ከዲያስፓራ መካከል እስክንድር ጫፍ የሚደርስ አንድም የለም‼️
ከእስክንድር ነጋ ራስ ውረዱ !…ትላንት ከሕወሓት የሚወረወርላችሁን ቂጣ ስትቆረጥሙ እስክንድር ነጋ ከፕሮፌሰር አስራት ጋር ስለ አማራው ይታገል ነበር። ከየት ነው የመጣው ማነው ብላችሁ ልታሳንሱት የምትሞክሩት ዛሬ ከአብይ አሕመድ የሚወረውላችሁን ቂጣ እየቆረጠማችሁ መሆኑን ስናይ አፈርን።
ትላንትም ነበርን ዛሬም አለን ነገም እንኖራለን ።እንመሰክራለን።
ፕሮፌሰር አስራት ሆዳም አማሮች ያሉት እንደናንተ አይነቶቹን የፍርፋሪ ፍርፋሪ ለቃሚ ነው። እስክንድር ነጋ ለመብትና ነፃነት የከፈለው መስዕዋትነት እናንተ አንዱንም አልከፈላችሁም። እስክንድርን ከምትተቹበት የተደላደለ መቀመጫችሁ ተነስታችሁ ጫካ ግቡና እንያችሁ፤ እስክንድር እንኳን ለወዳጆቹ በጠላቶቹም ዘንድ የተከበረ የአላማ ሰው ነው። ዛሬም በፋኖ ትግል ላይ እየሰራ ያለው ስራ በተግባር እንጂ እንደናንተ በትግል ጠለፋ እና ጥቅም በመሰብሰብ ላይ አለመሆኑን ጠላትም ወዳጅም ይመሰክራል። እስክንድር ነጋ የሚያስተባብረውን ትግል ኑና አስተባብሩ ብትባሉ አንድም ስራ መስራት አትችሉም….
ባለቀ ሳዓት እስክንድርና ድርጅቱን ለማፍረስ ስሙንም ለማጠልሽት የሚካሄደው ዘመቻ አለምክንያት አይደለም:: ከጀርባው ሌላ ተንኮል ከሌለው በስተቀር በቅንነት የተነገረ ትችት ነው ብሎ ለመረዳት አስቸጋሪ ነው:: ዛሬ አማራው ድል አፋፍ ባለበት ወቅት እስክንድር ለፋኖ አስተባባሪነት አይመጥንም ማለት አማራ ነኝ የሚል ሁሉ ሊያወግዘው ይገባል:: ድል አፋፍ ያደረስን አንድነታችን ነው:: ጠላት ሊያጠቃ የሚፈልገው ይህንን ጥንካሬአችንን ነው:: ስንት ተፃፈ? ለዘመናት ስንት ውይይት ተደረገ? የስንት ሰው ህይወት ተፈተሽ? ከዚያ ዘመን በሁዋላ ዛሬ ፋኖ ወደወሳኙ የትግል ምእራፍ ሲያሽጋግረን ተናጋሪዎች፣ ፀሀፊዎች፣ አንደበታቸውንና እውቀታቸውን ከሜዳ ትግል ጋር ማገናኘት ባቃታቸው ወቅት: ብቅ ያለው እስክንድር ብቻ ነው:: እኛ ነን የበለጠ የምንመጥነው ካሉ ከሞቀ የአሜሪካ መኖሪያቸውና ቤታቸው ወጥተው ለምንድነው በረሀ እንደእስክንድር የማይገቡት? እስክንድር ቦታውን ይለቅላቸዋል። ተራ ፋኖ ሆኖ ያገለግላል:: አንመጥናለን የሚሉ ሁሉ ይውጡ!
