>

ፋኖን ለምን ትደግፊያለሽ? ለምትሉኝ መልስ መስጠት እፈልጋለሁ

ፋኖን ለምን ትደግፊያለሽ? ለምትሉኝ መልስ መስጠት እፈልጋለሁ

ዶ/ር ትእግስት መንግስቱ  ኃይለማሪያም
ይህ የሚያሳዝን ዘመን መጥቶብን ኢትዮጵያዊ ነኝ ብቻ ማለት አልበቃ ብሎ ዘር መቁጠር ጀምረናል ባንድ ወቅት ኢትዮጵያዊ ነኝ ያለ ሁሉ አማራ ነው  እየተባለ መታወቂያው ላይ እንዲፃፍለት የወያኔ መንግስት አዞ ነበር፡፡ አብይ አባቱ ኦሮሞ : እናቱ አማራ መሆኗን ነግሮናል:: ነገር ግን የአማራ ሴት ጡት ያልጠባ ይመስል ይህንን ህዝብ እንዴት እንደሚያንገላታው እያየን ነው:: የናት ጡት ነካሽ የሚለው አባባል ትዝ አለኝ:: እኔ ራሴን ኢትዮጵያዊ ነኝ ብዬ ነው የማምነው::
ልጅ ሆኜ እናቴ ጎጃሜ መሆኗን እሰማለሁ ; የአባቴ ቤተሰቦች ከአዲስ አለም እንደመጡ አውቃለሁ : ነገር ግን አንድም ቀን አማራ የሚለውን ቃል ሲነገር አልሰማሁም :: ያደግኩት ኢትዮጵያ ትቅደም የሚለውን መፈክር እየሰማሁ ነው:: ለኔ ይህ መፈክር ብቻ ሳይሆን ጥልቅ የሰመጠ እምነት ነበር::
 ራሻ ሄደን ከሌላ ኢትዮጵያኖች ጋር ስንገናኝ ነው ለመጀመሪያ ጊዜ እናቴ አማራ እንደሆነች የተነገረኝ:: የአባቴ እናት ብዙዬም የሸዋ አማራ ነበሩ:: አያታቸው ወልዶ አማኑኤል ከምኒልክ ጋር በአድዋ የተዋጉ ጀግና:: ለጀግንነታቸውም አዲስ አለም ምኒልክ መሬት ሸለ ሟቸው ::የወልዶአማኑኤል የልጅ ልጅ ( የአባቴ አጎት ) ድረስልኝ የሁለተኛ አለም ጦርነት ጀግና አርበኛ ነበር  ጣልያንን ሲዋጋ ተይዞ በአደባባይ የተሰቀለ:: ለሀገራቸው መሰዋትነት የከፈሉ አርበኞች ኢትዮጵያ ኖች , አረንጋዴ ቢጫ ቀይ ባንዲራን ይዘው ከተዋጉ  ዘር በመፈጠሬ እኮራለሁ:: ወያኔ መጥቶ በብሄረሰቦች እኩልነት ስም ሃገራችንን ከፋፈላት የብሄረሰቦች መብት ማስከበሪያ ሳትሆን የተረኛ ፖለቲካ ማረማመጂያ ሆነች::
 ወያኔ መጥቶ ዘመኑ የትግሬ ነው ብሎ ሌላውን ሲረግጥ ቆየ:: ለውጥ መጣ ብለን ደስ ሲለን አብይ መጣ : አሁን ደሞ ጊዜው የኦሮሞ ነው ተባልን:: ከወያኔ ጊዜ የባስ እንጂ የተሻለ አልመጣም:: ግርድፍን አባርሬ እንትፎን አመጣሁ ነዉ የሆነው:: ኢትዮጵያንና አረንጋዴ ቢጫ ቀይ ባንዲራን ሲያይ የሚያመው ጎጠኛ ኢትዮጵያን እስከመራ ድረስ ኢትዮጵያኖች ከዚህ ከአዙሪት የተረኝነት ጎጠኛ ፖለቲካ አንላቀቅም!!
 ፉኖ አነሳሱ የ አማራን በደልና ጭፍጨፋ ለማስቆም ቢሆን መድረሻው ግን ይህን የተረኝነት ፖለቲካ ላንዴና ለመጨረሻ አስቁም : ኢትዮጵያኖች ከማንኛውም ብሄረሰብ ቢወለዱም እንደፈለጉ በየትኛውም በኢትዮጲያ ክፍል እየተዘዋወሩ : ሳይገደሉ : ሳይፈናቀሉ: መብታቸው ተጠብቆላቸው: መመረጥም  መምርጥም መብት አግኝተው እንዲኖሩ; ሃብት አፍርተው ; ቤተሰብ እያስተዳደሩ ሊኖሩ እንዲችሉ ለማድረግ ነው::
 መንግስት ፅንፈኛ ጃውሳ ወሮበላ እያለ ሊያጥላላ ቢሞክሮም ነገር ግን ተግባር ከቃል በላይ ነው:: ማነው የሚዘርፈው : ማሳ የሚያቃጥለው: እርጉዝ የሚገለው የመንግስት ታጣቂዎች ወይንስ ፋኖ? ማነው ገበሬውን የሚያንገለታው? ማዳበሪያ በትርፍ የሚሸጠው? ማነው አምቡላንስ በድሮን የሚመታው? ለብዙ አመታት የናፈቅነውን እና ማሳካት ያቃተንን የብሄረሰቦች እኩልነትን በ አንዲት ኢትዮጵያ ሊያሳካ የሚችለው ፋኖ ብቻ ነው ብዬ ስለማምን ነው የምደግፋቸው!!
 አብይ ‘እግዚአብሄር *እያለ ጆሮራችንን ያደነቁረናል ነገር ግን ፍርሃተእግዚአብሄርን በተግባር የሚያሳየን ማነው? ፋኖ የለቀቃቸውን ምር ብኞች መንግስት ይገላል ያንገላታል:: አሁን ነው ሰዓቱ
 ሁሉም ተረባርቦ ፋኖን መደገፍ ያለበት:: ትግሉን ለማሳጠርና መስዋትነቱን ለመቀነስ ፋኖን የምደግፈው አማራ ስለሆንኩ ብቻ አይደለም !!
 ፉኖን የምደግፈው ኢትዮጵያዊ ስለሆንኩ ነው ፡በ አንዴት ኢትዮጵያና በአረንጓዴ ቢጫ ቀይ ባንዲራ ስለማምን ነው !!
 ደል ለፍኖ!! 
ድል ለኢትዮጵያ!! 
ኢትዮጵያ ትቅደም !! 
እናሸንፋለን!!
Filed in: Amharic