>

አማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት (አፋሕድ) ለ15 ቀን የሚቆይ ዘመቻ ኮ/ል ታደሰ እሸቴ አውጇል!

ከአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት (አፋሕድ) የተሰጠ የዘመቻ ትዕዛዝ!

ዘመቻ ኮ/ል ታደሰ እሸቴ ታውጇል!!  

 የካቲት 24/2017  የአማራ ሕዝብ የኀልውና ትግል መሪ የሆነው ፋኖ ባደረጋቸው መራር ተጋድሎዎች፣ አማራ ላይ የዘር ማጥፋት(ጄኖሳይድ) ያወጀው ሥርዓት ቀብር በመፋጠን ላይ ይገኛል፡፡
በኀልውና ትግሉ ውስጥ ብቸኛው የአማራ ሕዝብ አታጋይ ድርጅት የሆነው አፋሕድ፣ በሚያደርገው ድርጅታዊ ትግል በአገዛዙ ላይ ከባድ ኪሳራ በማድረስ ላይ ቢገኝም፣ ትግሉ መራር መስዋዕትነት በማስከፍል ላይ ነው፡፡
 በዚህም የትግል ወንድማችንን ጀግናው ኮሎኔል ታደሰ እሸቴ፣ የካቲት 22/2017 ዓ.ም ከሌሎች የትግል ወንድሞቻው ጋር በጀግንነት ተፋልመው በክብር መሰዋዕት መሆናቸው ይታወሳል፡፡ ኮሎኔል ታደሰ እሸቴ ለተሰውሉት የተከበረ ዓላማ የአማራ ፋኖ ህዝባዊ ድርጅት ያለውን ቁርጠኝነት በሰዓቱ በማሳወቅ፣ መላ ሠራዊታችን፣ ደጋፊዎቻችንን እና ህዝባችን በተከታታይ ለምናስተላልፋቸው መመሪያዎች እና ትዕዛዝ በተጠንቀቅ እንዲጠብቀን አሳስበናል።

 በዚህም መሰረት፡-

 የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት፣ ሥራ አስፈጻሚ ዛሬ ባደረገው ስብሰባ፣ “ዘመቻ ኮ/ል ታደሰ እሸቴ” አውጇል፡፡ የዘመቻው አፈጻጸም ምስጠሩን በሚጠበቅ መልኩ በወታደራዊ ዝርዝር መመሪያው ወደሁሉም ጠቅላይ ግዛት ዕዞች ይወርዳል። በአፋሕድ ስራ አስፈፃሚ ውሳኔ መሠረት፡-
 1. የዘመቻው ሥያሜ “ዘመቻ ኮ/ል ታደሰ እሸቴ” ሲሆን፤ ዘመቻው ለአስራ አምስት ቀናት ይቆያል፡፡ ይህ ዘመቻ ሰማዕቱ ኮሎኔል ለዐማራ ሕዝብ ኀልውና፣ ለኢትዮጵያ ዘላቂ ነጻነት ለከፈሉት ውድ የሕይወት ዋጋ መታሰቢያቸው ይሆናል፡፡
 2. “ዘመቻ ኮ/ል ታደሰ እሸቴ” የትግል ወንድማችን የትግል አደራ፣ በአፋሕድ ውስጥ ክቡር ቦታ እንዳለው የተግባር ማሳያ ነው፡፡ የትግሉ ዳርቻ ኮሎኔል ታደሰ እሸቴ እና ሌሎች ሰማዕታት እህት ወንድሞች ዋጋ የከፈሉለት የዐማራ ሕዝብ ኀልውና መረጋገጥ፣ ብቻ ሳይሆን በድርጅታችን የትግል ዓላማ መስመር ላይ እንደተመለከተው የዐማራን ሕዝብ ካጋጠመው የኀልውና አደጋ በማውጣት የፍትሕ፣ ነጻነትና እኩልነት የሰፈነበት ሥርዓት ባለቤት የማድረግ የትግል ዓላማውን ለማሳካት ያለመ ዘመቻ ነው፡፡
 3. ዘመቻው የድርጅታዊ አንድነት የትግል ምልክት ብቻ ሳይሆን፣ ይህ ዘመቻ የኀልውና ትግሉ የትግል ቃል ኪዳን ማደሻ ነው፡፡ ትግላችን በፅኑ መሰረት ላይ የቆመ ፍትሐዊ ትግል እንደሆነ የምናሳይበትም ነው፡፡
 4. በዘመቻው በትግላችን ጠላቶቻችን ብቻ ሳይሆን ሞትን ጭምር እንደምናሸንፍ የምናሳይበት ይሆናል፤ ሌሎች የፋኖ አደረጃጀቶችም ዘመቻውን እንዲቀላቀሉና ተግባራዊ የትግል ምላሽ እንዲሰጡ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡
 5. ለ15 ቀናት የሚደረጉ ውጊያዎች እና ዘመቻዎች ሁሉ “ዘመቻ ኮ/ል ታደሰ እሸቴ” ተብለው የተሰየመ ልዩ ኦፐሬሽን መሆኑ ታውቆ፣ ሚዲያዎች የድርጅታችንን የአውደ ውጊያ ውሎዎችን ሲዘግቡ በዚሁ አግባብ እንዲጠሩ በይፋ እናሳውቃለን፡፡
 እነ ኮሎኔል ታደሰ እሸቴ የሕይወት ዋጋ የከፈሉለትን የትግል ዓላማ ከግብ እንደምናደርስ በትግሉ ሰማዕታት ስም እናረጋግጣለን፡፡ “ዘመቻ ኮ/ል ታደሰ እሸቴ”
ክብር ለሰማዕታት! 
ድል ለአማራ ፋኖ 
ድል ለአማራ ሕዝብ
ድል ለኢትዮጵያ! 
Filed in: Amharic