>

እስክንድር ነጋ 'የአማራ ሕዝባዊ ድርጅት' መሪ ማን ነው?

እስክንድር ነጋ ‘የአማራ ሕዝባዊ ድርጅት’ መሪ ማን ነው?

 

በትግሉ ሠመረ

 

የአስክንድር የትውልድ ቦታ አስተዳደግና ትምህርት

እስክንድር ነጋ  ከፍተኛ የትምህርት ደረጃ ከነበራቸው ከአሜሪካን ሀገር ሁለት ዲግሪ እንዲኹም ከቀዳማዊ ኃይለሥላሤ ዩኒቨርሲቲ የህግ ዲግሪያቸውን ካኙትና  እንደ ሼል ላሉ ታላላቅ ኩባንያዎች የህግ አማካሪ ኾነው ይሠሩ ከነበሩት ከወላጅ አባቱ አቶ ነጋ ፈንታ እንዲኹም  ከታዋቂው የቤሩት የአሜሪካን ዩኒቨርሲቲ በኽክምናው ዘርፍ የድህረ ምረቃ ዲግሪያቸውን ካገኙትና በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ያስተምሩ ከነበሩት ከወላጅ እናቱ  ከወ/ በላይነሽ አወቀ ጥቅምት 27, 1962 . አዲስ አበባ ተወለደ። 

እስክንድር ነጋ እድሜው ለትምህርት እንደደረሰ አዲስ አበባ በሚገኘው የሳንፎርድ የእንግሊዝ ትምህርት ቤት ገብቶ የመጀመሪያ ትምሀርቱን ተከታትሏል።  1966 ቱንአብዮትተከትሎ የደርግ መንግሥት በማህበረሰቡ ላይ በተለይም የተማረው የአማራው ማህበረሰብ  ላይ ያደርስ በነበረው ጫና ምክንያት 1972 . የእስክንድር ቤተሰቦች እስክንድርን  ይዘው ወደ አሜሪካን ሀገር ለመሰደድ በመገደዳቸው፤ እስክንድር የሁለተኛ ደራጃ ትምህርቱን በአሜሪካን ሀገር የተከታተለ ሲኾን፤   የኢኮኖሚክስ ዲግሪውን እዛው አሜሪካ ዋሽንግተን  ከሚገኘው ከዩኒቨርሲቲ ኦፍ አሜሪካ  ወስዷል። 

እስክንድር ዲሞክራሲ በኢትዮጵያ እንዲሰፍን የመናገር የመጻፍ መሠረታዊ መብቶች እንዲከበሩ የበኩሉን አስተዋጽኦ ለማድረግ በማሰብ  ወያኔ 1983 . አዲስ አበባ በገባ በዓመቱ 1984 .  ወደ አዲስ አበባ  ከአሜሪካን ሀገር ወደ ሀገሩ ኢትዮጵያ ተመለሰ። 

እስክንድር የመናገርና የመጻፍ ነጻነት እንዲከበር ያደረገው ተጋድሎና የከፈለው መስዋዕትነት

እስክንድር ወደ አዲስ አበባ ከተመለሰ በዃላ  ዲሞክራሲንና የመናገር የመጻፍ ነፃነትን  ለማስፈን የበኩሉን አስተዋጽኦ ለማድረግ  ‘ኢትዮጲስየተሰኘ ጋዜጣን ማሳተም በመጀመር  የወያኔን ፍትሃዊ ዘረኛ ሥርዓት፤  ገና በእንጭጩ እያለ  በመጀመሪያው እትሙ ይሞግተው ጀመር።  ‘ኢትዮጲስጋዜጣ ገና በመጀመሪያ እትሟ የጋዜጣና የመጽሔት ህትመት ሪከርዱን በመስበሯና የወያኔን ጎራ በማሸበሯ፤  እስክንድርና ጋዜጣዋ  በወያኔ ባለሥልጣናት ጥርስ ውስጥ ገቡ። ጋዜጣዋፋሺዝም በትግራይየሚል ጽሐፍ በሁለተኛ እትሟ ይዛ ስትወጣ ወያኔ የህዝቡን ተቃውሞ ያባብስብኛል ብሎ  በመፍራቱ ጋዜጣዋን ዘግቶ፤ እስክንድርና አብሮት ይሠራው የነበረውን ታዋቂ ጋዜጠኛ ተፈራ አስማረን ለአስር ዳረጋቸው።  27 ዓማታት የዘለቀው የእስክንድር የዲሞክራሲና የፕሬስ ነፃነት  መብት ትግል የጀመረው ከዚኽ ጊዜ ጀምሮ ነበር።   እስክንድር ወያኔ በሥልጣን ላይ  በቆየባቸው 27 ዓመታት ውስጥ ኢትዮጲስ፣አስኳል፣ ሣተናው ምኒልክ  እና The Habesha  የተሰኙ  ጋዜጦችን በማሳተም ወያኔን  በሰላ ብእሩ ታግሎታል፣ ወያኔ በበኩሉ አስክንድርን ከትግል ለማስቆም ባያስችለውም በተለያዩ 10 ጊዜያት የሃሰት ክስ እየመሰረተበት ወደ እስር ቤት በማስገባት  ከፍተኛ በደል ፈጽሞበታል። በደሉ በእስክንድር ላይ ብቻ የቆመ ሳይኾን በቤተሠቡም የተረፈ ጭምር ነበር። የእስክንድር ባለቤት የኾነችው ጋዜጠኛ ሠርካለም ፋሲል በዚኹ  ምክንያት ልጆን በእስር ቤት ለመውለድ የደረሰ ግፍን ከባለቤቷ ጋር ተቋድሳለች።