⇐ ይዝመቱ!! ወይም አርፈው ይቀመጡ:: በስንት መከራ የተገኘውን እንድነት አይከፋፍሉ::ምን ዓይነት እውቀትና አመለካከት ነው በእስክንድር የሚያስቀና? ማን ነው ከዲያስፓራ መካከል እስክንድር ጫፍ የሚደርስ? በውጭም በውስጥም ትግሉን አስተዋውቆና አስተባብሮ መሸጋገሪያው ሊያደርስን የሚችል የመሪነት፣ የአስተባባሪነት ምግባርና ተአማኒነት ያለው ባለንበት ወቅት እስክንድር ብቻ ነው:: መአድ ሲመሠረት እስክንድር መስራች አባል ነበር.:: ከዚያም በፊት ሆነ በሁዋላ የተመዘገበ ታሪኩ እንድሚያሳየው እስክንድር ለአማራ ትግል መስዋእትነት ሲከፍል የቆየው የዛሬ ተቺዎች የትግል ሜዳ ላይ ፈጽሞ ባልነበሩበት ጊዜ ነው።
ዛሬ ፋኖ የብአዲንን መዋቅር በጣጥሶና የፋሽስቱ የኦሮሙማንና አውዳሚ ሃይል ደቁሶ ወደ አዲስ አበባ እየተቃረበ ሲሄድ ስልጣን የሸተታቸው ሁሉ ከየጓዳቸው በመውጣት የአማራን የህልውና ትግል ለመጥለፍና ለማደናቀፍ ብዙ የድል አጥቢያ አርበኞች አሰፍስፋችኋል። ትእግሥት ይኑራችሁ! በሚገነባው አዲስ የፖለቲካ ሥርአት ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ስለሚኖር ስልጣን ፈላጊዎች ዕድላችሁን ለመሞከር ለዚያ ጊዜ ተዘጋጁ! እዚያ ለመድረስ ግን ዛሬ በአንድነት መታገል አማራጭ የለውም:: ከሌሎች ጀግና የፋኖ አመራሮች ጋር ሆኖ እዚያ ሊያደርስን የሚችለውን እስክንድር ነጋን ለማስናከል መሞከር ግን ትግሉን አሳልፎ ለጠላት መስጠት ማለት ነው:: ከጠላት ጋር መሰለፍ ማለት ነው።
አሁን ካለንበት ተነስተን ታላቁ ግባችን ላይ ያተኮረ ሥራ ለመሥራት ሙያ፣ እውቀት፣ ቅንነት፣ ትክክለኛ የፖለቲካ አቋም ያላቸው ታጋዮችን በየዘርፋ በአስቸኳይ ማሰማራት ለወሳኙ የትግል ምእራፍ አማራጭ የለውም:: ከዚህ ወዲያ ያለው ትግል ሙሉ ለሙሉ ታላቁ ሰዕል ላይ ማለትም አራት ኪሎ ላይ ያተኮረ መሆን አለበት። ምንም ይሉኝታ፣ ፍርሀት፣ ጥርጣሬ፣ መከፋፈል የሌለበት ቁርጠኛ ትግል መሆን አለበት:: ትኩረታችን በአማራው ላይ የዘር የማጥፋት፣ የማፈናቀል፣ ቤተእምነቶቻችንንና ታሪካዊ ቅርሶቻችንን የማፍረስ ወንጀል በፈጸሙብን ላይ መሆን አለበት። የአማራ እናቶችንና ሴት ልጆችን በደፈሩት ላይ መሆን አለበት። እርስታችንን በማስመለስ ላይ መሆን አለበት። ለዘለቄታው የአማራን ሕልውና በማረጋገጥ ላይ መሆን አለበት። ትኩረታችን ከላይ የተጠቀሱትንና ሌሎች ወንጀሎችን በአማራው ላይ የፈጸሙትንና ያስፈጸሙትን ሁሉ ለፍርድ በማቅረብ ላይ መሆን አለበት። በእነዚህ ዓላማዎችና በፋኖ መሀከል ገብቶ በእዚህ ያለቀ ሰዓት ሌላ ከፋፋይ እጀንዳ የሚያሲይዙ ላይ ጥብቅ ውግዘት መፈፀም አለበት:: ግን ከኋላቸው እነማን ተስልፈዋል ብሎ መጠየቅም ተገቢ ነው። ሁሉም ለራሱ ሲል ይጣፍጥ:: የፋኖን ቁርጠኛነት ምንም ሀይል አያቆመውም!
በምንሊክ ሳልሳዊ