>
5:16 pm - Friday May 24, 7540

እስክንድር ነጋን ማጥቃት የለየለት ባንዳነት ነው!

እስክንድር ነጋን ማጥቃት የለየለት ባንዳነት ነው!

 

በ ትግሉ ሠመረ

 

እስክንድርን ባለፉት 30 ዓመታት ከተከሰቱ ፖለቲከኞች ልዩ ከሚያደርጉት በርካታ ነጥቦች ውስጥ ለሦስት አስርት አመታት የተፈተነው የዓላማ ፅናቱ ዋነኛው ነው። እስክንድር ለጀግንነቱ ወደር  የለውም። ለእምነቱም ምኒልካዊ ቀናኢ ፀሎተኛ ነው። የእስክንድር ፍጹም ትህትናና ጨዋነት በኢትዮጵያ ፖለቲካ መድረክ ላይ ብቅ ጥልቅ ከሚሉት ሁሉ ይለያል። ነፍሱ ከሀገሩ ጋር የተጣበቀች፣ የሸቀጥና የክህደት የሥልጣን ጥመኞች ፖለቲካ የማያስጎመዠው እንደ እስክንድር ያለ ቆራጥ ፖለቲከኛ እንኳን በኢትዮጵያችን በዓለማችን  በዚኽ ዘመን ፈልጎ ለማግኘት በጣም አዳጋች ነው። ኢትዮጵያ እስክንድርን የመሰለ ጀግና  ወልዳለች።  አማራው ብሎም የኢትዮጵያ ህዝብ ልክ እንደ ጥንት አባቶቹ ጀግናውን ማክበር የመስማትና መከተል ሃላፊነት አለበት። ጀግናውን የማያከብር ህዝብና ትውልድ ብዙ ዋጋ ይከፍላል። 

እስክንድርና የዘመኑ አደናጋሪ ፖለቲከኞች አክቲቪስቶች

 እስክንድር አርቆ አስተዋይ የአምባገነኖችን ጠባይ በጥልቀት የሚረዳና፣ ሀገር ላይ የሚያመጡትን ቀውስ ቀድሞ የሚገነዘብ (visionary) ፖለቲከኛ ምሁር ነው። ብዙ ፖለቲከኞች፤  የእስክንድርን አርቆ አሳቢነት መረዳት ባለመቻላቸው ከገዢው ሥርዓት ጋር ተደርበው ላለፉት አምስት ዓመታት ሲታገሉት ቆይተዋል። እስክንድር ከመነሻው፣  አዲስ አበባን የመሰልቀጥ  የ”ተረኝነት” ፕሮጀክቶችን ሲቃወም፣ ነባር ሃይማኖቶች የመናድ ደባ  ሲቃወም፣ የደሃውን ማህበረሰብ ከቤት ንብረቱ መፈናቀል ሲቃወም፣   የከተማዋና የሀገር ቅርስ መፍረስ ሲቃወም፤ አማራው በያለበት ሲገደልና ሲጨፈጨፍ ሲቃወም፤   ጉምቱ ፖለቲከኞች እነ ብርሃኑ ነጋና  አንዳርጋቸው ጽጌ እንዲኹም ተከታዮቻቸው ”አውሬውን እናምነዋለን ከማንም በላይ ኢትዮጵያዊ ነው” በማለት በእስክንድር ላይ ይሰነዝሩዋቸው  በነበሩት ትችቶች ምክንያት፣ የአዲስ አበባን ህዝብ ብዥታ ውስጥ በመክተታቸው፣ የአዲስ አበባ ህዝብ የተጋረጠበትን አደጋ የሚመጥን ምላሽ በትክክለኛው ሰአት  እንዳይሰጥ ኾኗል። ይህ የነ ብርሃኑ ነጋ አርቆ አስተዋይነት የጎደለው የአጎብዳጅ የፖለቲካ አቋም፤ በህዝብና በሃገር ላይ ያደረሰው ከፍተኛ ጥፋት ታሪክ ይቅር የማይለው ነው። የአዲስ አበባ ህዝብ ዛሬ በአውሬው መንግሥት እንደ አሮጌ እቃ ከቤቱ እያወጣ ሜዳ ላይ እንዲጣል ያደረገው፣ በነዚህ  አቋም የሌላቸው ደካማ (a spineless cowards) ያረጡ የፖለቲካ ሙሰኞች (morally bankrupt politician) ምክንያት ነው። የአዲስ አበባ ህዝብ የአውሬውን ኦሮሙማ መንግሥት አካኼድ ቀድሞ የተረዳውን ባለ ራእይ መሪውን እስክንድር ነጋን በተገቢው ሰዓት መስማት ቢችልና ቢታገል ኖሮ ፣ አሁን እየኾነ እንዳለው ጫፍ የረገጡ ሰገጤዎች መጫወቻና መሳለቂያ ባልኾነ ነበር።

አሁን ደግሞ     ‘መነሻችን የአማራ ህልውና መዳረሻችን የኢትዮጵያ አንድነት’ በሚል በአንድ  እስትራተጂካዊ አስተሳሰብ  ፋኖን አስተባብሮና  አንድ አድርጎ፣ አውሬዎቹን የኦሮሙማ ኃይሎች ለመፋለም ወደ ጫካ የገባውን እስክንድር ነጋን ከዋናው ጠላት ባልተናነሰ  እየታገሉት ያሉት፤  ስሪታቸው ብአዴናውያን  የኾኑ ኾድ አደር ፖለቲከኞችና የአድር ባይነትን ጠባይን እየተለማመዱ ያሉ  (opportunist) ተባባሪዎቻቸው ናቸው።   እነዚኽ የአማራ ወዳጅ መሳይ  ጠላቶች ‘አንድ አማራ’ በሚል የተደራጁ ተኩላዎች፣  መጀመሪያ ፋኖ መሪ የለውም እያሉ የሞራል ማላሸቅ ሚናቸውን ሲጫወቱ የቆዩ ሲኾን አሁን ደግሞ  የፖለቲካ ክንፉን(political wing) የሚመራ ‘የአማራ ህዝባዊ ግንባ/የአማራ ህዝባዊ ሠራዊት’ን  ሲያቋቁምና  በአራቱም የአማራ ጠቅላይ ግዛት የሚገኙ ፋኖዎች አስተባብሮ ትግሉን ሲያጎመራው፤ የግንባሩ አመራር የነበሩት እነ ሻለቃ ዳዊት ላይ፣    የሥም ማጥፋት ዘመቻ በመክፈት እንዲኹም እያጋነኑ በሚነዟቸው ተራና ጥቃቅን የገንዘብ ጉዳዮች፤ የአማራውን ማህበረስብ ከትልቁ እነ እስክንድር ካስቀመጡት አውሬውን የኦሮሙማ ቡድን፣ ከ4ኪሎ የምኒልክ ቤተመንግሥት የማስወገድና የአማራውን ህልውና የማረጋገጥ ግብና መዳረሻ፤ አይኑን እንዲያነሳና የትኩረት አቅጣጫውን በጥቃቅን ጉዳዮች ላይ እንዲያደርግ እየተረባረቡ ነው። በዚኽ ረገድ በጣም ውስን የፖለቲካ ልምድና እውቀት ያላቸው ደረጃቸውንና አቅማቸውን  ለይተው  የማያውቁ፤  ነገር ግን ብዙ ተከታዮችን ያፈሩ የሚዲያ ጦርነቱ ላይ ተሳታፊ የነበሩ አክቲቪስቶች ማሊያ ቀይረው በእነ እስክንድር ላይ የተከፈተውን ዘመቻ በአጨብጫቢነት እየተሳተፉ ይገኛሉ።  በተለይ ዘመድኩን በቀለ  በግንባሩ ሥም የተሰበሰበው ዶላር ላይ አይኑን ተክሎ፣ ወሬው ሁላ ዶላር ኾኗል። ባለማይክራፎኖቹ እነ ዘመድኩን በቀለ የፖለቲካ እውቀት አድማሳቸውም ቢኾን  በጣም ጠባብ ከመኾኑ የተነሳ ቶሎ በስሜት የመነዳት ጠባይ ስላላቸው፤ ትግሉን ሊጠልፉ ለተነሱ የኦሮሙማ ኃይሎችና ስሪተ ብአዴን ማፊያ ቡድኖች፤ እንዲኹም  አንድ አማራ ነን የሚሉ የህወሃት ሰርጎ ገብ ኃይሎች  ጋር ጭምር በመተባበር ትግሉን ለማዳከም  እየሠሩ ይገኛሉ። በገንዘብ ላይ የተንጠለጠለ ንፅህና የሌለው አክቲቪዝም መደምደሚያው  በሕዝብ መተፋትና ውርደ እንደኾነ  ረስተውታል። አማራውና አዲስ አበቤው እነዚህን ገንዘብ አፍቃሪ ከሃዲ አክቲቪስቶች ይቅር ላይላቸው ይተፋቸዋል።  የአማራ ትግል፣ እስክንድርና ጓዶቹ ሌት ተቀን ከአንዱ ጠቅላይ ግዛት ወደ ሌላው በእግራቸው እየተጓዙ እየተንከራተቱበት ያለ መራራ ትግል ነው።  የፋኖ ትግል በገንዘብ የሚመነዘር አይደለም። የፋኖ ትግል ገንዘብ ሳይኾን  የአማራ ልጆች ሕይወት እየተገበረበት ያለ ቅድስናን መሠረት ያደረገ ትግል ነው። የፋኖ ትግል  እንደ ማይክራፎኑ ትግል የአልጋ ባልጋ ትግል አይደለም።እስክንድር ነጋን የሚያክል፣ ታላቅ ሰው፤ ትንንሽ የአእምሮ ሚዛን ባላቸው ሰዎቸ ሥሙ ሲብጠለጠል መስማት ህሊናን ያቆስላል። በተለይ ተማርኩ ከሚለው፣ ከአማራው ወገን ሲመጣ እጅግ በጣም ያስተዛዝባል።

