ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት ሀሰተኛ መረጃ በመርጨት እና ለብልፅግና ሴራ አጋዥነት ተሳትፎ ተወነጀሉ!!

አቶ ኤልያስ መሰረት ሀሰተኛ መረጃን ረጭተዋል፣ ምንጫቸው እና ተልዕኮ የሰጣቸውም አገዛዙ ነው።
(አርበኛ እስክንድር ነጋ፣ የአፋህድ ሊቀ መንበር)
“ፋክት ቸክ” በሚል መረጃን በማስረጃ የማቅረብ መንገድ እከተላለሁ የሚል ፕሮፖጋንዳ በመንዛት ስሙን የተከለው አቶ ኤልያስ መሰረት ሀሰተኛ መረጃን በማሰራጨት ተወነጀሉ።
ትላንት ጥር 18/2017 ዓ.ም የአቶ ኤልያስ መሰረት የግል ንብረት በሆነው መሰረት ሚዲያ በኩል “በአቶ እስክንድር ነጋ የሚመራው የፋኖ ክንፍ ከመንግስት ጋር ድርድር ጀመረ” በሚል ምንም አይነት ማስረጃ ቸክ በሌለው፣ ሀሰተኛ ያልተባለን የEthio 360 ሚዲያን በማስረጃነት አጣቅሶ ያወጣው ስሁት ዘገባ በስም በጠቀሳቸው ሚዲያ እና ግለሰቦች በሀሰት መረጃ አሰራጭነት ተከሷል።
መሰረት ሚዲያ መረጃውን ሰማሁ ያለበት Ethio 360 ሚዲያ በፖለቲከኛ ሀብታሙ አያሌው እና በጋዜጠኛ ብሩክ ይባስ በኩል ኤልያስ መሰረት የተተቸ እና በሀሰት መረጃ አሰራጭነት የተወነጀለ ሲሆን “በእኛ ሚዲያ በኩል አቶ ኤልያስ መሰረት በኩል ማስረጃ ሆኖ የወጣው አይነት መረጃ አልተሰራጨም፣ ስለ ፋኖ ድርድርም አንዳች ውይይት አላደረግንም” ሲሉ አቶ ኤልያስ መሰረትን በሀሰት መረጃ አሰራጭነት ከስሰው ሚዲያው ለጥፋቱ ይቅርታ ጠይቆ ዘገባውን እንዲያነሳ ጠይቀዋል።
በመሰረት ሚዲያ ስማቸው የተጠቀሰው እና ድርድር እንዳደረጉ የተባሉት የአፋህድ መሪ አርበኛ እስክንድር ነጋ በበኩላቸው “አቶ ኤልያስ መሰረት ፈፅሞ ሀሰተኛ መረጃ ከማሰራጨታቸውም በላይ፣ በራሳቸው ፋክት ቸክ እንኳ ለማጣራት ያልሞከሩበት ተራ በሬ ወለደ የብልፅግና አሻጥርን ተግባሪ ባለተልዕኮ ሀሰተኛ መረጃ ነው፣ አላማውም ሁለት ነው።
የአማራ ፋኖ አንድነትን መበጥበጥ እና የፋኖን መራራ ትግል ውጤት በህዝብ አመኔታን ማሳጣት በሚል ማብራሪያ ሰጥተዋል።
⇐ ጋዜጠኛ ኤሊያስ መሠረት አሶሺየትድ ፕሬስ የፍሪላንስ ጋዜጠኝነት ስራው የተባረረው ሐሰተኛ ዜና በመስራት ነበር ።
@minilikcom