የሥርዓት ለውጥ ለኢትዮጵያ!!! ወይስ የማያባራ የህዝብ እልቂትና የዘር ፍጅት?
ጊዜው አሁን ነው!!! የአራት ኪሎው ቌጥኝ በመንዝና ግሼ!!!
(ክፍል አንድ)
ፀ/ት ፂዮን ዘማሪያም (ኢት-ኢኮኖሚ /ET- ECONOMY)
REGIME CHANGE IN ETHIOPIA
‹‹ባትዋጋ እንኳን በል እንገፍ እንገፍ፣
የአባትህ ጋሻ ትኃኑ ይርገፍ!!!››
‹‹በኢትዮጵያ አንድ ሚሊዮን ወጣቶች በማያባራ ጦርነት ያስጨረሰውና ሃያ ስምንት ቢሊዮን ዶላር የመሠረተ–ልማቶች ውድመት ያስከተለ ከሃያ ሚሊዮን ህዝብ በላይ ለርሃብ አደጋ ያጋለጠ፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ህዝብ ከቀያቸው ተፈናቅለው የሚሰቃባት ኮነሬል የአብይ መንግሥት አገዛዝ በቃ!!!››…የኢትዮጵያ ህዝብ ከኦህዴድ ብልፅግና ከኦነግ ሸኔ የኦሮሙማ ስልቀጣ ለመዳን በህብረት መታገል ጊዜው አሁን ነው!!!…የፋኖ አንደኛ ተገዳዳሪ ኃይል ሆኖ መውጣት፣ ለመላ ኢትዮጵያ አንድነት ኃይሎች ታላቅ የምሥራች ነው፡፡ ኢትዮጵያን ለመታደግ ህብረ-ብሔር ‹‹የሽግግር መንግሥት መመስረቻ ጊዜው አሁን ነው!!!››
- ‹‹እኔ አልመለስም፡፡ ሻማው ተለኩሶላችኃል ሻማው እንዳይጠፋ!!!›› ፕሮፌስር አስራት ወልደየስ
- ‹‹የአማራ ጥያቄ የዴሞክራሲና እና የህልውና ነው፡፡ አማራ በክልሉ ውስጥ ሆኖ የህልውና ችግሮች አሉብን!!!››ብ/ጀ አሳምነው ፅጌ
- ‹‹በአማራ ህዝብ ላይ የተከፈተው ዘመቻ በአስቸኳይ ይቁም!!!›› ሻለቃ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ
- ‹‹የሽግግር መንግሥት መመስረቻ ጊዜው አሁን ነው!!!››….‹‹ዋና ትግላችን ከአክራሪ የኦሮሞ ብሔርተኞች ጋር ነው!!!›› እስክንድር ነጋ
- ‹‹የአሸባሪው ህወሓት መመታት ለኢትዮጵያ የሠላም ዋስትና ነው!!!›› ብ/ጀ ተፈራ ማሞ
- ‹‹ህወሓት በወልቃይት ተቀበረ!!!››…‹‹ለፌዴራል መንግሥቱ እጅ አልሰጥም!!!››ኮለኔል ደመቀ ዘውዱ
- ‹‹ከኮሮና ከሱዳን ሠራዊት በላይ ፋኖ እንዴት አሰጋ!!!›› መሣፍንት ተስፉ
- ‹‹የአማራ ህዝብ ታሞ ኢትዮጵያ ጤናማ ልትሆን አትችልም!!!››…..‹‹ከዚህ በኃላ ማንም ዱላ የያዘ ሁሉ እንደ ከብት አይነዳንም!!!››…ዘመነ ካሴ
የአራት ኪሎው ቌጥኝ!!! ሰውየው የሥርዓት ለውጥ (Regime Change) አዋላጂ ነው፡፡ ሰውዬው ለነጻነት፣ ለእኩልነትና ሉዓላዊነት ሞች ነው! እናት ሃገሩን ይወዳል፡፡ በንጉሱም ዘመን ‹ለመሬት ለአራሹ›ና ‹ለህዝባዊ መንግሥት› ታግሎ ባላባታዊውን ሥርዓት መንግሎል፡፡ በደርግ ወታደራዊ አገዛዝ ዘመንም በሻለቃ መንግስቱን አገዛዝ ላይ የመፈንቅለ መንግስት የውጭ አስተባባሪ ሆኖ ከሃገረ አሜሪካ ወደ ሱዳን ከአውሮፕላን ወርዶ፣ በመኪና ተጭኖ፣ በፈረስና በቅሎ ገስግሶ በእግሩ አቆራርጦ፣ በኤርትራ በርሃ ከሻብያ ጋር ይደራደር የነበረ የቁርጥ ቀን ልጅ ነው፡፡ ለጎደኞቹ ሞች ነው፣ ለመፈንቅለ መንግስት ጠንሳሾቹ ጀነራል መኮንኖች ‹‹ቃል ለምድር ለሠማይ!!!