>

ጠላት ፈንጥዟል- ወገን በድርጊታችሁ ፍጹም አፍሯል፣ እጅግም አዝኗል!!!

ጠላት ፈንጥዟል- ወገን በድርጊታችሁ ፍጹም አፍሯል፣ እጅግም አዝኗል!!!

All is not lost 

በአደባባይ የምታደርጉትን ውዝግብ በአስቸካይ አቁሙ!!

እራሳችሁንም ከቤንዚን አርከፍካፊዎች ፍጹም እርቁ!!!

ሚዲያው የሕዝብ ነው እያላችሁ እየተናገራችሁ እስካለ ድረስ እናንተ በዝግ ችሎት መፍታት ያልቻላችሁትን ጉዳይ ሕዝብ መፍትሄ አለውና ስብሰባ ተጠርቶ እልባት ይሰጥበት!!!

 

ጋዜጠኛ ወንድወሰን ተክሉ

ጠላት በደስታ ፈንጠዚያ ላይ ነው። ወገን ደግሞ አብዛኛው ልቡ በሀዘን ተሰብሮ እርር እያለ ነው። የኢትዮ 360ሚዲያ አባላት በቡድን ተባድነው መጠዛጠዙን እስከ ትናንት እለት ድረስ በርትቶ ቀጥላል። በዚህ ውዝግብ ፣ በዚህ መፈራረጅ፣ መካሰስ እና መዘላለፍ በደስታ ኩሬ እየዋኘ ያለው የአማራ ጠላት ብቻ እና ብቻ ሲሆን አማራዊያኑ ግን አንዳንዶች ገለልተኛ ለመምሰል ሲጥሩ፣ አንዳንዶች ደግሞ ቡድን ለይተው አንዱን ደግፈው እና ሌላውን ሲነቅፉ፣ ሲተቹና ሲያወግዙም ተደምጣል።

እስካሁን በአደባባይ ያስተዋልነው ክስተት የእነ ኢየሩሳሌም ቡድን በደቻቱ ቲክቶክ ቤት በባልደረባቸው ሀብታሙ ላይ ያስተጋቡትን ክስና ፍረጃ ሲሆን በሀብታሙ በኩል የሰማነው ነገር ባይኖርም የእነ ጄሪን ፕሮግራም ከአየር ላይ እንዳወረደ፣ ጄሪንም ወደ ስቱዲዮ እንዳትመጣ እንዳገደና ጉዳዩ በህግ የተያዘ መሆኑ የሰማን ሲሆን ጄሪ የስቱዲዮውን እቃ Vandalize  እንዳደረገች ከተላለፉት ፕሮግራሞች ማድመጥ ችለናል።

ሀብታሙ አያሌው ፣ ኢየሩሳሌም ተክለጻዲቅ፣ብሩክ ይባስ ከስምንት አመት በፊት በጋራ ከሚሰሩበት ኢሳት የብርሃኑ ነጋን ለአቢይ አህመድ አገልግሉን ትእዛዝ አንቀበልም፣ አቢይ አህመድንም አናገለግልም ብለው በማመጽ ከሌሎች አቻ ባልደረቦቻቸው ጋር ሆነው ከእስት በመውጣት ኢትዮ 360 ሚዲያን ያቋቋሙ ናቸው። ድፍን ሰባት አመትም በዚሁ መንፈስ አብረው በመስራት የዘለቁ ናቸው። ሚዲያውን ሲያቋቋሙ አብረዋቸው የነበሩት እነ ኤርሚያስ ለገሰ፣ ምናላቸው ስማቸው በአላማና በአቋም ለውጥ ምክንያት አብረው መጋዝ ስላልቻሉ ሚዲያውን ለቀው ሲወጡ  ሶስቱ ባልደረቦች ግን ጸንተው እስከዛሬ በጋራ የቀጠሉ ናቸው።

In between ሌሎች ጋዜጠኞች እየገቡ ብዙም ሳይቆይ ለቀው እየወጡ ሶሳቱ ግን – ሀብታሙ፣ ጄሪና ብሩክ እስከ ባለፈው ሳምንት ድረስ የውስጣቸውን በውስጥ አድርገው በጋራ እና በአንድነት ሚዲያውን ያስቀጠሉ ብርቱ የሀሳብ ተፋላሚ ባልንጀራሞች ነበሩ።  በተለይ በተለይ ኢትዮ 360 ሚዲያ በፋሺስቱ የብልጽግና ስርአት ዩቲውባቸው ከተዘጋባቸው ከነሀሴ 2023 ጀምሮ አንዳችም ገቢ Generate  ማድረግ በማይችልበት ሁኔታ ውስጥ ሆኖ በቆየበት በዚህ ሁለት አመት ውስጥ የሚከፈለውን ዋጋ እየከፈሉ የሚዲያውን ህልውና ያስቀጠሉ ጀግኖች ናቸው።