እስክንድር በተለይ በምርጫ 97′ ወቅት ምኒሊክ እና አስኳል  ጋዜጦችን  በመቶ ሺዎች ኮፒ በሳምንት ሁለቴ በማሳተም ዲሞክራሲ በኢትዮጵያ ለማስፈን የተደረገውን ትንቅንቅ በምሁራዊ  ብዕሩ በማገዝ ያደረገው አስተዋጽኦ እጅግ ከፍተኛ ነበር። ወያኔ ከምርጫ 97′ በኻላ የነፃውን ፕሬስ ሙሉ ለሙሉ ከዘጋው በኻላ፤  ብዙ ፖለቲከኞችን ጨምሮ በሽብር በመክሰስ ወደወህኒ ቤት አውርዶ፤  እስክንድርን ለአንድ ዓመት ከዘጠኝ ወር በማሳር ይቅርታ ጠይቆ በምኽረት እንዲወጣ ቢጠይቀውም፤  ይቅርታ አልጠይቅም በማለት የዓላማ ጽናቱን አሳልፎ ሳያሰጥ እዛው እስር ቤት በጽናት ቆይቷል።  መለስ ዜናዊን የተካው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በየካቲት 7 ቀን 2010 . ለሁሉም የፖለቲካ እስረኞች ያደረገውን ምኽረት ተከትሎ፣  ከእስር ሊለቀቅ ችሏል።

እስክንድር ነጋ ለፕሬስ ነፃነት ባደረገው ተጋድሎ ያገኛቸው ዓለም አቀፍ ሽልማቶች

እስክንድር በዓለም አቀፉ ማኽበረሰብ ዲሞክራሲንና የፕሬስ ነፃነትን ለማምጣት ባደረገው ተጋድሎ ያገኛቸው ሽልማቶች  ከብዙ በጥቂቱ የሚከተሉት ይገኙበታል፦

      1 .  PEN’s International’s 2012 Freedom to Write Award.

  1.  Golden Pen of Freedom in 2014;
  2. The International Press Institute’s World Press Freedom Hero for 2017;
  3. The 2018 Oxfam Novib/PEN Award

የእስክንድር ነጋና የፖለቲካ ተሳትፎው 

እስክንድር፤ ወያኔ ለኦነግ ታጣቂዎች ነፃ ፈቃድ ሰጥቶ  በአሩሲና በአርባ ጉጉ የአማራውን ህዝብ  ማስጨፍጨፍ በጀመረበት ወቅት፣  የአማራውን መጨፍጨፍ ለማስቆም በፕሮፌሰር አሥራት ወልደየስ ታህሣስ 2/ ቀን 1984 .  የተቋቋመው የመላው አማራ ሕዝብ ድርጅት(መአሕድ) መሥራች ደጋፊ አባል ነበር።   

የኦህዴድ ኃይሎች ብአዴንን ምርኩዝ አድርገው መጋቢት 24 ቀን 2010 .   የመንግሥትን ሥልጣን ከተቆጣጠሩ በኋላ አዲስ አበባ ኬኛ የሚልና፣ ልዩ ጥቅም የሚል ፖሊሲ ማራመድ ሲጀምሩ፤   እስክንድር ነጋ ሃሳቡን  በመቃወም  አዲስ አበባ የሁሉም ኢትዮጵያውያን ናት፣ ልዩ ጥቅም የሚባል ነገር የለም በማለት፤  የአዲስ አበባ ባላደራ  ምክር ቤትን  ነሃሴ 2011 . አቋቋመ።  የባላደራው ምክር ቤት በኦህዴድ መራሹ መንግሥት እየተፈፀመ ያለውን ጠበኛ ፖሊሲ ለማስቆም እንደማያስችል ከህዝብ ጋር በተደረገ ውይይት ስለተገለጠና መስማማት ላይ ሥለተደረሰ፣ ባላደራውን ወደ ፖለቲካ ፓርቲነት መቀየር አማራጭ የሌለው  መፍት መኾኑን በመተማመን ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲን ሜዳ ላይ በተደረገ ሥብሰባ  እስክንድር ነጋን በፕሬዝዳንትነት በመምረጥ በጥር 3 ቀን 2012 . ለመመሥረት ችሏል።   ባልደራስ በተመሠረተ አጭር ጊዜ ውስጥ  የኦህዴድን ሥርዓት እኩይ አላማን በአደባባይ በማጋለጥ፣ በርካታ ሰላማዊ የትግል እንቅስቃሴዎችን  በማድረግ ቅረሶችን ከመፍረስ ድሃው የከተማው ነዋሪ  ቤቱ ከመፍረስ ንብረቱ ከመውደም እንዲድን ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርጓል። 