››ብሎ ኤርትራ በርሃ ወርዶላቸዋል፡፡ ኮነሬል መንግሥቱ ሻለቃ ዳዊት የመፈንቅለ መንግስቱ ጠንሳሽ፣ ኤርትራ በርሃ መግባታቸውን ያወቁ ጊዜ እንጥላቸው ወርዶ፣ ለወራት መነጋገሪያ ጉሮሮቸው ተዘግቶ የኢትዮጵያ ህዝብ ጆሮ እፎይ ብሎ ነበር፡፡ ኮነሬል መንግሥቱ ሻለቃ ዳዊት ከኤርትራ በረሃ ወደ ኢትዮጵያ በረሃ ገብተዋል የተባሉ ጊዜ ክፍለግዛት መዘዋወር አቁመው ነበር ይባላል፡፡ ይህ ድርሰት የመሰለህ ኮነሬል መንግሥቱ ፍርሃት ‹የአራት ኪሎው ቆጥኝ መጣ› እውነተኛ ታሪክ ነው፡፡ ኮነሬል አብይ ‹ፋኖ መጣ!!! ፋኖ መጣ!!!› ብለው የጨፈሩትን ፘጮች ጩህት ጆሮው ጠልቆ፣ ለወራት የእራስ ምታት ህመም ገጥሞት በበሻሻ ቅቤ እርግብግቢቱ አናቱ ላይ እየተቀባ የዳነ ይላሉ ቲክቶክሮች፡፡
ሻለቃ ዳዊት የሐረር ሚሊተሪ አካዳሚ ምሩቅ፣ በህግ ዲግሪ ከአዲስአበባ ዩኒቨርሲቲ፣ ማስተርስ ኮሎንቢያ ዩኒቨርሲቲ፣ የኤርትራ አስተዳዳሪ፣ የአደጋና መከላከያ ኮሚሽነር፣ የውጭ ጉዳይ ምክትል ሚኒስትር፣ የርዋንዳ ጀኖሳይድ አጣሪ ዳይሬክተር፣ ሻለቃ ዳዊት በደሙና በብዐወወ ቀለሙ ኢትዮጵያዊነቱንና አማራነቱን የመጀመሪያውን ‹አንድ አማራ› ድርጅት መስራችነቱ፣ አሁንም ትንታግ ወጣቶቹ ‹አንድ አማራ› በእውን ያቆሞ ተከታዬች አፍርቶል፣ የታሪክ ተተኪነትን ለመጭው ትውልድ እውነተኛ ታሪክን የማስተላለፍ እዳ አለባቸው እንላለን፡፡ ዳክተር ዳዊት በዓለም የታወቁ መፅሃፎቹ ውስጥ በ(Red Tears) ጦርነት ፣ርሃብና የኢትዮጵያ አብዮትን የቀይ ሽብርን፣ የኮነሬል መንግሥቱን ፋሽስታዊ ስርዓት በማጋለጥ አገር ጥሎ የወጣበትን እውነተኛ ታሪክ ተርኮል(Eskedar) የአማርኛ ስነፁሁፍ (What A Life) የህይወት ታሪክና የኢትዮጵያን፣ አፍሪካንና የዓለም ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቶች ወርቃማ ዘመን ተረኮል፡፡ ሻለቃ ዳዊት የአፍሪካ ኢንስቲቲት ስትራቴጂክ የደህንነት ጥናት (The Africa Institute for strategic and security studies) ዋና ዴሪክተር ሲሆኑ በእስክንድር ነጋ የሚመራውን የአማራ ህዝባዊ ግንባር የውጪ ጉዳይ ኃላፊ በመሆን የውጭውን ትግል በዲፕሎማሲያዊ የዳበረ እውቀታቸው በአጭር ጊዜ የአማራ የዘር ፍጅት እንዲታወቅ በማድረግ፣ የጎጃም፣ የጎንደር፣ የሸዋና የወሎ ፋኖ ህብረት እንዲፈጠር የበኩላቸውን ሚና እየተጫወቱ ይገኛሉ፣ የፋኖ የአማራ ህዝባዊ ሰራዊት፣ ኃይልና ግንባር ወዘተ ሌሎችም ተጨምረው በጋራ ከመሥራት ውጪ የአማራ ህዝብ ትግል ሊኮላሽ አይገባውም፣ በትግል ወቅት ዴሞክራሲያዊ አሰራር ይኖራል ብሎ መጠበቅ አዳጋች በመሆኑ እስክንድር ነጋ ትግሉን ለማፋጠን ብሎ ‹‹የአማራ ህዝባዊ ግንባር›› ዘመነ ካሴ ‹‹የአማራ ህዝባዊ ኃይል›› ብለው