የእስክንድር አርቆ አስተዋይነትና የፖለቲካ ተጋድሎ

የእስክንድርን አርቆ አስተዋይነት በተለይም ከማንም በላይ የዘረኞቹን የወያኔዎችን፣አሁን ደግሞ የኦሮሙማውን ሴጣናዊ ሥርዓት እንዲሁም፣ በአማራ ህዝብ ላይ የተተከለውን የነቀርሳውን ብአዴንን አካኼድ ቀድሞ በመረዳት፤ ህዝብን  ታግሎ በማታገል እንዲጥላቸው፤ ውድ ሕይወቱን አስይዞ ለሦስት አስርት አመታት ያደረገውን  ያልተቋረጠ ትግል  ባጭሩ እንቃኝ።

እስክንድር ከወያኔ ጋር ያደረገው ተጋድሎ 

እስክንድር ደርግ ከሥልጣን ሲወርድ አሜሪካን የነበረ ቢኾንም፤ የወያኔን ፀረ-አማራና፣ፀረ-ዲሞክራሲ  ባህሪይ ቀድሞ በመረዳት፣ ወያኔን ለመታገል  ቆራጥ እርምጃ በመውሰድ ገና በ20ዎቹ እድሜው፣ ወደ ሀገሩ ተመልሶ፤ የኢትዮጵያ መፃኢ እድል እንዲቃና ሌት ተቀን የታገለ ጀግና ነው። የዛሬን አያድርገውና የዛሬ 30 ዓመት፣ የአዲስ አበባ ልጆች እንዲሁም የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች  ወያኔን ለመፋለም በባዶ እጃቸው የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ አንግበው አደባባይ እየወጡ፤ ፀጉራቸው ከተንጨፈረረ መትረየስ ከታጠቁ ወያኔዎች ጋር ዘረኝነትን በመቃወም ግብ ግብ እየገጠሙ በሚዋደቁበት በዛ ዘመን፤ እስክንድር መለስ ዜናዊንና ድርጅቱን ወያኔን   ”ፋሺዝም በትግራይ”  እንዲሁም “የማትረባ ፍየል” የሚሉ መጣጥፎችን በኢትዮጲስ ጋዜጣ በማሳተም የወያኔን ካምፕ አንገት ያስጎነበሰ፣ አዲስ አበባ ላይ ወያኔን ያሸበረ ጀግና ነው። በጊዜው ብዙ ምሁራን ከውጪም ከሀገር ውስጥም ስለሀገራቸው ተቆርቁረው፣ አርባ በሚጠጉ  ፖለቲካ ነክ ጉዳዮችን በሚያነሱ መጽሔቶች  ወያኔን ለመታገል ይጽፉ ነበር። አብዘኞቹ ምሁራን ከወያኔ ከሚደርስባቸው ውክቢያና ማስፈራሪያ እንዲሁም ከሥራ መባረር፣ እስርና እንግልት ፍራቻ ምክንያት በቀላሉ ተስፋ እየቆረጡ ከትግሉ ሜዳ እየተንጠባጠቡ ኮብልለዋል። እነዚህ ምሁራን ምን  አልባት ልክ እንደ እስክንድር በፅናት ያለመታከት መስዋእትነት እየከፈሉ ወያኔን ቢታገሉ ኖሮ ኢትዮጵያ አሁን የደረሰችበት አዘቅጥ ውስጥ ባልገባች ነበር። እስክንድር  ከብዙዎቹ ፖለቲከኞች የሚለየው በአርቆ አስተዋይነቱ ብቻ ሳይኾን   ለቆመለት ዓላማ የሚያሳየው የማይወላውል ጽኑ አቋሙ ነው። እስክንድር  አሁን ለደረስንበት ሀገራዊ ውድቀት ዋና ተጠያቂ የኾነውን ወያኔን 27 ዓመት  አምርሮ ታግሎታል። ታግሎታል ሲባል እንዲ ቀላል ትግል አልነበረም። እስክንድር ከ9 ጊዜ በላይ በወያኔ ለእስር ተዳርጎ ተሰቃይቷል።  እስክንድር አኹንም የአማራውን ትግል ፈር ለማስያዝ ጫካ ገብቶ እየታገለ ነው። የእስክንድር የትእግስትና የፅናት ምሳሌነቱ እዮብአዊ ነው።  እስክንድር በመጪው ትውልድ የትምህርት ካሪኩለም ውስጥ የታማኝነት፣ሀገር ወዳድነት፣ የጀግንነትና የጽናት ምሳሌ ኾኖ ለመማሪያነት የሚያገለግል ከትውልድ ትውልድ የሚተላለፍ ልዩ መጽሐፍ ነው።  

