ሕይወቱን ገብሮለት ነፃ አውጪ መጠባበቁን ልማድ በማድረጉ ይሆን? በቀደም በዚሁ በዐዲስ ድምፅ ሚዲያ አንድ ዐዲስ አበባ ያለ ወጣት ቱጃር በርሱና በቤተሰቡ ሕይወት ስለደረሰበት ሥጋትና በንብረቱ ላይ ስላጋጠመው ውንብድና ሲናገርና በመጨረሻም ለዚህ የዳረገውን ‹መንግሥት› ተብዬውን የማጅራት መቺዎች ቡድን ሲማፀን ተናደድሁም አፈርሁ፡፡ ወንድሜ ማለቃቀሱን አቁማችሁ ጊዜው ሳይረፍድ አንተና ብጤዎችህ በሀብታችሁ (እንዴት እንዳገኛችሁት የሚያውቀው ‹ባለቤቱ› እና እናንተ ናችሁ) ራሳችሁንም ሆነ አገርን አድኑበት፡፡ ርጉም ዐቢይ ሀብታችሁን ብቻ ሳይሆን ቆዳችሁን ከመግፈፍ አይመለስም፡፡ 

እናንተዬ ችግርግር ያለ ችግር ውስጥ እንዳለን ይሰማኛል፡፡ መውጫ ግን አለው፡፡ የእነዚህ ባንዶች መቀመጫ ጥቂት የዐምሐራ ከተሞች በመሆናቸው ለዚህ የሚመጥን ልዩ ኦፐሬሽን ያስፈልጋል፡፡ እዚህ ላይ ዝርዝር ውስጥ መግባት ባያስፈልግም ሁሉንም አማራጮች ያለ ርኅራኄ መጠቀም የግድ ነው፡፡ ውጊያ ላይ የተሰማሩት ጀግኖች ፋኖቻችን ብቻ ሳይሆኑ በአራቱም ክፍላተ ሀገራትና ከዛም ባሻገር የሚገኝ መላ የዐምሐራ ሕዝብ እነዚህን ባንዳዎች ባሉበት የማፅዳት ሥራ ይጠበቅበታል፡፡ እነሱን ሳንቀንስ ብሎም ሳናጠፋ አንድ ቀን መባከን ያለበት አይመስለኝም፡፡ የትግል ሚዲያዎቹም ይህ ልዩ ኦፐሬሽን እንዲሳካ ከመቼውም ጊዜ በላይ በንቃትና ትጋት መሥራት ይጠበቅባቸዋል፡፡ በቀጣይም የዘገባዎቻቸው አንዱና ዋናው ክፍል ባንዳዎችን በማፅዳት ረገድ የማጋለጥ ሥራና ስለሚወሰደው ርምጃ የሚመለከት ይሆናል፡፡ አግድም አደጎችን በሚመለከት ለምንናገረውና ለምንጽፈው ቋንቋ ሁሉ ሸሽተንና ተሽኮርምመን አንዘልቅም፡፡ ጀግኖቻችን ለልዩ ኦፐሬሽኑ ስትራቴጂና ስልት በመንደፍ በኩል ብቃቱ እንዳላቸው ብተማመንም በውስጥም በውጭም የምትገኙ ወታደራዊ ጠበብቶች ምክርና እገዛ እንዳይለያቸው እኔም የበኩሌን ጥሪ አቀርባለሁ፡፡

ድል ለዐምሐራ ፋኖ!!! ድል ለኢትዮጵያ!!!

ማሳሰቢያ፤ በዚህ ጽሑፍ ባንዳ/ከሀዲ የተባለው ብአዴን የሚባለውን ቀዳሚ የጠላት ስብስብ ነው፡፡ ፋሺስታዊው የርጉም ዐቢይ አገዛዝ የተለያዩ ማጭበርበሪያ ስሞችን ቢጠቀምም ማንነቱ ላይ የሚያመጣው ለውጥ የለም፡፡ ብአዴን በሚባለው ቆሻሻ ድርጅት ውስጥ የነበሩና ለሕዝባቸው በጎ ሥራ ሠርተው ያለፉ (ለትግሉ ምልክት የሆኑ ጭምር)  በጣት የሚቆጠሩ ግለሰቦች ከሕዝብ ጋር ባንድነት ለመቆም ሲወስኑና ይህንንም በተግባር ሲያስመሰክሩ በመንፈስም ሆነ በአካል ብአዴን አለመሆናቸውን አረጋግጠዋል፡፡ በመሆኑም እነዚህን ጥቂት የሕዝብ ልጆች አይመለከትም፡፡

Filed in: Amharic