>

በእኔ እይታ አንድ አገርና ሕዝብ ሉዓላዊ ነው የሚባለው

በእኔ እይታ አንድ አገርና ሕዝብ ሉዓላዊ ነው የሚባለው:-

መምህር ፋንታሁን ዋቄ

1) ሕዝቡ ከትውልድ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣው የአገር ዳር ድንበር ራሱን ችሎና የውጭ እር ዳታ ሳይጠብቅ መጠበቅ ሲችል

2) ሕዝብ በምግብ፣ መድኀኒት፣ መጠለያ ከባዕዳን ጥገኝነት  ነጻ ሆኖ ማረጋገጥ ሲችል፤

3) ሕዝብ የተፈጥሮና ሰው ሠራሽ አደጋ መከላከያ  አቅምና አደጋ ሲያጋጥም ሲያጋጥም ማገገሚያ አቅም የዕውቀት፣ አደረጃጀትና አስተዳደራዊ ሥርዓት፣ ሀብትና ጥበብ ሲኖረው

4) የተፈጥሮ ሀብቱን ያለ ውጭ ባዕዳን ጣልቃ ገብነት ማልማትና መመጠቀም የሚያ ስችለው አቅም ሲኖረው

5) ቤተ መንግሥቱና ቤተ እምነቱ ለእግዚአብሔር፣ ለሕዝብ፣ ለፍትሕ፣ ለእውነት ታማኝ በመሆን ሕዝብን ከማገልገል ውጭ ለሌላ ፍላጎትና ለውጭ ባዕዳን የማይታዘዙ ከሆነ ያ ሀገርና ሕዝብ ሊዓላዊነቱ ከኝግዚአብሔር በታች የተረጋገጠ ይሆናል። በእነዚህ መሥፈርቶ ኢትዮጵያና ሕዝቧ ሉዓላዊነታቸው ተገስሷል።

አብይና ሥርዓቱ፣ ወላጆቹ ወያኔና ኦነግ የባዕዳን አስተሳሰብ የአእምሮ ልጆችና ባሮች በመሆናቸው በሁሉም የሉዓላዊነት ዘርፎች አዋርደዉናል። ሁሉም የሕይወታችን ዘርፎች በአሻንጉሊት የፖለቲካ ልሂቃን አስፈጻሚነት በባእዳን ውሳኔ ይተገበርብናል፦

• የትምህርት ሥርዓትና ይዘት

• ሥርዓተ መንግሥትና ሥርዓተ ማኅበር 

• የጋብቻና የትዳር ትርጉምና አስተዳደር 

• ሰው የመሆን ትርጉም

• የኑሮ ደረጃ ልኬት (ስታንዳርድ)

• የሰላም፣ የጦርነት፣ የመብት፣ የጻነት  ትርጉም 

• የልጅ አስተዳደግ፣ የባልና ሚስ ግኑኝነት 

• የጾታ ትርጉም 

• ስንት በምን ጽድሜ መውለድ እንደሚገባን 

• የሕዝብ ብዛት ገደብ 

• የሃይማኖት እኩልነትና ልዩነት ትርጉም 

• የመሬትና የተፈጥሮ ሀብት አስተዳደር ወዘተ…  በውጭ ይበየናል።

—- የእኛ የፖለቲካ ሥርዓት እነዚህን ተቀብሎ ለማስተግበር እየፈጀንም ቢሆን ታዛዥነቱን ያረጋግጣል።  በዚህ ከወያኔ ቀጥሎ የአብይ አህመድን ኅሊና ቢስ የኦነግ ኦሮሙማ የአፓርታይድ ሥርዓት የሚያስንቅ የለም። በዚህ መሠረት አሁን ከዓለም ባንክና ከዓለም የገንዘብ ድርጅት ተንበርክኮ ትዕዛዝ እየተቀበለ ነው። የአገራችንን እና መነሳት የሕዝባችንን ሉዓላዊነት ለመመለስ የእያንዳንዳችንን ቁርጠኛ ተናስዖት ይጠይቃል። መፍትሔ ሰጭና ነጻ አውጭ መጠበቅ ባርነት ነው። Ethiopia’s Currency Devaluation Plan: A Likely Floodwater? IMF and World Bank Pushing https://borkena.com/2024/06/10/ethiopias-currency-devaluation-plan-a-likely-floodwater-imf-and-world-bank-pushing-while-wfp-is-warning/

 

 

Filed in: Amharic