ሰፋሪው ማነው?
ትዕግሥት መንግሥቱ ኃይለማርያም
ሃገራች ኢትዮጵያ በታሪክ ጥንታዊ ከሚባሉ ሃገሮች መሀል አንዷ ናት:: ታሪክ ዛሬ ጥንት ናቸው ተብለው ከሚጠሩት : ከሮም ከግብፅ ከግሪክ ጋር አብሮ ይተነትናታል:: ይህ ብቻም ሳይሆን የሰዉ ልጅ መነሻ ናት ተብሎ በጥናት ተመስክሮላታል::
በአፍሪካ ብቻ ሳይሆን በአለም ጥቁር ህዝብ ትልቅ ክብር የሚሰጣት ሃገር ናት:: በነፃነት መቆየቷ ብቻ ሳይሆን : ለሌላ አፍሪካ ሀገሮች ነፃ መውጣት ላደረጋቸው አስተዋጽኦ ታላቅ ክብር የሚሰጣት ሃገር ናት::የአፍሪካ አንድነት መስራች ሀገር ናት እናም የድርጅቱ ፅህፈት ቤት ማእከል ነች። ብዙ የአፍሪካ ሃገራት የኢትዮጵያን ባንዲራ ወስደው በተለያየ መልኩ የራሳቸው አርገውታል፡:
በአለም ላይ 11 ፊደሎች በጥቅም ላይ አሉ:: ከዚያም በላይ ነበሩ ነገር ግን በሂደት ብዙዎች ከጥቅም ዉጭ ሆነዋል:: እኛ የራሳችን ፊደል ያለን ብቸኛ የአፍሪካ ሀገር ነን:: ኢትዮጵያዊነት የሚኮራበት እንጂ የሚታፈርበት በግድ የተጣለብን ሸክም አይደለም::
በታሪካችን መኩራት ማለት እጃችንን አጣምረን ቁጭ እንበል ሳይሆን ታላቅነታችንን አንርሳ ማለት ነው:: አሁንም ከሰራን ከሞከርን ደግመን ታላቅ ሃገር መሆን እንችላለን ብለን እንድናስብ ስሜታችንን እንዲኮረኩረን ነው:: ወኔን ለመቀስቀስ ነው::
ታዲያ ይህ ሁሉ መኩሪያ እያለ ‘እኔ ኢትዮጵያዊ አይደለሁም’ የሚሉትና ኢትዮጵያዊትን ለማጥፋት ተግተው የሚሰሩት ሰዎችን ለመረዳት ተቸግሬያለሁ::
የአዲስ አበባ ቅርሶች መፍረስ በቀላሉ የሚታይ አይደለም:: ምናልባት ቆሻሻና ትኩል ሰፈር ማፅዳት የሚል ምክንያት ሊሰጥ ይችላል:: ግን ቲያትር ቤትና ትምህርት ቤቶችን ለምን ማፍረስ ያስፈልጋል? ለምንስ ከህዝቡ ጋር በውይይትና በምክክር አይሰራም?
በኔ አስተሳሰብ ይህ ጠባብ ዘረኛ ኦሮሞ መንግስት ተብዬው ኢትዮጵያዊትን የሚያስታውሰውን በሙሉ ለማጥፋት ተነስቷል::
ኢትዮጲያ የመቶ አመት ታሪክ ነው ያላት ብሎ ወያኔና ኦነግ ሊግተን ሞክሯል:: እኛ ኢትዮጵያኖች ግን በሺዎች የሚቆጠሩ ታሪክ አላት ብለን እናምናለን:: ታሪክን ስናስታውስ ጎጠኞች መቶ አመት ብቻ ወደኋላ እንድንሄድ ነው የሚፈልጉት:: ለምን? ስንት አመት ወደኋላ እንሂድ?500? 1000? 1500? ይህ ያዋጣል?
የኦሮሞ ብሄረሰብ ከዛሬ 500 አመት በፊት : ዛሬ ኬንያ ከምትባለው ሃገር ወድ ኢትዮጵያ ፈለስ:: በመጀመሪያ ቦረና ነበር የሰፈረው:: ኢትዮጵያ ከግራኝ አህመድ ጦርነት ጋር ካደረገችው እጅግ ረጅምና: ብዙ መስዋትነት ከተከፈለበት ጦርነት በምታገግምበት ጊዜ : በድክመቷ ጊዜ ማለት ይቻላል ይህ ሰላማዊ ሆኖ በቦረና የኖረው የኦሮሞ ህዝብ ጦረኛ ሆነ::
በዚህ ወቅት ነው በመንገዱ ላይ ያለዉን እየገድለ እየ ወረረ በግድም በውድም ኦሮምኛ ተናጋሪ እያደረገ ወደ ወለጋ :ጋሞ ጎፋ : ሲዳሞ: ባሌ: አርሲ: ሸዋ: እስከ ሰሜናዊቷ ኢትዮጵያ የደረሰው::
ግን፡ ከኦሮሞ ፈለሳ በፊት እነዚህ የተጠሩት ቦታ በሙሉ ማን ነበር የሚኖርባቸው? ኢትዮጵያውያን!
ዛሬ አዲስ አበባ ሳትቀር የኛ ናት ‘ሰፋሪውን እናባርራለን’ ለምትሉ ሁሉ ጠባቦች አንድ ጥያቄ ነው ያለኝ ሰፋሬው ማነው? የዛሬ 500 አመት ታሪክን እንደሌለ አርጋችሁ ፍቃችሁ ልታጠፉ አትችሉም::
ኢትዮጵያ መጥታችሁ ስትሰፍሩ ማንም አልነካችሁም እናንተን ጦር እስከምትመዙ ድረስ:: ጦር ስትመዙ ምን እንደሆነ ታውቁታላችሁ:: በግድ ኢትዮጵያን በሙሉ ኦሮሞ እናረጋለን ያላችሁት የዛሬ 500 አመት ሙከራችሁ አልሰራም :: ዛሬም አይሰራም! ታሪክ ራሱን ይደግማል::
አንድን ነገር ደግሞ ደግሞ እየሰሩ ልዩ ዉጤት መጠበቅ እብደት ነው ብሏል አይንስታይን:: በሰላም ከሆነ ከቀረዉ ኢትዮጵያ ጋር መኖር ይቻላል:: እንደዛሬ 500 አመቱ በግድ ግን አይሆንም:: ኢትዮጵያዊውን በገዛ ሃገሩ ሰፋሪ እየተባለ እየተሳደደ እየተገደለ የሚገኝ ሰላምና ብልፅግና የለም:: ይህ አያዋጣንም ይልቁንስ ልጆቻችሁን የውሸት መርዝ : ታሪክ እያላችሁ ማስተማር ተውና እንዴት ሁላችንም ተፋቅረንና ተቻችለን የምንኖርባትን ኢትዮጵያን እንደምንገባ አስተምሯቸው::
ይህ የጥላቻ መንገድ ማንንም አይጠቅምም::
ኢትዮጵያ ትቅደም!
ድል ለፋኖ!