>

በደም ነጋዴዎችና በአገው ሸንጎ እየተፈጸመ የሚገኘው የክህደት ሴራ‼️

በደም ነጋዴዎችና በአገው ሸንጎ እየተፈጸመ የሚገኘው የክህደት ሴራ‼️

 

✍️ የአማራ ህዝብ እያደረገው የሚገኘው የነፃነት ትግል የስርዓት ለውጥ ከማምጣት ተገትቶ በጥገናዊ ለውጥ የቡድኖች የስልጣን ጥም ማርኪያ እና የግለሰቦች የቢዝነስ source እንዲሆን ስራ በይፋ በደም ነጋዴዎች ተጀምሯል።

እነዚህ ቡድኖች በሕልውና ትግሉ በቂ ግንዛቤ የሌላቸውን ነገር ግን በነፃነት ትግሉ ዝና ያገኙ እና ተጠሪ የሆኑ ግለሰቦች በገንዘብ በመደለል ትግሉን ለማኮላሸት እየሰሩ ይገኛሉ ።

ይህ ስግብግብ ቡድን ከፋሽስቱ ኦህዴድ ጋር በመደራደር የክልሉን ስልጣን ለመረከብ እየሰራ ይገኛል ። ቡድኑ ይህ የክህደት አላማው እንዲሳካለት በአራቱም የአማራ ግዛት በሚገኙ የፋኖ አደረጃጀቶች የሴራ ገመዱን በመዘርጋት እየሰራ ይገኛል።  የፋኖ ሀይሎች አንድ ሆነው ጠላትን በጋራ እንደይታገሉ ከውስጥ ችግር በመፍጠር በአጀንዳ እንዲጠመዱ እያደረገ ይገኛል።

ይህንን የእብደት አላማ ለማሳካት በሁሉም ቀጠና ተልዕኮ አስፈፃሚ የሚሆኑ ግለሰቦች እያደራጀ የሚገኝ ሲሆን አላማውም የፋኖ ሀይሎች እርስ በእርስ እንዲጋጩ እና ተሰላችተው እንዲበተኑ በማድረግ አደረጃጀቱን አዳክሞ እራሱን የፋኖ ተወካይ በማድረግ ለድርድር መቅረብ ነው ።

ለዚህ የቅዠት እብደት ተልዕኮ አስፈፃሚ የተመረጡ ግለሰቦች ከአሁን ቀደም በተለያየ ወንጀል የተዘፈቁ የፋኖ ትግል አሸናፊ ከሆነ ለህግ ተጠያቂነት የሚቀርቡ እና ደጎስ ባለ ገንዘብ የተገዙ የደም ነጋዴዎች እንደሆኑ ሊታወቅ ይገባል ።

• እነዚህን ከሃዲዎች  በመጠቀም እውነተኛ የትግል ተቆርቋሪ እና  የሥርዓት ለውጥ እንዲመጣ የሚፈልጉ አመራሮች፤ በሀሰት በመወንጀል  ከትግሉ እንዲገለሉ በማድረግ እና ያልተሳካለትን እንዲገደሉ ለማድረግ እየሰራ ይገኛል ።

•  ይህ ስግብግብ ቡድን እየሰራው የሚገኘው ክህደት እንደ አማራ አንገት የሚስደፋ በመሆኑ ሁሉም አማራ ጉዳዩን በትኩረት እንዲከታተለው እና እውነተኛ የትግል መሪዎቹን መጠበቅ አለበት። በዚህ የክህደት ስራ የተሰማሩ ግለሰቦችን ሁሉም አማራ ሊታገላቸው እና ሊያወግዛቸው ይገባል ።

ሩጠው ያልጠገቡ ወንድሞቻችን የገበርንበት ትግል መሆኑ መረሳት የለበትም ።

ድል ለእውነተኛ ታጋይ‼️

ትእግሥት ዘገዬ

Filed in: Amharic