>

በወገኖቻችን ላይ የደረሰውን ስቃይ በማስመልከት በኖርዌይ ኦስሎ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሄደ

በወገኖቻችን ላይ የደረሰውን ስቃይ በማስመልከት በኖርዌይ ኦስሎ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሄደ (photo by Abebe Demeke)በሊቢያና በደቡብ ኣፍሪካ ባሉት ወገኖቻችን ላይ የደረሰውን ስቃይ በማስመልከት በዛሬው ዕለት በኖርዌይ ኦስሎ  ሰላማዊ ሰልፍ ተካሂዶኣል።  የኢትዮጵያውያን የስደተኞች ማህበር በኖርዌይ ባዘጋጀው በዚሁ ሰልፍ ላይ ከኦስሎና ኣካባቢዋ የመጡ ኢትዮጵያዊያኖች፤ የኢትዮጵያን ባንዲራና የተለያዩ መፈክሮችን በመያዝ   በተለምዶ ”ነብሩ” ከተሰኘው ቦታ መነሻውን ያደረገ ሲሆን፣ ሰልፈኞቹ የተለያዩ መፈክሮችን በማሰማት ወደ ፓርላማው  ያቀኑ  ሲሆን፣  ”ኖርዌይ ለገዳዩ ህወሓት/ኢህኣዲግ ስርዓት የምታደርገውን ድጋፍ በኣስቸኳይ እንድታቆም” ሰልፈኞቹ ኣሳስበዋል።
”በኢትዮጵያውያን ወገኖች ላይ በየስፍራው የሚደረገው የሰብኣዊ መብት ጥሰቶች  የህወሃት/ኢህኣዲግ ውጤት ነውና የኖርዌይ መንግስት ለዚህ ኣፋኝና ገዳይ ስርዓት የሚያደርገውን ድጋፍ እንዲያቆም ሰልፈኞቹ ኣሳስበዋል።በመጨረሻም ይህ የኢትዮጵያ ስደተኞች ማህበር በኖርዌይ ያዘጋጀው ሰልፍ ከመጠናቀቁ በፊት ኣዘጋጅ ኮሚቴው የፖለቲካና የሃይማኖት መሪዎች ንግግር ኣድርገው የሰልፉ ፍጻሜ ሆኖኣል።ሰልፉ የተካሄደው እኩለ ቀን  በስራ ሰዓት ላይ በመሆኑ ሰልፈኞቹ ከኖርዌይ ኦስሎ ነዋሪዎች ትኩረት እንደነበራቸው ለማወቅ ተችሏል።
በወገኖቻችን ላይ የደረሰውን ስቃይ በማስመልከት በኖርዌይ ኦስሎ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሄደ 2 (photo by Abebe Demeke)በወገኖቻችን ላይ የደረሰውን ስቃይ በማስመልከት በኖርዌይ ኦስሎ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሄደ 3 (photo by Abebe Demeke)በተመሳሳይ መልኩ ባለፈው ኤፕሪል 25 ቀን በኖርዌይ ኦስሎ ደማቅ ሰልፍ መካሄዱ ኣይዘነጋም።>
Filed in: Amharic