 ባልደራስ ላደረገው የትግል እንቅስቃሴ  የእስክንድር ነጋ አመራርና ተሳትፎ ከፍተኛውን ሚና ተጫውቷል።  ባልደራስ 2013 ሀገራዊ ምርጫ፣  በትንሽ ወጪና በጥቂት አባላት ባካሔደው የምርጫ ቅስቀሳ ብልጽግና በሸፍጥ ቢሊዮን ብር በመርጨት ከወሰደው የህዝብ ድምፅ ውጪ ያለውን የአዲስ አበባ ህዝብ ድምጽ በአንደኝነት ለማግኘትም ያስቻለውአዲስ አበባ ላይ፤  ልዩ ጥቅም የሚባል ነገር የለምአዲስ አበባን እራስ ገዝ እናደርጋታለንየሚሉ  በግልጽ የተዋወቁ የምርጫ አማራጮችን በማቅረቡ ነበር።  የመሪው እስክንድር ነጋግፍን እንጂ ግፈኞችን አንፈራምየሚለው የትግል አርማም በህዝብ ዘንድ እስክንድር የሚመራው ባልደራስ ከፍተኛ ተቀባይነት እንዲኖረው አድርጎታል። 

እስክንድር ነጋ ከባልደራስ  ፕሬዚዳንትነት  ነሃሴ  16 ቀን 2014 . በጻፈው ደብዳቤ  እስከለቀቀበት ጊዜ ድረስ አዲስ አበባ ላይ ገዢው የኦሮሙማ መንግሥት ምንም እንኳን ከባልደራስ ግልጽ ጦርነት እንደሚገባ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢገልጽና፤ የሃጫሎ ግድያን አስታኮ እስክንድር ነጋን ጨምሮ ሌሎች የባልደራስ አመራሮችና አባላትን ለአንድ ዓመት ከሰባት ወር እስርና እንግልት እንዲደርስባቸው ከማድረግ በስተቀር አዲስ አበባ ላይ ሊያደርገው ያቀደውን፤ አዲስ አበባን፣  ቢቻል በኦሮሚያ ሥር የመጠቅለል፣ ባይቻል አዲስ አበባን ጥቅም አልባ ከተማ (irrelevant city) የማድረግ ዐላማውን በተግባር ከመፈፀም ለጊዜውም ቢኾን  እንዲገደብ ለማድረግ አስገድዶት ነበር። 

ፋኖ እስክንድር ነጋ  በአማራ ፋኖ የትጥቅ ትግል ሂደት ውስጥ እያደረገ ያለው የመሪነት ተሳትፎ

አስክንድር ነጋ አዲስ አበባን ለቆ ፋኖን ለማደራጀት ወደ ጫካ ከገባ በዃላ፤ አዲስ አበባ ድምጽ የሚኾናት አጥታ   በሺዎች የሚጠጉ መሃል ከተማ የሚገኙ እንደ ፒያሳ አራት ኪሎና፣ ካሳንችስ የመሳሰሉ ታሪካዊ ቦታዎች ፈርሰው  ነዋሪዎች ወደ ከተማው ዳርቻ የሚገኙ መጠለያዎች ያለምንም ህጋዊ መሠረት ተወርውረዋል።

እስክንድር ነጋ የፋኖን ትግል ለማደራጃት ወደ ጫካ በገባ ስድስት ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥየአማራ ህዝባዊ ግንባር‘   የማታገያ ግቡን  ‘መነሻችን አማራ መዳረሻን የኢትዮጵያ አንደንት ያደረገ ፤ ፋኖዎችን በአንድ ያስተባበረ ድርጅት፤  ግንቦት 12 ቀን 2015 . በማቋቋም የፋኖ ትግል አቅጣጫ መልክ እንዲይዝና የአገዛዙን እድሜ ለማሳጠር የሚያስችሉ ከተሞችን እስከ መቆጣጠር የደረሰ የትጥቅ ትግል እርምጃዎች በሁሉም የአማራ ጠቅላይ ግዛቶች እንዲከሰቱ አድርጓል። 

አሁን ደግሞ፤ የአማራ ፋኖን ወደ አንድ ለማምጣት ከመላው የአማራ ጠቅላይ ግዛት በተውጣጡ የፋኖ ተወካዮች ለአንድ ወር በተደረገ ውይይት  ሐምሌ 9 ቀን 2016 . ውይይቱ ሲጠናቀቅ፣ ሁሉንም ፋኖ የሚያካትት  ‘የአመራ ሕዝባዊ ድርጅትየሚል ድርጀት መቋቋሙንና፤  የድርጅቱ መሪ ፋኖ እስክንድር ነጋ  እንዲኾን በድምጽ ብልጫ መመረጡ ታውቋል።

Filed in: Amharic