>

የሥርዓት ለውጥ ለኢትዮጵያ!!! የሽግግር መንግሥት መመስረቻ ጊዜው አሁን ነው! (ክፍል ሁለት)

የኢትዮጵያ የፌዴራልና ክልል ህዝብ ተወካዬች ምክር ቤት ፈርሷል!!! የፓርላማ ዞንቢዎች አይወክሉንም!!!

(ክፍል ሁለት) ፀ/ት ፂዮን ዘማሪያም (ኢት-ኢኮኖሚ /ET- ECONOMY)

REGIME CHANGE IN ETHIOPIA የሥርዓት ለውጥ ለኢትዮጵያ!!! የሽግግር መንግሥት መመስረቻ ጊዜው አሁን ነው!!!!

የፌዴራል ምክር ቤትና የክልል ምክር ቤት ፈርሶል!!! የአማራ ክልል የአስቸይ ጊዜ አዋጅ ይነሳ!!!

የፌዴራል ምክር ቤት ካሉት 547 (አምስት መቶ አርባ ሰባት) መቀመጫ ወንበሮች  ውስጥ የትግራይ ክልል 38 ወንበሮች ባልተወከሉበት፣ የአማራ ክልል 138 ወንበሮች እና  የኦሮሚያ ክልል 178  ወንበሮች ተወካዮችን በህዝባዊ አመፅና እንቢተኛነት የፓርላማ ወኪሎቹ ተወግደዋል፡፡ በዚህም ምክንያት ከፌዴራል ምክር ቤት 547 መቀመጫ ወንበሮች ውስጥ 354 ወንበሮች (ስልሳ አምስት በመቶ) ሕዝብ አይወክሉንም ብሎ ባባረራቸው ዞንቢዎች የተያዘ መቀመጫ ሆኖል፡፡ 

የክልል ምክር ቤት ካሉት 1900 (ሽህ ዘጠኝ መቶ) መቀመጫ ወንበሮች የትግራይ ክልል 152 ወንበሮች ባልተወከሉበት፣ የአማራ ክልል 294 ወንበሮች እና የኦሮሚያ  ክልል 537 ወንበሮች ተወካዮችን በህዝባዊ አመፅና እንቢተኛነት የፓርላማ ወኪሎቹ ተወግደዋል፡፡ በዚህም ምክንያት ከክልል ምክር ቤት 1900 መቀመጫ ወንበሮች ውስጥ 983 ወንበሮች (ሃምሳ ሁለት በመቶ) ሕዝብ ከክልሉ ባባረራቸው ዞንቢዎች የተያዘ መቀመጫ ሆኖል፡፡ 

የኦህዴድ ብልፅግና መንግሥታዊ መዋቅር ወላልቌል፡- የኢትዮጵያ የፌዴራልና ክልል ህዝብ ተወካዬች ምክር ቤት ፈርሷል!!! የሽግግር መንግሥት መመስረቻ ጊዜው አሁን ነው!!! ኢትዮጵያ ከክልሎች የዘር የጦር አበጋዞች መንግስትነት ተላቃ አዲስ ኮንፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ  የሥርዓት ለውጥ መሸጋገርያ የጊዜው አንገብጋቢ አጀንዳ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች በህብረት፣ በእኩልነትና በወንድማማችነት ኢትዮጵያን በመመሥርት ለርሃብተኛው የትግራይ፣ ኦሮማ፣ አማራ እና የኢትዮጵያ ህዝብ በአስቸይ እንድረስለት!!!