እስክንድርና አዲስ አበባ

”አዲስ አበባን ማዳን ኢትዮጵያን ማዳን ነው” እስክንድር ልክ ነበር። የአዲስ አበባ ህዝብ አዲስ አበባን ማዳን ይችል ነበር። የአዲስ አበባ ህዝብ የተካደው ‘ኢትዮጵያ’ ‘ኢትዮጵያ’ በሚለው ሰበካ  ህዝብን ባጃጃለውና ይዞት የመጣውን ዓላማ እያስፈፀመ ባለው የበሻሻ አውሬ አይደለም። የአዲስ አበባ ህዝብ የተከዳው ብዙ ተስፋ ጥሎባቸው በነበሩት  በነብርሃኑ ነጋና አንዳርጋቸው ጽጌ በሚመሩት ግንቦት 7 በዃላ ስሙን ቀይሮ ኢ.ዜ.ማ በኾነው ቡድን ነው።  የእነኚኽ ስብስብ በተለይ ዋናው አመራር እነ ብርሃኑ ነጋ ከ97 ምርጫ መጨናገፍ በዃላ ወደ አሜሪካን በመሰደድ  ግንቦት 7ን አቋቁመው፣ ወያኔን በትጥቅ ትግል እናሸንፋለን በማለት እስከ ኤርትራ በረሀ ገብተው የኢትዮጵያን ህዝብ  ዲያስፖራውን ጨምሮ፤  በተለይ የአዲስ አበባን ህዝብ ተስፋውን በነሱ ላይ እንዲጥል ማድረግ የቻሉ ነበሩ። ህወሓት መራሹ ኢሕአዴግ ለኦህዴድ መራሹ ኦሮሙማ ሥልጣኑን በአሜሪካኖች ድጋፍ ሲያስተላልፍ። አውሬው ‘ኢትዮጵያ’ ‘ኢትዮጵያ’ እያለ ህዝብን ሲያፈዝ ፣ በርካታው የአዲስ አበባ ህዝብ በግንቦት ሰባት አመራሮች ላይ ከፍተኛ ተስፋ ነበረው። ግንቦት ሰባቶች ወደ ኢትዮጵያ ሲገቡ የአዲስ አበባ ህዝብ በኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ያሸበረቀ ለአንድ ሳምንት የዘለቀ  ዝግጅት አድርጎ በአዲስ አበባ ስታዲየም ያደረገላቸው ደማቅ አቀባበል ለዚኽ ዋና ምስክር ነው። ብዙም ሳይቆይ አውሬው የአዲስ አበባን ዲሞግራፊ ለመቀየርና አዲስ አበባን ለመዋጥ፣ አጀንዳ ቀርፆ ለግብረአበሩ ለማ መገርሳ(ሱሴ) እንዲተገበር አዞ፣፤ ወደ ትግበራ ሲንቀሳቀስ፤ የግንቦት ሰባት ኃይሎች እነ ብርሃኑ ነጋ አውሬውን ተቃውመው ህዝቡን በመያዝ ይታገሉታል ተብለው ሲጠበቁ፣ ጭራሽ ከአውሬው ጋር ተቀራርበው መሥራት መጀመራቸውን በመንግሥት የቴሌቪዥን መስኮት ብቅ ብለው አበሠሩ። በዚህ ጊዜ ነበር እስክንድር ነጋ  የአዲስ አበባ ባላደራውን አቃቁሞ የአዲስ አበባን ህዝብ የአውሬውን የኦሮሙማ ቡድን አደገኛ እንቅስቃሴ ለመግታት ፈጣን እርምጃ የወሰደው።  እስክንድር ባላደራውን ካቋቋመ በዃላ ትግሉን ለማፋፋም በሚንቀሳቀስበት ወቅት፣ ከአዲስ አበባ ህዝብ ሊገጥመው የሚችለውን ከፍተኛ ተቃውሞ የገመተው አውሬው፤  መጀመሪያ እስክንድርን፤ እነ ብርሃኑ ነጋን ህሊና  ያሸጠበትን  ርካሽ ዘዴ ተጠቅሞ ለማማለል ሞከረ። እስክንድርን የባላደራውን ስብሰባ ቤተመንግሥት እንዲያደርግ ጋበዘው፤  የአውሬውን እቡይ ማንነት ቀድሞ የተረዳው ኩሩው እስክንድር ነጋ አውሬውን በአደባባይ  አሳፈረው። ያኔ አውሬው በእስክንድር ላይ ግልጽ ጦርነት አወጀ።  የግንቦት 7 መሪዎች እነ ብርሃኑ ነጋ  የእስክንድርን ሃሳብ የምን ‘ባላደራ ምናምን ነው’ በማለት፣ የእስክንድርን የትግል አቅጣጫ በመቃወም ከአውሬው(ፒኮክ)  ጎን በመቆም ይታገሉት ጀመር። ተስፋ የማይቆርጠው ብረቱ እስክንድር(the iron man) በዚኽ ሁሉ ተጽዕኖ ውስጥ ኾኖ ከአዲስ አበባ ባሻገር ዲያስፖራውንም በማስተባበር የፖለቲካ ፓርቲ በማቋቋም የኦሮሙማውን መንግሥት ከጥቂት ጀግኖች ከነ ስንታየሁ ቸኮል፣ የአዲስ አበባ ልጆች ጋር በመኾን  የቅርስ ፈረሳን፣ የደሃ መኖሪያ ቤቶች ፈረሳን እንዲሁም የነባር ሃይማኖቶች ላይ የሚደርሰውን የኦሮሙማ ሀገርና ታሪክን የማጥፋት ዘመቻ በመቃወም ብዙ ቅርሶች እንዳይፈርሱ  ለማድረግ ችሏል።  ለገሃር የሚገኘው የይሁዳ አንበሳ ሃውልት፣ በተለምዶ ሴጣን ቤት ተብሎ የሚጠራውን በምኒልክ ዘመን የተከፈተውን የመጀመሪያውን ሲኒማ ቤት፣ እንዲሁም የአንበሳ በድሃኒት ቤት እንዳይፈርሱ ለማድረግ ችሏል።  እነ ብርሃኑ ነጋና  አንዳርጋቸው ጽጌ አውሬው እግር ስር በመውደቅ የአዲስ አበባን ህዝብ ተስፋ በአደንዛዥ ቀቢፀ-ተስፋ ባንዳዊ-ምሁራዊ ምላሳቸው እንዲፋዘዝና በአውሬው እጅ ሥር ቀስ በቀስ ሙሉ በሙሉ ሞራሉ ላሽቆ(demoralized) ኾኖ እንዲወድቅ አድርገዋል።  በዚ ክህደታቸው የአዲስ አበባን ህዝብ እንዲሁም የኢትዮጵያን ህዝብ ከፍተኛ ዋጋ እንዲከፍል አድርገውታል።  እስክንድር ነጋ ‘አዲስ አበባን እናድን’ ፣ ‘ኢትዮጵያን እናድን’፣ ‘ተረኝነት እንጠየፍ’ ፣ ‘ቅርሶችን እናድን’ እያለ የአዲስ አበባን ህዝብ ሲወተውት፣ በጊዜው ሰሚ ባለማግኘቱ  ለግፍ እስርና እንግልት ተዳርጓል። ታሪክ እራሱን መድገሙ ስለማይቀር እነ ብርሃኑ ነጋ ከሥልጣን   ማማ ላይ ወርደውና ተዋርደው እንደ አሮጌ ጫማ አውሬው እንደሚወረውራቸው የሚጠበቅ ነው። ከነብርሃኑ በተጨማሪ የአዲስ አበባ ኦርቶዶክሳዊ ህዝብ ቅስሙ ተሰብሮ በራሱ ምንም ማድረግ የማይችል ሞራሉ የተሰበረ ማህበረሰብ (demoralized socity) እንዲኾን   የመጨረሻውን ሚስማር የመቱት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን ውስጥ  ሰርገው የገቡ እምነታቸው የማይታወቅ የሃይማኖት አባት ነን ባዮች ናቸው። ቤተክርስትያኗን ከውስጥ ኾነው ለማፍረስ  የተሰገሰጉት እነዚይ ቆብ የጫኑ ማፍያዎች፤ ቤተክርስትያን  እራሷን ለማዳን በጠራችው ሠልፍ ድፍን የአዲስ አበባ ህዝብ በነቂስ ጥቁር ለብሶ ይኽን የአውሬ መንግሥት ሊመነግለው ቆርጦ ሲነሳ ፣ በመጨረሻ ሰአት ለሃይማኖትና፣ ለቀኖና  ሳይኾን ለአውሬው ገንዘብ  የተገዙት ሰርጎ ገቦች ሰልፉን በማስቀረት የኦሮሙማውን የአውሬ ሥርዓት ታድገውታል። በዚህም ምክንያት የአዲስ አበባ ህዝብ በሃይማኖት አባቶቹ ላይ ያለው እምነት እንዲላላ አድርገውታል።  የአዲስ አበባ ህዝብ ይህ ጽሑፍ እየተፃፈ ባለበት ወቅት እንደ እስክንድር ነጋ ያለ ድምጽ የሚኾነው መሪ፣ ተከራካሪ አጥቶ፤ እንኳን የሀገር ቅርስ ሊያድን፣ ከልጅነት እስከ እውቀት ከኖረበት ሰፈሩ እየተጠረገ ቤቱ በላዩ ላይ እየፈረሰ ይገኛል።  እስክንድር አንድ በቅርስነት የተመዘገበ መድሃኒት ቤትና የመጀመሪያው በምኒልክ ጊዜ የተሠራውን የሴጣን ቤት በመባል የሚታወቀውን የሲኒማ አዳራሽ ብቻውን ተሟግቶ እንዳይፈርስ ሲያደርግ። ያኔ ዳር ቆሞ ያየውና የተዘናጋው አዲስ አበቤ ዛሬ አውሬው ድፍን ከተማውን መነቃቅሮ ሲያፈርስ፤ በተለይ መሃል ፒያሳን  ውቧን የድሮ ከተማ  መነቃቅሮ ሲንዳት፣ ማን ይናገረው?። የአዲስ አበባ ህዝብ ሚው! ቢል እስክንድር ከየት ይምጣ። የአዲስ አበባ ህዝብ አርቆ አሳቢውን እስክንድርን ሰምቶት ቢኾን ኖሮ አሁን እየኾነ እንዳለው አቅመቢስ(helpless) ኾኖ ከተማው ስትወድም ቁጭ ብሎ አያይም ነበር።  የአዲስ አበባ ህዝብ በአሁኑ ሰዓት  ”እየመጡ ነው” እያለ በተስፋ ፋኖን  መጠበቅ ብቻ ኾኗል ተስፋው። አዎ ፋኖዎች ይመጣሉ፤ ግን ግን፣ ይህ ምኞት እውን እንዲሆን ለፋኖዎቹ ለነ እስክንድር ነጋ የአዲስ አበባ ህዝብ የሚችለውን ሁሉ ድጋፍ መስጠት ይጠበቅበታል። ዝም ብሎ ፋኖ ፋኖ ማለት ብቻ፤ በቂ አይደለም።  የአዲስ አበባ ህዝብ አሁንም ቢሆን ብዙ አቅም ያለው ህዝብ ነው።  ፋኖ ከዲያስፖራው ከሚያገኘው የገንዘብ ድጋፍ በተጨማሪ እጥፍ የኾነ የገንዘብም ኾነ የቁሳቁስ ድጋፍ ማድረግ ይችላል። የአዲስ አበባ ህዝብ እስካሁን ከሞራል ድጋፍ ውጪ ለፋኖ ምንም ድጋፍ እያደረገ አይደለም።   አንድ ሚሊዮን የአዲስ አበባ ነዋሪ በተለይ አማራው በዘመዶቹ በኩል ወደ ፋኖ አንድ፣ አንድ ሺ ብር ቢልክ፤ በአንድ ጊዜ ፋኖ አንድ ቢሊዮን ብር ድጋፍ አገኛ ማለት ነው። አማራው በንግድ ባንክና በግል ባንኮች  ወለድ ለማግኘት ካስቀመጠው እየጋሸበ ከሚኼደው ተቀማጭ ገንዘብ ላይ ህሊናው የፈቀደውን ያህል እንዲኹም፤ በተለይ ‘አማራ ባንክ’ ሼር የገዛው  ወደ 135ሺ የሚጠጋ አማራ  በራሱ ተነሳሽነት ቢያንስ አንድ፣ አንድ ሺህ ብር  እያወጣ፤ ነጻ ሊያወጣው ደሙን እያፈሰሰ ላለው ለፋኖ መላክ ይኖርበታል።   የፋኖ አደረጃጀትም ገንዘብ ድጋፍ ምንጩን ከዲያስፖራው ብቻ ማድረጉን ትቶ የአዲስ አበባን ህዝብ በዘመዶቹ በኩል የገንዘብ ድጋፍ እንዲያደርግ መጠየቅ ይኖርበታል። ይኽ መኾን ከቻለ አማራውም ኸነ አዲስ አበባ፣ ከአውሬው መዳፍ የምትላቀቅበት ጊዜን ማቅረብ ይቻላል።   ከንፈር በመምጠት የሚገኝ ነፃነት የለም። አዲስ አበባ  መንፈሳዊ፣ ታሪካዊና፣ ቅርሳዊ ገጽታዋ  ፍጹም ደብዝዞና ጠፍቶ የሰው ስጋ የለበሱ ሴጣኖች መናኽሪያ ከመኾኗ በፊት ፋኖዎች  “እየመጡ ነው” የሚለውን እውን ለማድረግ መረባረብያው ጊዜው አሁን ነው። የአዲስ አበባ ህዝብ ባለውለታውን ፋኖ እስክንድር ነጋን የሞራልና በፕሮፖጋንዳ ጦርነት ድጋፍ ሊሰጠው የሚገባውም ጊዜው አሁን ነው።