ሁሉንም ፋኖ ሳያማክሩ መስርተውት ቢሆን እንኳን ትግሉን አቀጣጥለው የኮነሬል አብይ መንግስትን ለማርበድበድ የተጠቀሙበት ቴክኒክ መሆኑን በመረዳት ውጪ በእኛ ድርጅት ሥር ግባ፣ አትግባ የሚል ሹኩቻና ጠብ መቀስቀስ የለበትም፡፡ የአማራ አመራሮች ትግሉ ተጠናቆ ለሥልጣን እስኪደረስ ድረስ ማን በህይወት እንደሚኖርና እንደማይኖር ስለማይታወቅ ገና ከጅምሩ ለስልጣን መጣላት አይመጥናችሁም፡፡ የሻብያ፣ የወያኔ፣ የኢህአፓ፣ መኢሶን ወዘተ በጊዜው አመራር የነበሩ ብዙዎቹ ከስልጣን መንበሩ ስይደርሱ በክብር እንደተሰው የታሪክ ድርሳናት ዘግበዋል፡፡ የአማራ ፋኖ የሥልጣን መንበሩን ለመላ ኢትዮጵያዊያን ለማካፍል፣ ህብረ ብሔር የሽግግር መንግስት ለመመስረት እያለመ፣ በጎጃም ፣ ጎንደር፣ ሸዋና ወሎ አንድ የአማራ ወታደራዊ እዝ መካተት የአማራን ህዝብ ትግል ያፋጥነዋል፡፡ በኮነሬል አብይ ፋሽስታዊ ፀረ አማራ ጦርነት መጀመሪያ የአማራን ህዝብን ህልውና እስካልን ድረስ ስለምን ወንድም በወንድሙ ላይ የቃላት ጦርነት ይሠብቃል!!! የቃላት ጦርነት ወደ ወንድማማቾች ጦርነት እንዳይሸጋገር፣ የኮነሬል አብይ ስውር እጂ ክፍፍሉን በማስፋት ገንዘብ በመርጨት፣ የሰላዬች መጫውቻ ከመሆን ያድናችሁ፡፡ የተራበው የኢትዮጵያ ሃያ ስድስት ሚሊዮን ህዝብ የእናንተን መምጣት ይናፍቃልና፣ አደራ እንላለን፡፡ የፕሮፊሰር አስራት ወልደየስ ‹‹የመላው አማራ ድርጅት›› መአከላዊ ኮሚቴና መስራች እስክንድር ነጋ የጥንት የጠዋቱ የአማራ ህዝብ ታጋይ የነበረ መሆኑን የታሪክ መዛግብት ያትታል፡፡
እስክንድር ነጋ የህወሓት ኢህአዴግ የመለስ ዜናዊን የግፋ ዘረኛ አሰተዳደር በአራት ጋዜጦቹ ‹ኢትዩጲስ›፣ ‹አስኳል›፣ ‹ሳተናው› እና ‹ምኒልክ› ለህዝብ በማስነበብ ለኢትዮጵያ ጋዜጠኞች ፋና ወጊ ጋዜጠኛ በመሆን ዓለም አቀፍ ሽልማቶች ተበርክቶለታል፡፡ እስክንድር ነጋ ከእስር ቤት ሆኖ ‹‹ደብዳቤ ከኢትዮጵያ ጉላግ›› ብሎ የፃፈው በአሜሪካ በኒው ዮርክ ታይምስ ጋዜጣ ላይ ወጥቶ ነበር፡፡ የህወሓት ኢህአዴግ መንግሥትን ኢ–ዴሞክራሲዊ አገዛዝ፣ ህገ–መንግሥቱን አንቀፆች ዝግንትሉን በመዘርገፍ፣ የብሔር–ብሔረሰቦች ፊዴራላዊ አገዛዝ የዘር ጉልቻ በመፈንቀል፣ የመንግስትን ሶስት ጉልቻ በመናድ፣ ሙስናን በማጋለጥ፣ ስብዓዊ መብቶችን በማስተማር፣ ቅርሶች እንዲጠበቁ በመታገል፣ የአማራ ጄኖሳይድን ለኢትዮጵያ ህዝብ በማስተማር፤ የታላቁ እስክንድር ውለታ ተቆጥሮ አያልቅም፡፡ እስክንድር ከጊዜው የቀደመ ሰው ነበር!!! ኮነሬል አብይ አህመድ ወደ ሥልጣን እንደወጡ ‹‹ የኢትዮጵያ ህዝብ የሚፈልገው መሠረታዊ ለውጥ እንጂ ጥገናዊ ለውጥ አይደለም›› በማለት የተቃወመ እስክንድር ብቻ ነበር፡፡ ኮነሬል አብይ ባልደራስ ፓርቲ በተመሰረተ ጊዜ ባልደራስ የሚባል ነገር የለም ጦርነት እንከፍታለን ብለው እስክንድርን ለማስፈራራት ሞክረው ነበር፡፡ የታላቁ እስክንድርና የጀነራል