በተለይም Just  ከሁለት ወር በፊት በመስከረም 7 ቀን 2025  በዲሲ ባከበሩት የኢትዮ360 ሚዲያ ሀብታሙ አያሌውን እናክብር ፕሮግራም ላይ በታተመው መጽሄት ላይ ብሩክና ጄሪ ስለባልደረባቸው ሀብታሙ አያሌው የሰጡትን ምስክርነት ቃል ይዞ የወጣውን መጽሄት ከዚህ ጽሁፍ ጋር አያይዤ ስለለጠፍኩት ማየትና ማረጋገጥ ይችላል።

ይህ እንግዲህ የሆነው Just  ከሁለት ወር በፊት መሆኑን ስናይና ሰሞኑን የተፈጠረውን ውርክብ ስንመለከት ነው እንግዲህ እጅግ የምናዝነው፣ እጅግም የምንገረመው።

What happen ??

ለመሆኑ በዚህ ሁለት ወር ውስጥ ምንድነው የተፈጠረው ??

በልዩ ጸጋዬ (ደቻቱ ቲክቶክ ቤት) ባስተላለፉት የሁለት ቀን ፕሮግራም ውስጥ ጨምቄ የተረዳሁት የልዩነታቸው ምንጭ የአላማና የአቋም ልዩነት ያለመሆኑን ተረድቻለሁ። በእነጄሪ በኩል ኢትዮ ሰገነት ዩቲውብ ሚዲያን እንደ የግጭታቸው ዋና አስካል አደገው ካቀረቡ በሃላ ይህንን ለማጠናከሪያነትም የታፍነናል፣ ፕሮግራማችን ከአየር ላይ ወርዳልን በዋና መንስእነት በመግለጽ ተበደልን ያሉትን በርካታ ጉዳዮችን (ይህ ጸሀፊ እነዚያን ቃላቶችን መልሶ መጠቀም አይፈልግም) በመግለጽ የልዩነታቸውን መንስኤን ገልጸዋል። ጉዳዩ ወደ ፍርድ ቤት ደረጃ መድረሱንም ገልጸዋል። ይህ ሁሉ ሲሆን የሚዲያው ቦርድ አባላት የገለጹልን ነገር የለም። መጽሀፉም ዝም እነሱም ዝም ያሉ ሆነው አይተናል።

Unfortunately እነጄሪ ይህንን ተበደልን ያሉትን ሁኔታን ለመግለጽ ወደ መድረክ በመጡበት ወቅት በቅርቡ ትግሉን ክዶ ነፍሲያውን አስበልጦ ከሀገር ሸሽቶ ዩጋንዳ የገባውን ጌጥዬ ያለውን በማቅረብ ከፕሮግራማቸው እጅግ ያፈነገጠና በወዳጆቻቸው ላይ ድንጋጤና ተቃውሞን የፈጠረን ይዘት ያለው አገላለጽን ስለአፋሕድ፣ ስለሸዋ ጠቅላይ ግዛት እዝና ስለታላቁ አርበኛ እስክንድር ነጋ መሰረተቢስ ወሬ በማውራት ጉዳዩን ይበልጥ እንዲጦዝ ተደርጋል።

የጄሪ Intention ታላቁን አርበኛ እስክንድር ነጋን ጨምሮ የሸዋ ጠቅላይ ግዛት እዝን እና አጠቃላይ የአፋሕድን አመራር የማዋረድ አላማን ያላነገበ ሆኖ ሳለ Co-Host  ሆኖ አብራት የቀረበው ጌጥዬ ያለው ግን ትናንት ከኢትዮጲያ ለመሸሽ ህይወቴ አደጋ ላይ ውድ ቃል ብሎ እኛም እንዳስተጋባንለት ሁሉ ዛሬ የራሱን ግላዊ Relevance ለመፍጠር ከሀገር ለመሰደድ (ጌጥዬ ከሀገር ለመሰደድ የፈለገው እጅግ ቆይቷል) ድምጽ ሆኖ ያስተጋባለትን ሀብታሙ አያሌውን እና ብሎም ከባልደራስ ጀምሮ አብሮት ሲሰራ በነበረው ታላቁ አርበኛ እስክንድር ነጋ ላይ የክህደት ተግባር በመፈጸም አርብ ኛውን ተጠያቂ የሚያደርግ አሉባልታን በማቅረብ ከእነጄሪ አላማና ፕሮግራም ያፈነገጠ አፍራሽ ተግባር ላይ ተዘፍቆ በመገኘቱ ብዙዎችን እጅግ አስቆጥታል።