  1. ትግራይ ህወሓት፡- የብልጽግና ፓርቲ በተመሠረተ ጊዜ ህወሓት የብልጽግና ፓርቲን አልቀበልም ብሎ ወጣ፣  ከኦህዴድ ብልፅግና መንግሥታዊ መዋቅር ውስጥ በመውጣት መቀሌ መሸገ፣ ቀጥሎም ከኢትዮጵያ ጋር የሁለት አመታት ጦርነት ገጥሞ በፕሪቶሪያ ስምምነት መሠረት ጦርነቱ ቆመ፡፡ በዚህ ጦርነት አንድ ሚሊዮን ወጣቶች ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡ ሃያ ስምንት ሚሊዮን ዶላር መሠረተ-ልማቶች ወድመዋል፡፡  የህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ፓርቲ ከፌዴራልና ከክልል መንግሥት መዋቅሮች ተነቅሎ ወጥቶል፡፡ 
  • የህወሓት ተወካዬች ከፌዴሬሽን ምክር ቤትና የሕዝብ ተወካዬች ምክር ቤት አባልነት ወጥተዋል፡፡ ህወሓት ከኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥታዊ መዋቅር ወጥቶል፡፡ ለህዝብ ተወካዩች የፌዴራል ምክር ቤት ካሉት 547 መቀመጫ ወንበሮች  የትግራይ ክልል 38 ወንበር በህወሓት የተያዘ ነበር ኮነሬል አብይ አህመድ አምክኖታል፡፡ ለክልል ምክር ቤት ካሉት 1900 መቀመጫ ወንበሮች የትግራይ ክልል 152 ወንበሮች በህወሓት የተያዙ ነበሩ ኮነሬል አብይ አህመድ አምክኖታል፡፡ የትግራይ  ሰባት ሚሊዮን ህዝብ በፌዴራልና ከህዝብ ተወካዬች ምክር ቤት ውስጥ ምንም ተወካዬች የሉትም፡፡ የትግራይ ህዝብ የኦህዴድ ብልጽግናን የጦር አበጋዞች አንባገነናዊ መንግሥትን አስወግዶ ከፋኖ አማራ ህዝባዊ ትግል ጋር ተቀናጅቶ የኢትዮጵያ ህዝብ ቀጥይ ህልውና የሽግግር መንግሥት መመሥረቻ ጊዜው አሁን ነው፡፡ 

(2) አማራ ብአዴን፡- የብልፅግና ፓርቲ የተመሠረተው በቀሪዎቹ ዋነኞቹ ኦህዴድ፣ ብአዴን፣ እና ደኢህዴን ፓርቲዎች  ሲሆኑ በአሁኑ ጊዜ በፋኖ የአማራ ህዝባዊ ትግል ከአማራ ክልላዊ መንግሥት መዋቅሮች ውስጥ 95 (ዘጠና አምስት በመቶ) የብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን)  አባሎች ከክልሉ መንግሥት መዋቅር በህዝባዊው አመፅና እንቢተኛነት ተባረዋል፡፡ በዚህም መሠረት ብአዴን ተወካዬች ከፌዴሬሽን ምክር ቤትና የሕዝብ ተወካዬች ምክር ቤት አባልነት የህዝብ ውክልና የላቸውም፡፡ ብአዴን ከኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥታዊ መዋቅር ሳይወድ በግዱ ከሥልጣን መንበሩ ከአማራ ክልላዊ መንግሥት መዋቅራዊ አስተዳደሩ ተንኮታኩቶ ወድቆል፡፡ 

  • ለህዝብ ተወካዩች የፌዴራል ምክር ቤት ካሉት 547 መቀመጫ ወንበሮች  የአማራ ክልል 138 ወንበር በብአዴን የተያዘ ነበር ፋኖ የአማራ ህዝብ በትግሉ የበአዴን ተላላኪ ምስለኔዎች ነቅሎ ጥሎል፡፡ ለክልል ምክር ቤት ካሉት 1900 መቀመጫ ወንበሮች የአማራ ክልል 294 ወንበሮች በብአዴን የተያዙ ነበሩ ፋኖ የአማራ ህዝብ በትግሉ የብአዴንን ተላላኪ ምስለኔዎች ከክልሉ መንግሥታዊ መዋቅር አባሮ፣ ህዝባዊ የሽግግር መንግሥት መሥርቶ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል፡፡   የአማራ  ሠላሳ ሚሊዮን ህዝብ በላይ በፌዴራልና ከህዝብ ተወካዬች ምክር ቤት ውስጥ ህዝብ ያልወከላቸው አሻንጉሊት ተወካዬች ይገኛሉ፡፡ የአማራ ህዝብ የብአዴንን አንባገነን የጦር አበጋዞች መንግሥትን አስወግዶ በፋኖ አማራ ህዝባዊ ትግል ጋር ተቀናጅቶ የኢትዮጵያ ህዝብ ቀጣይ ህልውና የሽግግር መንግሥት መመሥረቻ ጊዜው አሁን ነው፡፡

