>

''ያደባባዩ ምሁር ፕሮፈሰር መስፍን ወልደማሪያም'' [ኣቶ ኣሰፋ ጫቦ እንደጻፉት]

profeser Mesfin Weldemariamዛሬ ፕሮፌሰር መስፍን 85 አመት ሆነው። ከዚህ ውስጥ ለ50 አመታት ያክል አውቀዋለሁ። ሔጄ፤ፈልጌ፤ወጥቼ ወርጄ አይደለም ያወኩት። እዚያ ስለ አለ ነው ያውኩት።ወይም፤አለማውቅ ስለማይቻል ነው ያወኩት ብል የሚሻል ይመስለኛል። ይህንን ሁሉ ዘመን አደባባይ፤የኢትዮጵያ አደባባይ ላይ ነበርና ነው።
አደባባዩ ላይ አንዳንዴ ከሰዎች ጋር ሆኖ ነዉየማዉቀዉ።፤ የመሬት ላራሹ ሰልፍ ፤ የፖለቲካ ድርጅቶች እሰጥ-አገባ ወስጥም አያለሁ። ብዙውን ጊዜ ብቻውን ሁኖ ሲናገር፤ሲጽፍ ፤ሲስብክ ነው የማየው ፤የምሰማው። ብቻውን ሁኖ ብቻውን ያለ አይመስልም።ቁመናው አጠር ፤ደጎስ ያለ ሆኑ ሳለ እንደጉዙፍ አንደተራራ አይንን የመሰባ፤የመሰማት ግርማና ተሰጥኦ ተፈጥሮ የለገሰው ይመስላል። በስተቀረም ብቻውን አለመሆኑ የሚያዉቅ ፤እኛም የምናውቅ ይመስለኛል። አገሪቱ ፤ኢትዮጵያ ከሚለው ጋር ነችና!! ስለግል ጉዳዩ ሲናገር ሰምቸውም ስለማላውቅ የግል ጉዳይ ያለውም አይመስለኝም።አሁን ድረስ!!
መስፍን ፤በኔ አስተያየት “ያደባባይ ምሁር “ የሚሉት ይመስለኛል። ባደባባይ ሲናገር፤ሲጽፍ የኖረው፤አሁንም የተያያዘው የጋራ፤ያገር ጉዳይ መሆኑ ያንን ስምና ክበር ያስገኝለታል ብዬ ከልብ አምናለሁ።”ያደባባይ ምሁር “ Public Intellectual የመዝገበ ቃላት ትርጉሙ ይኸዉና:
public intellectual
(idiomatic) A well-known, intelligent, learned person whose written works and other social and cultural contributions are recognized not only by academic audiences and readers, but also by many members of society in general.
ባለፈው 60 አመታት የተፈራረቁብን ገዥዎቻችን መስፍንን ወደውትም ጠልተውትም አያውቁም።ወደዉታልም ጠልተውታልም ለማለት ነው። ዝም ብሎ ያየው የለም። የኃይለ ስላሴ መንግስት ፤ወለጋ፤የግምቢ አውራጃ ገዥ ብሎ ሾመው። ወለጋ፣ የወለጋ ሰው ያልሆነ መሾም የቁም እስር መሆኑን ያውቃሉና። በደርግ ጊዜ ለግምቢ አስተዳዳሪነት ተሾሞ የነበረውን ፤ኢንጂነር ግርማን በስንት መከራ ነው ከዚያ ያላቀቅኩት። ደርግ ደሞ የመረማሪ ኮሚሽን አለቃ አደረገው። ከዚያ ደግሞ መንግስቱ ኃይለማርያምና ኮሎኔል ተሰፋየዬ ወልደ ስላሴ ስለመስፍን የተናገሩት ያው በመጽሐፍም ታትሞ የወጣ ነገር ነው። ወያኔ ገና በርሐ እያለ ጀምሮ መንግስቱ ኃይለ ማርያምና መስፍን ጊዮን ሆቴል በኛ ላይ ያድማሉ ሲል ነበር። ጊዜው ሲፍቅድ ከርቸሌም አወረዱት ። የኢሐፓ አለቃ ፤ኢያሱ አለማየሁም አንድ ስሞን አንድ ሁለቴ ኢትዮጵ ትባል በነበር መጽሔት ወርፎታል።
ምኑ ቅጡ!ያ ሁሉ ሁኖ መስፍን ያው አሁንም አደባባይ ላይ ነው። ፈቅም አላለም። አቦ እጁን የማይስጥ ጉድ ነው!!ይኸው 85 ሞላው። ረዥም እድሜ ነው የሚባለው? ይህ ደግሞ የዘለሰኛውን ግጥም አስታወሰኝ:-
አምላኬ ግብርህን እንዳታሳንሰው፤
እምቢ ብሎ አይቀርም አንተ የጠረሐው ሰው ይላል።
እኔ የምለው ፣ምነው ለመስፍን ጥሪው ከነአካቴው ባይላክለትና ተረስቶ እዚሁ እኛዉ ጋ ለሁሌም ቢቀር!!

Filed in: Amharic