የቡድን አመራር፤ የነ ግርማ ካሳ አዲሱ ጨዋታ
“እስክንድር ነጋ እመራዋለሁ የሚለው ያማራ ሕዝባዊ ሠራዊት የሚባል አለ ወይ? ይህ ድርጅት በወረቀት እንጅ በተግባር ያለ አይመስለኝም።” (ግርማ ካሳ፣ መጋቢት 2016)
“እስክንድር ነጋ ካማራ ፋኖ ሕዝባዊ አንድነት ድርጅት መሪነቱ ተነስቶ፣ የቡድን አመራር እንዲኖር ሁኔታወችን ለምን አያመቻችም። ኳሷ ያለቸው እስክንድር ነጋ ጋር ነው።” (ግርማ ካሳ፣ መስከረም 2017)
“በመጀመርያ ይንቁሃል፣ ቀጥለው ይዘልፉሃል፣ ከዚያም ይፋለሙሃል፣ በመጨረሻ ትረታቸዋለህ::” (ማህተማ ጋንዲ)
“First they ignore you, then they ridicule you, then they fight you, then you win.”(Mahatma Gandhi)
እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ግርማ ካሳና መሰሎቹ (መረጃ ቲቪ፣ ሮሃ ቲቪ፣ ግዮን ቲቪ፣ ዘመድኩን በቀለ ወዘተ) እስክንድር ነጋን በተመለከተ ይጫወቱት የነበረው ጨዋታ እስክንድር ጦር የለውም የሚለውን ጨዋታ ነበር። እስክንድር ጦር የለውም ይሉ የነበሩት ደግሞ በፋኖ ጨዋታ ላይ ምንም ሚና የሌለው የዳር ተመልካች ባይተዋር ነው በማለት እስክንድርን አኮስሰው ዘመነ ካሴን ለማግዘፍ ነበር።
መነሻችን አማራ መድረሻችን ጦቢያ የሚለውን እስክንድርን ነጋን አኮስሰው መነሻችንም መድረሻችንም አማራ የሚለውን ብአዴናዊውን ዘመነ ካሴን ለማግዘፍ የተነሰቱ ደግሞ የጦቢያ ዘላለማዊ ጠላቶች የሆኑት ወያኔና ኦነግ እንዲሁም የወያኔና የኦነግ ቀንደኛ ደጋፊወች የሆኑት ምዕራባውያን (በተለይም ደግሞ አሜሪቃና እንግሊዝ) በሰጧቸው ልዩ ተልዕኮ መሠረት ነው።
እነ ግርማ ካሳ እስከቅርብ ጊዜ ድረስ ይጫወቱት የነበረው ጨዋታ ግን እስክንድርን የማኮሰስ ዓላማቸውን ሊያሳካላቸው አልቻለም። ስለዚህም ጨዋታቸውን ለመቀየር ሳይወዱ ተገደዋል፣ ወደሽ ነው ቆማጢት እንዲሉ። አዲሱ ጨዋታቸው ደግሞ “እስክንድር ነጋ ካማራ ፋኖ ሕዝባዊ አንድነት ድርጅት መሪነቱ ተነስቶ፣ የቡድን አመራር እንዲኖር ሁኔታወችን ለምን አያመቻችም። ኳሷ ያለቸው እስክንድር ነጋ ጋር ነው” የሚል ነው። የቡድን አመራር የፈለጉት ደግሞ በቡድን ስም ገበተው እስክንድርን ከቡድኑ በማባረር እስክንድርን ከጨዋታ ውጭ ለማድረግ የተሰጣቸውን ተልዕኮ ለማሳካት ሲሉና ሲሉ ብቻ ነው።
ስለዚህም ውድ ወንድሜ እስክንድር ነጋ ሆይ፣ በርግጥም በበላበት የሚጮኸው ግርማ ካሳ በጽሑፉ እንዳጮኸው ኳሷ ያለችው አንተ እስክንድር ነጋ ጋር ነው። ስለዚህም የቁርጥ ቀን ጓዶችህን ይዘህ፣ ይህችን አንተ ጋር ያለች ኳስ ካማራ በመነሳት ጦቢያ ደርሰህ ግብህን መምታት ያለብህ አንተና አንተ ብቻ ነህ። በነ ግርማ ካሳ የቡድን አመራር ቅጥፈት ተታለህ፣ ይህችን አንተ ጋር ያለች ለጦቢያ ሕልውና እጅግ ወሳኝ የሆነች ኳስ (ካማራ ሜዳ እንወጣም በማለት በብአዴን ሜዳ ላይ ከሚልከሰከሱት) ከነ ዘመነ ካሴ ጋር እቀባበላለሁ ብትል ግን ግቧን ሳትመታ በከንቱ እንድትባክን ታደርጋታለህ። ያን ካደረክ ደግሞ ዕድሜ ልክህን የከፈልከውን መስዋዕትነት መና ታስቀራለህ፣ የታሪክ ተጠያቂም ትሆናለህ። መስዋዕትነትሀ መና እንዳይቀር፣ የታሪክ ተጠያቂም እንዳትሆን የጦቢያ አምላክ ይርዳህ።
መስፍን አረጋ
mesfin.arega@gmail.com