>

ይቺ ንብ ናት እወቋት ! [ሄኖክ የሺጥላ]

Yichi neb nat - Henok Yeshitilaይቺ ንብ ነች 

ከለም መሬት የገፋችን
በራብ እሳት የቆላችን
ካገር ገፍታ ያስወጣችን
በባህር ላይ የጣለችን
በባእዳን ያስበላችን ::
ይቺ ንብ ነች እወቋት
በእጃችን የያዝናት
ገና ድሮ ያወቅናት
ተናዳፊ ፣ የማር ሌባ
የአበባ ጸር የማትረባ
ሞታ ካፈር እስክትገባ
ክፋት ስራዋን አንረሳው
ያፈሰስነነውን እንባ ፣ እንደ አገር ልጅ ፣ አረ እንደ ሰው !
ይቺ ንብ ናት እወቋት
የችግር መጅ ፣ የሬሳ ቋት
የታሪክ ትል ፣ የደም አጏት
የውድቀት ጌጥ ፣ ተራ ኩራት
ትሆናለች የሳት ራት ::
ይቺ ንብ ናት እወቋት
በማር ተመስላ ሬት
ይቺ ንብ ናት ያገር ምሬት
የዋይታ ዳስ ፣ የሬሳ ቤት !
የዘር ጥንስስ ፣ የዘር ስሌት
ያገር ውርደት ፣ ያገር ቅሌት ::
ይቺ ንብ ናት ጠላታችን
እንዳንኖር ባገራችን
እየወጋች ያስወጣችን
እየደፋች የጣለችን
እየጫነች የሸጠችን ::
ይቺ ንብ ናት ፣ መንታ ምላስ
ማርና ደም የምትልስ
ህጻን ቀስማ የምታፈርስ
እርጉዝ ገላ የምታለቅስ
የህዝብ አጥንት የምትሞቅ
በመከራ የምትስቅ ::
ይቺ ንብ ናት እወቋት
ቀኑ ሲደርስ ላንለቃት
ላንምራት ላናኖራት
ሳንፈልጋት ፣ ንብ ሆናብን
በነብሳችን ላይ አዛብን
ደማችንን እየቀሰመች
አያ ንቦ ትኖራለች ::
ይቺ ንብ ናት እወቋት !
እስክንድርን የነደፈች
እነ ባልቻን ያስገደለች
እነ አስራትን የገደለች
እነ ሀብታሙን ያገተች ::
ይቺ ያገር ያበባ ጠር
የልብ ቃር ያይን ጠጠር
ይቺ ሌባ ፣ የንብ ዘላን
ጀርባችንን ነክሳ ይዛን
በመተንፈስ ሁሉ ከሳን
ትለናለች ግድብ ሰራን !

ይቺ ንብ ናት እወቋት
የችግር መጅ ፣ የሬሳ ቋት
የታሪክ ትል ፣ የደም አጏት!

Filed in: Amharic