በዚህ ሁሉ ሂደት ውስጥ እጅግ ድብቅ አጀንዳና አላማ ካላቸው ጌጥዬ ያለው እና ዛሬ እነ ጀሬን ደግፎ ሀብታሙን አውግዞ መግለጫ ካወጣው ኤርሚያስ ሺበሺ (ዲሲ ግብረ ኃይል ) በስተቀር በእነ ጄሪና በሀብታሙ መካከል የጥቅም ይገባኛል፣ የአፈጻጸም ጉድለት አለ ከማለት በስተቀር የአላማና የአቋም ልዪነትን ፈጽሞ አላየንም።

ስለሆነም ይህን ጉዳይ ለመፍታት የሚከተሉት ተግባራት መፈጸም አለባቸው ብዬ አምናለሁ።

፩ኛ- ጉዳዩን በሕግ ከመፍታት እኛ (ሕዝብ ) እንዲፈታው መደረግ አለበት። ለዚህ ደግሞ ሁለቱም ወገን ማለትም እነ ጄሪና ሀብታሙ ሙሉ ፍቃደኝነትን ሊሰጡን/ጡ ይገባል። 

፪ኛ- በዚህ አለመግባባት ጉዳይ ቤንዚን አርከፍካፊዎችን ማራቅና መለየት ይገባል።

፫ኛ- የሚዲያውን ጉዳይ ከፋኖ ትግል ውስጣዊ ጉዳይ ለይቶና ነጥሎ ማየትን ይጠይቃል።

፬ኛ- ሚዲያው በተለይም የቦርድ አባላት በአስቸካይ ህዝባዊ ስብሰባ መጥራት ይገባቸዋል። ሚዲያው የሕዝብ ነው እስከ ተባለ ድረስ ለይስሙላ ሳይሆን በተጨባጭ ተግባር ይህን ችግር ለመፍታት ሕዝባዊ ስብሰባ በአስቸካይ መጠራት አለበት

፭ኛ- የቲክቶኩ ፕሮግራም በአስቸካይ መቆም አለበት። እነጄሪ ቲክቶክ ላይ መምጣት መብታቸው ሳይጣስ በቲክቶክ የሚያቀርቡት ፕሮግራም ግን ስለ ውስጣዊ ችግራቸው መሆኑ ቀርቶ ስለትግሉ በቲክቶክ ፕላትፎርም ማስተላለፍና ማቅረብ ይገባቸዋል።

፮ኛ- የህልውና ትግሉን ሸሽቶና ፈርጥጦ ዩጋንዳ የገባው ጌጥዬ ያለው ስለፋኖ፣ ስለአፋህድ፣ ስለ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት እዝና ስለታላቁ አርበኛ እስክንድር ነጋና ሌሎች አመራሮች የሚረጨውን መሰረተቢስ የፈጠራ ወሬን በአስቸካይ ማቆምና በሚዲያው ስምም መድረክ ሊሰጠው አይገባም።

በተጨማሪም ጉዳዩ በምንም አይነት ተአምር ወደ ፍርድ ቤት መሄድ የለበትም። ችግራችንን እኛው መፍታት አለብን፣ መፍታትም እንችላለን። የኢትዮ 360ሚዲያ ባልደረቦች ሀብታሙ አያሌው ፣ ኢየሩሳሌም ተክለጻዲቅ፣ ብሩክ ይባስ፣ አፈወርቅ አግደው መካከል አንዳችም የአቋም እና የአላማ ልዩነት አላየንም። እናም ኢትዮ 360 ሚዲያ ተጠናክሮ፣ ችግሮቹንም ፈትቶ አስደናቂ ፕሮግራሙን እንደተለመደው እንዲቀጥል የሁላችንንም ቀና ትብብር እና ተሳትፎን ይሻል። ይህንም ማድረግ ይቻለናል። አበቃሁ።

Filed in: Amharic