እስንክንድርና የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ 

እስክንድር ነጋ ኢትዮጵያ ላይ ጎጠኞቹ  ወያኔዎች  በአማራ ጥላቻ ላይ ተመሥርተው የዘረጉትን የብሔር ፖለቲካ ጠንቅቆ ገና ከጅምሩ በመረዳት ፤  ወያኔዎችን በብዕሩ በመታገል ኢትዮጵያ ወደ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት የምትሸጋገርበትን  መንገድ ለማምጣት  ለ27 ዓመታት ሠላማዊ፣ የብዕር ተጋድሎ አድርጓል። እስክንድር ወያኔን የታገለው በሀገር ውስጥ  ያሳትማቸው በነበሩ ህዝብን ለትግል በማነሳሳትና፣ ህዝብ ለነፃነቱ  እንዲታገል መብቱን ሳይፈራ እንዲጠይቅ ያደርጉ በነበሩ ጋዜጦቹ ብቻ አልነበረም። እስክንድር በዓለም አቀፍ ደረጃ በቀዳሚነት በሚታወቁ  የጂኦፖለቲክስ ስትራተጂስቶችና ፖሊሲ ቀማሪዎች(policy makers) እንደ ደ/ር ሄነሪ ኪሲንጀር፣ ዚብግኒው ቤረዞቭስኪ ፣  ሳሙኤ ሃንቲንግተን፣ ሮበርት ካጋን ፣ ፍራንሲስ ፉኪሃማን የመሳሰሉ ሃሳብ አፍላቂ ልሂቃን(thinkers)፤ ሃሳባቸውን    በሚጽፉባቸው፣ በመላው ዓለም የሚገኙ የፖለቲካ ልሂቃን የሚከታተሉዋቸው እንደ ኒውዮርክ ታይምስ፣ ዘ ኒውዮርከር፣  ዋሽንግተን ፖስትን የመሳሰሉ ጋዜጦች ላይ፣ በእንግሊዘኛ ቋንቋ ያሳትማቸው በነበሩት ደረጃቸውን የጠበቁ ምሁራዊ ጽሁፎቹም ጭምር ነው።  እስክንድር አምባገነኑ የወያኔ  ጎጠኛ ሥርዓት  በህዝብ ላይ ያደርሳቸው የነበሩትን ኢሰብአዊ የመብት ጥሰቶችና ረገጣዎች በማጋለጥ፤ ምእራባውያኑ ትኩረታቸውን በኢትዮጵያ ህዝብ  ህመምና ስቃይ ላይ፣ እንዲያደርጉና፤ በኢትዮጵያ ውስጥ  ሰላማዊ የዴሞክራሲያዊ ለውጥ እንዲመጣ፣ ተፅዕኖ እንዲያደርጉ በማድረግ ፤   በሃገራችን ተወዳዳሪ በሌለው ሁኔታ ምሁራዊ ግዴታውን ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል  የተወጣ የነጻው ፕሬስ ጀግና ነው። ለዚኽም ነው እስክንድር ነጋ ታላላቅ ዓለም አቀፍ ሽልማቶችን  ለማግኘት የቻለው።  እስክንድር ነጋን በመናገር ነጻነት፣ በዲሞክራሲ ታጋይነት፣ በሰብዓዊ መብት ተሟጋችነት፣ በአክቲቪዝም ፣  በእውነተኛና ሀቀኛ የፖለቲካ መሪነት፣ አሁን ደግሞ ፋኖን በአማራ ህዝባዊ ሠራዊት ሥር  በማስተባበርና አንድ አድርጎ የመሪነት ሚናን በመጫወት ተደራራቢ ትግሎችን  በማድረግ የሚስተካከለው አንድም ኢትዮጵያዊ የለም። እስክንድር ህይወቱን ለሀገሩ ኢትዮጵያ አሳልፎ የሰጠ የነጻነት አርማ ነው። እስክንድር በዚኽ  የትግል ጽናቱ  ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ  ካገኛቸው ሽልማቶች  በጥቂቱ ብንጠቅስ፦

  1. በ2012   PEN/Barbara Goldsmith Freedom to Write Award፤
  2. በ2014 World Association of Newspapers’ Golden Pen of Freedom Award፤ 
  3. በ2017 International Press Institute World Press Freedom Hero፤ 

      4.በ2017 Oxfam Novib/PEN Award፤ ይገኙበታል።

 ላለፉት 30 ዓመታት በምእራባውያን ተጽእኖ ሥር  የወደቀው የኢትዮጵያ  ፖለቲካን፣ ከእስክንድር እኩል የሚያውቁ ፖለቲከኞች በጣም ጥቂቶች ናቸው።  እስክንድር በዚኽ ረገድ የፋኖን የህልውና ትግል ዳር ለማድረስ በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ያለው እውቅና ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል። እስክንድር በመላው አማራ ህዝብ ልብ ውስጥ ያለ፣ በመላው ኢትዮጵያ ህዝብ  አእምሮ ውስጥ የሚመላለስ ፣ዲያስፖራው እምነቱን የጣለበት፣  በአዲስ አበባ ህዝብ  አንጀት ውስጥ  በቁጭት የሚብላላ፤ ከትልቅ ከተደራጀ  ጦር በላይ ኃይልና ቁመና ያለው፣ የአማራውን ትግል ዳር አድርሶ ኢትዮጵያን የማዳን ተስፋን የሰነቀ ተወዳዳሪ የሌለው ታላቅ ኃይል ነው።ይህን የነጻነት አርማ ፈንጣቂ እንቁ የአማራ ልጅ፣ ኩሩ ኢትዮጵያዊ ጀግናውን፤   ከእነ ከርስ ቁምነገሩ ኾዳም አማሮች(ብአዴናውያን)ና ከጞጠኛ አውሬው የኦሮሙማና የህወሃት ተከፋዮች ፕሮፖጋንዳ እራስን በመጠበቅ፣ ከዚኽ ታላቅ ሰው ጎን በተጠንቀቅ በመቆም፣  ለአማራ ህዝባዊ ሠራዊት የሚያስፈልገውን እርዳታና እገዛ ሁሉ  ማድረግ፤  ኢትዮጵያን እወዳለሁ  ከሚለው ኢትዮጵያዊ ሁሉ፣  በተለይ ደግሞ የአማራን የህልውና ትግል ከተቀላቀለውና ድጋፍ እየሰጠ ካለው አማራው ወገን  የሚጠበቅ ነው። 

