>

ሼክ አላሙዲን በወያኔ መንግስት ስም ለክሊንተን ፋውንዴሽን 20 ሚሊዮን ዶላር መስጠታቸውን አዲስ የወጣ መጽሃፍ አጋለጠ [ቪዲዮ]

ቋጠሮ:
ገንዘቡ ለኪሊተን ፋውንዴሽን የተሰጠው ሄላሪ ክሊንተን የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር በነበሩበት ወቅት ሲሆን የተሰጠበት ምክንያትም አሜሪካ በሰባዊ መብት ጥሰት የዳጎሰ ሪከርድ ባለው የወያኔ መንግስት ላይ የተለሳለሰ አቋም እንድትይዝ የምልጃ ክፍያ ሳይሆን እንዳልቀረ ተገምቷል።
የክሊንተን ፋውንዴሽን የበጎ አድርጎት ስራ የሚሰራ ድርጅት ሲሆን በአጭር ግዜ ውስጥ ያካበተው ከፍተኛ የገንዘብ መጠን ድርጅቱ ከበጎ አድራጎት ስራው በስተጀረባ ይህን መሰል የተለያዩ ሃገራት መሪዎችን ከአሜሪካ ጋር የማማለድ ስራ ሳይሰራ እንደማይቀረ አስጠርጥሮታል።
ሼክ አላሙዲን ስለ ጉዳዩ ተጠይቀው መልስ መስጠት አልፈለጉም።ይህ እውነት ከሆነ የክሊንተን ቤተሰብ የኢትዮጵያን ህዝብ በ20 ሚሊዮን ዶላር ሸጠው ማለት አይሆንምን? ሙሉውን ዘገባ ከቪዲዮው ተመልከቱ፡ ከላይ በአጭሩ የተገለጸው በ18ኛው ደቂቃ ላይ ይገኛል።

Filed in: Amharic