(3) ኦሮሚያ ኦህዴድ፡ ለህዝብ ተወካዩች የፌዴራል ምክር ቤት ካሉት 547 መቀመጫ ወንበሮች  የኦሮሚያ ክልል 178  ወንበሮች በኦህዴድ የተያዙ ነበር፡፡ የኦህዴድ ብልጽግና መንግሥት  ብቻውን ተወዳድሮ ባሸነፈው (94 በመቶ ድምፅ) የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ ፓርቲ (ኦፌኮ)፣ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ኦነሠ፣ ወዘተ ከምርጫው እንዳይሳተፉ በማድረግ ኮነሬል አብይ ፓርቲ አሸናፊ መሆን ችሎል፡፡ አሁን የኦሮሞ ነፃአውጭ ሠራዊት (ኦነሠ) የኦሮሚያን ዘጠና በመቶ በመቆጣጠር የኦህዴድ ብልፅግና ፓርቲ ሹማማንትና ካድሬዎች ከኦሮሚያ ክልል ነቅሎ ካባረራቸው አመታት አልፎል፡፡ 

  • የኦሮሞ ህዝብ ለክልል ምክር ቤት ካሉት 1900 መቀመጫዎች የኦሮሚያ  ክልል 537 ወንበሮች በኦህዴድ የተያዙ ሲሆን የኦህዴድ ብልፅግና ፓርቲ ሹማማንትና ካድሬዎች ከኦሮሚያ ክልል ማስተዳደር አልቻሉም፡፡ የኦሮሞ ሠላሳ አምስት ሚሊዮን ህዝብ በፌዴራልና ከህዝብ ተወካዬች ምክር ቤት ውስጥ ህዝብ ያልወከላቸው ዞንቢዎች ተሰይመው ይገኛሉ፡፡ የኦሮሞ ህዝብ ከኦፌኮ፣ ኦነግ፣ ኦነሠ ጋር በመታገል የኦህዴድ ብልፅግና አንባገነን የጦር አበጋዞች መንግሥትን አስወግዶ በፋኖ አማራ ህዝባዊ ትግል ጋር ተቀናጅቶ የኢትዮጵያ ህዝብ ህልውና ለማረጋገጥ የሽግግር መንግሥት መመሥረቻ ጊዜው አሁን ነው፡፡

(4) ደቡብ ደኢህዴን፡ የብልፅግና ፓርቲ ከደቡብ ኢትዮጵያ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደኢህዴን) የሚመሩት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥታዊ አስተዳደርን ያለህዝብ ፍላጎት ዳግም በመሸንሸን ደቡብ፣ ሲዳማ፣ ደቡብ ምስራቅ በማለት አዳዲስ ክልላዊ መንግሥቶች ፈጥሮል፡፡  

  • ለህዝብ ተወካዩች የፌዴራል ምክር ቤት ካሉት 547 መቀመጫ ወንበሮች የደቡብ ብ/ብ/ህዝቦች  ክልል 123 ወንበር የደቡብ ብ/ብ/ህዝቦች  የተያዘ ነው፡፡ ለክልል ምክር ቤት ካሉት 1900 መቀመጫዎች የደቡብ ብ/ብ/ህዝቦች  ክልል 348 ወንበሮች በደኢህዴን የተያዙ ሲሆን   የደቡብ   አስራ ሰባት ሚሊዮን ህዝብ በፌዴራልና ከህዝብ ተወካዬች ምክር ቤት ውስጥ ተወካዬች ይገኛሉ፡፡ የደቡብ  ህዝብ ደኢህዴን የጦር አበጋዞች አንባገነን መንግሥትን አስወግዶ በፋኖ አማራ ህዝባዊ ትግል ጋር ተቀናጅቶ የኢትዮጵያ ህዝብ ቀጥይ ህልውና የሽግግር መንግሥት መመሥረቻ ጊዜው አሁን ነው፡፡