እስክንድር  ፋኖነት የታወቀው ዛሬ አይደለም

እስክንድር  በፋኖነት የሚታወቀው አዲስ አበባን ለቆ ወደ ሸዋ ኼዶ ፋኖዎችን ከተቀላቀለ በኻላ አይደለም።  እስክንድር  እስር ቤት እያለም ያሳስበው የነበረው፤    መሳሪያውን እንደያዘ ሸኔን የተቀላቀለው ፀረ-አማራ አጥፊ ጨካኝ አረመኔ የኦሮሚያ ልዩ ኃይልን፣ የአማራ ፋኖ ተጠናክሮ እንዴት መመከትና አማራውን ከጭፍጨፋ ማዳን እንደሚችል  ነበር። እስክንድር  ይህን ሃሳቡን ለማሳካት በእስር እያለ፤ ለፋኖዎች የሞራልና የቁሳቁስ ድጋፍ አንዲደረግ አድርጓል። በጎጃም ለሚንቀሳቀሱት ፋኖዎች ከእስክንድር የተላከውን እርዳታ በጎጃም ባህርዳር ፋኖ  ዘመነ ካሴ ሲቀበል፤  ‘እስክንድር ነጋ መሪዬ ነው’ ፣ ነበር ያለው።  በጎንደር አርበኛ ፋኖ ሻለቃ መሳፍንት  ‘እስክንድርን ካልኾነ በነፍጥ እናስፈታው’  ነበር ያሉት።  እስክንድር ነጋ በአውሬው ኦሮሙማ፣  የእግሩን ጣት እስከመሰበር ከደረሰበት የአንድ ዓመት ከሰባት ወር እስር በዃላ ከእስር ሲፈታ፤ አሜሪካን ልጄንና ሚስቴን ልይ ብሎ አላለም፤ ቅድሚያ የሰጠው  የቀናት እረፍት እንኳን ሳያደርግ  ወደ ጎንደር፣ ጎጃም ወሎና  ሸዋ በመዘዋወር የፋኖን እንቅስቃሴ ለማበረታታትና አንድ ለማድረግ፣   ቆራጥ ታጋዮችን፤ አሁን በእስር የሚገኘው ስንታየሁ ቸኮል፣ አሁን ሜዳ ላይ ነፍጣቸውን  አንግበው ህዝብን የማንቃትና የማደራጀት ሥራውን እየሠሩ ያሉትን ጀግኖቹን እነ ፋኖ ጌጥዬ ያለውንና ፋኖ ወግደረስ ጤናውን ጨምሮ ሌሎች ጀግኖች፤ የባልደራስ የሰላም ታጋዮችን ይዞ ነበር።   እስክንድር ከእስር ከተፈታ በዃላ  በሸዋ በተደጋጋሚ ተመላልሶ የፋኖ ሥልጠናዎችን ጎብኝቷል፣ ፋኖዎችን አበረታቷል።ፋኖ አሰግድ ለእስክንድር ነጋ የአስማረ ዳኜን ምሥል በስጦታ በሠልጣኝ ፋኖዎች ሥም ያበረከተለት ገና የፋኖ ትግል እንደዛሬው  ጎምርቶ የአውሬውን መንግሥት ማስጨነቅ ሳይጀምር፣ አሜሪካን ሀገር ከመሄዱ በፊት ነበር።  

እስክንድር ከአሜሪካን ቤተሰቡን አይቶ ተመልሶ የመጣው ይኼንኑ  ቀድሞ የጀመረውን በጎንደር፣ በሸዋ፣ በወሎ እንዲሁም በጎጃም የሚገኙ ፋኖዎችን ለማስተባበርና አንድ ለማድረግ ነው። እስክንድር ፤ የአውሬውን  የፖለቲካ ቁማር ስሌት ጠንቅቆ የሚያውቅ ነው። አውሬው መከላከያ ሠራዊቱን ተጠቅሞ ቀድሞውኑ ትግራይን በሻሻ እንደደረጋት ኹሉ፤ ፋኖና የአማራ ልዩ ኃይል የህወሓትን ጦር ከመኻል ሀገር ገርፈው ካባረሩት በዃላ፣   ፊቱን አማራው ላይ በማዞር አማራውን በሻሻ ለማድረግ እንደሚሠራ፣  እስክንድር ቀድሞ አውቆታል።  አውሬው ነፍስ አልባው ብአዴንን ተጠቅሞ የአማራ ልዩ ኃይልን ትጥቅህን ፍታ፣ ፋኖን ትጥቅህን ፍታ ያለው፣   አማራን በሻሻ ለማድረግ ነበር።  በዚኽ ቀውጢ ጊዜ እስክንድር አዲስ አበባን ቀድሞ ለቆ በሸዋና በጎጃም በመንቀሳቀስ፤ ህዝብን ለትግል ሲያነቃና ሲያደራጅ፣  ፋኖዎችን ሲያበረታታና  በአንድነት በተናበበ መልኩ እንዲሠሩ ለማድረግ የሚችለውን ሁሉ ሲያደርግ ነበር።  እስክንድር ይኽን ዓላማውን ለማሳካት እስትራተጂካዊ  እሳቤን በማመንጨትና ሥመጥር ምሁራንን   ከዲያስፖራው ወገን በፊት አውራሪነት በማሰለፍ   ”የአማራ ህዝባዊ ግንባር”ን አቋቁሟል።  የአማራ ህዝባዊ ግንባር መቋቋም የአማራ ፋኖ ትግል አንዲቀጣጠል እንዲጎመራ በር ከፍቷል። የሸዋ፣ የጎንደር፣ የወሎ፣ የጎጃም ፋኖዎች ከተሞችን መቆጣጠር ደረጃ የደረሱት ግንባሩ ከተቋቋመና ከፍተኛ የሞራልና የገንዘብ ድጋፍ ከዲያስፖራው፣ ምግብና የቁሳቁሰ ድጋፍ ከገበሬው እንዲሁም ከአዲስ አበባ ህዝብ የሞራል ድጋፍን ማስግኘት ስለ ቻለ ነበር።  

