>

እነ ዘመነ የብአዴንን ነፍስ ለመዝራትና የአውሬውን ዕድሜ ለማርዘም እየሰሩ ነው።

እነ ዘመነ የብአዴንን ነፍስ ለመዝራትና የአውሬውን እድሜ ለማርዘም እየሠሩ ነው!

በ ትግሉ ሠመረ

ዘመነ ካሴና አስረስ ማረ በብአዴን ከለላ ውስጥ ኾነው እንደሚንቀሳቀሱ ብዙ አካላት ቀደም ሲል ጀምሮ ይፅፉና ይናገሩ የነበረ ቢኾንም ብዙሐኑ ፋኖና  የአማራ ሕዝብ መረጃውን ለማመን ተቸግሮ ነበር።   አሁን ግን በይፋ  በፋኖ ሥም የብአዴንን ነፍስ ለመዝራትና የአውሬውን እድሜ ለማራዘም እየሠሩ መኾናቸውን የሚያሳዩ በርካታ መረጃዎች እየወጡ ነው። እስክንድር ነጋን ከአውሬው መንጋጋ ደጀን ላይ ወጣቱ  እስከ ባህርዳር ድረስ ተከታትሎ ባስለቀቀው እለት  ባህርዳር እስር ቤት ድረስ ሄዶ ዘመነን ጠይቆት እንደነበር ያስታውሷል።

 በሌላ በኩል የዛሬ ዓመት  የአውሬው መከላከያ ሠራዊት ፋኖ እስክንድር ነጋን እግር በእግር ከደብረ ኤልያስ ገዳም  ጀምሮ  እያሳደድኩት ነው ብሎ  ባወጀበት ማግስት፣ በእለተ እሁድ፤ ከእሥር ተለቆ በብአዴን ታጣቂዎች አጀብ   ወደተዘጋጀለት  ቪላ ቤት ተወስዶ ሲያንገራብድ  የነበረው  ዘመነ ካሴ፤ በወቅቱ  ስለ እስክንድር ነጋ መሳደድ ትንፍሽ አለማለቱ፣ የአውሬው የኦሮሙማ ጦር  እስክንድርንና ጠባቂ ፋኖዎቹን  ደምስሶ ሲያበቃ በእስር ያጀገነውን ዘመነ ካሴን የፋኖ ትግል መሪ አድርጎ ለመተካት  የተደረገ ሤራ ሊኾን እንደሚችልም የጠረጠሩም ብዙ ነበሩ።

ምስጋና ለጀግናው ፋኖ ይግባውና አውሬው አልተሳካለትም እንጂ ‘ተቃዋሚያችንን ለመቆጣጠር ምርጡ መንገድ እራሳችን  የተቃዋሚውን ጎራ መምራት ነው (The best way to control the opposition is to lead it ourselves).’ የሚለውን የሌሊንን የፖለቲካ ስልት ተግባራዊ ሊያደርጉት ነበር ማለት ነው። አስረስ ማረ ፤ እስክንድር የጎጃምን ህዝብ እየተዘዋወረ ለማንቃት በተንቀሳሰቀሰበት መስመር መንገድ እየዘጋ አደጋ ሊጥልበት እንደሞከረ የአማራ ወጣቶች ማህበር በኻላ ወደ ፋኖነት የተቀየሩት ወጣቶች በቅርቡ የነአስረስንና ዘመነን ሤራ ባጋለጡበት ጽሑፍ አስነብበውናል።

ዘመነና አስረስ ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ ያልተዋጉበትን ነፍጥ  አንዴ ክንዳቸው አንዴ ጭናቸው ላይ እያንጠለጠሉና እያስቀመጡ፣   አንዱ ላፕቶፕ አንዱ መጽሐፍ እያገላበጡ፣ ጫካ ውስጥ የተነሷቸውን የተለያዩ ለፕሮፖጋንዳ የሚጠቅሙ ፎቶግራፎችና ቪዲዮዎችን ጨምረው፣ ለሚዲያ ካስተላለፉዋቸው  የፋኖ እስክንድር ነጋን ሥም ማጠልሸት ዘመቻ እንዲኹም     ያልተተገበሩ ቁጥራቸው የበዛ፤ በክብር በወደቁ ፋኖዎችና በንፁሐን ሰማዕታት ሥም የተሰየሙ የዘመቻ ጥሪዎች በስተቀር ምንም አይነት የጦር ሜዳ ጀብዱ ሲፈጽሙ ያለመታየታቸው ሁኔታ፣ ቀድሞውኑም  እነ ዘመነ፤   የብአዴን ተስፈኞች እንደነበሩ  ህዝብና ፋኖ ለመረዳት እያስቻለው ነው።

