>
5:33 pm - Tuesday December 5, 3995

እንጠይቅ...! ከእስክንድር በላይ ለአማራ የታገለው ማነው?

እንጠይቅ…!

ከእስክንድር በላይ ለአማራ የታገለው ማነው?

ዕውነት አሸናፊ

♦ አ”ባታችን ፕ/ሮ አሥራት ስለአማራ ሲታገሉ አብረዋቸው ከታገሉ እና ዛሬም በአማራው ትግል ውስጥ ካሉት 3 ከማይሞሉ ታጋዮች ውስጥ አንዱ ማነው? ታላቁ እስክንድር አይደለምን?
♦ የፕ/ሮ አሥራትን መአሕድን (የመላው #አማራ ሕዝብ ድርጅትን) ወደ መኢአድ (የመላው #ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት) ሲቀይሩት፣ መቀየር የለበትም!” ብሎ ሲታገል የቆየው ማነው? ታላቁ እስክንድር አይደለምን?
♦ የዛሬ 20+ አመት በጋዜጣው ላይ በድፍረት “አማራ ታሪኩን ያድሳል!” ብሎ ይፅፍ የነበረው ማነው? ታላቁ እስክንድር አይደለምን?
♦ ፕ/ሮ መስፍን “አማራ የለም።” ብለው ሲፅፉ በግልፅ በአደባባይ በመረጃ እና በማስረጃ ሲሞግታቸው የነበረው ማነው? ታላቁ እስክንድር አይደለምን?
♦ ጩጬው አራት ኪሎን ከተቆጣጠረ በኋላ”አማራው የዘር ማጥፋት (ጄኖሳይድ) እየደረሰበት ነው፣ አብረን ይህንን ማስቆም አለብን።” ያለው የመጀመሪያ ሰው ማነው?ታላቁ እስክንድር አይደለምን?
 (በሌላ በኩል አሁንም ጄኖሳይድ አልደረሰበትም የሚሉ ታጋዮች አሉ።) 

 

♦ የትግራዩ ጦርነት እንዳለቀ በወለጋ እና በሌሎች የኦሮሚያ ክልል ቦታዎች የሚጨፈጨፉ አማራዎችን ሞት ለማስቆም ፋኖም መዝመት አለበት ያለው ማነው? ታላቁ እስክንድር አይደለምን?

 ♦ የዛሬ ሶስት አመት ጎንደር የሚገኙ ፋኖዎች ላይ አገዛዙ ጦር ሲያዘምትባቸው ከታዋቂ ሰዎች ብቸኛ በአደባባይ (በ Twitter ) የተቃወመው ማነው? ታላቁ እስክንድር አይደለምን?
♦  አርበኛ ዘመነ ሊደራደር ባህርዳር  በሄደበት አታለው ካሰሩት በኋላ የቆመውን የፋኖ ትግል ጫካ ገብቶ ዳግም የቀሰቀሰው ማነው? ታላቁ እስክንድር አይደለምን?
♦ የዛሬ አራት አመት በተደረጉለት ቃለመጠይቆች ያለምንም መሸማቀቅ አማራው ራሱን ለመከላከል መደራጀት አለበት ያለው ማነው? ታላቁ እስክንድር አይደለምን?
የማንም ወንዝ አመጣሽ ዛሬ “አማራ፣ አማራ” ማለት ጀመረና፣ ከ30 አመት በላይ ለአማራ የታገለውን ታላቁን እስክንድር ለመተቸት በቃ?። በመይሳው ካሳ የደረሰው ነው በፋኖ እስክንድር ነጋ ላይ እየደረሰ ያለው።
Filed in: Amharic