የእስክንድርናነብስ አልባው ብአዴን የአማራ ትግል ላይ ያደረሰው ተጽእኖ

እስክንድር ነጋ ደጋግሞ የሚናገረው አማራው ብአዴንን ይዞ ነፃ መውጣት እንደማይችል ነው። ይሄ ደግሞ ትክክል ነው።  አዲሱ ትውልድ ከብአዴን ተላላኪ ስብእና ኾድ አደር የድንቁርና  አመራር  ሳይላቀቅ፤ አማራም ኾነ ኢትዮጵያ ነፃ መውጣት አትችልም።  የኢትዮጵያን ህዝብ  በዋናነት አማራውን ሲያስጠቃ የኖረው ብአዴን ነው። እንደ ብአዴን ያለ ጠንቀኛ ቡድን በአማራው ላይ በአማራ ስም፣ ባይጫንበት ኖሮ አማራው እራሱን አይደለም ኢትዮጵያን ከዘረኞች መንግጋጋ በቀላሉ ላቀቀ ነበር። በወጣት የተማሩ ኃይሎች የተቋቋመው አማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አ.ብ.ን) እራሱን ከብአዴን ንክኪ ማላቀቅ ባለመቻሉ አመራሮቹ ገሚሶቹ አማራው ወጣት ፋኖ ደሙን እያፈሰሰ ባለበት በአሁኑ ወቅት አውሬውን እያጀቡ የሰጣቸውን የደም ሥልጣን እያጣጣሙ ይገኛሉ። የአውሬውን አካሄድ በሚገባ ባለመረዳት አውሬውን በክርክር እንሞግታለን እናሳምናለን ያሉት የዋኽ የአብን አመራሮች እነ ክርስትያን ታደለና ደ/ር ደሳለኝ ጫኔ  ደግሞ እስር ቤት በግፍ እየተንገላቱ ይገኛሉ።  ከብአዴን ጋር ተነካክቶ አማራን ስቃይ መታደግ፤ መጻኢ እድሉን ማቃናት እንደማይቻል የሚያውቀው እስክንድር ነጋ፤ ዛሬ ሜዳ ወርዶ ትግሉን በማገዝና በማፋፋም ላይ ይገኛል። በትክክለኛው ሰዓት በሚገባው ቋንቋ አውሬውን ማስጨነቁን ቀጥሏል። ለ30  ዓመታት  ለወያኔ የአሽከርነት አገልግሎት በመስጠት፣ አማራውን ሲያስደቁስ የኖረው ብአዴን፤ አሁን ደግሞ አማራን እየጨፈጨፈ ከምድረ-ገጽ ለማጥፋት የተነሳውን የኦሮሙማ አውሬ  መንግሥት በመደገፍ የፋኖን ትግል ጠልፎ ለማኮላሸት እየተሯሯጠ ነው። ጀግናው  ጀነራል አሳምነው ጽጌን ለአውሬው ኦሮሙማ መሪ  አሳልፎ የሰጠው፣  ይሉምታ ቢሱን  ብአዴንን አምኖ፤ የትግል አጋር ለማድረግ ማሰብ በአሳምነው ላይ የደረሰውን ክህደት በአዲሶቹ የፋኖ መሪዎች ላይ ለመድገም ከማሰብ ተለይቶ አይታይም። አማራ የሃምሳ ዓመት የውድቀት ታሪኩን ለመቀየር ፋኖ ኾኖ ተነስቷል። ይህም የአማራ ህዝብ ትግል ዳር የሚደርሰው ብአዴንን  የሚፀየፈው ፋኖ፣ወደ አዲስ አበባ በመገስገስ ጠላቱን ድል አድርጎ የማእከላዊ መንግሥት ሥልጣንን በእጁ ሲጨብጥ ብቻ ነው።  የአማራ ህዝብ ብአዴኖች ቆዳቸውን ገፈው በፋኖ ጀርባ ላይ ተንጠልጥለው ጫንቃው ላይ ዳግም እንዲቀመጡበት አይፈልግም። እስክንድር ብአዴኖችን ገለል ብለው ንስሃ እንዲገቡ የመከራቸው፣ በመጪው ትውልድ ውስጥ የብአዴን ውራጅ ስብእና በአማራ ማህበረሰብ ውስጥ እንዳይተላለፍ በማሰብ ነው።  

እስክንድርና ግንባሩ/አማራ ህዝባዊ ሠራዊት ላይ እነማን ተነሱበት? ለምንስ ተነሱበት?