አሳምነው ፅጌ የባህር ዳር ቀጠሮ ምን ነበር? እስክንድር ብቻ የሚያውቀው ሚስጢር ምን ይሆን? ጊዜ ለኩሉ ብለን እንለፈው፣ ገድሉ ብዙ ነውና እሱን ማሳነስ አይቻልም፡፡ የተቀባም፣ ያልተቀባም ፤የተቀሸረም ያልተቀሸረም፣ ከጣት ጣት ይበልጣልና ስም በማጥፋት ወንጀል ተጠያቂነት አንድ ቀን አለና!!! ሁለቱን ብርቅዬ የአማራ ምሁራን ላይ ኮነሬል አብይ የዲጂታል ሚዲያ ተከፋዬች ዘመቻን ሁሉም እንዲመክት የአማራ ህዝብ የዓይኑን ብሌኖች ነቅቶ ይጠብቅ፣ ጀግና ተሰባሪ ነውና አማራ ንቃ!!! “Eskindir Nega is aEthiopian journalist, blogger and politician who has been jailed at least 10 times by the Ethiopian government on conviction’s for treason and terrorism……………He founded his first newspaper, Ethiopis in 1993. He also founded other newspapers like Askual, Satenaw and Menelik……..on July 24,2013, Nega’s “letter from Ethiopia’s Gulag” was published as a New York Times Op-ed.
የአራት ኪሎው ቌጥኝ!!! እውቁ ደራሲ በዓሉ ግርማ በኦሮማይ መፅሃፉ ውስጥ የሳለው ገጸ–ባህሪ ‹ሠለሞን በትረ–ጊዬርጊስ› እውኑ ዳዊት ወልደጊዬርጊስ መሆኑን ስንቶቻችን እናውቃለን፡፡ ኦሮማይን በማንበብ ዳዊት ወልደጊርጊስን ስብዕና አገር ወዳድነት፣ ንጽህና፣ ተጠያቂነት የአርትራ ክፍለሃገር ገዢ የነበረበት ወቅት የኤርትራ ህዝብ እንዴት እንደሚወደው መረዳት ትችላላችሁ፡፡ ማን ያውራ የነበረ ነውና፡፡ የአራት ኪሎው ቌጥኝ ፋኖዎችን ለማስታረቅ ጎጃም፣አባይ በርሃ ወረደ ቢባል ኮነሬል አብይ ኦሮሙማ ተሸዓተ አይሉምትላላችሁ? Baalu Girma changed the names of real-life Derg officials.
እስክንድር ነጋና ሻለቃ ዳዊት ወልደጊርጊስ በሥርዓተ መንግሥት ለውጥ የኮነሬል አብይ አህመድን ኦህዴድ ብልጽግና ኦሮሙማ መንግስትን ጥለው ጊዜያዊ ህብረ-ብሔር የሽግግር መንግሥት ለመመሥረት አስፈላጊውን ፍኖተ ካርታ በመንደፍ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና ማህበራዊ ጉዳዩችን ፖሊሲን ለሁሉም ብሔር ብሔረሰቦች አስተያየት አካተው ወደ ተግባር የሚለውጡበት ጊዜው አሁን ነው፡፡ የሱማሌ፣ አፋር፣ ትግራይ፣ ኦሮሞ፣ አማራ፣ ሲዳማ፣ ጋንቤላ፣ ቤኒሻንጉል፣ ሃረሪ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ ደቡብ ህዝቦች ክልላዊ መንግስቶች ትግላችሁን ከአማራ ህዝብ ጎን አድርጋችሁ ለአዲስ ስርዓት ለነጻነት፣ እኩልነትና ወንድማማችነት የአማራ ፋኖ የትግል ጥሪ ያቀርባል፡፡
የህሊና እስረኞች ይፈቱ!!!