እነ ዘመነ በአሁኑ ሰዓት ከሥም ማጥፋት ባለፈ የብአዴን  ጥበቃን፣ ገንዘብና ኔትወርክ እየተጠቀሙ እውነተኛ ፋኖዎችን  ማሳደድ መጀመራቸውን በአፈ ቀላጤያቸው በአስረስ ማረ  የመአዛ መሃመድ ሮሃ ሜዲያ ላይ በሰጠው መግለጫ በድጋሚ አረጋግጠውልናል። እነ አስረስ ብአዴን የሰጣቸውን ተልእኮ ለማስፈጸም እርምጃ እንደሚወስዱ  መናገራቸው ብቻ ሳይኾን እርምጃ መውሰድ መጀመራቸውን  በጎጃም፣ በጎንደር፣ በሸዋና በወሎ  የሚንቀሳቀሱ ፋኖዎች እያሳወቁ ይገኛል።     እነ ዘመነ አማራውን ህዝብ የሚከፋፍል የፖለቲካ ሤራም እየሠሩ  መኾኑ እየተነገረ ነው። በጎጃም  ሰገልና አቸፈር ላይ አገው ደገንጎ  የሚል ክፍለ ጦር  መሥርተዋል።

የነዘመነ የብአዴን ‘ፋኖ’ ቡድን በአሁኑ ሰዓት ቁጥር አንድ ጠላቱ አድርጎ እያሳደዳቸውና  እያፈናዋቸው ከሚገኙ በጎጃምና በጎንደር ከሚንቀሳቀሱ ፋኖዎች ውስጥ  እነ ኢንጅነር ማንችሎት ፣  ዶ/ር እንማው ፣  ባህርዳር ዙሪያ የአውሬውን ጦር ሲያስጨንቁ የነበሩት በጎጃምና በደቡብ ጎንደር ይንቀሳቀሱ የነበሩ ፋኖዎች፣  ጎጃም ተወልደው ወደ ጎንደር ተሻግረው ሃሙሲት ዘንዘልማ  አካባቢ የሚዋጉ  ፋኖዎች፣ እንዲኹም በባህርዳር  የአማራ ወጣቶች ማህበርን ይመሩ የነበሩ በዃላ ወደ ፋኖነት የተቀየሩትን ወጣት የተማሩ ፋኖዎች ይገኙበታል። እነዚኽ እየተሳደዱ ያሉና እየታፈኑ ያሉ ፋኖዎች፤ የአማራ ሕዝባዊ ግንባር ከተቋቋመ በዃላ በኮሎኔል ፋንታሁን ሙሃባ ፈር ቀዳጅነት  ፋኖ ከተሞችን መቆጣጠር በጀመረበት ወቅት፤  ባህርዳርን ለመቆጣጠር ከፍተኛ ፍልሚያ ሲያደርጉ የነበሩ  ናቸው። እነዚኽ ጀግኖች  በነዘመነ ቡድን በጠላትነት መፈረጃቸው፤  እነ ዘመነ በግልጽ የብአዴንን ዓላማና ተልእኮ ለማስፈጸም እየሠሩ ያሉ የብአዴን ተስፈኞች ለመኾናቸው ማስረጃ ነው።

ከተሞችን ተቆጣጥሮ የኦሮሙማውን ጦር ከአማራ ምድር የማይነቅል የፋኖ ትግል ምንም እንደማይፈይድ ይታወቃል። ፋኖ ከተሞችን እንዳይቆጣጠር የሚፈልግ ኃይል ቢኖር አውሬውና ፣ ተላላኪዎቹ ብአዴኖች ብቻ ናቸው ሊኾኑ የሚችሉት። ለዚኽም ነው ብአዴን ወጣቶቹ እነ ዘመነን ጠልፎ ይዞ ነፍሱን ለማዳን ያለ የሌለ ገንዘብና ኔትወርኩን እየተጠቀመ  የሚገኘው።  እነ ዘመነና አስረስ  በአፋቸው ብአዴንን የሚቃወሙና የሚታገሉ እያስመሰሉ ወደ መስመራዊ የጦር ውጊያ እያደገ የነበረውን  የትጥቅ   ትግል፤  ከመስመራዊ ወደ  ሽምቅ፤  ከሽምቅ ውጊያ ወደ ትጥቅ መፍታትና  ድንጋይ መኮልኮል ትግሉን ዝቅ ለማድረግ ‘የአማራ ታላቅ አብዮት(Grand Amhara Revolution)’ የሚል ሃሳብ ዘርተው እየሠሩ ይገኛሉ።