እስክንድር  በአማራው ትግል ላይ ያለውን ሚና ለማጣጣል የሚሞክሩ ኃይሎች በአራት ሊጠቃለሉ ይችላሉ፦  

  1. እስክንድር ላይ በዋናነት  ዘመቻ እያደረጉበት ያሉት በብአዴን ተጽዕኖ ውስጥ የወደቁ በተናጠልና በድርጅት በአማራ ሥም የተቋቋሙ፣  ትግሉን መጨረሻ ለማድረስ ብአዴንን ሳንይዝ ሊሳካ አይችልም የሚል አስተሳሰብ ላይ የደረሱ የጋዜጠኞች፣ የአክቲቪስቶች፣ እንዲሁም የምሁራኖች ስበስብ ነው። እነዚህ ኃይሎች አውሬውን የኦሮሙማ ኃይል ከአማራ ክልል ነፃ ለማውጣት የሚቻለው ቀናኢ ከኾኑ  ብአዴኖች ጋር አብሮ በመሥራት ነው የሚሉ ናቸው።  እነዚኽ ኃይሎች ከብአዴን አካላት  ጋር ንክኪ የፈጠሩና የብአዴንን  ኔትወርክና ሰዎች ተጠቅመው  እንቅስቃሴ ሲያደርጉ የነበሩ ናቸው። እነኚኽ ኃይሎች  የፋኖ መሪዎችን በዚኽ አስተሳሰብ ለማነፅ ሲሠሩ የነበሩም  ናቸው። እነዚኽ ኃይሎች የአውሬውን መንግሥት አዲስ አበባ ድረስ ዘምቶ ለመጣል የሚደረግ ትግል አዋጪ  አይደለም የሚሉና   ከአውሬው ጋር በሚደረግ አስገዳጅ ድርድር የሚያምኑ የአማራው ጥያቄ የብአዴንን ጉልበት በአዲስ መልክ በአማራ ክልል በማጠናከርና በመጠቀም    በድርድር ይፈታል የሚል ሃሳብን የያዙ ናቸው። ልክ ኦህዴድ ብአዴንን ተጠቅሞ   ህወሓትን ሥልጣን የቀማበትን ዘዴ አይነት መኾኑ ነው።  እነኚህ ኃይሎች  አሁን በሀገር ውስጥ በአብዛኛው በእስር ላይ ያሉት በዶ/ር ወንዶሰን የሚመራው ኃይል ሲኾኑ ሌላው በውጪ የሚገኘው በእነ አቶ ቴዎድሮስ እና በእነ አቶ  ጌታቸው  የአማራ ማህበር በሰሜን አሜሪካ (AAA)  የሚመራው ነው። ይኽ ኃይል  አማራው በብአዴን ተሳታፊነት በአሜሪካኖች አደራዳሪነትና ጣልቃ ገብነት ካልኾነ አማራው ነፃ ሊወጣ አይችልም ብለው የሚያምኑ ኃይሎች ናቸው።   ሌሎች በተናጥል ሃሳቡን የሚደግፉ ምሁራኖች እንደነ አቻሜለህና ደ/ር ሃብታሙም የመሳሰሉ ይገኙበታል።  እነዚኽን ኃይሎች ከእስክንድር  ህዝባዊ ግንባር አሁን  የአማራ ህዝባዊ ሠራዊት ጋር የሚለያቸው ዋና ጉዳይ አደባባይ ወጥተው ግልፅ አያድርጉት እንጂ ብአዴንን የትግሉ አካል አድርገው የመሥራታቸው ጉዳይ ነው። ይሁንና እነዚኽ ኃይሎች ከእስክንድር ጋር የግል ፀብ ያላቸው አይደሉም የስትራተጂ ሠፊ ልዩነት ግን አላቸው። እነዚኽ ኃይሎች በጥገናዊ ለውጥ ዙሪያ እስክንድርን አስገብተው  ከዚህ ቀደም ለመሥራት የሞከሩ ቢኾንም ይህ የስትራተጂክ እሳቤያቸው ከእስክንድር ሥር ነቀል ለውጥ እሳቤ ጋር የሚጣጣም ባለመኸኑ  በእስትራተጂ ልዩነት ብቻ የተለያዩ ናቸው። ከብአዴን ጋር ተጣብቆ ከመምከን ይልቅ እራሳቸውን ለስር ነቀል ለውጥ አዘጋጅተው ከግንባሩ/ከአማራ ህዝባዊ ሠራዊት ጋር መሥራት ከቻሉ ትግሉን በፍጥነት ዳር ለማድረስ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ሊያደርጉ ይችላሉ።  
  2. ከላይ ከተጠቀሱት ኃይሎች  ሃሳብ ላይ ተንጠልጥለው የፋኖንና  የአማራው ትግል የሚያሳስባቸው የሚያስመስሉ  በሜዲያ የተደራጁ እንደ አንከር  ሜዲያና  ቲቪ ዙሪያ የተሰባሰቡ ቀድም ሲል ለአውሬው  ሎሌ ኾነው ማገልገልን የፈቀዱ  ኃይሎች ናቸው። እነዚኽ ኃይሎች ግንባሩንም ኾነ እስክንድርን በቀጥታ ሳይኾን በተለጣፊነት እያጠቁ ያሉ ናቸው።   እነዚኽ ኃይሎች  ከአውሬው ሥርዓት ጋር አሁንም ቢኾን ግንኙነት ያላቋረጡና የፋኖ ደጋፊ መስለው ለአውሬው መንግሥት እንደሚሠሩ የሚጠረጠሩ ናቸው። የእነዚኽ ኃይሎች  ሞቲቭ ይሄ ነው ብሎ ለመግለጽ ቢያስቸግርም ለአክቲቪስቶቹና ጋዜጠኞቹ ከግል ጥቅም የዘለለ እንደማይኾን መገመት አያዳግትም። እንደ ዶ/ር ዮናስ ብሩ ያሉት ግን ጠለቅ ያለ ግለሰባዊ ከዝቅተኝነት ስሜት  የሚመነጭ የተደበቀ የአማራ ጥላቻን ያዘለ  ሥነልቦና ጋር ሊገናኝ እንደሚችል ከሚጽፉት ጽሑፍ በመነሳት መገመት ይቻላል። የዶ/ር  ዮናስ ብሩ ጽሑፎች በአብዛኛው የግንባሩን/የአማራ ሕዝባዊ ሠራዊት  መሪዎች እስክንደር ነጋንና  ሻለቃ ዳዊት ላይ ያነጣጠሩ መኾናቸው ዶ/ር ዮናስ የአውሬው መንግሥት እንዳይገረሰስ እየሠሩ መኾናቸውን የሚያረጋግጡ ናቸው።  ዶ/ር ዮናስ የእነ ዶ/ር ወንዶሰንን  ስም እያነሱ እንደ ውስጥ አዋቂ በመምሰል ግንባሩን/የአማራ ሕዝባዊ ሠራዊት የማጥላላት ዘመቻ  የከፈቱት በአማራው ኃይሎች ውስጥ ያለውን እስትራተጂካዊ የሃሳብ ልዩነት  ወደ ለየለት ክፍፍልና መወነጃጀል ብሎም ወደ መጠላለፍና መጠፋፋት እንዲያመራ ለማድረግ በማለም መኾኑ ግልጽ ነው።
  3. ሦስተኛው ቡድን ከዳር ኾኖ የሚመለከተውና አሜሪካኖች ድርድር አመቻችተው የሥልጣን  ክፍፍል እስኪያደርጉ የሚጠባበቀው ግሩፕ ነው። ይኽ ግሩፕ አሜሪካ የተሰባሰባውን የእነ ይልቃል ሮኻ ሜዲያ ግሩፕ እንዲሁም የልደቱ አያሌው ግሩፕ ነው። ይኽ የፖለቲካ ኃይል የቀደመ የፖለቲካ ትግል ታሪኩ ላይ በመመርኮዝ  በአሜሪካኖች እውንታ ወደ ሥልጣን ለመምጣት፣ ለዘመናት ሲሠራና ሲጠባበቅ የኖረ ቡድን ነው። አሁን አሜሪካኖቹ እየገፋፉ ያሉትን ድርድር መሬት ላይ ያለው የፋኖ ኃይል እንዲቀበል በየሜዲያው በተዘዋዋሪ ቋንቋ የሚወተውቱ  በድርድሩ ተሳታፊ በመኾን በመጪው መንግሥት ውስጥ ሚና እንዲኖራቸው ተስፋ ያደረጉ ናቸው።  የዚኽ አላማቸውን ለማሳካት  እንቅፋት ኾኖ ያገኙት የግንሩን/የአማራ ሕዝባዊ ሠራዊት  ድርድር የለም፤ ድርድድር የሚኖረው  ፋኖ  አውሬውን የኦሮሙማ መንግሥት አስወግዶ አራት ኪሎ የምኒልክ ቤተመንግሥትን ከተቆጣጠረ በዃላ ነው የሚለው  ቆራጥ አቋም ነው። ለዚኽም ነው በተለያየ ጊዜ የእስክንድርን እና የግንባሩን/የአማራ ህዝባዊ ሠራዊት በአማራው ትግል ላይ ያለውን የፖለቲካ ሚና በተዘዋዋሪ የሚያጣጥሉ አስተያየቶችን የሚሰጡት። በነዚኽ ኃይሎች ወቅታዊ  የፖለቲካ ግንዛቤ አውሬው  የኦሮሞ ህዝብ ድጋፍና የማይነቀነቅ ኃይል አለው ስለኾነም ፋኖ አራት ኪሎን ለመቆጣጠር ያዳግተዋል ወደሚል ድምዳሜ የደረሱ ይመስላል። በመኾኑም፣ እንደ አማራጭ አሜሪካኖችን አምኖ በሚያደላድሉት በድርድር የሚገኝ የሥልጣን ክፍፍልን በጉጉት መጠባበቅን መርጠዋል። እነዚኽ ኃይሎች አውሬው የሚነቀነቅና በፋኖ ምት የሚወድቅ   እንደኾነ መገንዘብ ቢችሉ፤ በፕሮፖጋንዳው ዘርፍ ለፋኖ ከፍተኛ ኃይል መኾን በቻሉ ነበር። በተለይ አማራውን ደጋፊ በመምሰል የፋኖን ትግል ከፋፍሎ ለማዳከም  እየተጋጋጡ ያሉትን  ከአንከር ሜዲያ ጀርባ የተሰባሰቡትን እንደ ደ/ር  ዮናስ ብሩ ያሉ መሰሪ ጸረ-አማራ ኃይሎችን አፍ የማዘጋት አቅም ነበራቸው።
  4. በአራተኛ ደራጃ ያሉት አክቲቪስቶች ናቸው። እነዚኽ አክቲቪስቶች አብዛኛውን ጊዜ  ዓላማቸው ገንዘብና ገንዘብ ስለኾነ  ወደከፈላቸውና ወዳደላበት እጥፍ ለማለት ችግር የሌለባቸው ናቸው።  በአሁኑ ወቅት አውራ ከሚባሉት አክቲቪስቶች ውስጥ ቅሌት ውስጥ የገባው ዘመድኩን በቀለ ነው። ዘመድኩን በቀለ መለፍለፍ ይችላል፣የለፈለፈውን ይጽፋል። ሌት ተቀን የሚለፈልፈው   ከፋዮቹ(his owners)  በዘረጉለት መስመር ይዘውሩታል። ዘመድኩን በቀለ የሚታወቀው በግፍ አማራው ላይ የሚደርሱ ግድያዎችን የሚያሳዩ ዘግናኝ ቪዲዮዎችን በመልቀቅ ነው። ወፎቼ እና ጀነራሎቼ በሚላቸው በአሜሪኖቹና በኦሮሙማው ቡድን ‘ከቻልክ አሳምነው ካልቻልክ አደናግረው’ (Convince or Confuse) ኤጀንቶች መረጃዎችን በደቂቃና በጥቂት ሰዓታት አንዳንዴም በሰከንድ ልዩነቶች እየተቀበለ ለህዝብ ያሰራጫል። የነዚህ ኃይሎች የሳይኮሎጂካል ጦርነት፤  የህዝብን አእምሮ የማላሸቅ (Demoralization)  ለረጅም ጊዜ በመሥራት የሞራል ውጊያ መሳሪያ ኾኖ አገልግሏል። ዘመድኩን ይህን የረቀቀ የሞራል ውጊያ ሲሠራ ሀገሩን ያዳነ ገዳዮችን ያጋለጠ ሊመስለው ይችላል። ነገር ግን፣  ህዝብን ከሞራል ውጊያና አእምሮን ከማላሸቅ ዘመቻ  አንፃር ምን መገደብ ምን መተላለፍ እንዳለበት የሚያውቅ ባለመሆኑ፤ ብሎም ህዝብ እንዴት ከእንደዚህ ካሉ አረመኔያዊ ጥቃቶች  እራሱን መከላከል እንደሚችል ማስተማርና  ማንቃት የሚያስችል  ፖለቲካዊ እውቀትና ግንዛቤ ስለሌለው፤ በዘፈቀደ የመጣለትን ሁሉ እንደመሰለው እየለቀቀ ህዝብ እራሱን መከላከል በማይችልበት ሁኔታ በላይ በላዩ አሰቃቂ ግድያዎችን በመልቀቅ ቀላል የማይባል፤ ህዝብ ላይ የሞራልና የተስፋ መቁረጥ የፍርሃት ድባብ እንዲጫነው ተጽእኖዎችን ፈጥሯል። አሁን አዲስ አበባ ላይ፣ መሃል ፒያሳ ሲፈርስ ህዝቡ ምንም የመከላከል  ፍላጎት ያላሳየው፤ እንደዚኽ ባሉ ቀን በቀን በሚሠራጩ ፤ ማህበረሰብን ተስፋ ለማስቆረጥ በተከፈቱ የሥነልቦና ጦርነቶች ሰለባ በመኾኑ ነው።   ዘመድኩን በቀለ አሁን ደግሞ  የእስክንድርን ሥም እያነሳ ማብጠልጠል ጀምሯል። የአማራን ትግል አግዛለኹ ብሎ ኡ ኡ ሲል የኖረበትን መስመር ትቶ፤ የአማራን ትግል የሚበታትን  ሴራ  ዋና ተሳታፊ እየኾነ ነው። ይህ ዘመቻ  ወፎቼ የሚላቸው የአሜሪካኖቹና ግሎባሊስቶቹ ፍላጎት(interest) ከማስጠበቅ አንፃር የተቀናጀ ዘመቻ አካል ይመስላል።  በሁሉም የአማራ ጠቅላይ ግዛት በወሎ፣በሸዋ፣በጎንደር፣ በጎጃም የሚገኙ  ፋኖዎች ዘንድ እንዲኹም በአዲስ አበባ ህዝብና በዲያስፖራው ማህበረሰብ ከፍተኛ ተቀባይነትና ተወዳጅነት ያለውን ብቸኛው የአማራ ፋኖ ህዝባዊ ሠራዊት መሪ እስክንድር ነጋን  ገሸሽ በማድረግና፣  የፋኖን ትግል ወደ እርስ በርስ ወሎ፣ሸዋ፣ጎንደር፣ ጎጃም ፉክክር በማውረድ፤ በእነ እስክንድር እስትራተጂ አንድ ኾኖ እየተገነባ ያለውን የአማራ ፋኖን ከፋፍሎ አቅም በማሳጣት የብአዴን ንክኪ ያላቸውን ጥቂት የተደናገሩ ፋኖዎችንና አሜሪካ የተቀመጡ  የብአዴን ቅምጥ ፖለቲከኞችን  ከአውሬው ጋ ለማደራደር፤ አሜሪካኖች እያደረጉ ላሉት የተቀናጀ እንቅስቃሴ ዋና መሳሪያ ሆኖ እንዲያገለግል እንደ መጨረሻ ካርድ እየተጠቀሙበት ነው። የዘመድኩንን ጉዳይ  ተከታዮቹ በበቂ ሁኔታ፤ የተቃውሞ መልስ እየሰጡት ይገኛሉ። በመሆኑም የመጨረሻ እጣ ፈንታው ህዝብ ዳኛ ይፈርድና ልክ እንደነ ኤርሚያስ ለገሰ፣  ሲሳይ አጌና፣ ታማኝ በየነ  ከአማራም ሆነ ከኢትዮጵያ ፖለቲካ ለዘለቄታው የሚሰናበት ይሆናል።

