>

የዐማራ ፋኖ አንድ ወጥ የመታገያ ድርጅት እንዳይኖረው ለምን ተፈለገ?

የዐማራ ፋኖ አንድ ወጥ የመታገያ ድርጅት እንዳይኖረው ለምን ተፈለገ?

 

 

የዐማራ ፋኖ አንድ ወጥ የመታገያ ድርጅት እንዳይኖረው ሁለት አካላት በቅንጅት ተግተው በመስራት ላይ ይገኛሉ። እነሱም አብይ አህመድ እና የሣልሣይ ብአዴን አዋላጆች ናቸው! 

አብይ  አህመድ እና ስርዓቱ ይህን ማድረጋቸው አያስገርምም። ምክንያቱም በአንድነቱ የሚፈጠረው የአማራ ፋኖ ጥንካሬ ከባድ የራስ ምታት እንደሚሆንባቸው እና የማሸነፋችንም ቁልፍ ያለው የዐማራ ፋኖ አንድነት ላይ መሆኑን ጠንቅቀው ስለሚያውቁ ነው። 

እጅግ የሚያስገርመው ግን አንዳንድ  “የዐማራ ፋኖ አመራሮች” ዐማራ ሆነው ዐማራ አንድ ወጥ ድርጅት እንዳይኖረው ከአብይ አህመድ የበለጠ የፋኖ አንድነት ጠንቅ ሆነው በትጋት ሲሰሩ መገኘታቸው ነው! 

በዚህም  የሰው በላውን ስርዓት እድሜ በማራዘም ለአብይ አህመድ ትልቅ ውለታ ውለውለታል ። ለራሳቸውም ታሪክ የማይረሳው ጠባሳ አስመዝግበዋል። 

በተለይ የብአዴን ወጣት ሊግ ደቀመዛሙርት ዘመነ ካሴ ፣አስረስ ማረ እና አበበ ፈንቴ ያሳዩት መናበብ፣ የሮሃ ሚዲያ፣ የማረጃ እና ABC ቴሌቪዥን ያሳዪት ቅንጅት ታሪክ የማይረሳው ነው! 

ይህ ስብስብ ባለፉት ስድስት ወራት ለምን አዲስ ድርጅት መፍጠር አቃተው? አዲስ ድርጅት ከመስራት ይልቅ ለምን ድርጅት ማፍረስ ላይ ለማትኮር ፈለገ? የሚለውን ቁልፍ ጥያቄ ማንሳት ያስፈልጋል። 

የዚህ ሰብስብ ዋና ፍላጎት ሦስት ነው። 1ኛ. ስልጣን 2ኛ. ስልጣን 3ኛ. ስልጣን ብቻ ነው!

ይህ የሣልሣይ ብአዴን አዋላጅ ስብስብ የአማራ ህዝብ ሰቆቃ ግድ የማይሰጠው፣ በego የተወጠረ ራስ ወዳድ፣እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል የሚል  ጨካኝ ስብስብ ነው። 

ከነሱ የተሻሉ ሰዎች ይኖሩበታል ብለው በሚያስቡት ድርጅት ውስጥ መካተት አይፈልጉም! ከዚህ ይልቅ ከነሱ በእውቀትም፣ በተምህርትም፣ በንቃተ ህሊናም ያነሱ ሰዎችን በዙሪያቸው ሰብስበው በነሱ ላይ መንገስ ይመርጣሉ። 

ለምን? 

ድርጅት ውስጥ ግምገማ አለ፣ ትችት አለ፣ ድርጅት ውስጥ ውድድር አለ። መሪ ለመሆን ተመዝኖ ማለፍ ፣ ተወዳድሮ ማሸነፍ ይጠይቃል። እነዚህ ግለሰቦች የመጡበት መንገድ /  track record ይህን አያሳይም። 

የብአዴን ወጣት ሊግ አባልና አመራር ሆነው ያገለገሉት ተወዳድረው፣ አሸንፈው አይደለም። በመንደር፣ በሰፈር፣ በጎጥ፣ ለድርጅቱ በነበራቸው ታማኝነት ወዘተ ነው። ከብአዴን የቀሰሙት ቁልፍ ትምህርት ይህ ነው። ሮል ሞዴላቸው ህወሃት ናት። 

እነዚህ ግለሰቦች ከዚህ የተለየ እውቀት የላቸውም! ማሰብም አይችሉም። በብአዴን ቤት የምታድገው ወንድምህን ጥለህ፣ በርሱ ላይ ተረማምደህ ነው። 

በውሸት ግምገማ ጓደኛህን/ ወንድምህን አፈር አስግጠህ፣ ከሱ በላይ ለድርጅቱና ለአለቃህ ታማኝነትህን አስመስክረህ፣ አሽቃብጠህ ነው!

ለዚህ ከደመቀ መኮንን ጀምሮ ሁሉንም የብአዴን ባለስልጣናት ወደኋላ ተመልሶ ማየት በቂ ማሳያ ነው! አንዳቸውም በacademic merit ወደስልጣን አልመጡም ለድርጅቱ ባላቸው ታማኝነት እንጂ! 

እነዚህ ግለሰቦችም በዙሪያቸው ታማኝ የሰፈርና የመንደር ሰው ሲሰበስቡ የዐማራን ህዝብ ትግል ዳግም ወደመንደር አወረዱት! 