ይኽንን የትጥቅ ትግሉን የማኮላሸትና የብአዴንን ብሎም የአውሬውን  ዓላማ ለማሳካት  ‘ከተማን መቆጣጠር ውድመትን ያስከትላል’ የሚል ማስፈራሪያ መልእክቶችን በጎጃም ለሚገኙ ፋኖዎች ባገኙት አጋጣሚ እየሰበኩ ይገኛሉ። ይኽን ተከትሎ በጎጃም የሚገኙ ፋኖዎች እንቅስቃሴ እንዲዳከምና ፋኖዎች ቀስ በቀስ ከውጊያ ውጪ እንዲኾኑ እየሠሩ ነው። ለዚኽም ምስክር የሚኾነው   በህዝባዊ ግንባሩ ዙሪያ ተሰባስቦ የነበረውንና የአውሬውን የኦሮሙማ መከላከያ ሠራዊት መቆሚያ መቀመጫ ሲያሳጣውና ሲያሽመደምደው  የነበረው በጀግናው ሻለቃ ዝናቡ ይመራ የነበረው ከፍተኛ የፋኖ ኃይል በከፍተኛ ግፊትና ጫና ወደ የአማራ ፋኖ በጎጃም የነዘመነና አስረስ የብአዴን ‘ፋኖ’  ከተቀላቀለ ወዲኽ  በጎጃም ያደርግ የነበረው  የትጥቅ ትግል እንቅስቃሴ እየተቀዛቀዘ መምጣቱ ነው።  በዚኽ ምክንያት በጎጃም   የአማራ ፋኖ ህዝባዊ ሠራዊት ዕዝ  ብርጌዶችና ክፍለ ጦሮች  ከሚያደርጉት ወታደራዊ ፍልሚያና  እንቅስቃሴ በስተቀር በአሁኑ ሰዓት በጎጃም ይኽ ነው የሚባል በነዘመነ በኩል የሚደረግ ከኦሮሙማው ሠራዊት ጋር የሚደረግ ፍልሚያ የለም።

ብአዴን  በጎጃም እያደረገ እንዳለው በሸዋ  እነ አሰግድን አሠማርቶ የትጥቅ ትግሉን ለማቀዛቀዝ ያለ የሌለ ገንዘብና ኔትወርኩን እየተጠቀመ ይገኛል። የአሰግድና የዘመነ ካሴ የብአዴን ‘ፋኖ’፤ በቅርቡ የፋኖዎች አንድነትን ለማምጣት እየተደረገ ያለውን  ንግግር በሤራ ተቆጣጥሮ የአመራሩን ቦታ ለመያዝ ብአዴን የሚሰጠውን ገንዘብ በመርጨትም ላይም ነው።   አሜሪካን የሚገኘው የብአዴን ክንፍ በበኩሉ  እነ ዘመነን  ለማስመረጥ   የፕሮፖጋንዳ ዘመቻ የከፈተ ሲኾን ዓላማውን  ለማሳካት   እንደ ዘመድኩን በቀለ ያሉ ከህዝብ ህሊና የተፋቁ የደም ነጋዴ ነውረኛ የአማራ ወዳጅ መሳይ  ጠላቶችን ጭምር  እየተጠቀመ  ይገኛል።

አውሬው ካሠማራው የኦሮሙማ መከላከያ ሠራዊት ጋ  እየተፋለመ ያለው ፋኖ፤ እንደ ኦነግና፣ህወሐሃት ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን  ለ መካድ  የሚዳዳቸው ‘መነሻችን አማራ መዳረሻችን አማራ’ የሚሉ የብአዴን ተስፈኞች በኾኑት በእነ አሰግድና ዘመነ ካሴ  የአማራው የህልውና ትግል    ተጠልፎ   በእርቅ ሰበብ 4ኪሎ  የምኒልክ ቤተ መንግሥት የተቀመጠውን ግብረ ሠይጣን አውሬ  ሥልጣኑ  እንዲያራዘም  እንዲያደርጉ ሊፈቅድላቸው አይገባም። ብአዴን ላይ በተንጠላጠለ ትግል የአማራ ህልውና ሊከበር አይችልም። ብአዴን በእርቅ ሥም ተመልሶ በአማራው አናት ላይ ተቆናጦ በአማራ ህዝብ ደም እንዲነግድ   ሊፈቀድለትም አይገባም።  በመኾኑም የበድኑን ብአዴን ነፍስ ለመዝራትና በተዘዋዋሪ የኦሮሙማ የአውሬው ኃይል አማራውን እንዲያስገብር እየሠሩ ያሉትን እነ ዘመነ፣ አስረስንና አሰግድን በዚኽ ብአዴን ሠራሽ አስተሳሰባችኹ ልትመሩኝ አትችሉም፣ ለድልም አታበቁኝም ከፊቴ  ገለል በሉ ሊላቸው የሚገባው ሰዓት አሁን ነው።

የአማራ ህልውና ሊረጋገጥ የሚችለው በትጥቅ ትግል ብቻና ብቻ ነው። ይኸውም የአማራን ህዝብ ሲያስቀጠቅጥ የኖረውን ብአዴን  ነፍስ እንዳይዘራና   እንዳይመለስ  ወደ መቃብር ሸኝቶ የ4 ኪሎውን ደም መጣጭ  አውሬ ከምኒልክ ቤተ መንግሥት ለመመንገል ወደ አባቶቹ ነገሥታት መቀመጫ ወደኾነችው  አዲስ አበባ ሲገሰግስና የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ በመሃል አዲስ አበባ  ከፍ አድርጎ ሲያውለበልብ ብቻ ነው።

Filed in: Amharic