ማጠቃለያ ሃሳብ

የአማራን የህልውና  ጥያቄ በክልል ጥያቄዎች አጥሮ፣ የአማራን ህልውናን ለዘለቄታው ለማረጋገጥ እንደማይቻል የተገነዘበው እስክንድር ነጋ ”መነሻችን የአማራ ህልውና መዳረሻችን የኢትዮጵያ አንድነት” በሚል መርሕ የትግሉን አቅጣጫ ትክክለኛ መስመር ላይ እንዲገባ አድርጎታል። መነሻችን አማራ ማለት፣ አማራን ከብአዴን ብልፅግና እጅ ማስወጣት፣ ስር የሰደደ የብአዴን የአገዛዝ መረብ መበጣጠስና ”በቃ” ብሎ የተነሳውን የአማራ ወጣት ፋኖ ትግሉን አፋፍሞ አማራውን ከብአዴን ኢትዮጵያን ከአውሬው ኦሮሙማ ጎጠኛ መንግሥት  መንጋጋ  አላቆ  እራሱንና ሀገሩን የሚቀይርበትን መንገድ መቅደድ ነው። ፋኖ የብአዴንን የጥርነፋ መረብ ከአማራው ህዝብ ጫንቃ ላይ ማላቀቅ ከቻለ፣  አማራ  ነፃ ወጣ ማለት ነው። አማራ እራሱን ከራሱ ኾዳም ተላላኪ አስጠቂ የብአዴን ነቀርሳዎች ካላቀቀ  ደግሞ ጉዞውን ቀጥታ ወደ አዲስ አበባ በማድረግ አውሬውን ከሥልጣን በመመንገል ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የባንዶችን እጅ ቆርጦ አማራውን ወደ ቀደመ ክብሩ ኢትዮጵያንና ህዝቧን ወደ ሰላማዊ ኑሮ መመለስ ነው። በመኾኑም፣ በአሁኑ ሰአት እስክንድር ነጋንና የአማራ ህዝባዊ ሠራዊቱን ለመቃወምም ኾነ ለመተቸት የሚነሳ ኃይልም ኾነ ግለሰብ፤ አንድም የገዢው ኦሮሙማ አይዲዮሎጂ አቀንቃኝ፣  የአማራ ህዝብ ቀንደኛ ጠላት ነው፤ አልያም በኢትዮጵያ  ሥም ሲምልና ሲነግድ የኖረ ለሹመት ሲል   ህዝቡን ክዶ አውሬው እግር ስር የወደቀው፣ ያረጠው የፖለቲካ ቡድን ነው። አልያም በወጣት አማራው  ሥም ሲምልና ሲገዘት የነበረ  ለመኪናና ለሹመት፣ የአውሬው እግርን የሳመ፣ ከሃዲ፤ ቀድሞውንም ከብአዴን ጋር ንክኪ የነበረው የጀማሪ አፍላ ፖለቲከኛ ቡድን ነው።   አልያም የመንደር ጎጠኝነት ስሜቱ አሸንፎት፣ ትልቁን የአማራ ፋኖ ህብረት እንዲናድ ለጠላት መሣሪያ እየኾነ እያገለገለ ያለ  ነው፤ አልያም የብአዴንን ፍርፋሪ በልጦበት የገዛ ህዝቡ ላይ መከራን ለመጫን የሚሯሯጥ፣ ህሊናቢስ ‘ኾዳም-አማራ’ ነው፤ አልያም ወዳደላበት በመገለባበጥ ፍራንክ ለቀማን ዋናው ዓላማው አድርጎ የሚሠራ የአክቲቪስቶች ቡድን ነው፤ አሊያም ከላይ በተጠቀሱት ኃይሎች የሀሰት ውንጀላና ፕሮፖጋንዳ ሰበካ ምክንያት ፣ የተደናገረና  እውነተኛ ጀግናውን መለየት የተሳነው፣ መሃል ላይ የሚዋልል ብኩን ኃይል ነው፤ እነዚኽ ሁሉ ተደማምረው፣ የአማራን ፋኖ አንድ አድርጎ ለድል ለማብቃት ሌት ተቀን እየታገለ  ያለውን፣ የፋኖ ህብረት ማእከል የኾነውን  በእስክንድር ነጋ የሚመራውን የአማራ ህዝባዊ ሠራዊት እየታገሉ ያሉ ናቸው።  የእነዚኽ ኃይሎች መሰሪ ሥራና ተግባር መሬት ላይ ያለው አብዛኛው የአማራ ፋኖ የሚያውቀውና እየታገለው ያለው ጉዳይ ቢኾንም፤ ለፋኖ ድጋፍ የሚሰጠው   በመላው ዓለም የሚገኘው የአማራው ዲያስፖራው ማህበረሰብ በነዚኽ መሰሪ ኃይሎች  ፕሮፖጋንዳ ሳይዘናጋ፤ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ሕዝባዊ ሠራዊቱን መደገፍ ያለበት ጊዜ መኾኑን ተገንዝቦ፣ ከብርቅዬው የዘመናችን ወደር የማይገኝለት ጀግና፤ እስክንድር ነጋ ጎን ተሰልፎ የአማራውን ህልውና ለማረጋገጥና የኢትዮጵያን ትንሳኤ ለማቅረብ የሚደረገውን ርብርብ በይበልጥ አጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል። በተለይ የአዲስ አበባ ህዝብ፣ እስካሁን ለፋኖ ይሰጥ የነበረውን የሞራል ድጋፍ ወደ ቁሳቁስና ፋይናንሻል ድጋፍ ጭምር ማሳደግ ይጠበቅበታል።  ጀግናው እስክንድር ነጋ የሚመራውን የአማራ ህዝባዊ ሠራዊት በመደገፍ ፣ የአማራን ህልውና ለማረጋገጥ እንዲኹም አዲሰ አበባን ከጎጠኛው የኦሮሙማ ኃይል መዳፍ ለማውጣትና የኢትዮጵያን ትንሳኤ ለማብሰር በአንድነት ተባብረን መሥሪያው ጊዜው አሁን ነው።

ድል ለጀግኖቹ ፋኖ ወንድሞቻችን ለእነ እስክንድር ነጋ!!! 

 

 

Filed in: Amharic