ዘመነ ድርጅት መስራት ሲያቅተው ተሰርቶ ያለቀ ድረጅት ወደማፍረስ ገባ። ጎንደር ላይ በበርካታ ማዋከብ ሻለቃ ሃብቴ ወልዴን ከህዝባዊ ድርጅቱ በማስወጣት የመጀመሪያውን “ስኬት” አስመዝግቧል! በዚህም ሳያፍሩ እሱና መሰሎቹ በአደባባይ ደስታቸውን ገለፁ። 

ይህ  ስብስብ ወደ ሸዋም ተሻግሮ ከስርዐቱ ጋር በመቀናጀት ፕሮፓጋንዳ በመንዛት ክፍለጦሮችን ለማፈራረስ እና አመራሮች ላይ ግድያ ለመፈፀም በርካታ ያልተሳኩ ሙከራዎችን አድርጓል! 

አሁን ደግሞ ወደ ወሎ በመሻገር በኮሎኔል ፈንታው ሙሃቤ እና በሚመሩት ክፍለ ጦር ላይ መጠነ ሰፊ ዘመቻ ከፍቷል። ወከባና ግራ ማጋባቱ ተጠናክሮ ቀጥሏል። 

ይህ ስብስብ እንደ ስኬት የሚቆጥረው የራሱን ስራ ሳይሆን በሌሎች የተሰራውን ማፍረሱን ነው! 

ዘመነ ካሴ ለመሪነት ብቁ አይደለም ሲባል በማስረጃ ነው። እርሱ የተማረው እና በደንብ የሚያውቀው ፓለቲካ የሴራ ፓለቲካ ነው! የመጠላለፍ፣ የትግል ጓድን ጠልፎ መጣል! ስም የማጥፋት፣ የማጠልሸት፣ ጭቃ የመቀባት ኋላ ቀር እና ቆሞ ቀር የወያኔ ፓለቲካ! 

እነዚህ ግለሰቦች የሃሳብ ፓለቲካ አላርጂካቸው ነው። ከመንደር ፓለቲካ ወደ ሃሳብ ፓለቲካ እነዚህን ግለሰቦች ማምጣት እጅግ በጣም ከባድ ነው!

በሃሳብ የበላይነት በማመን፣ በሃሳብ አሳምኖ፣ የአመለካከት ልዮነት አምጥቶ ሰዎችን በዙሪያቸው ከማሰለፍ ይልቅ በሴራ በሌላ አደረጃጀት ውስጥ ያሉትን በማፍረስ ይደሰታሉ! ይረካሉ፣ እንደትልቅ ስኬት ይፈነጥዛሉ። ለዚህ ነው የሻለቃ ሃብቴ ከአማራ ፋኖ ጎንደር እዝ መውጣት አብይ አህመድን ከማሸነፍ በላይ ያስፈነደቃቸው! 

ሌላው የሚገርመው ባህሪያቸው እነደ አያታቸው ህወሃት ሁሉ የተለየ አመለካከት ያለው ሰው መስማትም ማየትም አይፈልጉም። እንደወያኔ ሁሉ ያስራሉ፣ ያሳድዳሉ፣ ይገድላሉ። 

ለምሳሌ አርበኛ ካፕቴን ማስረሻ ሰጤ ላይ በተደጋጋሚ ጦር አዝምተዋል፣ ጋዜጠኛ ወግደረስ ጤናውን፣ በቅርቡ ቢፈታም ዶ/ር እንዳላማውን አስረዋል፣ ጀግናውን ኮሎኔል ጌታሁንን ደብዛውን አጥፍተዋል! 

እኔም በዚህ ሰዓት ጎጃም ውስጥ ብሆን ኖሮ ያለጥርጥር ይህን ፅሁፍ ካጋራሁ በኋላ ራሴን የማገኘው ከወግደረስ ጤናው ጋር በአንዱ እስር ቤት ነበር። ታዲያ አብይ አህመድ ምን አጠፋ? 

አብይ አህመድ  ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይን፣ መስከረም አበራን የመሳሰሉ በርካታ የዐማራ ልጀች አሰረ አሰቃየ ፣ ጀነራል ተፈራ ማሞን አሳደደ! “የጎጃሙ ጠ/ሚ “ዘመነ ካሴ ወግደረስ ጤናውን አሰረ፣ ኮሎኔል ጌታሁንን እና ካፕቴን ማስረሻ ሰጤን አሳደደ። ታዲያ በሁለቱ አምባገነኖች መካከል ያለው ልዪነት ምንድነው? 

ለኔ የሚታየኝ ልዩነት አንደኛው ከበሻሻ ነው ሌላኛው ከሜጫ!  አንደኛው ኦሮሞ ነው ሌላኛው አማራ ነው! አንደኛው ኦሮሞኛ ያወራል ሌላኛው አማርኛ! Nothing else! Done! 

ይህን እብደት ከወዲሁ መቃወምና ማስቆም ከሁሉም ዐማራ ይጠበቃል። ስለምንነቅለው ብቻ ሳይሆን ስለምተክለውም ስርዓት ማወቅና መጨነቅ አለብን! 

“ይህች ባቄላ ካደረች አተቆረጠምም”

ዳግማዊት ጌታነህ

Filed in: Amharic