(5) አጋር ድርጅቶች፡- የኦህዴድ ብልፅግና ፓርቲ አጋር ድርጅቶችን እኩል ተሳታፊ እንዲሆኑ አድርጎል፡፡ የክልሎቹ የፖለቲካና ኤኮኖሚ ነፃነት በኮነሬል አብይ ፈላጭ ቆራጭ አገዛዝ ስር ይገኛል፡፡ 

  • ለህዝብ ተወካዩች የፌዴራል ምክር ቤት ካሉት 547 መቀመጫ ወንበሮች  አፋር አብዴፓ ስምንት፣ ሶማሌ ሶሕዴፓ ሃያ ሦስት፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ቤጉሕዴፓ ዘጠኝ፣ ጋምቤላ ጋሕአዴን ሦስት ፣ ሃራሪ ኦሕዴድ/ኢሕአዴግ/ሐብሊ ሁለት፣ ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ኢሕአዴግ/ሶሕዴፓ ሁለት፣ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢሕአዴግ ሃያ ሦስት መቀመጫ ወንበሮች  አሎቸው፡፡
  • ለክልል ምክር ቤት ካሉት 1900 መቀመጫ ወንበሮች  አፋር  አብዴፓ 96፣ ሶማሌ ሶሕዴፓ 186፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ቤጉሕዴፓ 99፣ ጋምቤላ ጋሕአዴን 152፣ ሐረሪ ኦሕዴድ/ኢሕአዴግ/ሐብሊ 36፣ ወንበሮች አሎቸው፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ በሚካሄደው ህዝባዊ ትግል አሻራችሁን ማኖር ይጠበቅባችኃል፡፡

ፋኖ የአማራ ህዝባዊ ኃይል ነፃ ከወጡ ግዛቶች ግብርና ታክስ እየሰበሰበ ህዝብን ማስተዳደር አለበት፡፡

መንግስት ይሄዳል ይመጣል፣ ፋኖ ነፃ በወጡት ግዛቶች ውስጥ አዲስ ህዝባዊ መንግሥታዊ መዋቅሮች በመዘርጋት በዴሞክራሲያዊ ስርዓት ህዝባዊ መንግስት መመሥረት ያስፈልጋል፡፡ ፋኖ የአማራ ህዝብ ትግል መጀመሪያ የክልሉን የገጠርና የከተማ መንግሥታዊ መዋቅሮችና መሬቱን ተቆጣጠረ፣ በመቀጠልም ከመከላከያ ሰራዊቱ የጦር መሣሪያዎች ክላሸን ኮቨ፣ ስናይፐር፣ ሞርታል፣ ቢኤም፣ ሮኬት፣ ላውንቸር፣ መድፍ፣ ዙ23፣ ድሽቃ ወዘተ ማረከ፣ አሠልሶም የመንግስትና የግል ባንኮችን የህዝብ ኃብት በማድረግ፣ ቢሊዮንና ትሪሊን ብሮች የሚያስቀምጡ ባንክና ኢንሹራንስ ድርጅቶች ደህንነታቸውን በማስጠበቅ ህዝባዊ አገልግሎታቸውን እንዲቀጥሉ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ ፋኖ የአማራ ህዝብ ትግል በገጠርና በከተሞች የሚገኙ መንግሥታዊ መሥሪያ ቤቶች የቢሮክራሲያዊ ዘርፎችና  ሦስቱ መንግሥታዊ መዋቅሮችን የህግ አስፈፃሚ፣ የህግ አውጪና የህግ ተርጎሚ ዘርፎች ሥራዎችን በመዘርጋትና ዳግም በማዋቀር ላይ ይገኛል፡፡  ፋኖ የአማራ ህዝብ ትግል የፍርድ ቤቶች፣ የፖሊስ ኃይል፣ የሚሊሽያ ዘርፍ፣ ትምህርት ቤቶች፣ የጤና፣ መብራት ውኃ፣ ቴሌኮሙኒኬሽን ስልክና ኢንተርኔት አገልግሎት፣ የባንክና ኢንሹራንስ፣ የግብርና፣ ኢንዱስትሪ፣ የአገልግሎት ዘርፎች የውጭ ንግድ ገቢና የገቢ ንግድ ወጪ ዘርፎች ሥራ ማጠናከር ያስፈልጋል፡፡  ፋኖ የአማራ ህዝብ ትግል የአማራ ክልላዊ መንግሥት 154709 (መቶ ሃምሳ አራት ሽህ ሰባት መቶ ዘጠኝ) ኪሎሜትር ስኩየር ኩታ ገጠም መሬት ያለው ሲሆን፣ አስር አሰተዳደራዊ ዞኖች፣ አንድ ልዩ ዞን፣ መቶ አምስት ወረዳዎች እና ሰባ ስምንት የከተማ ማዕከሎች ይገኛሉ:: ኦህዴድ ብልፅግና ፋሽስታዊ አገዛዝ መንግሥታዊ መዋቅሮች በሙሉ ወላልቀው፡፡ ብአዴን ብልጽግና መዋቅር በመፈራረሱ  ምክንያት ግብርና ታክስ መሰብሰብ አልቻለም፡፡ ለመንግስት ሰራተኞች ደሞዝ መክፈል አልቻለም፡፡

የአማራ ክልላዊ መንግሥት በ2015 ዓ/ም 8.4 ቢሊዮን ብር ከግብርና ታክስ ገቢ (tax collection) ተሰብስቦ ነበር፡፡ 2016 ዓ/ም በመጀመሪያዉ ዓመት ሪፖርት 6.2 ቢሊዮን ብር የግብርና ታክስ ገቢ እንደተሰበሰበ ተገልፆል፡፡ የአማራ ክልል 17.9 ቢሊዮን  ብር ለመሰብሰብ አቅዶ ነበር፡፡  ፋኖ የአማራ ህዝባዊ ኃይል በሚያስተዳድራቸው  ግዛቶች ውስጥ  የንግዱን ህብረተሰብ እያማከረ ግብርና ታክስ በመሰብሰብ  ለትምህርት ቤቶች ለመምህራን ደሞዝ፣ ለጤና  ሠራተኞች ደሞዝ ክፍያ፣ ለውኃ፣ መብራት፣ ስልክ፣ ወዘተ የመንግስት ሠራተኞች ደሞዝ ለመክፈል ግብርና ታክስ መሰብሰብ ከወዲሁ አስፈላጊ ነው እንላለን፡፡ ፋኖ ከዲያስፖራ ወንድሞቹ የሚላክለትን እርዳት አመስግኖ በመቀበል፣ ፋኖ  በራሱ የገቢ ምንጭ ህልውናውንና ነፃነቱን መጎናጸፍ ይችላል፡፡  ኢትዮጵያ መንግሥት በ2015ዓ/ም በጀት አመት 193.3 ቢሊዮን ብር ከግብርና ታክስ መሰብሰቡ ይታወቃል፡፡   In the first quarter of the Ethiopian Year, the Amhara region collected 6.2 billion birr in revenue, falling significantly short of its planned 17.9 billion birr target for the same period. Amhara Media Corporation (AMC) has reported that the poor performance is attributed to the region’s security situation. Fikre Mariam Dejene, Deputy Head of the Amhara region Revenue Office, explained that the security challenges in the region have had a detrimental effect on tax collection, resulting in an 11.6 billion birr collection deficit. He emphasized that this underperformance will have a severe negative impact on development projects in the region, stating, “Failure to meet our tax collection targets means our healthcare institutions and schools will face operational challenges.”Fikre Mariam Dejene also pointed out that in the previous Ethiopian budget year, 8.4 billion birr in revenue was collected during the same period………….(1) 

ምንጭ

  1. Ethiopia : Poor Tax Collection Performance in the Amhara Region/November 1, 2023
Filed in: Amharic